በትግራይ ክልል ሕዝቡ ሕወሃት እንዳሰበው መደበቂያ ሳይሆን፡ ሕግና ፍትህን የጠየቁ ሠልፎች ተደረጉ!

26 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ወንጀላቸው እየተባባሰ ስለተጋለጠ፡ ሕወሃት የፈጸማቸውን የዘረፋ፡ ግድያና የሰብእዊ መብቶች ወንጀሎችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ታግሎ በማጋለጡ፡ ዛሬ ሕወሃቶች የሚገቡበት ጠፍቷቸዋል። ባለፈው እሁድ ሕዝቡን አስገድዶ ለሠልፍ አሥወጥቷል።

የሕወሃትን ሃሣብ ደገው ሠልፍ የወጡ ቢኖሩም፡ የሠልፉን ጸረ-ኢትዮጵያዊ ዓላማ ቢጻረርም— ዝርያንም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች — የሕዝቡ አመለካከት ምን እንደሚመስል ከሥር በጽሁፉ ተጠቅሷል!

ምንድነው ሕወሃት እየደበቀ ያለው? ከአዲሱ ዜና ብንጀምስ?

የነበሩትንና ለጊዜው ትተን አዲስ ከተጋለጡት እንጀምር።

በሶማሌ ክልል የፕርሬዚደንቱ አማካሪ በኢሣት 60 ደቂቃ ላይ እንደተናገሩት፣ የወያኔ ሲቪልና ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊዎች (የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስግር ቤተሰቦች ጭምር) በዋቤ ሸበሌ ቤዚን ዙርያ —እስካሁን እደታወቀው — አንድ መቶ ሺህ ካሬ መሬት አሳጥረው መያዛቸውን ሰኞ ለኢሣት ገልጸዋል።ይህ የተፈጸመው በተደጋጋሚ ርሃብ በሚያጠቃው ክልል በመሆኑ፡ ይህንን ድርጊት የፈጸሙትን ግለሰቦች ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሣይሆን የሰው ልጆች ደኅንነት ጠላትነትን የሚያሳይ ነው!

ጋዜጠኛው ለፕሬዚደንቱ የሕግ አማካሪ ስም እንዲነግሩት ቢጠይቅም፡ ምርመራው ስላልተጠናቀቀ በዚያን ወቅት ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም።

ከትግራይ ሠልፎች መካከል

ከትግራይ ሠልፎች አንዱ (Ourfanos)

Credit: OurFanos

ይህም  የሕወሃት ጠብ አጫሪነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ክፉኛ በማስቆጣት ሕዝቡ አስተያየቱን በሶሻል ሚዲያዎች አሳውቋል።

ምን ዐይነት ኅሊናና ጭንቅላት ያለው ስው ነው፡ እነዚህ የማፍያ ወንጀለኞች አይመርመሩ በሕግ አይጠየቁ ብሎ የትግራይን ሕዝብ  ተጠቃሚው ይመስል በሠላማዊ ሠልፍ ተባባሪው ለማስመሰል ሕወሃት የሞክረው? 

 

%d bloggers like this: