ከገጽታ ዕደሳት ባሻገር፡ ታከለ ኡማ ከሥዩም ተሾመ ጋር በልዩነቶች ላይ መክረው ችግር ለመፍታት ያሳዩት ሊለመድ የሚገባው ፖለቲካ!

8 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ዛሬ [ሐሙስ] ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር ፍሬያማ የሆነ ውይይት አድርገናል። ባለፈው ካወጣሁት ፅሁፍ ጋር በተያያዘ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ግልፅ የሆነ ውይይት አድርገናል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየቴን በነፃነት መግለፄን በማድነቅ አበረታተውኛል። በቀጣይም በከተማ መስተዳደሩ ሆነ በሌሎች የመንግስት አካላት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመንቀስና በመተቸት ትኩረት እንዲያገኙና ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የጀመርኩትን ጥረት አጠናክሬ እንድቀጥል መክረውኛል። እኔ በበኩሌ የከንቲባው የመኖሪያ ቤት ኪራይን ጨምሮ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በማንሳት ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ለወደፊት ማንኛውም ዓይነት ጥያቄና አስተያየት ሲኖረኝ በስልክ ሆነ በአካል ተገኝቼ መረጃና ማብራሪያ መጠየቅ እንደምችል አረጋግጠውልኛል። የሃሳብና አመለካከት ነፃነትን አክብሮ በቀናነት የመወያየት ልማድ በሁሉም ዘንድ ሊዘወተር የሚገባ ነገር ነው። የተለየ ሃሳብና አስተያየት በሰጠሁ ቁጥር በሰከነ መንገድ ከመወያየትና ሃሳብ ከመለዋወጥ ይልቅ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያዘንቡ ለሚውሉ ጭፍን ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ይሄ ጥሩ ማሳያ ነው። የሃሳብ ልዩነት መጨረሻ የሰከነ ውይይት እንጂ ዛቻና ማስፈራራት መሆን የለበትም።

/ከሥዩም ተሾመ ፌስቡክ

ተዛማጅ:

የሥዮም ተሾመ ደብዳቤ ለኢንጂ. ታከለ ኡማ: ም/ከንቲባው 3ኛ ቤታቸውን ሊቀይሩ ዝግጅት ላይ ናቸው! እቺ እውነትም እየታደሰች ያለችው ኢትዮጵያ ናትን? ሕዝብ በቁሙ ሲታረድ እነማን ነን? የት ነው የምንሄደው አይቀሬዎች ናቸው!

 

Leave comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: