በሲቪል መንግሥት ዴሞክራሲን ለመገንባት የተነሳሳችው ኢትዮጵያ የመከላከያን ቀን ማክበር አለባትን? ዘርፈ ብዙ ዕንቁ መልዕክት!

15 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ይህ ዓመታዊ ወታደራዊ ሠልፍ በብዙ ሃገሮች ውስጥ ይካሄዳል። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የፕሬዚደንት አብርሃም ሊንከንን ግድያ ተከትሎ፡ በሙት ወራቸው በሃዘን የተጎዳውን ሕዝብ ለማጽናናት ሲባል በተተኪው ፕሬዚደንት አንድርው ጆንስን ትዕዛዝ በ1863 ታላቅ ወታደራዊ ሠልፍ ተደርጓል።

ከዚያ በኋላ ስድስት ጊዘ ብቻ ወታደራዊ ሠልፎች በሃገሪቱ የተደረጉ ሲሆን፣እነዚህም፤

  • የአንድኛውን የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ለማክበር በ1919 ዓ.ም. በኒውዮርክ ፊፍዝ አቨኑ (Fifth Avenue) ላይ 25, 000 የአሜሪካን ወታደሮች ተሠልፈዋል— የተለያየ ቁጥርም ያላቸው ሠልፎች በየስቴቶቹ ተካሂደዋል፤
  • በ1942 ዓ.ም. ዩናይትድ ስቴትስ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ ስትገባ፡ የመንግሥት ሠራተኞች ከወታደርቱ ጋር በመሆን ለወታደሮቻቸው ያላቸውን ድጋፍ ለማብሰር ታላቅ ሠልፍ በኒውዮርክ ከተጦርነት ማ ተደርጎ ነበር፤
  • በ1946 የአሜሪካ 82ኛው የአየር ወለድ ሠራዊት ጦርነቱን ድል ማድረጋቸውን ለማብሠር በኒውዮርክ 13000 ጦር ከሕዝቡ ጋር በመሠለፍ ድላቸውን ማክበራቸው ተዘግቧል፤
  • በ1953 አይዘናወር ፕሬዚደንት ሲሆኑ— የቀድሞ ጄኔራል ከመሆናቸውም በላይ በኮሪያ ጦር የመሩና ሶቪየቶችን በጣም ስለተጠራጠሩ—በመሣሪያ ሠልፍ በማሳየት የሃገራቸውን ሃያልነት ለሶቭየቶች መልዕክት ለማስተላለፍ የታቀደ ነው ይባላል፤
  • የኪኔዲ ፕሬዚደንትነታዊ ሲመት በ1961 ሲከበር ቀዝቃዛውን ጦርነት ምክንያት በማድረግ የመሣሪያ ዕይታ ሠልፍ ተካሂዷል፤
  • በ1991 አሜሪካ የገልፍ ጦርነት አሸናፊነት ለማክበር የተደረገው ሠልፍ ተወዳዳሪው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሽናፊነቷን ለማክበር የተደረገው ሠልፍ ብቻ ነው ይባላል!

ከእነዚህ ዕውነታዎች ውጭ በአሜሪካ የወታደር ባሕላዊ ዓመታዊ ሠልፍ አይደረግም!

በአሁኑ ዘመን አውሮፓ ውስጥ ራሺያና የምሥራቅ አውሮፓ ሃገሮች ሠልፎች ያደርጋሉ። አውሮፖ ውስጥ ከሚድረጉት የተለያዩ ወታደራዊ ሠልፎች ስመ ጥር የሆነው የፈረንሣዩ ሐምሌ 14 የሚከበረው የባስቲ ቀን (Bastille Day military parade) ሠልፍ ነው።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሰባተኛው የመከላከያ ቀን አከባበር ወቅት በአዳማ ንግግር ሲያደርጉ! (ኢዜአ ፎቶ)

የባስቲ ቀን ሠልፍ ዓላማ ባስቲ የሚባለው እሥር ቤትን በፈረንሣይ ሕዝብ በ1880 መደምሰሱን ለሰው ልጅ መብትና ከብር የተድረገ መሆኑን በመቀበል፣ ለፈረንሣይ ትልቁ በዓል ቀን ነው። ይህ አከባበር ተቀዛቅዞ የነበረው ከ1875-1879 ዲሬክተሪ (Directory) በተሠኝው የፈረንሣይ ወታደራዊ አስኝተዳደር ዘመን ነበር።

ምክንያቱም ሠልፉን ወታደራዊው አስተዳደር ሕዝባዊ ባሕሪውን አጥፍቶ ወታደራዊ ሠልፍ ስላደረገው ነበር። ከናፖሊዮን መፈንቅለ መንግሥትና ሬፐብሊኳ ከተመለሠችበት ጊዜ አንስቶ ግን ባስቲ ቀን በየዓመቱ ሲከበር እዚህ ደርሷል።

ፕሮዚደንት ትራምፕም ፈረንሣይን በሠልፉ ወቅት በ2017 ጎብኝተው አሜሪካም ተመሣሣይ ወታደራዊ ሠልፍ እንድታደረግ አቅደው፡ በተቃውሞ መቅረቱ ይታወሳል!

በሌላ አባባል፣ የዚህ ዐይነት ወታደራዊ ሠልፍ ዓላማ— በኢሣት ውይይት እንደተነሳውም (video ከላይ)— ሲቪል ኅብረተሰብን ወታደራዊ ለማድረግ ሣይሆን፣ ወይንም የሠራዊቱ ኃይል በሲቪል ኅብረተሰብ ላይ የበላይነት ተጽዕኖ እንዳይመስል ጥንቃቄ ለማድረግ ነው።

የባስቲ ሠልፍ ከታሪክና ከሰው ልጅ ነጻነት ጋር የተያየዘ በመሆኑ፡ የተለይዩ ሃገር መሪዎችም በየዓመቱ በሠልፉ ተሳታፊ ይሆናሉ!

****

እኔም ኢሣቶች ያነሱትን ሃሣብ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዩኒፎርም ዙርያም ሆነ በወታደራዊ ፕሮቶኮል ረገድ፡ ሲነሱ የነበሩትን የሲቪል ኅብረተሰብ ግንባታ ዓላማና የሕግ የበላይነት ጥሪያቸውን ድርጊታቸው እንዳይጻረር የሚለውን ሃሣብ አብክሬ ደግፋለሁ!

ሌሎች ሃገሮች የሚያደርጉት እንደዚህ ስለሆነ፣ ኢትዮጵያም መለኪያዋ ያ ነውና ኮፒ እናድርገው ለማለት አይደለም የዚህ ገጽ ዓላማ! ወታደራዊ ሠልፍ ወታደራዊ የበላይነትን ጫኝ በመሆኑ ነው የተለያዩ ሃገሮች የሞክሩትን ሞክረው (አሜሪካ) የቀየሩት።

ኢትዮጵያ ደሞክራሲን ገንቢ ሃገር ለመሆን ሕዝቧ ቆርጦ ተነስቷል። ይህ በምንም መንገድ መደናቀፍ የለበትም! የመለስ ዜናዊ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሽምጥ ውስጥ እንዳንቀር ጥንቃቄ ያስፈልገናል!

 

/ የመረጃ ምንጮች፡ የዜና አውታሮችና ዊኪፔዲያ
%d bloggers like this: