ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሴቶች ቀን: “ማንም ምንም ቢሞክር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና ትቀጥላለች”!

9 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በወጣትነት ዘመን እንዳለው ጀግንነት ማስፈራራት ብቻ ሳይሆን፣ በአዛውንትነት ዘመን የሚመጣውን ቁጭትና ጸጸት ታሳቢ አድርገን፣ ለጦርነትና ወንድምን ለመግፋት ያለንን ጉልበት ለሰላም፣ ለአንድነትና አብሮ ለመኖር መጠቀም ይኖርብናልም!

ያኔ ምድር ስትፈጠር አንድ ወንድና አንድ ሴት መኖሩ ብቻ ሣይሆን፣ ዛሬም በዓለም ላይ ሰባት ቢሊዮን በላይ ሕዝብ አለ ቢባል፣ ግማሹ ሴት ነው። በኢትዮጵያ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ አለ የተባለ እንደሆነ፣ ግማሹ ሴት ነው። ያኔ አዳምና ሔዋን እንደጀመሩት፣ ዛሬም ሃምሣ ሃምሣ የሆነበት ዋና ምክንያት እኩልነትን ተፈጥሮ ስለምትገነዘብ ነው!

ጉልበታሞች ብቻ የሚበዙበት ዓለም ቢሆን ኖሮ፣ ሴቶች ቁጥራቸው እያነሰ ወንዶች በበረከተ ነበር። ተፈጥሮ ግን ሁለቱን አስተካክላ የያዘችው እኩልነትና አብሮነት ወሳኝ መሆኑን ስለምትገነዘብ፣ ከተፈጥሮ ተቃርነን ብንቆም፣ ሁሌ እንደምንጮኸው፣ ለእኩልነት፥ ለሰላም ለአንድነት የምንጮህ እንጂ የሚሳካልን ስላልሆነ፥ ሃምሣ ሚሊዮን ሴት አሥር የሚኒስቴር ቦታ ብቻ ሣይሆን፣ በኢኮኖሚ፣ ሰላም በማረጋገጡም፣ ድንበር በመጠበቁም በብሄር መካከል የሚነሳ አርቲፊሲየል ጥላቻንም በመከላከልም ሚናዋን መጫወት ይኖርባታል…ኢትዮጵያ የጀግኖች አምባ ብትባልም፣ ዛሬ ከፍተኛ የጀግና ችግር አለባት።”
 


 

“ኢትዮጵያ ውስጥ ጀግኖች የሉም፣ መንጋ ተከታዮች እንጂ!ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደውን መስድብ የሚሳደቡ፤ የተለመደውን መግደል የሚገድሉ፤ የተለመደውን መሥረቅ የሚሠርቁ፤ የተለመደውን መግፋት የሚገፉ እንጂ ይህንን የመንጋ አስተሳሣብ ተቃርነው፣ በፍጹም መሥረቅ ነውር ነው፤ ወንድምን መግፋት ነውር ነው፤ ወንድም ወንድሙን መጥላት ነውር ነው–ትግራይ አማራን፣ አማራ ኦሮሞን፣ ኦሮሞ ደቡብን መግፋት ነውር ነው የሚሉ ጀግኖች ኢትዮጵያ የሏትም!ኢትዮጵያ ያላት በርታ፣ ታጠቅ፣ ግደል የሚሉ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ደግሞ የተለመደውን የወረሱ እንጂ፣ ጀግኖች አይባሉም።

ጀግኖች በችግር ውስጥ በተቃርኖ ዕውነትን ይዞ መቆም መቻል ስለሆነ፣ ይህንን ክፍተት ለመሙላት፣ ማርች 8ን ስታከብሩ፣ ጀግና ሴቶች ከትግራይ ጀግናችሁ ባሕር ዳር በመሄድ ነውር አይደለም እንዴ? እንዴት? ወንድም ወንድሙን ለመግደል ይነሳል ስትሉ ያ ነው የሴቶች ጀግነነት የሚባለው…ከባሕር ዳር ጀግኖች መቀሌ ሂዳችሁ…ከባሕር ዳር ጀግኖች ሐዋሳ ሄዳቹ…ጅጅጋ ሄዳቹ…አፋር ሄዳችሁ የተጠናወተን ነውር፣ የተጠናወተን አሳፋሪ ልምምድ እንዲቆም —ምንም እንኳ የሚጮህና የሚደግፋችሁ ቲፎዞ ቢያንስም—በጀግንነት ስትጋፈጡ —ያኔ ኢትዮጵያ እውነትም የጀግኖች አምባ ትባላለች።

ብዙውን መከተል ጀግንነት አያሰኝም፤ ለእውነት መቆም ነው ጀግንነት የሚያሰኝውና ይህንን ተግባር ለመፈጸም፡ ሴቶች ምሶሶ ተሸካሚዎች ሠጭዎች ስለሆናቸሁ፡ ሌሎች ኃላፊነታቸውን እንዲያስታውሱና የሃገራቸውን ክብርና አንድነት እንዲያውሱ፣ በጀግንነት ይህቺን ቀን ስታስቡ ቀጣይ ሥራዎቻችሁም የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት፣ መፈቃቀርና ይቅርታ እንዲሆን በታላቅ ትህትና ልጠይቃችሁ ፈልጋለሁ!

…”

 

%d bloggers like this: