የሌተና ጄኔራል መሃመድ ተሰማ “ነጻ እርምጃ እወጃ” በተመሥገን ደሣለኝ (ጋዜጠኞች) ላይብቻ ይወሰን ይሆን?

14 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“በመከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትሪኔሽን ድሬክቶሬት ድሬክተር ሜ/ጂኔራል መሃመድ ተሰማ ሐምሌ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በርካታ ጉዳዮችን ለማብራራት ሞክረዋል። የባሕር ዳሩንና የአዲስ አበባውን ሰሞነኛ ጉዳይ አንስተዋል”— ብሎ ይጀምራል ተመሥገን ደሣለኝ።

ይህም ሆኖ የጄኔራሉ መልዕክት ማጠነጠኛ “የመከላከያን ስም የሚያጠፉ፥ አመራሩንና ሠራዊቱን ለማራራቅ የሚያሴሩ” በሚል የኮነኗቸውን ጋዜጠኖችና ሚዲያዎች ጦሩ እያሳደደ በነጻ እርምጃ እንዲደመስስ መፈቀዱን ‘ማብሰር’ እንደነበር ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሁሉ የተረዱት ዕውነታ ነው። ከዚህ ቀደም በነበሩ የተቋሙ መሪዎች በደባባይ (በሚዲያ) ሲነገሩ ያልተደመጡ ክብረ-ነክ ኃይለ ቃሎችን ተጠቅመዋል።

ሙሉውን የጋዜጠኛ ተመሥገንን ትንተና ከዚህ ቪድዮ መከታተል ይችላሉ።

 

 

ይህ በቅርቡ ከወደ መከላከያ ብቅ ማለት የጀመረው አዝማሚያ፥ አያሌ ዜጎችን በተለያዩ ጽሁፍች፡ መድረኮችና በሶሻል ሚዲያ የጄነራሉን አባባሎች ለወንጀል ድርጊት ወታደሮችን የሚቀሰቅስና ኢትዮጵያን ወደባርነት ለመመለስ የተጠነጠነው ሴራ አካል መሆኑን፣ ብሄራዊና ዓለም አቀፍ ሕግጋትን ጭምር የጣሰ መሆኑን ጠቁመዋል! ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾችና እንዲሁም አጥኚዎችና ተንታኞችን ጭምር ሥጋት ውስጥ የከተተ ከአንድ ከፍተኛ መኮንን የማይጠበቅ ኃላፊነት የጎደለው ሃገሪቱን የሚጎዳ መሆኑን ብዙዎች ለማሳየት ሞክረዋል!

 

ይህ ደግሞ በመከላከያ ብቻ የተወጠነና የሚወሰን አይሆንም!  መላ ሃገሪቱ ውስጥም የአፈና ሕጋዊነትን የመከናነብ አዝማሚያ ከከፍተኛው የመንግሥት ሥልጣን በኩልም በዛቻና በጸያፍ ቃላት መደመጥ መንገዱን እየቀደደ መሆኑ አያጠራጥርም!

 

 

%d bloggers like this: