የኦሮሚያ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የመንግሥትን ሀብትና ንብረት ከብክነትና ብልሽት የሚታደግ ሶፍትዌር አበለጸግሁ ይላል!

20 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአዘጋጁ አስተያየት:

በዚህ ሙስናን በዘመናዊ መንገድ ለመከላከል ስለሚያስችለው ሶፍትዌር የሚነሣ ጥያቄም ሆነ አስተያየት ያንገፈግፈኛል!

በ2012 ለሕንድ ኩባንያ በጸረሙስናው አቶ ዓሊ ሱሊማን አማካይነት ሃገራችን $250 ሺ ለሕንድ ኩባንያ መከፈሉን አስታውሳለሁ! ኩባንያው ይብላው ወይንም ጅቦቹ ይረባረቡበት የታወቀ ነገር የለም! ሕንዶች በእውነትም ይሁን በሃሰት ስማቸው ቢነሳም፡ በነርሱም በኩል የጎረሰ ነበር መሰለኝ ስማቸውን እንኳ ለመጠበቅ አለትንፈራገጡም!

አምባሳደርነት የዘረፉና መገለል ያለባቸው ስዎች መደበቂያ በመሆኑ፡ የጸረ ሙስና ኮሚሽና ኃላፊም አንቱ ተብለው ከለውጡ ወዲህ፡ ባሕር ተሻግረው ማዕረጋችውም ወደ አምባሳደርነት ተቀይሯል። ይህ ሲታይ ሹመታቸው ማንንም ስላላገለጥክ እናመስግናለን ይመስላል!አ

ሁንም ሃገራችን ሁለቴ ተታላ፣ አንጡራ ሃብቷን አስረክባ በቂልነት የሚያዩአት ይበራከታሉ ብዬ ሠጋለሁ!

ምን ዋስትና አላት ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ገንዘብ ሚኒስቴር ተዘጋጀ የተባለው ሶፍትዌር ያለፈው ዘረፋ ክፍል ሁለት ቢሆንስ? ምናልባት የኦሮሞዎችን ሥልጣን ላይ መውጣት “ተረካቢው”፥ “ባለተራው” ወዘተ የሚሉት እውነትነት ቢኖራቸውስ?

ለመሆኑ በሕጉ መሠረት የባለቤትነት ለመሆኑ በሕጉ መሠረት የባለቤትነት  መብት ይኖረዋል ወይስ ዘው ብሎ “ኬኛ” ነው ያለው?

 

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14፣ 201 1 (ኤፍ. ቢ. ሲ) የኦሮሚያ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የመንግሥትን ሀብትና ንብረት ከብክነትና ብልሽት የሚታደግ ሶፍትዌር ማበልጸጉን አስታውቋል።

በመጪው ጥቅምት ወር  በሥራ ላይ ይውላል የተባለው ይህ ሶፍትዌር የመንግስትን ሀብት ሙሉ ታሪክ የሚመዘግብ ፣ የት ቦታ፣ ለምን አግልግሎት፣ በማን እጅ እንዳለ ሞዴሉና በምን ያህል ዋጋ እንደተገዛ ወይም እንደተገነባ የሚያመላክቱ መረጃዎችን በጥንቃቄ የሚመዘግብ ነው ።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፋና ብሮደካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጨመዳ እንዳሉት፥ ሶፍተዌሩ በአሠራር የማይፈፀመውን  የግዥ አሠራር ፈር ያስዘዋል ብለዋል።

የመልካም አስተዳደር መጓደል  ተደርጎ ከሚወሰዱት ማሳያዎች መካከል የሃገርንና የሕዝብን ሀብት በአግባቡ አለመጠበቅና እንዳይጠበቅ ማድረግ አንዱና ዋነኛ ማሳያ መሆኑ ይነገራል።

በአግባቡ ማቀድ፣ በዕቅዱ መሠረት መፈጸምና ይህን ሥርዓትም በተገቢው መንገድ ስለመተግበሩ የሚያረጋግጥ አሠራር አለመዘርጋትም ችግሩን ከሚያባብሱ ምክንያቶች ተጠቃሾች ናቸው።

ከዚህ ባለፈም በሀገሪቱ ያለው  የተጠያቂነት ባህል አለማዳበሩ የሀገርን ሀብት የማባከንና የመበዝበዝ ችግር እንዲስፋፋ አስተዋፅኦ እንዳለው ብዙዎችን ያስማማል።

ኤፍ ቢ ሲ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎችም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በመንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ በግብታዊነት ተገዝተው ያለሥራ የተከማቹ፣ በታቀደው መሠረት ተገዝተው ለሚፈለገው ዓላማ ሳይውሉ በየመጋዘኑ የታሸጉ ዕቃዎች በርካታ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ  እንዳስታወቀው እነዚሀን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ሶፍትዌር ማበልጸጉን አስታውቋል ።

ከዚህ ቀደም የነበሩት ኋላ ቀር የንብረት ቁጥጥር አሰራር ዘዴዎች በክልሉ ስር የሚገኙትን 20 ዞኖች ፣ 290 ወረዳዎች እና 46 የከተማ መስተዳድሮች ውስጥ ያለውን ንብረት በሚፈለገዉ ደረጃ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሮ መቆየቱን የቢሮው ምክትል ሃላፊ ተናግረዋል።

ክልሉ በየአመቱ ከሚመደብለት በጀት 63 በመቶ ለግዥ የሚያውል ሲሆን፥ከዚህ ውስጥ ደግሞ 40 በመቶው ቋሚ ንብረት ውስጥ የሚካተት መሆኑ ተገልጿል።

ለዚህ ደግሞ ከአንድ አመት በፊት በክልሉ ያሉትን ተሽከርካሪዎች የሚቆጣጠር ሶፍትዌር እውን እንዲሆን ተደርጓል።

ይሁን እንጂ  ሶፍትዌሩ ሁሉንም የክልሉን ንብረት ከግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ ሙሉ ሃላፊነትን ለመወጣት አላስቻለም ነው የተባለው።

አሁን ላይም ከኦሮሚያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን እና ጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር  የክልሉን ንብረት መቆጣጠር የሚያስችል ሶፍትዌር እውን መሆኑ ተገልጿል።

በግዥ ስርዓቱ ላይ ልጓም እንደሚያበጅ የሚጠበቀው ሶፍትዌሩ፥ ያለውንና የሌለውም ንብረት በአሰራሩ የሚታወቅ በመሆኑ በድጋሜ የሚገዛ ሀብትን ለመከላከል ያስችላል።

ባለፈው ግንቦት ወር አጠቃላይ ሶፍትዌሩን የማበልጸግ ተግባር መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ተስፋዬ  በተለያዩ ምክንያቶች በስራ ላይ ይውላል ከተባለበት ጊዜ መዘግየቱን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቀት በመጪው ጥቅምት ወር  2012 ዓ.ም  በስራ ላይ ለማዋል የቅድመ ዝግጅት ስራው እየተጠናቀቀ መሆኑን ነው የተናገሩት።

 

%d bloggers like this: