ኢንተርኔት በሚቋረጥበት ሃገር የኢንተርኔት ነፃነት ጉባኤ?

26 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(BBC News አማርኛ)  የኢንተርኔት ነፃነትን የተመለከተ ‘ፎረም ኦን ኢንተርኔት ፍሪደም ኢን አፍሪካ’ የተሰኘ አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች በመዲናዋ ተሰባስበው ጉባኤውን እየተካፈሉ ነው።

ለቀናት የኢንተርኔት አገልግሎት በሚዘጋበት አልያም በሚቆራረጥባት አገር፤ የኢንተርኔት ነፃነት ቀንን የማክበር ተቃርኖ ያልተዋጠላቸው ብዙዎች ናቸው።

በአንድ በኩል ጉባኤው ኢትዮጵያ ውስጥ መካሄዱ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ላይ ውይይት እንዲካሄድ መንገድ እንደሚጠርግ የሚያምኑ አካላት አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥ የንግግር ነፃነት የሚገደብበት አገር ላይ ጉባኤው መካሄዱን የሚተቹም ብዙ ናቸው።

• የኢንተርኔቱን ባልቦላ ማን አጠፋው?

• በሞባይል ኢንተርኔት መቋረጥ የተገደቡ እንቅስቃሴዎች

• መንግሥት በምን የሕግ አግባብ ኢንተርኔት ይዘጋል?

ከወራት በፊት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እየተካሄደ ሳለ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። በአማራ ክልል “የመፈንቅለ መንግሥት” ሙከራ ተደርጓል መባሉን ተከትሎም ለቀናት ኢንተርኔት ተዘግቶ ነበር።

በመላው ዓለም የኢንተርኔት አገልግሎትን የሚቃኘው ‘ኔትብሎክስ’ ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ስታቋርጥ በየዕለቱ ወደ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምትከስር አስታውቋል።

ጉባኤውን ኢትዮጵያ ውስጥ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ?

ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጦማሪያን፣ የሕግ ባለሙያዎችና ሌሎችም መንግሥትን ይተቻሉ።

በብሔራዊ ደረጃ ከ15 በመቶ የማይዘለው የኢንተርኔት ዝርጋታ ሲቋረጥ ማኅበረሰቡም እሮሮ ማሰማቱ አይቀረም። ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ የመብት ተቆርቋሪዎች መንግሥትን ከሚነቅፉበት ምክንያት አንዱም የኢንተርኔት መቋረጥ ነው።

እነዚህን ነጥቦች በማስረጃነት በማንሳት ኮንፍረንሱን ለምን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማካሄድ እንደተወሰነ አዘጋጆችን ጠይቀን ነበር።

የ ‘ፎረም ኦን ኢንተርኔት ፍሪደም ኢን አፍሪካ’ የፕሮግራም ኃላፊ አስናህ ካልሜራ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ የዜጎችን ኢንተርኔት የማግኘት መብት በመግፈፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ አገር በመሆን ትታወቅ የነበረ ቢሆንም፤ ባለፈው አንድ ዓመት አንጻራዊ ለውጥ መጥቷል።

ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች፣ የመብት ተሟጋቾችና ጦማሪያን ከእሥር መለቀቃቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ እንዳያሰራጩ ተደርገው ከነበሩ ድረ-ገጾች ላይ እገዳው መነሳቱ እንዲሁም ለወራት ኢንተርኔት ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ መደረጉን ያጣቅሳሉ።

ሆኖም ግን ከ “መፈንቅለ መንግሥት” ሙከራው ጋር በተያያዘ ኢንተርኔት ተቋርጦ እንደነበርና ከዚሁ የ “መፈንቅለ መንግሥት” ሙከራ ጋር ይገናኛል በተባለ ክስ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች መታሠራቸውን ይናገራሉ።“ቢሆንም ኢትዮጵያ ለለውጥ ቁርጠኛ አገር መሆኗን አይተናል። በኢንተርኔት ነፃነት ረገድና በሌችም ጉዳዮች ላይ ከሚሠሩ የመብት ተሟጋቾች ጋር በጋራ የመሥራት እንቅስቃሴም አስተውለናል” ሲሉ ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ የታየው አንጻራዊ ለውጥ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተምሳሌት ቢሆንም፤ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማስፋትና መረጃ የማግኘት ነፃነትን በማክበር ረገድ ብዙ የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን በኢንተርኔት መረጃ የማግኘት መብት እንዲያከብር የሚያሳስብ የጋራ ስምምነት ሰነድ ለመፈራረም መወጠናቸውንም አስናህ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች በሚገኙበት ኮንፍረንስ ስለ ዴሞክራሲ መስፈን እና የሰብአዊ መብት መከበር በመነጋገር፤ የመብት ተሟጋቾችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚገፉበትም አክለዋል።

‘ፎረም ኦን ኢንተርኔት ፍሪደም ኢን አፍሪካ’ ከዚህ ቀደም በኡጋንዳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በጋና እና ሌሎችም የአፍሪካ አገሮች ተካሂዷል። ኮንፍረሱ አፍሪካ ውስጥ የኢንተርኔት የመረጃ ስርጭት እንዳይገደብ እንዲሁም የመናገር ነፃነት እንዲከበር ንቅናቄ በማድረግ ይታወቃል።

ምሕረት ዩሃንስ
አጭር የምስል መግለጫምሕረት ዩሃንስ

የኢንተርኔት መቋረጥ በነጋዴዎች ላይ የሚያሳድረው ጫና

በመላው ዓለም የኢንተርኔት አገልግሎትን የሚቃኘው ‘ኔትብሎክስ’ እንደሚለው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ በየዕለቱ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ታጣለች።

የኢንተርኔት መቋረጥ በአገር ደረጃ የሚያደርሰውን ቀውስ በግል ከሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች አንጻር ለመመልከት ያነጋገርናት ምሕረት ዮሐንስ አዲስ አበባ ውስጥ ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኝ የኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ትሠራለች። ካፌው ሥራ ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢንተርኔት አገልገሎት መቆራረጥና ሲከፋም ተዘግቶ መቆየት ፈተና እንደሆነባት ትናገራለች። በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመልቀቂያ ፈተና ምክንያትም ሆነ ከተለያዩ ፖለቲካዊ ክስተቶች ጋር በተያያዘ የኢንተርኔት ግልጋሎት መቋረጥ ሲያጋጥም አብሮ የሚዘጋው ሥራችንም ነው ትላለች። በእነዚህ ጊዜያት “ሥራ የለም ማለት ይቻላል። እስኪከፈት ከመጠበቅ ውጭ ምንም ማድረግ የምንችለው ነገር የለም” ስትል ለቢቢሲ ታስረዳለች።”ኢንተርኔት ባይቆራረጥ፣ መዘጋቱ ቢቀር ጥሩ ነው” የምትለው ምሕረት የምትሠራበት ካፌ ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ የጽሕፈት መሣሪያዎችን በጎን የሚሸጥ ሲሆን፤ ከእነዚሀ ሽያጮች በሚያገኘው ገቢ ወጪዎቹን ለመሽፈን ይጥራል። “እኛ ሌላ ሌላ ገቢ ስላለን ነው እንጅ [ኢንተርኔት በማስጠቀም] የምናገኘው ገቢ በጣም ዝቅ ያለ ነው” ትላለች።

• ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጣች

• ኢትዮቴሌኮም ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ እንደማይችል አስታወቀ የመደብር ኪራይን ከመሳሰሉ ወጪዎች በተጨማሪ ለኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው ኢትዮ-ቴሌኮም መፈፀም ያለባቸው ክፍያዎች አገልግሎቱ በሚቋረጥባቸው ጊዜያትም እንደሚቀጥሉ ምሕረት ትናገራለች።”የምንከፍለው በወር ነው፤ አገልግሎቱ ቢኖርም ባይኖርም መክፈላችንን እንቀጥላለን” ትላለች ምሕረት ከቢቢሲ ጋር በነበራት

 

ተያያዥ ርዕሶች:

የመረጃ መረብ / ኢንተርኔት

አፍሪካ

ኢትዮጵያ

 

 

%d bloggers like this: