“አንድ ወደፊት ስንሄድ ሁለት ወደኋላ የሚመልሱንን ኃይሎች ማስቆም አለብን”- ጠሚ ዐብይ አሕመድ

3 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከአዘጋጁ፡

ከሩስያ መልስ ባለፈው ሣምንት ጠሚሩ በየቦታ ተዟዙረው ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ዓላማ ማግባባትና ማስታረቅ ያሰበ መስሎ ነበር።  ብዙ መለማመጥ ስለታየበትም ቅሬታዎች መፈጠራቸውም  የሚካድ አይደለም። ግራ ሲያጋባም ከርሟል፡፡ ይህ ሊቀጥል ይችላል በሕግ የሚከናወነው እስካልታየ ድረስ። 

የዛሬው የጠሚሩ መግለጫ  ጠቃሚ መረጃ የያዘ ቢሆንም፡ ቁጠኛ ይዘቱ የችግሩን መንስዔ ዒላማው አላደረገም :: “አንዳንዶች እንዲማሩ” ከተባለው ባሻገር—አጥፊዎቹን በሚገባ በመርህና እምነት አቋም ላይ ተመሥርቶ መገሠጽ ሲቻል፣ ሁሉንም በአንድ ሙቀጫ አስመስሎታል።

“ከሟቾቹ መካከል 76 ሰዎች በእርስ በእርስ ግጭት” ጠፍተዋል ሲባልስ፣ ለጠሚሩ የታጠቀና የተደራጀ ኃይል ጥቃት  የመክፈቱ መድበስበስ  አይታያቸውምን?  ለዚህ ጠንካራ መከላከያ አለ ለማለት የሚደፍር የተሻለ መረጃውን ቢያዘጋጅ ይጠቅማል።  የመንግሥት አካሄድ ግን የችግሩን መንስዔ ባልተገቡ ቅጽሎች  ደርቶ ለማጥፋት የተሰላ ነገር ይኖራል የሚል ሥጋት አሳድሯል።

ዜጎች እንደሃገር ከጠሚሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሰማ፣ ቁጣን ማሳየታቸው ምክንያቱ ግልጽ ነው። ሆኖም ሕዝቡ አንጀቱ እርር ብግን ብሎ መንግሥት ባብዛኛው ለዜጎች ከለላ ባልሆነበት ሁኔታ— ስሜቱን በጨዋነት መግለጹና ከመንግሥት ጋር መቆሙ በእርሳቸውም በኩል ክብደት ሊሠጠው በተገባ ነበር።

እርሳቸውም ይህንን በመገንዘብ ይመስለናል፣  “ነገሩን ሁሉ …ከስሜት በላይ ሆነን የተጋረጠብንን አደጋ በብልሃት መቀልበስ እንድንችል የዘወትር ትብብራችሁ እልዳይለየን እጠይቃለሁ” ብለው በመግለጫችው ወቅት ጥሪ ያደረጉት።

ስለሆነም ከዚህ በፊት ተግባራዊነታቸው ያላመረቃ —አሁን በታደሱ—የሚከተሉት አምስት ቃል ኪዳኖች እንደገና በአዲስ የድርጊት አቅጣጫ ሆነው ተጠቁመዋል:-

(ሀ) “አንዳንዶች እንዲማሩ ተብሎ ሠፊ ልብና ትክሻ ሲሠጣቸው አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት ቀርተው የዜጎች ሕይወት ለአደጋ የሚጋለጥበት ምክንያት መፈጠሩን…” በዚህም ረገድ “ዋልታ ረገጥ የብሄርና የእምነት ጫፍ ላይ ቆመው ችግሮችን የሚያባብሱ ወገኖችም አስተያየቶቻቸውና መልእክቶቻቸው ተጨማሪ ዕልቂትና ጥፋት ከሚያመጣ ማናቸውም ተግባር እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።”

(ለ) “መንግት የዜጎችንና የተቋማትን ደኅንነት ለመጠበቅ የሃገሪቱ ሕግ ባስቀመጠው መሠረት እንደሚሠራ፤

(ሐ) “በአንድ በኩል የፖለቲካውንና የዴሞክራሲውን ምኅዳር ለማስፋት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፍትህንና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም አስታውቅዋል።”

(መ) “ያለፉትን ስህተቶች ለማረም እየሠራን በሌላ በኩል ደግሞ ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ ሕጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን። በዚህ አግባብም አልሚ ሁሉ ራውን፤ አጥፊ ሁሉ ደግሞ በጥፋቱ ልክ ተጠያቂ እየሆነ እንደሚሄድም አስታውቀዋል።”

(ሠ) “የሃይማኖት አባቶች፣ የጎሣ መሪዎች፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች መንግት የሃገሪቱን ሰላም፣ ደኅንነትና አንድነት ለማስጠበቅ ሲል ግና ርዓትን እንዲያስከብር ደጋግመው መጠየቃቸውን በማንሳት፥ ጥያቄያቸው ተገቢ መሆኑንና መንግትም ሕግ የሚፈቅድለትን ሁሉ ለማድረግ አቅምም፣ ዝግጁነትም፣ ብቃትም እንዳለው አስታውቅዋል።”

እነዚህ ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ የመጎትጎቱ፣ የመናገሩ፣ የመጻፉና የመሟጎቱ ኃላፊነት የዜጎች ነው! መንግሥት ካልተገደደ እንደነዚህ ዐይነት የዜጎችን ደኅንነና መብቶች የሚያበራክቱትን ሕጋዊና መዋቅራዊ ጉዳዮችን በበጎ ፈቃድ ብቻ ተግባራዊ  አያደርግም! ካለፈው የአዲስ አበባና ባሕር ዳር ግድያ በኋላ የዐቢይም መንግሥት ምን ያህል በባሕሪውና ተግባሩ እንደተሸራተተ እናስታውሳለን!

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አንድ ወደፊት ስንሄድ ሁለት ወደኋላ የሚመልሱንን ኃይሎች ማስቆም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶክተር አብይ አሕመድ በመግለጫቸውም ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት የ86 ሰዎች ሕይወት አልፏል ያሉ ሲሆን፥ ከሟቾች መካከል 82 ወንድ፣ 4 ሴቶች መሆናቸውምን አስታውቀዋል።

በብሄር ደግሞ 50 ኦሮሞ፣ 20 አማራ፣ 8 ጋሞ፣ 2 ስልጤ፣ 1 ጉራጌ፣ 2 ሀዲያና አንድ አርጎባ ሲሆኑ፥ የአንዱ ሟች ብሄር እንዳልታወቀም አስታውቀዋል።

በሃይማኖት ደግሞ ከሟቾቹ መካከልም 40 ክርስቲያን ሲሆኑ፥ 34 ሙስሊምና 12 የሌላ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በመግለጫቸው ያስታወቁት።

ከሟቾቹ መካከል 76 ሰዎች በእርስ በእርስ ግጭት፤ 10 ሰዎች ደግሞ በፀጥታ ኃይሎች ሕይወታቸው ማለፉንም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በመግለጫቸው፥ ይህ ክፉ ክስተት በኢትዮጵያ የግጭት እሳት ሲነሳ አንዱን ክፍል አቃጥሎ ሌላውን አሙቆ የሚያልፍ እንዳልሆነ ያሳየ ነው ብለዋል።

መንግሥት የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ሆደ ሠፊነቱን አብዝቶ ሲያስታምም ከርሟል ብለዋል።

ከኃይልና ጉልበት ይልቅም፤ ትምህርትና ምክክር ይሻላል ብሎ መታገሱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ትዕግሰቱ ፍርሃት፤ ማስታመሙ ድካም፣ የመሰላቸው ካሉ ግን ተሳስተዋል ብለዋል።

አንዳንዶች እንዲማሩ ተብሎ ሠፊ ልብና ትክሻ ሲሰጣቸው አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት ቀርተው የዜጎች ሕይወት ለአደጋ የሚጋለጥበት ምክንያት መፈጠሩንም አንስተዋል።

መንግስት የዜጎችንና የተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ የሀገሪቱ ህግ ባስቀመጠው መሰረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

 

 

%d bloggers like this: