በሊቢያ በISIS የታረዱ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አፅም በሃገር ቤት በክብር ሊያርፍ ነው!

30 Jan
  1. Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Anti ISIS protest in Addis Ababa with victims picture in 2015 Wazema picture

 

ዋዜማ ራዲዮ- ከአምስት ዓመት በፊት በአሸባሪዎች በሊቢያ በግፍ የተገደሉ 34 ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዉያን አፅም ወደ ሃገራቸው ገብቶ በወግ እንዲቀበር ለማድረግ በመንግሥት በኩል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያውያንና ኤርትራዉያኑ አፅም ከአንድ ወር በፊት የሊቢያ የሽግግር መንግሥት በቁጥጥር ሥር ባዋላቸው አሸባሪዎች ጥቆማ ስርት በተባለችው ከተማ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ አንድ እርሻ አጠገብ መቃብሩን ማግኘት ተችሏል። የመቃብሩ ቦታ መገኘቱ እንደተሰማም የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሊቢያ የልዑካን ቡድን ልኮ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግሯል።

የተገኘውን አፅም በዲ ኤን ኤ (DNA) ምርመራ የማጣራትና የመለየት ሥራ እየተካሄደ ሲሆን ከሟች ቤተሰቦች መካከል ለዲ ኤን ኤ ምርመራ የተጠሩና ናሙናም የሰጡ መሆናቸውን ቤተሰቦች ነግረውናል።

የሟቾቹን አፅም የማምጣቱ ሂደት የሚያስፈልገውን ሕጋዊ ሂደት ለማሟላትም በመንግሥት በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያለን መረጃ ያመለክታል።
34 ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዉያን አይ ኤስ በተባለው አሽባሪ ቡድን መገደላቸው ይታወሳል። ወጣቶቹ በስደት ወደ አውሮፓ በመጓዝ ላይ ነበሩ።

የዋዜማ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ ቤተሰቦች ከኃዘኑ ተከትሎ በደረሰባቸው የስነልቦናና የጤና ቀውስ የአልጋ ቁራኛ እስከመሆን የደረሱ እንዳሉ ያስረዳሉ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ለመፈፀም ቃል ከገቧቸው ጉዳዮች አንዱ ስደተኞችን ከሥቃይ እስር ቤቶች ወደ ሃገራቸው መመለስና በሊቢያ የተገደሉትን ወጣቶች አፅም አፈላልጎ በወግ እንዲቀበሩ ማስቻል የሚል ይገኝበታል።

 

/ዋዜማ ራዲዮ

 

ተዛማጅ:

Did the TPLF commando think he saw an ISIL fighter? A member of the Agazi commandos, the butchers that have been killing Ethiopians all over the country, attacking a young man in Ramboesque manner to ensure continued survival of his employer–TPLF (Foto Negere Ethiopia).

 

Ethiopians express in 2015 spontaneous anger at ISIS, despite state violence;

grief is turned into vote of no confidence against TPLF regime

 

 

 

%d bloggers like this: