ዘመናት የፈጀው የዐቢይ አገዛዝ ስለታገቱት ዜጎች የሠጠው መልስ ጥያቄዎችን አጭሯል!

30 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

* አፋኞቹ እነማን ናቸው?

* መንግሥት እስካሁን ለምን ዘገየ?

*የዚህ አካባቢ ብዙ ወንጀሎች—ባንክንና ሕዝብ ላይ ዘረፋዎች— ሲፈጸሙ ሁለት ዓመት አልፈዋል! ኃይሉ ተደመስሷል ከተባለ እንዴት አንዳችም ተማሪዎች ማስለቀቅ አልተቻለም?

* እስከዛሬ ም ዕራብ ኦሮሚያ ነው የችግር ምንጭ የተባለው! አሁን ደግሞ አጋቾቹ ጋምቤላ ናቸው ተብሏል! ኦነግ ሸኔ ጋምቤላ ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ እንዴት እስካሁን አልተነገረም?

* በተደጋጋሚ በሕዝቡ በኩል የዐቢይ አስተዳደር ለሕዝብ ንቀት አለው የሚባለው ካለፈው ተደጋግሞ ተሰምቷል! እንዲህ ያለ ነገር የሚከሰተው፣ የዐቢይ አስተዳደር መሸፋፈን የሚፈልገው ጉዳይ ስለመኖሩ ያለፈው ባሕሪው ያሳያል—በተለይም ካለፈው ጥቅምት ጃዋርን ለመታደግ ሕዝባችን ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ማስታወሱ ይጠቅማል!

    •   መንግሥት አሁንም ሕዝቡን በማክበር  ልጆቹን በሚመለከት ላቀረባቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ይሥጥ!

 

 

 

%d bloggers like this: