የሃሰተኛ መረጃ ሥርጭትንና የጥላቻ ንግግር አዋጅን ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው አፀደቀ! ችኮላው ለምን ይሆን?

13 Feb

Posted byThe Ethiopia Observatory (TEO)

“The draft “Hate Speech and Disinformation Proclamation”, however, would threaten freedom of expression. As constructed presently, it could reinforce rather than ease ethnic and political tensions.”

David Kaye,  UN Special Rapporteur David Kaye on the right to freedom of opinion & expression

አዲሱ የጥላቻ ንግግር አዋጅ የመናገር መብትን ሊያፍን ይችላል!

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን አፀደቀ።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በዛሬው እለት አካሄደ።

ምክር ቤቱ በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል።


 Ethiopian lawmakers should significantly revise the draft law on hate speech and disinformation currently before parliament, Human Rights Watch said today. If approved, the Hate Speech and Disinformation Prevention and Suppression Proclamation could significantly curtail freedom of expression. Human Rights Watch


አዋጁ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምሪት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር እና ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በህብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት እየደቀኑ በመሆናቸው እንዲሁም እነዚህን ችግሮች አሁን ባሉት ህጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ዴሞክራሲያዊ ውይይት እና ክርክር ለማድረግ እንቅፋት በመሆኑ ከብሄር እና ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የጥላቻ ንግግር እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨትን እንዲሁም ዘርን፣ ጾታን እና አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል።


The proliferation of “hate speech” and false information has become a global phenomenon, and Ethiopia is no exception — but a new attempt to curb the vice with new legislation might just do more harm than good.

There are concerns that Ethiopia’s new Hate Speech and False Information law will stifle freedom of expression and return Ethiopia to its repressive past. Global Voices


እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በህግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱም ተነግሯል።

የምክር ቤቱ አባላትም በአዋጁ ላይ ያላቸውን ሃሳብና አስተያየት የገለጹ ሲሆን፥ ለአብነትም ይህ አዋጅ የዜጎችን ሃሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት የሚጋፋ እንደሆነ ያነሱ ሲሆን፥ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቶበታል።በዚህም አዋጁ በህገ-መንግስቱ ላይ ከተቀመጠው የመናገር መብት ጋር እንደማይቃረን፣ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 29 (6) እና (7) ከተቀመጡት ገደቦች ውስጥም አንዱ ምክንያት ሰብአዊ ክብርን መጠበቅ ሲሆን፥ የጥላቻ ንግግር ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ዋነኛው በመሆኑ ከተቀመጠው ገደብ ጋር የሚገናኝ መሆኑ ምላሽ ተሰጥቶበታል።

ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በ23 ተቃውሞና በ2 ድምጸ ተአቅቦና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

 

 

%d bloggers like this: