ከለውጡ በኋላ በወንጀል ተጠርጥረው የታሠሩትን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል ጉዳያቸው ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል – ጠ/ሚ

19 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአዘጋጁ ማስታወሻ 

በዕለተ ማክሰኞ ፕሮግራሙ Ethio360 ሠፋ ያለውይይት በአማራ ክልል ሹምሽር ላይና በወንጀል የታሠሩ ባለሥለጣንትና የጠ/ሚሩ ትዕዛዝ በሚል ውይይት አካሂዶ ነበር። ከፋና የተገኘውን መረጃ ቀን በትዊተር መረጃውን ስለቅ፣ የዜናው ይዘት ምን እንደሆነልገነዘብ የምችልበት ሁኔታ አልነበረም። ስለሆነም በሚከተለው መልክ እንደወረደ—ምንም አስተያየት ሳልጨምር ለቀቅሁት!

 

በመሆኑም ያልነበረኝን መረጃ ያካፈለኝ Ethio360 ፡ ስለምኅረት የተነሣው ሃሣቡ ገና ያልረጋና ከሕወሃት ጋር የሚደረገውን ዕርቅ ወይንም ዘላቂ ግጭት ላይ ያጠነጠነ መሆኑን ነው። መከታተል ለሚሹ ቪዲዎቹ እዚህ ይገኛሉ! (Ethio360 (1) Ethio360 (2) Ethio360(3)

በተለይም —ምንም እንኳ ዜና ውስጥ የብልጽግና አባል የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ያነሱት ጥያቄ ለምኅረቱ መንሥዔ ቢመስልም—እንደ Ethio360 ዘገባ ቀድም ብሎ አሜሪካ በአዲስ አበባና ትግራይ መካከል መግባባት እንዲደረስ ሲሠሩ እንደነበረ ተመልክቷል።

አስገራውሚው ግን—ትላንት እንደሰማነው —መንግሥት ገና መሬት ስላላወረደው ፖሊሲ ይመስላል “ጉዳያቸው በአግባቡ በህግ ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ [ተቀምጧል]” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ምን ማለት ነው? አንብበው መገንዘብ ለሚችሉ ግለሰቦች እንዲህ ነው ብሎ መደጋገሙ ስለማይጠቅም፡ ዜናው እንዴት በሁለት መንግሥታዊ የዜና አውታሮች እንደቀረበ፡ የፋናንየኢዜአን የመጀመሪያውን አንቀጾቻቸውን (Lead paragraphs) መመልከት ይቻላል።

ፖሊሲው ግን ውይይት ተደርጎበት፣ ስለተግባራዊነቱ አንድ ስምምነት ተደርሶ የተጸነሰ ቢሆን ኖሮ፣ በተለይም በአደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናገሩ በኋላ—መንግሥት በጓሮ በር ተመልሶ— “በተለያዩ አካባቢዎች በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩትን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል ጉዳያቸው በአግባቡ በህግ ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ በመቀመጡ” መካከልና||”የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል በሙስናና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተይዘው የፍርድ ሂደታቸውን ከሚከታተሉ ግለሰቦች ውጭ ያሉ እስረኞች ጉዳይ ፈጣን እልባት እንዲያገኝ”ልዩነት በመፈጠር በኢዚአ በኩል ማሻሻያውን ዘግየት አድርጎ ያላንዳች ኮሽታ ለቋል።

ዛሬ ዛሬ እንዴት ነው በዚህች ሃገር ፖሊሲ የሚቀረጸውና የሚተገበረው?

እቺ የ3000 ዓመታት መንግሥታዊ (statehood) ልምድ ያላት ሃገር ብዙ መዳበርን ባታሳይም በፖሊሲ አንጻር የነበራት ልምድና ጥንካሬ ተኖ ፖሊሲ በጉዞ የሆነው?

 

 

ሀ.  የፋና ዘገባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከለውጡ በኋላ በተለያዩ አካባቢዎች በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩትን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል ጉዳያቸው በአግባቡ በሕግ ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትግራይ ተወላጅ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ተወካዮች ከትግራይ ተወላጅ ወታደራዊና ሲቪል ባለስልጣናት እስር ጋር በተያያዘ ጥያቄ አቅረበዋል።

እነዚህ አባላት ከለውጡ በኋላ በርካታ አመራሮች ከሁሉም አካባቢዎች መታሰራቸውን በመጥቀስ፤ አብዛኞቹ ግን የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በህዝብ ዘንድ ቅሬታና የመጠቃት ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል።

ታሳሪ ግለሰቦቹ ወንጀል ይስሩ ወይም አይስሩ የፍርድ ቤት ጉዳይ መሆኑ ሳይዘነጋ ለሕዝብ ሰላምና መረጋጋት ሲባል ከለውጡ በኋላ የታሰሩ ዜጎች ክስ ቢቋረጥና ጉዳዩ የእርቅ እና የይቅር ባይነት ማሳያ ተደርጎ ቢወሰድ ሲሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከኢኮኖሚ አንፃር ትግራይን በኢኮኖሚ ለመጉዳት እየተሰራ ነው የሚል አስተሳሰብ እየሰፋና የለውጥ ሃይሉ ፀረ ትግራይ ተደርጎ እንዲታይ በርካታ ስራ እየተሰራ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የትግራይ ህዝብ መሪ በመሆናቸው ማብራሪያ ተጠይቀዋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ህዝብ ዘንድ ከፌዴራል መንግስትና ከጎረቤት ሀገራት ጥቃት ሊመጣ ይችላል የሚል ስጋት ስለተፈጠረ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝቡ ደህንነት አንፃር ምላሽ እንዲሰጡም ነው የተጠየቁት።

በዚሁ መድረክ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው፥ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘ ባነሱት ጥያቄ የምንገኘው በለውጥ ወቅት በመሆኑ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የታሰሩ ዜጎች በሆደ ሰፊነት ጉዳያቸው እንዲታይ አንስተዋል።

በባሕር ዳር፣ በኦሮሞ አስተዳደር ዞን እና በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ዜጎች ጉዳያቸው በህግ ታይቶ ምህረት ቢደረግ ለሀገራዊ እድገት እና መግባባት ጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምላሻቸው፥ ከለውጡ በኋላ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተከስተው ከነበሩ ግጭቶች እና ከለውጡ በፊት ተፈፅመው ከነበሩ የሙስና ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የታሰሩ ዜጎች ጉዳያቸው ታይቶ ለፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ሲባል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ እንዲፈታ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

እስረኞች በሁሉም አካባቢዎች ስለሚገኙ ወንጀለኛን ከብሄር ጋር ማገናኘት ግን በድምሩ ሀገርን ይጎዳል ነው ያሉት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

እስረኞችን የመፍታቱ ሂደትም የህግን አግባብ ተንተርሶ መከናወን እንዳለበት ነው የገለጹት።

ዜጎቹ የሚፈቱት ተጨባጭ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለመፈፀማቸው ተረጋግጦ፤ ለውጡን ለማስቀጠል እና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እንዲሁም በመንግስት ሆደ ሰፊነት እንደሆነም ነው ያስታወቁት።

በውይይቱ የትግራይና አማራ ክልሎች ጥያቄዎች ጎልተው ቢቀርቡም የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ጉዳያቸው ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ መቀመጡ ተመላክቷል።

ከኢኮኖሚ አንፃር ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡትም ምላሽ፥ የበጀት ቀመር የሚቀመጠው በፌዴሬሽን ምክር ቤት ስለሆነና የፌዴራል መንግስቱ ትግራይን የመጉዳት ሀሳብ ሊኖረው ስለማይችል ትችቱ መሰረተ ቢስ መሆኑን ተናግረዋል።

በተያዘው ዓመት በትግራይ ክልል 8 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት እንደተያዘ እና በዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 400 ሚሊየን ብር መመደቡንም አስታውቀዋል።

ይህ በጀት በትላልቅ የክልሉ ከተሞች የሚሰሩ የውሃ ፕሮጀክቶችን፣ የመስኖ ልማት ስራዎችን፣ በፌዴራል መንግስት የሚገነቡ መንገዶችን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችን የማያካትት መሆኑንም ነው ያስረዱት።

ከሁሉም በላይ ግን በአሁኑ ወቅት ሃብት በመከፋፈል ላይ ሳይሆን ሃብት በመፍጠር ላይ ልናተኩር ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የሀገሪቱ በጀት ግን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መከፋፈሉ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

ከፀጥታ አንፃር የትግራይ ህዝብ ከፌዴራል መንግስት ጥቃት ይደርስብኛል ብሎ ይሰጋል ብዬ አልገምትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህ የኮንትሮባንድ የጦር መሳሪያ ነጋዴዎች አሉባልታ ነው ብለዋል።

መንግስት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት እና በጀት የሚመድበው ለትግራይ ክልል እንደሆነም በመግለፅ።

በየትኛውም መንገድ የሚያሰጋ የውጭ ጥቃት በክልሉ ላይ እንደሌለም ነው ያረጋገጡት።

የትኛውንም ክልል የሚያጠቃ የውጭም ሆነ የውስጥም ሃይል የለም፤ ይህ ከሆነ ግን ጥቃቱ የኢትዮጵያ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ።

 

(ለ) የኢዜአ ዘገባ

በሙስናና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ምክንያት በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች ውጭ ያሉ እስረኞች ጉዳይ ፈጣን እልባት እንዲያገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2012(ኢዜአ) የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል በሙስናና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተይዘው የፍርድ ሂደታቸውን ከሚከታተሉ ግለሰቦች ውጭ ያሉ እስረኞች ጉዳይ ፈጣን እልባት እንዲያገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መመሪያ ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ ከትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ አመራር አባል ዶክተር አብርሃም በላይ አመራሮቹን ወክለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

 

 

 

%d bloggers like this: