የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዛሬ ምሳ ሰዓት ላይ በቡራዩ ከተማ በጥይት ተገደሉ

21 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ እንዳሉት ከኮማንደር ሰለሞን ጋር የነበሩት ሌሎች ሶስት ሰዎች በጥይት ተመተዋል።

ከኮሚሽነር ሰለሞን ታደሰ ጋር አብረው ከነበሩት መካከል የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የልዩ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ድንቁ አንዱ ሲሆኑ፤ ኮማንደር ተስፋዬም በጥይት ተመተው የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ከተቀሩት መካከል አንዱ ድምጻዊ መሆኑን ከኮሚኬሽን ቢሮ ኃላፊው ሰምተናል።

ሁለቱ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ላይ ጥቃቱን የሰነዘረው አካል ማንነት እስካሁን ግልጽ አለመሆኑንና እስካሁን በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው አለመኖሩንም የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

• በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ የመንግሥት ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ

• በምዕራብ ኦሮሚያ በ12 ወራት ቢያንስ 8 የአካባቢው ባለስልጣናት ተገድለዋል

• “በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም” የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ

አቶ ጌታቸው እንዳሉት በአራቱ ግለሰቦች ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው ቡራዩ ከተማ አስተዳደር አቅራቢያ ምሳ እየተመገቡ ሳሉ ነበር።

ኮማንደር ተስፋዬን ጨምሮ በጥይት የተመቱት ሶስቱ ግለሰቦች ወደ ኮሪያ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተሰጣቸው እንደሚኝ አቶ ጌታቸው የተናገሩ ሲሆን፤ ግለሰቦቹ ስለሚገኙበትን ሁኔታ ግን ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

 

/ቢቢሲ አማርኛ

 

ተዛማጅ፦

“We were assaulted by the police”: Artist Hawi H. Qeneni

OLF “deeply saddened” by the “intensified political repression” in Ethiopia

 

%d bloggers like this: