ኢትዮጵያ በዋሽንግተን የዚህ ሣምንት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እንደማትሳተፍ አሳወቀች!

26 Feb

Posted by  The Ethiopia Observatory (TEO)

በአሜሪካ ዋሽንግትን ዲሲ ሐሙስና አርብ ሊካሄድ ታስቦ በነበረው ቀጣዩ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ኢትዮጵያ እንደማትካፈል የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ምንም እንኳ የመጨረሻውን ድርድር ለማድረግና ስምምነት ላይ ለመድረስ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በግድቡ ጉዳይ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት አወያይቶ ስላልጨረሰ በመድረኩ ሊሳተፍ እንደማይችል አሳውቋል።

ነገ በሚጀምረው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ መገኘት እንደማትችል ለአሜሪካ ፋይንስ ቢሮ መነገሩ ታውቋል።

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ የተካሄዱት ውይይቶች ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ከ9 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ስላሉት የድርድር አካሄድ እና አቅጣጫ ላይ ውይይት መደረጉ ይታወሳል።

በዛ ውይይት ላይ ሚኒስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ሌሎችም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ግለሰቦችን በውይይቱ ተሳትፈው ነበር።

ለመገናኛ ብዙሃን ዝግ በነበረው ውይይት ላይ ኢትዮጵያ በቀጣዩ የዋሽንግትን ስብሰባ እንደማትሳተፍ ስለመወሰኑ የታወቀ ነገር የለም።

በአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ አደራዳሪነት በአዲስ አበባ፣ ካይሮ፣ ካርቱም እና ዋሽንግተን ዲሲ ሲደረጉ የነበሩት ውይይቶች ያለውጤት እንዲበተኑ የሆነው የግብጽ መከራከሪያ ነጥቦች መለዋወጥ መሆኑ ተጠቁሟል።

ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንደተረዳው ምንም እንኳን የሚካሄደው ውይይት በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም በግብጽ በኩል ድርድሩ የውሃ ድርሻ ላይ እንዲያተኩር ግፊት እያደረገች ነው።

######

 

ከዚሁ ከዐባይ ግድብ ሥራ ጋር በተያያዘ፣ የአደራዳሪዎቹን አድልዎ በመቃወም፣ በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በስቴት ዲፓርትመነት ፊት ለፊት በነገው ዕለት ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርጉ መረጃዎች ያሳያሉ። በወቅቱ የሚያዙት መፈክሮች የሚከተሉት እንደሚሆኑ ታውቋል፦

1) THE WORLD BANK – TAKE YOUR HANDS OFF THE NILE

2) US TREASURY – ETHIOPIA IS NOT FOR SALE

3) TRUMP – DON’T MESS UP WITH ETHIOPIA

4) MARCH 1, 2020 IS THE 124TH ANNIVERSARY OF ADWA

5) ETHIOPIA PAID HEAVILY FOR ITS INDEPENDENCE AND IS NOT WILLING TO KNEEL NOW!

6) THE WORLD BANK – DO NOT TIE LOANS WITH SIGNING THE NILE AGREEMENT

7) ETHIOPIA IS IN TRANSITION AND UNABLE TO SIGN LONG-TERM DEALS ON THE NILE NOW

8) EGYPT – TALK DIRECTLY TO ETHIOPIA NOT THE WHITE HOUSE

9) PM ABIY’S GOVERNMENT HAS NO MANDATE TO SIGN LONG-TERM DEALS ON THE NILE

10) WE ARE THE CHILDREN OF ADWA

11) MENELIK DID NOT TEACH US TO KNEEL DOWN UNDER PRESSURE – WE ARE ETHIOPIANS

12) TRUMP – WE HAVE NOT FORGOTTEN YOUR ‘SHIT-HOLE” COMMENT.

13) TRUMP CANNOT BE TRUSTED ON AFRICA AND THE NILE

 

 

%d bloggers like this: