Authoritarianism የሥልጣን ብልግና መገለጫዎች በኢትዮጵያ: በየቀኑ ነጠቃ፣ ማሠር፣ መፍታት፣ ዜጎችን ማንገላታት መደብደብ!

5 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በኤልያስ መሠረት

ከኮሮና ቫይረስ ዜና ወጣ ስንል:

– የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ለሰላምና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ አብዱሰላም ሸንገል ለ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዉ ሐሙስ ማረሚያ ቤት እንደተወሰዱ መረጃ ደርሶኛል። ሌሎች ሁለት የፓርቲው አመራሮች የሆኑት አቶ አብዱራሂም ጠሐና አቶ አቡዱ አህመድም አብረዉ ታሥረዋል።

ከአቶ ዮሐንስ ተሰማ የደረሰ መረጃ እንደሚያመለክተው በአሶሳ ያለ ማረሚያ ቤት “አዲስ እሥረኛ አንቀበልም” ስላለ የፓርቲው አመራሮች አንድ ቢሮ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ። የታሰሩበት ምክንያትም “ሕገ-ወጥ ስብሰባ አድርጋችኋል” የሚል ነው ብሏል አቶ ዮሐንስ።

– የአገው ብሄራዊ ሸንጎ መጋቢት 6 በእንጅባራ ከተማ የድርጅቱ የዞንና የወረዳ አመራሮች የሚሳተፉበት የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ የመጡ ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚዎች አልጋ ከያዙበት ክፍል ከምሽቱ 4:30 ላይ ታስረዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አላምረው ይርዳው እንደነገሩኝ አባላቱ እስካሁን እስር ላይ ይገኛሉ። “መጀመርያ ሁከት ፈጥረዋል ተባለ፣ ከዛ ደግሞ በፀረ- ሽብር ህጉ ይከሰሳሉ ተባለ፣ አሁን ደግሞ የትግራይ ተላላኪዎች ናቸው እየተባለ ነው” ብለዋል።

ከሁለቱም ክልሎች በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደሩግኩት ሙከራ እስካሁን አልተሳካም። ተጨማሪ መረጃ ካለ እመለስበታለሁ።
 

 

 

One Response to “Authoritarianism የሥልጣን ብልግና መገለጫዎች በኢትዮጵያ: በየቀኑ ነጠቃ፣ ማሠር፣ መፍታት፣ ዜጎችን ማንገላታት መደብደብ!”

Comments are closed.

%d bloggers like this: