“ሊመጣ ያለው ጥፋት ያሠጋናል”

12 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን ትብብር ለፍትኅ መ ግ ለጫ

 

ሚያዝያ 1 ቀን 2012

ሊመጣ ያለው ጥፋት ያሰጋናል በሚል ርዕስ ኢሰመጉ (የኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ጉባዔ) ባለፈው የካቲት ወር 2012 ዓመተ ምህረት በርዕሰ አንቀጹ ላይ ለሰጠው መግለጫ የተጠቀመበት ርዕስ ነበር ፡፡

በዚህም ሊመጣ ያለው ጥፋት ያሰጋናል በሚል የሀገራችንን አደገኛ ጊዜያዊ ሁኔታ አስመልክቶ ሰፋያለ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ዝቅ ብሎም ያለፈው ወርሃ የካቲት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ ታሪካዊ ገድሎች የታዩበት ወር እንደነበር ያስረዳል፡፡

በየካቲት ወር ከደረሰው አሰቃቂ የህዝብ እልቂት ተብሎ በታሪክ የተመዘገበው ፋሽስት ጣልያን በወረሃ የካቲት 12 ቀን በአንድ ጀምበር ከ30 ሺህ በላይ ንጹሃን የኢትዮጵያ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ያለቁበት ሲሆን ከዚህ በባሰ መልኩ የህዝብ እልቂት ሊያስከትል የሚችል ፋሽስታዊ አዝማሚያ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እየተስተዋለ ነው በማለት ስጋቱን ያብራራል፡፡

ይህንን እውነተኛ ስጋት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዉን ትብብር ለፍትኅ የምንጋራው እና ይመጣል ብቻ ሳይሆን አሁን ባለንበት ዘመን እየተፈጸመ መሆኑን በአንክሮ እየገለጽን ፤ ሀገራችን ወደለየለት ዘርን ማእከል ያደረገ እልቂት ውስጥ እየገባን እንደሆነ ብዙ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

ለዚህ በግንባር ቀደምትነት በጽንፈኞች ኢላማ ቀለበት ውስጥ የገባው በኢትዮጵያውነቱ የማያወላውል አቋም ያለው የአማራው ማኅበረሰብ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ እንደሆኑ ምስክር የሚያስፈልገው ጉዳይ አይሆነም።

ኢትዮጵያ በታሪኳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጦርነቶችን አስተናግዳለች ፤ በእነዚህ ጦርነቶች ሁሉ በኢትዮጵያውያን ሆንተብሎ የተቀሰቀሱ ሳይሆን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶችዋ የተቀነባበረ መሆኑ ነው ፤ በነዚህም ጦርነቶች ሁሉ ጠላቶቹን በድል አድራጊነት አሳፍራ መልሳለች ፡፡

በአሁኑ ዘመን ግን ልዩ የሚያደርገው ከአብራኳ የወጡ ዘረኞች ፤ በቀደመው የጋራ ታሪካችን ውስጥ ጉድፍ እጅ ያላቸው ከሃዲዎች እና የባንዳ ልጆች ፤ ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በመታገዝ የተረት ተረት ታሪክ ፈጥረው ህዝብን በህዝብ ላይ በማነሳሳት ብሎም ሀገርን የመናድ ሴራ በሰፊው ተያይዘዉታል ። ይህ በግልጽ የሚታይ ሽብርና ግድያ

ሥሙ በግልጽ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን የሚሰራ ፤ ከዚህ በፊት ዛሬ ወይም ነገ ፍትህ ሲጓደል ለኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳየት እና የተጓደለው ፍትኅ አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲሟላ የሚሰራ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ነው ።

  • ከኖሩበት ቀዪ መፈናቀልና መባረር ፤ ቤትና ንብረት መዘረፍ ፣ መታገት ፤ መሰደድ በአብላጫው ለአማራው ማህበረሰብ እድሉ ከሆነ ይሄውና ሶስት አስርት አመታት አስቆጥሮአል ።

ከሁለት አመት በፊት መልካም ዕድል ተገኘ ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ለውጥ አጋጣሚውን አጨልሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ለበለጠ አደጋ አጋልጦ ይገኛል ። ይህ የአንድነት ኃይሉን የሚያሰጋ ብሎም ሀገሪቱን ወዳልታሰብ እልቂት የሚመራ በመሆኑ ሁላችንንም ያሰጋናል ።

“መንግሥት አሸባሪ ነው”! “መንግሥት ስላደረሰው በደል ይቅርታ እንጥይቃለን”! “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው”!

“መግደል የተሸናፊነት ምልክት ነው”! “እመኑኝ እኔ አሸጋግራችኋለሁ”! የሚሉትን መፈክር አሁን ላይ ሁነን ዞር

ብለን ስናስታውስ በለውጥ ስም ምንኛ በአደባባይ የፖለቲካ ሥራ እንድተሰራብን ልብ ብለን ልናጤነው ይገባል።

እንዲያ እያሉ በአደባባይ እየሰበኩን ስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡ በኋላ የተደበቀ ባህሪያቸውን በግልጽ ተግባራዊ እያደረጉ ይታያሉ ። ሀገር ሲናድና ንጹሀን ሲገደሉና ስታገቱ እያዩ ደጋፊ መሆናቸውን በዝምታና በቸልተኛነታቸው አስምስክረዋል ። ይህ ሂደት የኢትዮጵያዊያን ተስፋ እንዲጨልም ምክንያት ሆኗል ።

በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት የሚሰራው የፈላጭና ቆራጭ አካሄድ የአንድ ማኅበረሰብን ጥቅምና ሉአላዊነትን በማስከበር ተግባር ላይ የተወጠረ ነው ቢባል ስህተት የሚሆነው እምኑ ላይ ነው?

በአጠቃላይ ሲገመገም የሽግግር መንግሥት በሁለት አመት ውስጥ ጥርጊያ መንገድ ማዘጋጀት ሲገባው በአገኘው አጋጣሚ በመጠቀም ስፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ በአደባባይ ክዶአል ቢባል ስህተት አይሆንም ።

የሚመሩትን ህዝብ መናቅም ሆነ አልፎ ተርፎርም ማሰቃየት ፤ መግደል ፤ ማሳደድ ፤ እምነቱ ላይ ደባ መፈጸም ፤ የአንድነት ምልክቱ የሆነውን ሰንደቅ አላማ መያዝ እንደወንጀል እየተቆጠረ የሚታይበት ዘመን ላይ ደርሰናል ።

ከታሪክ እንደምንረዳው በህዝብ ላይ ግፍ የፈጸሙ ግዙፍ ወታደርና ኃይል ገንብተናል ብለው የሚኩራሩት ሃያላን ተብዬዎች በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ ማወቅ ትምህርት ሊሆነን በተገባ ነበር ። በሰላሳ ዙር ለብለብ ስልጠና ህዝብን አምበርኮ መግዛት አያስችልም ። ይህ አዝማሚያ በእጅጉን ያሳስበናል ፣ ሁላችንም ልብ ልንለው ይገባል ።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እውቅና በጽንፈኞቹ የጦር መሪዎች እየተመራ በሌሊት ጎንደር ከተማን በመክበብ ኢሰባዊ ድርጊት ተፈጸሞአል ፤ ይህ ድርጊት ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ያስቆጣ ሃላፊነት የጎደለው እርምጃ ነው ብለን እናምናለን ።

ለዚህም ሲሰጥ የቆየው ምክንያት ፋኖን ትጥቅ እናስፈታለን የሚል እንደነበረ በግልጽ ተቀምጧል። በመሰረቱ ፋኖ ከአማራው አብራክ የወጣ የተደራጀ ወጣት ከመባል ሌላ ምንም አይነት ስም ሊሰጠው አይገባም ፡፡ ለመቋቋሙም ግልጽ የሆነ መመሪያ ያለው ፤ ለአማራው መብት የቆመና ያልተመለሱ የዚህን ማህበረሰብ ጥያቄና መብት የሚያስከብር ብሎም በአባቶቻችን ያቆዩልን ኢትዮጵያን ለመገንባት ታጥቆ በቅን እየሰራ ያለ የወጣቶች ማኅበር መሆኑ ይታወካል። ። ዛሬ በፋኖ ላይ ነገ ደሞ ቀጣዩ ማን እንደሆነ ትንበያ የሚያስፈልገው አይደለም።

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትብብር ለፍትኅ

ሥሙ በግልጽ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን የሚሰራ ፤ ከዚህ በፊት ዛሬ ወይም ነገ ፍትህ ሲጓደል ለኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳየት እና የተጓደለው ፍትኅ አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲሟላ የሚሰራ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ነው ።

መንግሥት የአማራው ወጣቶች በተለያየ ማኅበር በተደራጁበት ከተሞች ሁሉ አመራር ላይ ያሉ ወጣቶች እየተለቀሙ እየታሰሩ ናቸው ። ለዚሁ እንዲረዳው እስርቤቶችን አጽድቶ በአማራ ወጣቶች ማጎሪያ እያደረገ ነው ። እነዚህ ወጣቶች እና ፋኖ ባንክ አልዘረፉም ፤ ለልማት መስክ የወጡ የውጭ ሃገርና የሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ከነ መኪናቸው አላጋዩም ፤ ወጣቶችን እና አረጋዊያነንን አላገላቱም ፤ አልደፈሩም ፤ ጡትም አልቆረጡም ፤ በምዕራብ ወለጋ እንደታየው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት ተቃውመው ሰልፍ አልወጡም ። ጠመንጃ ይዘው መንግሥትን እናወርዳለን ብለው አልተነሱም ። ማለት የሚቻለው አዝማሚያው ወደለየለት ተጨማሪ የዘር ማጥፋት የሚደረግ ሂደት ነው ቢባል ስህተት አየሆንም ።

የዚህ ችግር ዋና መሰረታዊ ጥያቄ የአማራው ማኅበረሰብ የራሴ የሚለው የሚያስተባብረው ፤ ለዐላማውና ለአንድነቱ የቆሙለት ፤ በመሰረተ ልማት የሚያሳትፉ፤ የኔ የሚለው ፤ ተወካይ የሆነ ጠንካራ ድርጅት የለውም ። እዚህ ላይ ሳይሰመርበት የማይታለፈው ግን ቀደም ሲል በህዋት ዘመን እነታምራት ላይኔ ፣ እነተፈራ ዋልዋ ፤ እነበረከት ስሞኦን ጨምሮ እስከታች መዋቅር ድረስ የህዋት ሎሌዎችን በማስቀመጥ በሚልዮን የሚቆጠር የአማራውን ህዝብ አስፈጀተዋል ። በልማትና በማኅበራዊ እድገትም በዓለም ላይ የመጨረሻውን የደሀኅነትን ደረጃ ይዞ ይገኛል ።

አሁንም በግልጽ እንደሚታየው በአመራሩ በህዋት ዘመን የነበረውን አሰራር ዘይቤ በመከተል ወደባሰ እልቂት እየገባ ነው ። ጠ/ሚ በኢንሳ ውስጥ አብረዋቸው ደፋ ቀና እያሉ ለዘመናት ለህዋት ይሰሩ የነበሩና በኋላም አማካሪያቸው የነበሩትን የቅርብ ጓደኛቸውን ለአማራው ህዝብ አንስተው መድበዋል። ከጸጥታው ጀምሮ አስከታች ድረስ የሚያገለግሉ ምስለኔዎች ተስይመዋል ። በኛ እይታ ይህ ድርጊት ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑ እሙን ማስረጃ ነው ፡፡

መሰረተ ልማት ፤ ማህበራዊ ተቋማት ፤ መገናኛ ፤ ትምህርት የስራ አጡን ቁጥር በሚመለከት በአማራው ክልል በፊትም ሆነ አሁን ጨርሶ የሚነሳ ጉዳይ አይደለም ። ዋና ተብሎ የተያዘው ፋኖ በሚል ስም እና ሽፋን አማራውን ለበለጠ የዘር ማጥፋት ብሎም አማራውን ለመከፋፈል ተፈልጎ በርቀት ከማሸበር በራፉ ላይ ጦርነት መክፈቱ አማራጭ ሆኗል ።

አሁን ባለንበት ወቅት የዓለም ህዝብና መንግሥት አስከፊ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየታመሰ ያለበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል ፤ ከዚህ አስከፌ በሽታ ለህዝባቸው የቆሙ መንግሥታት ህዝባችውን ለመታድግ ሌትና ቀን እየተሯሯጡ ይገኛሉ ። የሃገራቸውም ጦር ኃይል መሳሪያውን አስቀምጦ ሞያ ያለው በሞያው ፤ ሙያ የሌለው ደግሞ በጉልበቱ ለህዝብ መከታነቱን እያሳየ እና እየተሰዋም ነው ።

መንግሥት ወደ 50ሺህ የሚጠጋ ሜካናይዝድ የሆነ ጦር ወደ ተለያዩ የአማራው ክልል በተለይም ወደ ጎንደር ከተማ አዝምቷል ። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለፋኖ ወይም ለአማራው ግድ የሌለው መንግሥት ይህንን ወቅት በኃይል ለመጠቀም ለምን ተመረጠ?

ሥሙ በግልጽ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን የሚሰራ ፤ ከዚህ በፊት ዛሬ ወይም ነገ ፍትህ ሲጓደል ለኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳየት እና የተጓደለው ፍትኅ አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲሟላ የሚሰራ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ነው ።

በፋኖ አሳቦ መንግሥት የከፈተው የትጥቅ ማስፈታት ዋናው ተልኮ በመጀመሪያ ፋኖን ቀጥሎ ህዝቡንና ገበሬዉን ትጥቅ ማሰፈታት ብሎም አማራውን ለመከፋፈል መሆኑን ለመተንበይ ነብይ መሆን አያስፈልገም ፡፡

ይህን የእብሪት ወረራ ሊያስከትል የሚችለውን ጦስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ህብረት ለፍትኅ የሚያወግዘው ሲሆን መንግሥትም ሊመጣ ካለው ጥፋት ሊቆጠብ ይገባል ።

ለማጠቃለል ያህል ከዚህ በታች የተቀመጡት ፍሬ ነገሮች መመለስ የተፈጠረውን ችግር ለማስወገድ መፍትሄ ይሆናል ብለን እናምናለን፤

 

1ኛ/ የፈደራል መንግሥትና ልዩ ኃይል በአስችኳይ ፋኖን ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል ስም ህዝብን ማሸበሩን እንዲአቆምና ክልሉን ለቆ እንዲወጣ፤

 

2ኛ/ አሁን ያሉት የክልሉ መሪዎች ህዝብ ያልመረጣቸውና ምንም አይነት የህዝብ ውክልና የሌላቸው ስለሆኑ ሰላምን ለማስፈን ሲባል ስልጣን መልቀቅ ይኖርባችዋል ። የአማራው ክልል የራሱ የሆኑና በወርዱና በስፋቱ የሚወክሉትን ከላይ እስከታች ያሉ መሪዎቹን ነጻና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲመርጥ መደረግ ይገባዋል ። ያሉት መሪዎች በእውቀትም ሆነ በስራ ልምድ አማራውን የሚመጥኑ አየደሉም ።

 

3ኛ/ የተከሰተውን የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በተመለከተ በክልሉ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ህዝባቸውን ክዚህ መቅሰፍት ለመታደግ ታሪካዊ ሃላፊነት አለባችው ። ለዚህም ህዝቡ (ከሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ) ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ።

መንግሥት ይህንን የወረርሽኝ ጊዜ የተጠቀመው ሆን ብሎ መሆኑ የታወቀ ነው ፣ በመሆኑም በየደረጃው ለሚመለከተው የዓለም ማህበረሰብ ማሳወቅ የግድ ይሆናል። በሕግም ፊት ሊያስጠይቅ የሚያስችል ወንጀል በመሆኑ በቸልተኝነት የሚታይ አይደለም ።

 

4ኛ/ በተለያዩ መድረኮች እኛም ድምጻችንን ከፍ አድርገን የጠየቅነው ስለታገቱ ወጣት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ ይሆናል ። በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከታገቱ ይኸውና ከ4 ወር በላይ ሆኖታል ። እስካሁን ምንም አይነት አሳማኝ ምላሽ ከመንግሥት አካባቢ እየተሰጠ አየደለም ፡፡ይህ ጉዳይ ከቤተሰብና ከሀገርም አልፎ የዓለም ስባዊ መብት ጥያቄ እያቀረበ ያለበት ጉዳይ ነው።

መንግሥት በብዙ መንገድ ጉዳዩን አደባብሶ ለማልፍ ይፈልጋል ፡፡ ወላጆችን ከማጉላላትም አልፎ እስከማሰር ደርሷል ። አሁንም መንግሥት ይህንን ጉዳይ ተከታትሎ ካሉም በህይወት ከሌሉም ጉዳዩ በትክክል ለህዝብ ግልጽ መደረግ ይኖርበታል ።

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትብብር ለፍትኅ

ሥሙ በግልጽ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን የሚሰራ ፤ ከዚህ በፊት ዛሬ ወይም ነገ ፍትህ ሲጓደል ለኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳየት እና የተጓደለው ፍትኅ አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲሟላ የሚሰራ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ነው ።

 

5ኛ/ በየስር ቤቱ የሚማቅቁ የሰራዊቱ አባሎችና መኮንኖች ፤ የአማራ ወጣቶች ፤ እንዲሁም የሌሎች ማህበረሰብ አባላት በአላቸው የፖለቲካ አመለካከታችው ብቻ በእስር ይማቅቃሉ ። እነዚህ የኅሊና እስረኞች በአስቸቋይ ከስር እንዲፈቱ አጥብቀን እንጠይቃለን ።

 

ኢትዮጵያ በልጆችዋ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን ትብብር ለፍትኅ

 

 

%d bloggers like this: