ኮቪድ-19ና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸምና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በኢትዮጵያ

27 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የኮቪድ-19 ወረርሸኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በኢትዮጵያ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ማስፈጸሚያ ደንብ በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተከናወነ የሕግና ሰብዓዊ መብቶች ትንተና

ግንቦት 2012
***********************************************************************

Legal/Human Rights Analysis of the Declaration of State of Emergency in Ethiopia in the Context of the COVID-19 Pandemic
7 May 2020
***********************************************************************

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመቆጣጠር መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀ ሲሆን ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን ተቀብሎ አፅድቋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አውጥቷል፡፡ ኢሰመኮ የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የማስፈፀሚያ ደንብ የግድ የሚያስብል አንገብጋቢ የማህበረሰብ ጤና ጉዳይ መኖሩን እና ይህም አካሄድ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን በይፋ በሕግ እንዲታወጅና ሕግን መሠረት አድርጎ እንዲተገበር ከሚያዘው የሕጋዊነት መርህ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ይገነዘባል፡፡

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ባደረገው ጥናት የተወሰኑ የአስቸኳይ ጊዜ ደንቡ ድንጋጌዎች ከኢፌዲሪ ሕገ መንግስትና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መርሆች ጋር የማይጣጣሙ ሆነው በመገኘታቸው፤ ከሕገ መንግሥቱና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ እንደገና እንዲመረመሩና ተገቢው ማሻሻያ እንዲደረግ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና ደንቡ የሚመነጩ አንኳር ስጋቶች እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊና ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች መርሆችን ሳይሸራረፉ ለማረጋገጥ አበርክቶ ያላቸው የኮሚሽኑ ምክረ ሀሳቦች የተካተቱበትን ሙሉ የሕግና የሰብዓዊ መብቶች ትንተና ሰነድ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ለማግኘት ከታች የተመለከተውን ማስፈንጠርያ ይጫኑ፡፡

ማስታወሻ፡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ በኮሚሽኑ በተዘጋጀዉ የሕግ ትንተና እና ምክረ ሃሳቦችን አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የማስፈፀሚያ ደንቡ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 93ን መሰረት በማድረግ እንዲሁም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 93 /4/ ሐ ስር እና ሀገሪቱ ፈርማ ባፀደቀቻቸው የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ የማይታገዱ (non-derogable) ናቸዉ ተብለው የተጠቀሱትን መብቶችና ነፃነቶች በማይጥስ መልኩ እና ወረርሽኙን ለመከላከል እና እንዳይስፋፋ ለማድረግ የሚያግዙ እርምጃዎችን ብቻ መሰረት በማድረግ የወጡ እንደሆኑ አስረድቷል። በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎቹ ዋነኛ አላማ መብቶችን ለመገደብ ሳይሆን “የመብቶች ሁሉ እናት የሆነውን በህይወት የመኖር መብት ለማስጠበቅ እና በዚህም እነዚህን እርምጃዎች ሳንወስድ ብንቀር ሊከሰት የሚችለውን ሌሎች በርካታ የዜጎች መሰረታዊ መብቶች የሚጣሱበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመከላከል እና ለማስቀረት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል” በሚል ገልጿል።

Legal/Human Rights Analysis of the Declaration of State of Emergency in Ethiopia in the Context of the COVID-19 Pandemic (7 May 2020)

On 8 April 2020, the Ethiopian Government declared a national state of emergency to combat the spread of the COVID-19 pandemic and the Federal House of Peoples’ Representatives approved the state of emergency proclamation on 10 April 2020. The Council of Ministers has subsequently issued the Regulation to implement the state of emergency. EHRC recognizes the public health emergency needs for the issuance of the State of Emergency Proclamation and Regulation by the Ethiopian Government which is also consistent with the principle of legality that any such emergency powers should be officially declared and exercised in accordance with the law.

On the other hand, a study by EHRC has identified some provisions of the Emergency Regulation which are inconsistent with the Constitution and international human rights standards and need to be considered for review and possible amendment with a view to ensuring their full compatibility with the Constitution and international human rights standards.

Click on the link below to download Amharic and English versions of the full analysis outlining key human rights concerns arising from the State of Emergency Proclamation and Regulation as well as EHRC’s recommendations.

Note:

In response to EHRC’s analysis and recommendations, the Office of Federal Attorney General explained that the state of emergency was proclaimed in accordance with Article 93 of the FDRE Constitution and in a manner that does not impinge on the rights and freedoms that are not subject derogations under Article 93 (4) (c) and human rights treaties ratified by Ethiopia and based solely on measures that are meant to prevent and control the spread of the pandemic. Furthermore, it stated that the primary purpose of the emergency measures is not to restrict rights, but to “protect the right to life which is the mother of all rights and to prevent the infringement of many other fundamental human rights that would otherwise occur if [government] failed to take these actions.”

 

 

/  Ethiopian Human Rights Commission

 

 

 

%d bloggers like this: