አውድማ:                                             (ሀ) እነማናቸው የተጎዱት? እነማናቸው የሚረዱት? ቤይሩት ያልታየው የኤምባሲዎች የማቋቋም ሚና!                                (ለ) ድንቄም ሃገራዊ ውይይት—ፓርቲዎች ከጠቅላዩ ጋር—አሽሙርና ሽርደዳዎች በገፍ!

30 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ትዕዝብት ለማን አለብኝነት!

 

በዚህ ገጽ ላይ በተቀመጠው ቪዲዮ ሁለት የውይይት ርዕሶች ተካተዋል:—

አንደኛ የሃጫሉ ሁንዴሣን ቤተሰቦች በኤምባሲዎች ጭምር ገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ተሰብስቦ ለመደገፍ ስለመታሰቡ የሚያስታውስ ነው! በእኩልነትና ብሔራዊ አንድነት የሚያምን መንግሥት ሌሎች የተጎዱት ኢትዮጵያውያንስ የሚለው ምነው ለአንድ አፍታ እንኳ ውል አላለውም?

የሃጫሉ ቤተሰቦች መረዳት አለባቸው! ሌሎች ከእርድ የተረፉትን የተፈናቅሉትን ወገኖቻችንንስ ማን ይታደጋቸው?

ዜግ ቻችንን ቤይሩት ያልታደገ ኮንሱሌት ነው አሁን ፍቱንነቱ ታምኖበት ለአውሮፓ ኤምባሲዎቻችን መልዕክት ቀረበ? ቤይሩት የቤት ሠራተኞች ስለሆኑ ይሆን የኢትዮጵያዊነት መብቶቻቸውን የተገፈፉት?

እሺ የኢምባሲዎች ልመና ይሳካ። ከቤቶቻቸው የተፈናቀሉትን ዜጎቻችንንስ ማን ይታደጋቸው? ስለዐባይ ግድብ ብዙ ይፎከራል? ፍትሕ የተነፈገውን ኢንጂነር ስመኘውንስ ቤተሰብ ማን ይታደጋቸው?

ሁለተኛው የውይይት አርዕስት ኢትዮጵያውያን ሊያፍሩበት የሚገባ ለብሔራዊ መግባባት ለመገንባት ተብሎ ጠ/ሚሩ የመሩት ስብሰባ ነው።

ይኸም ከውይይት ይልቅ—ሥልጣን ብዙ አላስፈላጊ አሽሙሮች ሽሙጥና ለተወያያቹ ያለውን ንቀት ያሳየበት ስብሰባ፣ ነበር። በውጭ ቁንቋ lampooning ይባላል!

ብሔራዊ መግባባት ይልቅ የቀረንንም ለማፍረስ የተወጠነ መስሏል። ልጆቻችንም መስማትና መማር የሌለባቸው!

ውድ ኢትዮጵያውያን እቺ ሃገራችን ወዴት እየተገፋች ነው?

ዐባይ ሚዲያም ከመዘጋቱ በፊት ይህን ቶሎ አዳምጡት! እኔ ረቡዕ ማታ ከተመለከትኩት በኋላ ሲበጠብጠኝ አድሯል። በማግሥቱም አንድ ወዳጄን አይተኸዋል ብዬ ስጠይቀው፡ እርሱም ብስጭቱን ነው ያሰማኝ!

ምነው ጠቅላይ ሚኒስትር?

 

 

 

 

%d bloggers like this: