ሃገር ወዳዱ መምህራችን ፕሮፌ መሥፍን ወልደማርያም አረፈ!

30 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

The late Prof. Mesfin Woldemariam (FANA)

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የጂኦግራፊ መምህር፣ ፖለቲከኛ፣ ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።”

በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪ በነበርኩበት ወቅት እ.ኤ.አ. 1969-70 ፕሮፌ መሥፍን ወልደማርያም አስተማሪዬ ነበር። ጊዜ ገፍቶ ትውውቃችንም ከተማሪና አስተማሪ ወደ መካሪነትና ጓደኝነት ተለውጦ ነበር።

አሜሪካን ሃገር ለሁለተኛ ዲግሪዪ ሥሠራም አበረታቺዬና መካሪዬ ስለነበር በብዙ መልኩ ጊዜውን ስለሠጠኝ የእርሱ ባለዕዳ ነኝ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥሠራ ወዳጅነታችን ቀጥሎ፡  እንዲሁም ውጭ ሃገር በዲፕሎማትነት በሠራሁባቸው ዓመታት ኒውዮርክ ብዙ ይመላለስ ስለነበር በጣም ተቀራርበን የኔም የቀድሞ ባለቤቴም የቅርብ ጓደኛችን ነበር።

በእኔ ዕይታ ፕሮፌሰር መሥፍን ደፋርና ለዚህች ሃገር ጥቅም የቆመ ሃቀኛ ሰው ስለነበር፡ ማንነቱን በሚገባ ከገለጸባቸው የሚዲያ ገጾች፡ ከጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ጋር  በአባይ ሚዲያ “እንግዳችን” ፕሮግራም የነበረው የሃሣብ ልውውጥ (https://www.youtube.com/watch?v=WNke6uMkOKc) እጅግ በሚገባ ማንነቱን ያረጋገጠበት፣ የሃገራችንንና የባለሥልጣኖቻችንን ሽፍንፍንም ያጋለጠበት ነበር ማለት እችላለሁ።

ለፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም ያለኝ ፍቅርና አክብሮት ዘለዓለማዊ ነው!

 

ፕሮፌሰር መሥፍን ስለማዊ የዕረፍት ጊዜ ይሁንልህ!
የእኔ ኢትዮጵያ ባንተ ትኮራለች!

ከፍያለው ገብረመድኅን

 

%d bloggers like this: