ሣህሉ! ተቀበል ምላሼን በትዊተር በጠየቅኸኝ መሠረት Sahelu @Sahelu_bs

6 Oct

የኢትዮጵያ ቀደምት ጉዳዮችና ተግባሮች ምንድናቸው ለሚለው የሃገሪቱ አሠራር ምንነት ቀጥተኛ/ትክክለኛ መልስ መሥጠት አይቻልም። ጠ/ሚሩ ድንገት የመጣባቸው ሃሣብ የሃገሪቱ ቀዳሚ ዓላማ ተደርጎ ሲሠራ ይታያል።

በዘመናዊ የመንግሥት አሠራር፣ ማቀድ፣ ያለውን ሃብትና ንብረት አብቃቅቶ በተግባር መተርጎም ምርጡ መንገድ ሲሆን፣ የመስቀል አደባባይ ዐይነት ፕሮጄክት፣ በድንገት ቤተ መንግሥቱን ውስጡንና ውጭውን እንደሸገር ሁሉ ማስዋብ ቅድሚያ እየተሠጠው በሃገሪቷ ገንዘብ አጠቃቀም ረገድ አላስፈላጊ ሽሚያ ፈጥሯል።

ይህ ከሆነ ግን እንዴት ነው ሥራውና  ውጤቱ ፊናንስ የሚደረገው? እንደሰማነው የተደረገው ተደርጎ ግን አጋጣሚ ሲገኝ የመንግሥት ኃላፊዎች ድል እንዳደረጉና፤ ጥሩ ውጤት መገኘቱ ይነገረናል!

አብዛኞች ሌሎች ሃገሮች የተወሰኑ ዓመታት ዕቅድ አላቸው። ለዚህ ገንዘብ በበጀት ይያዛል። ይህንን ፕሮግራም አስፈጻሚዎች እንዲከታተሉት በሕግ ይጸድቃል። ብሄራዊ ኦዲተር ጂኔራል በዚህ ላይ ለፓርላማ ሪፖርት በማቅረብ የሥራ አፈጻጸሙን ይገመግማል።

እኛ ሃገር የመንግሥት አመእራር ለኦዲተር ጄነራሉ ጊዜ እንደሌው በጠ/ሚሩና አፈ ጉባዔው ተዶልቱ ሃገሪቱ 76 ቢሊዮን ብር በጀት ስታፀድቅ ኦዲተሩ ድርሽ እንዳይሉ ኮቪድ ምክንያት ተደርጎ ነገሩ ሁሉ ተደነቃቅፎ አረፈው—ሪፖርተር እንደዘገበው።

ፕሬዚደንቷ ያለፈውን ዓመት በስኬትና  ጉድለት የታጀበ ነው ቢሉንም፣ (ሀ) ዲፕሎማሲው ጥሩ ውጤት ማስገኘቱን ሲያነሱ አስደንግጦኛል። (ለ) የዓለም የቡናና የወርቅ ዋጋ ሲያንሠራራ የኛ ሥራ ውጤት የፎሬክስ ገቢያችንን እንዳበራከተ ተደርጎ ተነስቷል።

እኛ ሃገር ግን የዕቅድና የሥራ ውጤት ሣይሆን፣ ከላይ እንደተጠቀስው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚያስደስቸው ነገር ሲፈጸም ነው የምናየው።

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ በኩል ችግር እየገጠማት መሆኑ ቢታወቅም፣ ድል እንዳደረገች ተደርጎ ሲነገር መስማቱ አይመችም። በኖቤል የሰላም ሽልማት በሚመራት ሃገር፣ እሥራትና የስብዓዊ መብቶች ጥሰትና የዜጎች ግድያ እይተባለ በተደጋጋሚ ይነሣል—መፍትሄው እስካሁን ባይታወቅም።

የሕግ የበላይነትን ፕሪዜደንቷ ቢያነሱም፣ ያለፈው ዓመት ጥቅምት ወር 86 ሰዎች ቢገደሉም ተጠያቂ የተደረገ ግለሰብ የለም–ለሕይወታቸው መጥፍፋት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ቢታወቅም! መንግሥት የዜጎችን ድኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን ሲወጣ አላየንም! ”በአጠቃላይ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ ሃገራዊውን ሰላም የማረጋገጥ ሥራ ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ ይሰራል” ነው ፕሬዚደንቷ ያሉት። ምንድነው የታሠበው? የአብዮት ጥበቃ፣ ወይንስ ለብልፅግና ዘብነት?

ፕሬዚደንቷ ትክክል ናቸው፤ የዲሞክራሲ መርሆች ዜጎችንና መንግሥትንን አቀራርቦ በመቻቻል እንዲሠሩ የሚያደርግ ነው—ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ላይ ያለው ሥልጣን የሌለውን መዝለፍ እየተባባሰ ቢሆንም!

እጅግ አዝናለሁ ለጠ/ሚ ዐብይ ምንጊዜም ፖለቲካ ተቃዋሚው ተፋላሚያቸው ነው። ተፃራሪ ነውና በስብሰባ አዳራሽ እንኳ ከፍ ዝቅ እያደረጉ ማብጠልጠልና አላስፈላጊ ያልሆነ ከእርሳቸው የማይጠበቅ አሽሙርተኝነትና ዘለፋን ሲወረውሩ ማዳመጥ የተለመደ ሆኗል። ይህ የመንግሥታቸው ችግር አይደለምን? እርሳቸው ሲመሰገኑ፣ ሌላው ለምን ይብጠለጠላል?

ይህበ ምንም መልኲ የሃገር አመራር ጥበብ ወይንም ዲፕሎማሲ አካል ነው ብዬ አላምንም! በሌሎች ስሞቹ ማስፈራራት ወይንም ማሸማቀቅ ነው! @EthiopiaMoment

EthiopiaObservatory (TEO)

%d bloggers like this: