ዕሠይ ኢትዮጵያ! ሠራዊታችን መላ ትግራይን ተቆጣጥሯል! ወንበዴዎቹን እንደ ዐይጥ ከየጉድጓዳቸው ነቅሶ መልቀም ለነገ የማይባል ግዴታችንነው!

29 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በሕወሃት ወንበዴዎች ላይ የተቀደጀቻቸው ድሎች ለዜጎች የአዲስ ሕይወትን ተስፋ ይፈነጥቃሉ። አዳዲስ ግዴታዎችን በመንግሥት፥ ሕዝብና ሃገር ላይም ያስከትላሉ!

ሃገሪቱ በነፃነትና ዲሞክራሲ መንገድ እንድትጓዝ: እያንዳንዱ ዜጋም በዲሞክራሲያዊት ሃገሩ ያለፍርሃትና ሥጋት እንዲራመድ፣ ማለትም ዜጎች የሠጭ ተቀባይ ሣይሆኑ በራሳቸው መሪነትና ተጠያቂነት ሕልማቸውን ተግባራዊ የሚያደርጉበት የአስተማማኝ ጅማሮ ፈር ቀዳጅ ተደርጎ መታያት ይኖርበታል። ለዚህም ነው የዛሬውና የሚከታተሉት ድሎች፥ እስከዛሬ የሕወሃት ዘራፊዎችና ሸፍጠኞች ኢትዮጵያውያንን የነፈጓቸውን የዴሞክራሲና በትክክልም ድህነት ከኢትዮጵያችን የሚያስወግድ መንግሥታዊና ሁሉን አቀፍ እኩልነትና ልማት ላይ የምታተኩር ሃገርና ዜጎች በመሆን፡ ለተቃጠሉት አሥርታት ማካካሻ ለመሥራት እንገደዳለን።

የሕወሃት ሥልጣን ላይ ለዘላለም ሃገራችንን መዝረፍ ብቻ ሣይሆን፡ እነርሱ ለእነርሱ— ኢትዮጵያውያን በዘርና ዘርማንዘር በመከፋፈል—ኢትዮጵያ አንድ ሃገር እንዳትሆን የማድረግ ዓላማቸውን በተግባር ለመተርጎም ‘አንድ ሐሙስ…’ ነበር የቀራቸው በሚለው አባባል ብናስቀምጠው ማጋነን አይሆንም!

ይህም ድል ዜጎች ያገኙትን የወደፊቱን ተስፋና አዲሱን የድል ፍሬ የሚመዝን፥ የሚተርክና መሆን ይኖርበታል። ለዜጎች አዲሱን ተስፋ የሚያማትሩበትና በራሳቸውም መሪነት ሕልማቸውን ተግባራዊ የሚያደርጉበት መሆን ይኖርበታል።

ለዚህም ነው የቅዳሜውና የሚከታተሉት ድሎች፥ ወንበዴዎቹ ዘብጥያ ሣሉ ሁሉም ዜጎች በነፃንትና እኩልነት በጥረቶቻቸው ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሕልሞቻቸውን ዕውን ማድረግ እንዲችሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ ቃል የሚገባበት!

የሃገሪቱ ዳኞችና ፍርድ ቤቶችም— ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማየት እንደጀመርነው—በአሣፋሪነት ለፖሊስ ፍላጎት ተገዥ መሆናቸው ተወግዶና ተኮንኖ፣ የሕወሃት ከሃድያን በሠራዊታችን ጥንካሬ እንዳበቃላቸው፣ ይህም ብልግና እዚህ ላይ ተኮንኖ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃው ይባል! የድርጊቱ ፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች ለፍርድ ይቅረቡ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካሁን ዲሞክራሲንና ሙሉ ነፃንትን የሚያውቃቸው በወሬና የማይተገብሩለት መንግሥታት በሚገቡለት ባዶ ተስፋ ብቻ ነው! ውስጣዊ ግጭቶችና የመንግሥትም ሆነ ቡድኖች በሚሠጧቸው ባዶ ተስፋዎች ወጣቶችን የሚያንከላውሱት ተወግደው፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃገሩ ያለፍርሃት በነፃነት እንዲራመድ ሁኔታዎች መመቻቸት ይሆርባቸዋል።

ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሰል የውንብድና ቡድኖች እየተዘረፈና እየተገደለ መኖሩ—ቤተሰቡ ፍትህ እንኳ ማግኘት የማይችልበት ሁኔታ—የሕወሃት ወንበዴዎች ጋር አብሮ ማክተም አለበት!

ከወያኔዎች ቀጥሎ የሕዝባችን ምሬቶች ፖሊስ ሠራዊት ውስጥ ተሠግሥገው የዜጎችን ሕይወት በየአስባቡ የሚቀጥፉ ወንበዴዎች በዩኒፎርምና ሥልጣናችውን ተገን በማድረግ በእነርሱ የሚጠቀሙ ሹማምንትም በመላ ሃገሪቱ ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል!

ኢትዮጵያን በልማትና በዲሞክራሲ ጎዳና ማራመድ የሚቻለው መዋቅሮቻችን —እንቅልፍ ላይ ሆኖ ዜጎችን የሚያስጠቃው ፓርላማ ጭምር—ከእንቅልፋቸው ነቅተው ለተቋቋሙባቸው ዓላማዎች በጽናት መቆም ሲችሉ ብቻ ነው!

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ መንግሥትም በእያንዳንዷ እንቅስቃሴው፥ ከሕግ በላይ አለመሆኑን በቅጡ ቢገነዘብ፡ ሃገራችን አንድነቷ፥ ተስፋዋና ጥንካሬዋ ይፈረጥማል!

ድል ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!

ዘረኞችና ከፋፋዮች ይውደሙ!

ኢትዮጵያ ሠላሟና ልማቷ ይብዛ!

%d bloggers like this: