አይ ሕወሃት! አቤት ቅሌት!አ ይ ጊዜ!

10 Jan

The Ethiopia Observatory (TEO)

ስብሃት ነጋንም ኣጓጉል አደረግሽዉ አይደል! ሰዉ ነንና ይህን ፎቶ ያየ ሁሉ ሠቅጠጥ ይላል!

ስብሃት ነጋ ሌላ ሰው ቢሆን ‘አይ ምሥኪን’ ብዬ ውስጤ ትንሽ መራራት ሊሰማኝ ይችል ነበር! ነገር ግን ቀበጦቹ/ባለጌዎቹ ሕወሃቶች ኢትዮጵያን ልታከናንቡ ያዘጋጃችሁላትን ውርደት በዚህ በሚታየው መልክ ራሳችሁ ተላበሳችሁት!

የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ክብሩ ይስፋ! 

ምርኮኛዉ ስብሃት አዲስ አበባ ደርሶ ወደ ‘መጨረሻ’ ማረፊያው ሲወስድ! (Picture credit: Fana)

የሕወሃቱ ስብሃት ነጋ! የክፋትህ መጠን~~አነተም ጓደኞችህም~~በጠቅላላው ሁላችሁም የተጠናወታችሁ መጥፎነት፣ ሌላው ቀርቶ በአሁኑ ሰዓት ሕዝባችን ደግነቱን እንዲነፍጋችሁ አድርጓችኋል! ዛሬ ስብሃት ነጋ በወከላችሁ ሃፍረትና አመድ መሰል ሁኔታውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊቱን ቢያዞር አልገረምም!

የሚገርመው ስታንጓጥጠው የኖርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ዛሬ በአንድ እግርህ ብቻ ካልሲ አድርገህ፡ እውነተኛውን ማንነትህን በሚገልፅ መልክ መቅረብህ፣ ትላንት አንተ የነበርክበት ቦታ ዛሬ እንዳንተው ሁለት እጆቻቸውን ኪሶቻችው ውስጥ ሰንቅረው—’አለኛም ሰው የለም ባዮቹን— ‘ከኔ ሁኔታ በጊዜ ትምህርት ውሰዱ!’ በላቸው! ‘አሁን የኔ ለፈጸምኩት ግፍ፡ ጥጋብና ወስላታነት የምከፍለው ዕዳ ነው!’ በላቸዉ!

በዚህ እርጅና ባዳከመው ዕድሜ ተከብረህ መኖር ሲገባህ፣ ያላጣኸውን ስታሳድድ፣ ሁሉንም አጣኸዉ! ለዓመታት ያንተና የጭፍሮችህ ‘መሬት አልበቃ አለችን’፡ ሃገራችንን ብዙ ጎድቷል! ብዙ ወገኖቻችን ሕይወቶቻቸውን አጥተዋል!

የኢትዮጵያ አምላክ ግን ኢትዮጵያን እንደማይጥላት አሳይቷል! የትግራይ ሕዝብስ በምን ዕዳዉ?

ኢትዮጵያ ይህ በሽታ ከሥሩ እንዲነቀል ትሻለች!

እኔም ጆሮዬን አቁሜ የቀሪዎቹን ወንበዴዎች ፍፃሜ ጠብቃለሁ!

የኢትዮጵያ መከላካያ ሠራዊት በዳዮቿን ለመቅጣት በቀላሉ ሰው ከማይደርስበት ድረስ ወርዳችሁ—ፊቱ ሳይላላጥ፡ የቡጢ ምልክት ሳይኖርበት፡ ሳይሠበር፡ ሳይገረፍና ሳይጎሳቆል መምሰል የሚገባውን አስመስላችሁ በማቅረባችሁ—በምወዳትና በምኮራባት ብቸኛ ሃገሬ ስም ፍቅሬንና ከበሬታዬን እገልጽላችኋለሁ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

%d bloggers like this: