Archive | corruption in Ethiopia RSS feed for this section

የሕወሃት፡ የጸረ-ሙስና ኮምሺንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ለዛ ቢስ ጨዋታ

23 Nov

በአዘጋጁ ዕይታ፡

ሙስና በሃገራችን ክፉኛ የተስፋፋ በሽታ ነው። በ2013 ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናልም ኢትዮጵያን ከ177 ሀገሮች 111ኛ ሙስና የተጧጧፈባት ሃገር ብሎ መሰየሙ ይታወሳል። እንደተለመደው ዛሬም የሕወሃት ጥቅም አስከባሪ የሆነው ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ለሕወሃት ዘራፊዎች እንዲያመቻቸው፡ ችግሩን ለአፋር፡ ሶማሌና ቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝብ አሳቢ ይመስል የእነርሱ ብቻ ችግር ለማስመሰል ሲሞክር ከዛሬው የሪፖርተር ዘገባ ይታያል።
Continue reading

TRANSPARENCY INTERNATIONAL data show Ethiopia suffers from high level of bribery

7 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Latest research shows that Ethiopia’s citizens and institutions have been suffering from high levels of bribery. Not surprisingly, Ethiopia’s score on the 2013 Corruption Index Ethiopia is 33, where 100 means very clean and 0 means highly corrupt.
Continue reading

የከፉ መዝባሪዎች ቆመው ክፋቱ የጣለው ላይ ምሣሩ ዘመተ

6 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው።
Continue reading

ኢትዮጵያ በሙስናና በፕሬስ አፈና በዓለም ከሚታወቁት ተመሳሳይ አገሮች መካከል መስለፏ ሊያስገርም አይገባም፤ ያልዘሩት አይበቅልምና

4 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory

ማክሰኞ ኅዳር 3፣ 2013 ይፋ የተደረገውን የትራንስፔረንሲ ኢንተርናሽናልን ዓመታዊ ዘገባ መነሻ በማድረግ ሪፖርተር፡ “ኢትዮጵያ ከሙስና ጽዱነት ተርታ ውጭ ከሆኑና በሙስና ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈረጁ አገሮች አንዷ ሆና መገኘቷን ይፋ” መደረጉን መንሳኤ በማድረግ ይህንን አሳፋሪ ዜና ሕዝብ በዛሬው ዕትሙ ለኢትዮጵያ አቅርቧል።
Continue reading

የኢትዮጵያ ሙስና ስፋትና ጥልቀት አሁን ገና ሥዕሉ በትንሹ መታየት ጀመረ! ግን ማነው ያልተነካካው?

23 Oct

በታምሩ ጽጌ ከሪፖርተር – Posted by The Ethiopia Observatory

ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ያስገቡት 20 ድርጅቶች:

  ኒያላ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያና መለዋወጫ ዕቃ አስመጪ፣ ፔትራም፣ ሞኤንኮ፣ ጌታስ ትሬዲንግ፣ አልሳም፣ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ አይካ አዲስ (የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ)፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ፣ ሆላንድ ካርስ (ከስሮ ተዘግቷል)፣ ቶታል ኢትዮጵያ፣ ሚድሮክ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን፣ ድሬ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ፣ ኢትዮ ሌዘር፣ ኢትዮ ቆዳ ፋብሪካ፣ ባሰፋ ትሬዲንግ፣ ነፃ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ጌታስ ኢንተርናሽናልና ኮሜት ትሬዲንግ ናቸው፡፡
  Continue reading

ኮሚሽኑ የተሿሚዎችን ሀብት ለሕዝብ ለማሳወቅ የሶፍት ዌር ስምምነት ፈረመ – ለመሆኑ በምኑ ይፋ ለማደርረግ ነበር ለታህሳስ 2012 ቃል የገባው?

20 Aug
  የአዘጋጁ አስተያየትት:

  ኮሚሽኑ የክትልና የምርመራ ሥራውን በጥንቃቄ መሥራት እንዳለበት ይታመናል። ከላይ እንደተጠቀስው፡ በታህሳስ 2012 ላይ ምዝገባዎቻችንና ማጥራቱን አጠናቀናል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የባለሥልጣኖች ሀብት ለሕዝብ ይፋ ይድረጋል ሲሉ ከርሞ አሁን ደግሞ የሶፍት ዌር ምክንያት ይዞ ቀርቧል።

  የእናቴ ቀሚስ እያደናቀፈኝ ነው እንዳይመስልበት: እስከናካቴው ቢተው ይሻላል – ምንም ለውጥ ላያመጣ – በተለይም ተጨማሪ የሀገሪቱ ገንዝብ በዚህ ዐይነት ጨዋታ ከሚባክን!

  እውነቱን ለመናገር ይሄ ነገር ምንም አላማረኝም!

 

Posted by The Ethiopia Observatory

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 14 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሿሚዎችን ፣ የተመራጮችንና በሕግ ግዴታ የተጣለባቸውን የመንግሥት ሠራተኞች የሀብት ምዝገባ በመረጃ ቋት የሚይዝበትን ስምምነት ከአንድ ኩባንያ ጋር ዛሬ ተፈራረመ።
Continue reading

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

18 Jun
  የአዘጋጁ አስተያየት፡

  እዚህ ጽሁፍ ውስጥ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ከዚህ በፊትም አንዳንድ ንክኪ የተሰማባቸው እንድመሆናችው፡ አግባብ ያለው ምርመራና ምላሽ የሚጠይቁ ናቸው። አንደኛ ሟቹ መረጃ ይዘው መምጥታቸው ይታወቃል። ለምን ጥበቃ ወይንም ሽፋን አለተሰጣቸውም? ለምን ቀብራቸውስ ተፋጠነ ምርመራ ሳይደረግላቸው?

  ሁለተኛ፡ እንደሚታወቀው፡ ጋምቤላ የብዙ ንጹሃን ዜጎች ደም ፈሷል። ሶስተኛ፡ በአገሪቱ ንበረት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ ተፈጽሟል። መንግሥት ምን አድረገ?

  መንግሥት ትክክለኛና ግልጽ ምርመራ በማካሄድ ውጤቱን ለቤተስቦቻቸውና ለሕዝቡ ይፋ ማድረግ ይጠበቅበታል!

  ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ኮር የማፊያ ቡድን እንቅስቃሴ እያደረገ ነውን ለሚለው ጥያቄ አሉታዊ መልስ ለመስጠት ያዳግታል!

Continue reading

%d bloggers like this: