Archive | Ethiopa RSS feed for this section

የሥዮም ተሾመ ደብዳቤ ለኢንጂ. ታከለ ኡማ: ም/ከንቲባው 3ኛ ቤታቸውን ሊቀይሩ ዝግጅት ላይ ናቸው! እቺ እውነትም እየታደሰች ያለችው ኢትዮጵያ ናትን? ሕዝብ በቁሙ ሲታረድ እነማን ነን? የት ነው የምንሄደው አይቀሬዎች ናቸው!

31 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ይድረስ ለኢንጂነር #ታከለ_ኡማ 
=====================
ይህ መልዕክቴ እንዲደርስዎ በቀና መንፈስ እንዲያዩትም በትህትና እጠይቃለሁ። አራት ኪሎ እሪ በከንቱ መጠጊያ የሌላቸው እናቶች ህፃናቶቻቸውን ይዘው ጎዳና ላይ ወድቀዋል። ህፃናቱን እና የእናቶችን እንባ በዚህ ሁኔታ ማየት ልብ ያደማል እረፍት ይነሳል። በእርስዎ አስተዳደር ስር ያሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እነዚህን ምስኪን መጠጊያ የሌላቸው ድሆች ህገወጥ ናችሁ በማለት መጠለያቸውን ድምጥማጡን አጥፍተው በዚህ ሁኔታ ለስቃይና ልእንግልት ዳርገዋቸዋል።

እርስዎ በዶክተር አብይ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ከመሾምዎ በፊት ኪራይ ቤቶች አስተዳደር በሰጠዎት ቤት ይኖሩ እንደነበረ አውቃለሁ። ስልጣን በተሰጥዎ ማግስት ግን ያ ባለ ሶስት መኝታ አፓርታማ ለክብርዎ አይመጥንም በማለት ከመንግስት ካዝና ከነዚሁ ዛሬ እያነቡ ጎዳና ከወደቁ እናቶች በታክስ ከተሰበሰበ ገንዘብ በወር 140 ሺህ ብር ገደማ ኪራይ ወደሚከፈልበት ክብርዎን ይመጥናል ወደተባለ ቤት መዘዋወርዎም ይታወቃል።

ይህም በራሱ በቂ ሆኖ አልተገኘምና ሳር ቤት የሚገኘው የጀነራል አደም መኖሪያ የነበረው ግዙፍ ቪላ ቤት በከፍተኛ ወጪ እድስት ተደርጎ እየተዘጋጀልዎ እንደሆነም በሚገባ አውቃለሁ። የተከበሩ ከንቲባ ኢትዬጵያ አቅም ኗሯት ከዚህም በላይ ብታደርግልዎ ባልከፋኝ ነበር። ነገር ግን እርስዎ በዚህ ደረጃ ሲከበሩ ህፃናት በገዛ አገራቸው በእርስዎ አስተዳደር ህገወጥ ተብለው ሜዳ ላይ ሲወድቁ ማየት ግን እውነት እልዎታለሁ የግፍ ሁሉ ግፍ ነውና ስለፈጠርዎ እነዚህን ህፃናት ይታደጓቸው።

ዐቢይ አሕመድ ከሰኔ 18/2010 የፓርላማ ንግግሩ ወዲህ ሌላው ያረካኝ የወደድኩለት መልዕክቱ!

29 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

“ዓለም የማይሠጣትን ሰው አታቅም፤ ያልሠጣትን ሰው አትቀበልም፣ አታገንም፤ አታከብርም፤ ዓለም ገብጋባ አይደለችም፤ ግን ለሚሠጥ ሰው ክብር አላት፤ ያልሠጣትን ስው ከነመፈጠሩም አታስታውስውም!”

 

 

በዚያ ቀውጢ ሰዓት የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ አደንዛዥ ዕፅና ወርቅ ይነግድ ነበር! ባያስገርምም ባፋጣኝ ማጣራቱ ነገን መቆጣጠር ያስችላል!

25 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

መንግሥትና ኦነግ ተኩስ በማቆም የኦነግ ሠራዊት በጥቂት ቀናት ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ አሳለፉ! ኦነግ በቃሉ ለመጽናት ብርታት ያገኝ ይሆን?

25 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ኣባ ገዳዎች የአርቅ ስምምነቱ ላይCredit: Fana

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ማቆም ውሳኔ አሳልፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኦነግ ሰራዊት በጥቂት ቀናት ውስጥ ካለበት ጫካ ወጥቶ ወደ ካምፕ እንዲገባም ውሳኔ አሳልፈዋል።

መንግስት እና ኦነግ ውሳኔዎችን ያሳለፉት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት በዛሬው እለት በአምቦ ከተማ ባዘጋጀው የእርቅ ስነ ስርአት ላይ ነው።

በዛሬው እለት በተዘጋጀው የእርቅ ስነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ወጣቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እና የአምቦ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይም መንግስት እና ኦነግ በኦሮሞ ባህል መሰረት ኮርማ በሬ በማረድ በይፋ የእርቅ ስነ ስርአት ፈጽመዋል።

ሁለቱም አካላት ከዚህ በኋላ ወደ ደም መፋሰስ እንደማይገቡ እንዲሁም ያለፈውን ነገር በመተው ስለወደፊቱ ብቻ በጋራ ለመስራት በእርቅ ስነ ስርዓቱ ቃል ገብተዋል።

በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከስምምነት የደረሱባቸው ዝርዝር የውሳኔ ነጥቦች ይፋ ተደርጓል።

ዝርዝር ስምምነቱንም የቴክኒክ ኮሚቴውን በመወከል የፖለቲካ ተንታኝ እና አክቲቪስት አቶ ጀዋር መሃመድ ያቀረቡ ሲሆን፥ ሁለቱንም አካላት በማነጋገር በዝርዝር ውሳኔው ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።

በዚሀም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ጦርነት መቆሙን አስታውቀዋል።

ወደ ግጭት የሚያስገቡ ትንኮሳዎችን ሙሉ በሙሉ መከልከሉን እንዲሁም አንዱ በሌላው ላይ ከዚህ በኋላ መግለጫ ማውጣት ሙሉ በሙሉ መከልከሉንም ገልፀዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሰራዊት ካለበት ቦታ በሙሉ ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ መወሱን እና ይህም ከበቂ ጥበቃ ጋር በክብር አቀባበል ወደ ካምፕ እንዲገቡ እንዲደረግ መወሰኑንም ገልፀዋል።

ሰራዊቱን ወደ ካምፕ የማስገባት ስራም በ20 ቀን ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለበት ተወስኗል ያሉት አቶ ጃዋር፥ ከእዚህም ውስጥ 10 ቀናት ዝግጅት የሚደረግበት፤ ቀሪው 10 ቀናት ደግሞ ሰራዊቱ ወደ ካምፕ የሚገባበት ነው ብለዋል።

ወደ ካምፕ የማስገባት ሂደቱም በሶስት ደረጃዎች ተከፋፍሎ ይካሄዳል ያሉ ሲሆን፥ በዚህም የመጀመሪያም ወደ ወረዳ ከተሞች እንዲሰባሰቡ፣ በመቀጠል ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ እንዲገቡ ማድረግ በመጨረሻም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት አቀባበል ማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህ ወቅት ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እና ይህን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም አካል ላይ መንግሰት ህግን የማስከበር ስራ እንዲሰራ ተፈቅዶለታል ብለዋል።

የኦነግ ሰራዊት ካምፕ ከገባ በኋላም አጠቃላይ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጎ የመንግስት የፀጥታ አካላት መቀላቀል ለሚፈልጉ እንደሚያሟሉት መስፈርት እንዲቀላቀሉ መወሰኑንም አስታውቀዋል።

ከዚህ ውጭ ያሉት ደግሞ እንደየፍላጎታቸው በፈለጉት ዘርፍ ስልጠና ወስደው እንዲሰማሩ ድጋፍ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

ወደ ካምፕ የገባው ሰራዊትን አያያዝም የቴክኒክ ኮሚቴው በየጊዜው እየሄደ የሚጎበኝ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሰራዊት አባላት እስካሁን ላጠፉት ጥፋት ይቀርታ መደረጉንም የቴክኒክ ኮሚቴው ተወካይ አቶ ጀዋር አስታውቀዋል።

ከላይ የተዘረዘሩትን ስምምነቶች ጥሶ የተገኘ ማንኛውም አካል ላጠፋው ጥፋት ተጠያቂ እንደሚደረግም ነው የገለፁት።

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ያዘጋጀው የእርቀ ሰላም መድረክ ባሳለፍነው ማክሰኞ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል መካሄዱ ይታወሳል።

በመድረኩ ላይም የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በመካከላቸው የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።

እንዲሁም የኦነግን የታጠቀ ሰራዊት ትጥቅ ለማስፈታት እና ሰራዊቱን ወደ ካምፕ ለማስገባት እንዲሁም ሌሎች ስምምነት ላይ የተደረሱ ጉዳዮችን ለማስፈፀም 71 አባላት ያለው የቴክኒክ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፥ የቴክኒክ ኮሚቴውም ከምሁራን 11፣ ከአባ ገዳዎች 54፣ ከኦዲፒ 3 እንዲሁም ከኦነግ 3 አባላት ያለው ነው።

 

 

“ለውጡ አሁንም ሕዝባዊ መሠረት” እንደያዘ ነው የሚለው ኢሕአዴግ “ሕዝባዊ መሠረት የሌላቸው ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦችም በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ በመሆኑ ለለውጡ ተግዳሮት” መሆናቸውን ገለጸ

20 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ  ጥር 10/2011 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ሰላምን፣ የሕግ የበላይነትንና ፍትህን ማረጋገጥ እንዲሁም ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ ማድረግ ቁልፍ ተልዕኮ መሆኑን አስታወቀ።

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከጥር 7 እስከ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ያካሄደውን መደበኛ ስብሰባ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ግምገማ በማካሄድና አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ ገልጿል።

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዳስታወቀው፤ በኢትዮጵያ በመስኖ ልማትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የተቀዛቀዘውን አገራዊ ኢኮኖሚ ለማነቃቃት መረባረብ ይጠይቃል።

ማንኛውም ለግጭትና አለመረጋጋት የሚዳርጉ ሁኔታዎች በግልጽ በመለየት በአስቸኳይ መታረም እንዳለባቸው የጠቆመው መግለጫው፤  ሁሉም የግንባሩ አባል ድርጅቶች በዝርዝር ገምግመው የጋራ ባደረጉት ስምምነት መሠረት በተግባር እንዲመሩ አሳስቧል።

መንግስትሕግን የማስከበር ቁልፍ ኃላፊነቱን በጥብቅ መወጣት እንዳለበት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል።

ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ ሌብነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፈጽሞ እንዳይደገሙ በቂ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የገለጸው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው፤ ለዚህ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ዝንባሌዎችን በሁሉም የሥራ መስክ እየፈተሹ መጓዝ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጧል።

አገራዊ ለውጡ ጥልቅ፣ ሰፊና ትልቅ ተስፋ ይዞ የመምጣቱን ያህል ከተስፋው በተቃራኒ ስጋቶችንም ያዘለ መሆኑን በአፅንኦት ገምግሟል።

ለውጡ አሁንም ሕዝባዊ መሠረት ይዞ በኢሕአዴግ እየተመራ ያለ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ ሕዝባዊ መሠረት የሌላቸው ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦችም በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ በመሆኑ ለለውጡ ተግዳሮት እንደሆኑ ገልጿል።

ከለውጡ በተቃራኒ ያሉ ኃይሎች ህዝቡን ለማደናገርና ድጋፍ ለማግኘት እንዲያመቻቸው በሕዝቡ ውስጥ ያሉ ብዥታዎችንና በለውጡ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአመራር ግድፈቶችን እንዲሁም ማንነትንና ሌሎች አጀንዳዎችን ምክንያት በማድረግ ጽንፈኛ አካሄድ በመከተል የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈጸም ሲሉ በዜጎች ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስና ዜጎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ እየሰሩ እንዳሉ ኮሚቴው ገምግሟል።

እንዲሁም የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች በሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር በመታገዝ ግጭትና መፈናቀል እንዲፈጠር፣ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በመሰሉ የኢኮኖሚ አሻጥሮች በመሳተፍ ለውጡን ለመግታት እየተረባረቡ እንደሚገኙም ገምግሟል።

ድርጅቱ በውስጥ አሁንም በለውጡ ምንነት፣ በለውጡ ውስጥ ባለ ሚና እና በወደፊት አቅጣጫዎች ላይ የተሟላ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ፈጥሮ በእኩል ሚዛን እየተጓዘ አለመሆኑን ጠቁሞ፤ የታችኛው መዋቅርም አለመደገፉ እና በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ያሉ የአካሄድ ዝንፈቶችና የእርስ በርስ መጠራጠር በግልጽ ተነስተው ትግል እንደተደረገባቸው ኮሚቴው አስታውቋል።

በድርጅቱ ያሉ ችግሮች በቀጣይ እንዲስተካከሉ መግባባት ላይ መደረሱን የገለጸው፤ ኮሚቴው እንደ አገርና ህዝብ ያለው አማራጭ ጽንፈኝነትን በማክሰም አንድነቷ የተጠናከረ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመገንባት ለውጡን ማስቀጠል ላይ መግባባት መፈጠሩን አመልክቷል።

ለውጡ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ እንዲሆን በማድረግ በኩል አሁንም ከፍተኛ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ችግሮች እንዳሉ ያነሳው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፤ የለውጡ ዘላቂነት የሚረጋገጠው ሰላምን በመገንባት፣ ፍትህን በማረጋገጥ፣ ዴሞክራሲን በማስፋት፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ችግሩን በመፍታት፣ አገራዊ አንድነትናክብርን በዘላቂነት ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ እንደሆነም ገልጿል።

ኢህአዴግን ማጠናከር፣ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማህበረሰብና የምሁራንን አቅም መገንባት፣ የመንግስት ሠራተኛው በእውቀትና በትጋት ላይ ተመስርቶ እንዲሰራ ማስቻል ዋነኛ ተግባሮቹ እንደሆኑ ኮሚቴው አፅንዖት የሰጠው ጉዳይ እንደሆነም ገልጿል።

እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር ያለውን መደጋገፍ ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ኮሚቴው ያስቀመጠው አቅጣጫ ያመለክታል።

ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ያላቸውን ሀብት በሙሉ በማስተባበርና በማቀናጀት መላ ህዝቡን ወደ ልማት ማስገባት ዋና አገራዊ ዘመቻ መሆን እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ኮሚቴው አስታውቋል።

በዲፕሎማሲው ረገድም የአገሪቷን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።

በትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችና ምሁራን ለውጡን ለመደገፍ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ ፀረ ለውጥ ለሆኑ ቅስቀሳዎች ሰለባ ሳይሆኑ የተጀመረውን ለውጥ የማስቀጠል ሚናቸውን እንዲወጡ በማድረግ በኩል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት አለመወጣታቸውን ገምገሟል።

ሁኔታውን ለመቀየር የሚያስችሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታውቋል።

መገናኛ ብዙኃን በነፃነት የሚሰሩበት ሁኔታ የተፈጠረና የህዝብ ድምፅ የመሆን ጅምር እንዳላቸው ያወሳው መግለጫው፤ የህዝቦችን አንድነት የሚያጠናክርና የተሻለች አገር ለመገንባት የሚያስችል አተያይ የመፍጠር እና ተዓማኒነታቸውን የሚፈታተን የስርጭት ችግር እንዳለባቸው ኮሚቴው ገምግሟል።

“ለውጡ ያስፈለገው በትናንቱ ለመቆዘም ሳይሆን ወደፊት ለመወንጨፍ ሲሆን መገናኛ ብዙኃን የህዝቡን አተያይ በመቅረጽ በኩል ብዙ ይቀረዋል” ሲል የገለጸው ኮሚቴው፤ በተለይ ማህበራዊ ሚዲያው እየተጫወተ ያለው አዎንታዊ ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ አሉታዊ ሚናው እየጎላ በመምጣቱ ከለውጡ ጋር በተዛመደ መልኩ የሚታረምበትን አካሄድ መከተል እንደሚገባ አመላክቷል።

የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከለውጡ ተነስተው በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚቻል አቋም መያዛቸውንና የጋራ ውይይት መጀመራቸውን አድነቋል።

አንዳንድ ፓርቲዎች ግን ጽንፈኝነትን በመስበክ የቆየውን የህዝቦች አንድነት በመሸርሸርና የህግ የበላይነትን ባለማክበር እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ የገመገመ ሲሆን፤ ከዚህ ተግባራቸው በመቆጠብ በሐሳብ ልዕልና እና በውይይት ለመድበለ ፓርቲ ስርዓቱ መጎልበት ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

የድርጅቱ አባላት፣ አመራርና መላ የአገሪቷ ህዝቦች የተጀመረውን ለውጥ በማስቀጠል አገሪቷን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ርብርብ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እንዲሁም ለኮሚቴው አቅጣጫዎች ተፈፃሚነት ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል።

 

 

በአፋር ክልል የሶማሌ ማኅበረሰብ የሚኖሩባቸው ልዩ ቀበሌዎች የተከሰተው ግጭት

20 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ጅግጅጋ  ጥር 10/2011 (ኢዜአ) በአፋር ክልል የሶማሌ ማህበረሰብ የሚኖሩባቸው ልዩ ቀበሌዎች የተከሰተው የፀጥታ ችግር በውይይት እንዲፈታ የሶማሌ አገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ባደረጉት ትዕይን ሕዝብ እንዳመለከቱት ልዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ጠይቀዋል።

በአፋርና በሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌዎች በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸው ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ኅዘን ገልጸዋል።

በሰልፉ ላይ ከተካፈሉት አገር ሽማግሌዎች መካከል ሱልጣን ፉዚ መሐመድ እንዳሉት የሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች የቅርብ ዝምድና ያላቸው፣ ለዘመናት አብሮ የኖሩና  የጋራ እሴቶችን እንደሚጋሩ አስታውሰው፣በልተገባ መንገድ ወደ ግጭት የሚያስገባቸው አካላት በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ብለዋል።

ሱልጣን አብዲራህማን በዴ የተባሉ የአገር ሽማግሌ በበኩላቸው የፌዴራል፣የአፋርና የሶማሌ ክልሎች የማህበረሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

አቶ መሐመድ አደን የተባሉ የሰላማዊ ሰልፍ ተካፋይ በበኩላቸው በሁለቱ ሕዝቦች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭት ለማስቆም ሁሉም አካላት ለውይይት ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ሰልፈኞቹ ”የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝቡን ሕገ መንግሥታዊ የማንነት ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲያስከብር እንጠይቃለን!”፣ ”ችግሩ በውይይት እንዲፈታ እንፈልጋለን!”ና  ”የችግሩ ፈጣሪዎች ለሕግ መቅረብ አለባቸው!” የሚሉ  መፈክሮችን ይዘው ነበር።

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲጠቃለሉ የተደረጉት አዳይቱ፣ ኦንዱፎ፣ ገርበ ኢሲና ገዳማይቱ የተባሉ ከተሞችና አካባቢያቸው ናቸው።

ከተሞቹ ከጂቡቲ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ ይገኛሉ።

 

 

የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጉልህ መንገድ ጠቋሚው ምክር ለለውጡ አመራርና ወገኖች—መደመጥ ያለበት!

17 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

 

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ኦነግን ያደናገረ የፖለቲካና ወታደራዊ ስልት

15 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

%d bloggers like this: