ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ

1 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ቢ.ቢ.ሲ. አማርኛ

የሰላሳ ዓመቷ ሩሚያ ሱሌ መስከረም 01 ቀን 2010 ዓ.ም ከጂግጂጋ ተፈናቅላ የመጣች ሲሆን “ራበን ዳቦ ስጡን” የሚል ጥያቄ በማንሳቷ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉን የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዛሬ ያወጣው ሪፖርት ያትታል።

ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ከጥር 29 2009 ዓ.ም እስከ ጥር 2010 ዓ.ም ያለውን ጊዜ ይሸፍናል።

በኢትዮጵያ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በባለፉት ሁለት ዓመታት የብዙዎችን ህይወት ቀጥፏል፣ ንብረት ወድሟል እንዲሁም የሀገሪቷን ህልውናም አደጋ ላይ ጥለውታል።

በተለይም በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔር ተወላጆች መካከል ያለው ግጭት እጅጉን ተባብሶ እና መልኩን ቀይሮ ወደ ጥቃት በመቀየር አስከፊና አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሷል።

•    በርካታ ሰዎች ከሞያሌ በመሸሽ ወደ ኬንያ ገብተዋል

•    በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድንበር ግጭት የገዳ ስርዓት መፍትሔ ለምን አላመጣም?

ከግጭቱም ጋር በተያያዘ ሰላምን ሊያስከብሩ የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት፣ በልዩ ፖሊስና የፀጥታ አካላት በሰብዓዊ መብት ጥሰት በቀጥታ ተሳታፊ እንደሆኑም ሪፖርቱ ያትታል።

ብዙዎችን በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በዝርፊያና በማሰቃያት ተሳታፊ ናቸው በማለትም ይወነጅላቸዋል። ደብዛ የማጥፋት ወንጀሎች በሁለቱም ክልሎች መፈፀማቸውን ጠቁሟል

በሁለቱ ክልሎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችም እንደተደፈሩ ሪፖርቱ አስቀምጧል።

ከነዚሀም ውስጥ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመት ተማሪ የነበረች አንዲት ሴት በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ለሶስት ከመደፈር በተጨማሪ፣ በዱላ እንደተደበደበችና በጩቤ እንደተወጋች ሪፖርቱ ጨምሮ ያትታል።

የደረሱት የሰብዓዊ መብት ጥቃቶች ለመስማት የሚዘገንኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአምስት ወታደሮች የተደፈረችና ለ28 ቀናትም በፊቅ ተራራ ላይ የታሰሩ ሴት ይገኙበታል። በስለት ታርደው የተገደሉ፣ በእሳት ተቃጥለው የሞቱና ከዚሀም በተጨማሪ የሶስት ዓመት ህፃን ልጅም እንደተገደለም ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ተቋሙ በልዩ መግለጫው ላይ ወደ 30 በሚጠጉ የሁለቱ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በተደረገ ማጣራት ከ500 በላይ ዜጎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳት እንደተዳረጉ አስታውቋል።

በዚሀም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ላይ ያሉ ሲሆን የሰመጉ ባለሙያዎች በሚያነጋግሯቸው ወቅት በተደጋጋሚ ራሳቸውን እየሳቱ ይወድቁ ነበርም ይላል።

ከማንነት፣ ከአስተዳደርና ከድንበር ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በሚገኙ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት ከሁለቱም ክልሎች የተፈናቀሉት ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሚሊየን በላይ እንደሚበልጥም ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና OCHA3 በጋራ ያወጡት ሪፖርት ያሳያል።

የችግሩን አሳሳቢነትም የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ቢንያም አባተ ይናገራሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ቃሎች የተገቡ ቢሆኑም ወደ ተግባር ሊቀየሩ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ይናገራሉ።

በጥቃቱና በግጭቱ እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጀምሮ በቂ ትኩረትና ዘለቄታዊ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ አቶ ቢንያም እንደ መፍትሔ የሚያስቀምጡት ነው።

ሰመጉ የተጎጂዎች ቁጥርና ጉዳት መጠኖችን በዘረዘረበት ባለ 55 ገፅ ልዩ ሪፖርቱ ፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ፣ለወደፊቱም እንዳይደገሙ የመከላከል ርምጃ እንዲወሰድ ፣ጉዳት የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸውና ተጠያቂዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።

Ethiopia-Eritrea peace:             Hopes & some future concerns

1 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

by Yohannes Zerai, Eritrean Opposition Movement: The Political Imperative of Self-Renewal

Recent political developments in Ethiopia seem to have generated internal dynamics that promise to fundamentally alter the political landscape in the country and perhaps even in the region. The emergence in April of Ethiopia’s newly elected prime minister, Dr. Abiy Ahmed has potentially opened the way for unprecedented social and political change and appears to have already set the country’s progress on a new trajectory. In assuming state responsibilities and addressing national issues, the new leader hit the ground running and pushed his fledgling administration to introduce hitherto unimagined political and economic reforms at a speed that Ethiopians and outsiders alike find breathtaking. The consistent message of respect, tolerance, reconciliation, love, and peace he articulates is palpably altering the mood of his nation although it remains to be seen if his future policies and decisions will be strictly guided by those ideals.

The boldness of his domestic initiatives has been mirrored in his handling of the country’s foreign affairs. In quick succession, the prime minister paid state visits to each of the IGAD countries (except Eritrea), Egypt and the Middle Eastern powers of Saudi Arabia and the United Arab Emirates. The visits were reportedly aimed at expressing Ethiopia’s interest in closer bilateral relations so essential for fostering development cooperation and economic integration among countries in the region. Ethiopia’s new strategy towards Eritrea, with whom it was in a state of war for two decades, was a peace offer entailing unconditional acceptance of the terms of the Algiers Agreement and the UN Boundary Commission ruling along with a commitment to full implementation of the latter.

The process of rapprochement set in motion by that initiative has since been reinforced by a series of diplomatic moves: Eritrea dispatched a delegation to Addis Ababa, the Ethiopian leader visited Asmara and his Eritrean counterpart reciprocated the action – all in the short span of barely a month. It has now begun yielding concrete results as heralded by the 5-point Declaration of Peace and Friendship the two leaders signed in Asmara.

The fast pace at which events continue to unfold has sent at least the urban populations and the mass media in both countries into an unprecedented frenzy. Hence, until the dust settles and public mood sobers up, it would not be easy to guess how things may evolve in the near-term much less to predict what may transpire in the middle- and long-term. Consequently, this article presents just general observations regarding (i) public reaction to the reconciliation between the two countries and (ii) what this turn of events means to Eritrea’s democracy movement.

Public Reaction to Ethiopia-Eritrea Rapprochement

Mass-media accounts of the peace initiative indicate that public reaction in Ethiopia has been somewhat mixed. Some who never accepted Eritrean independence have enthusiastically supported the peace deal because they see it as providing a chance for eventually incorporating the port of Assab, if not Eritrea itself, into Ethiopian territory. Another section of the population – mostly Tigrayans – are opposed to the deal because they fiercely reject the possibility of ceding territories even those that the EEBC identified as Eritrean. The majority, however, are known to support the initiative because of its potential to bring the socio-economic dividends of peace that they yearn for.

Similarly, Eritrea’s diaspora population have been polarized in their reaction. Supporters were as uncritical of the regime’s delay in responding to the peace offer as they were supportive of its eventual decision to go overboard in its conciliation with Ethiopia. In contrast, the opposition was quick to show enthusiasm for Ethiopia’s declaration and to lavish praise on its prime minister while viciously attacking Eritrea’s leader. Citing his arrogance, authoritarian tendencies, and confrontational approach, many prematurely asserted that the leader will do everything possible to scuttle prospects for reconciliation and derail the initiative.

But when the strongman finally acted, his response caught everyone by surprise and threatened to turn the political tables. His sudden, all-out move for conciliation – symbolized by sending a delegation to Addis Ababa – and his emissaries’ cozying up and capitulation to an erstwhile foe may well prove to be a turning point in Eritrea’s politics of despotism. Some opposition elements are reported to have since softened their stance under the fake rationale that the regime has now begun addressing issues. On the other hand, the regime’s newfound priority of ensuring a “stable Ethiopia” over demarcating the border has infuriated some of its traditional supporters.

The complexities and requirements of border demarcation also were the subject of intense public discussion. Opposition media outlets disseminated information in the form of articles, comments, interviews, panel discussions, etc. that dealt with these issues and which drew from party representatives, activists, analysts and ordinary individuals. Many contributors offered well-informed and considered opinions that impart knowledge, provide insight into past and present realities and hint at prospects. The inputs of some others relied on wild guesses, exaggerations, and biases to push outrageous claims and outlandish predictions all laced with hatred for Isaias. Still, a few others advanced opinions that were remarkable for their haste and callousness and notable for the intellectual impairment they displayed.

The State of  Eritrean Opposition: A Movement at a Crossroads

The rapid end to the long-standing Ethio-Eritrea hostility has not only exposed the sorry state of the Eritrean opposition but has presented its constituent groups both an opportunity for an honest self-assessment and a challenge to justify their existence.

 1. A. In Search of Consensus: Opposition views on the peace initiative are generally random in nature and bear little or no commonality in underlying political principles. One is thus unable to discern any common thread(s) or coalescence of views that can be identified as consensus or majority opinion of one or more political groups. Even statements that leaders of political groups issued on the subject are, in tone and substance, neither authoritative nor representative. They simply reflect the views of the leaders themselves and perhaps a handful of colleagues that make up the group – not those of a mass following which they, of course, never had!If the movement is to gain momentum, its constituent groups must articulate their vision for the country, expound their strategies and programs for realizing it and mobilize Eritreans in the diaspora and, to the extent possible, inside the country. The aim should be to build a broad-based popular support evidenced by a registered membership large enough to win recognition and assistance from external political forces.
 2. Ending Intolerance and Division: The movement for democratic change has been a victim of the political climate of division, intolerance, and hostility that the PFDJ promoted. But, it has also done its share of exacerbating the resulting chaos by engaging in internecine fighting internally and with adversaries. In the process, it developed into an inward-looking, closed political camp that has continued to drift into isolation, stagnation, and fragmentation.It is high time that opposition groups came out of their present seclusion by tearing down barriers of suspicion and animus that the despotic regime has erected among the population in order to weaken the opposition. Pro-change groups must believe in the power of ideas and challenge each other intellectually. Their members should shun politics of hatred, engage regime supporters in discussions/debates and attend their social and political events. They should employ the art of negotiation and give-and-take to narrow differences with allies and adversaries and perhaps even to win some of the latter over to the movement. To do these, however, groups and their membership must first break out of the mold and cultivate civility and a more embracing attitude.
 3. Resetting Strategies: Public political discourse reveals that many in the opposition blame the country’s woes on Isaias Afewerki, not on the political system he presides over. They express indignation at his cruel, repugnant decisions and actions of the past, not the ideology, policy and strategy that made them possible. In short, many seem to labor endlessly to demonize the dictator. But they must understand the futility of trying to demonize a demon! Isaias Afewerki has long come to symbolize cruelty, despotism, belligerence and deception in the eyes of his own people, the region and the international community that has been relentless in its efforts to contain and isolate him.Opposition forces should instead focus their efforts on gaining insight into the dictator’s political thinking, his strategizing and political planning by co-opting insiders in his regime, luring PFDJ’s agents and activists abroad, networking with the diplomatic community in host countries and other creative ways. Placing themselves ahead of the political game in this way would enable the opposition to counter/challenge/circumvent the regime’s moves and actions more effectively.

The outlook for the Future

Ethiopia’s new prime minister has been doing great things for his country showcased by the impressive political and economic reforms that he introduced early in his tenure. Indeed, he must be applauded for what he has been able to achieve thus far and for his efforts to bring peace to the region. Despite these positive impressions, however, it is difficult to guess what Dr. Abiy’s ultimate goal really is, what kind of a leader he will eventually evolve into and how his country will fare in the months and years ahead.

The peoples of Eritrea and Ethiopia and, indeed, of the wider region have long yearned for peace. A bilateral or multilateral “peace project” that is fair, just and equitable in its formulation and implementation – hence, is capable of bringing to the regional stability and prosperity – would be embraced by all. It is inescapably obvious, however, that there exist forces poised to exploit this rare opportunity for genuine peace to achieve their abominable goals.

In this regard, it is imperative that our overexcited Ethiopian friends understand that the road to Eritrea’s future does not pass through Addis Ababa. That road is destined to be laid, as it had in the past, only by the Eritrean people through blood, sweat, and tears!  Likewise, those “Eritreans” who hallucinate about bringing back to life a “cadaver of a notion” about Eritrea’s future, must be helped to see reality: their cheerleading for “Abiy” in the hope of having their dream realized is as delusional as was the now-expired wish of bringing change to Eritrea by “riding Weyane tanks to Asmara”!

Denial of democracy in Eritrea is a problem that has hampered national progress, but recent political developments in the region have lately elevated it to the level of existential threat. The dawn of peace in Ethio-Eritrea relations is, in and of itself, capable neither of removing the threat nor of instituting democracy in the country. Such outcomes will be achieved only through a popular political struggle waged by Eritreans themselves. To do so, elements of the movement for change must undertake a critical appraisal of their organization, strategy, and performance as a basis for self-renewal and transformation into a more effective movement. They should then carry the struggle forward unphased by the turbulent forces at play in the Horn and cutting through the political cross-currents that muddy the region’s waters. The forces of change should stay on course guided by the beacon of hope that the vision of justice and democracy sustains.

/ Awate.com

 

ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ሕወሃቶች ስለመግደላቸው መረጃ ወጣ!

30 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

በፌስ ቡኳ ጽዮን ብርሃኑ ብዙ መረጃ ማውጣቷ ይነገራል! ቴዲ ማንጁስ ዋናው ገዳይና እነዳንኤል ብርሃኔም በግድያውና በሌሎች ኢትዮጵያን የማናጋት ወንጀሎች እጃቸው እንዳለበት ጽዮን ብርሃኑ መረጃ ያለችውን ጠቃቅሳለች!

እርሷ መረጃውን እንዴት እንዳገኘች ግን የተጠቀሰ ነገር የለም!

 

ፖሊስ ኮሚሽነር ዘይኑ በኢንጂ ሰመኘው በቀለ ግድያ ዙርያ ጥሩ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቆሙ!

29 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

በኢ/ር #ስመኘው ግድያ #የሜቴከና_ህወሓት እጅ አለበት ይባላል!

26 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሥዩም ስዩም ተሾመ

ሰኞ ዕለት ጠ/ሚ አብይ አህመድ “የህዳሴ ግድብ አሁን ባለው አካሄድ የዛሬ አስር አመት አይጠናቀቅም” ማለቱ ይታወሳል፡፡ ትላንትና ደግሞ የመብራት ሃይል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር #አዜብ_አስናቀ ከመከላከያ ኢንጂነሪግ እና የህወሓቶች ዘረፋ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነት ሊነሱ እንደሆነ ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል፡፡ በዚህ መሠረት የዶ/ር አመራር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የግንባታ ሂደቱ እንዳይፋጠን ዋና ማነቆ የሆኑትን የመከላከያና ህወሓት ባለስልጣናት ከቦታው ጠራርጎ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ኢንጂነር ስመኘው ብዙ ሚስጥር ያወጣል፡፡ ስለዚህ ኢንጂነሩ ይህን ከማድረጉ በፊት የመከላከያና ህወሓት ገድለውታል ወይም አስገድለውታል፡፡ ከዚህ በፊት ወዳጄ William በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥልቅ ትንታኔ የያዘ ፅሁፍ አውጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ፅሁፍ ለግድቡ ግንባታ መጏተት ዋናው ምክንያት በዶ/ር #ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቦርድ እና #የሜቴክ ጄኔራሎች መሆናቸው በግልፅ ጠቅሶ ነበር፡፡ ይህን ባደረገ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሀገሩ እንግሊዝ ተጏዘ፡፡ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ሲል ቪዛ ተከለከለ፡፡ ይህ ጋዜጠኛ ከሞት የተረፈው እንግሊዛዊ በመሆኑና ቢሞት ከሀገሪቱ የውጪ ደህንነት መስሪያ ቤት (MI6) ምላሹ የከፋ ስለሚሆን ብቻ ነው፡፡ ጋዜጠኛው እውነታውን በመዘገቡ ምክንያት ይህን ካደረጉ ሙሉ መረጃውን በተግባር የሚያውቀው ኢንጂነር ስመኘውን ደግሞ ከመግደል ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡ ይህን ያደረጉት ደግሞ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የተመደበውን ገንዘብ ሲዘርፉ የኖሩት የመከላከያና ህወሓት ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ኢንጂነሩ ለደህንነቱ በመስጋት ወደ ውጪ ሀገር ለመሸሽ ሞክሮ የነበረ መሆኑ፣ እንዲሁም አንዳንድ የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች ደግሞ ቀድመው ሙሾ ሲያወርዱ የነበረ መሆኑ ጠቋሚ ነው፡፡

/ምንጭ  Hashim Ethio Ethio

በዚህ ፌስቡክ ላይ ይህ ጥቆማ መጻፍ አጋጣሚ አስገርሞኛል፡፡ ረቡዕ ማምሻውን የዋዜማን ዜና ካነበብኩ በኋላ፣ እኔም በትዊተር ሚከተለውን በትኜ ነበር። ማን ኢንጂነሩን እንደገደላቸው ይጠቁማል ለማለት ሳይሆን፡ ምርመራው ሠፋ እንዲል ይረዳል።

እኔ ካለፈው በማስታወስ የጻፍኩት ስለኢንጅነር ስመኝው ሳይሆን፡ ይህ ፌስቡክ እንዳነሳው የሜቴክ ወንጀልኛነት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ቀደም ሲል የፈጸሙት ውንብድና ላይ ያተኮረ ነበር እንደሚከተለው፡-

እስከ መቼ ይሆን፣ ወሮበሎቹና ዘራፊዎች ጥቅማችን ተጓደለ ብለው ጥቃታቸውን እንዲያስፋፉ የሚፈቀድላቸው?

ምኅረትና ይቅርታ ጥሩ ነገር ናቸው። ነገር ግን ከወር በፊት እንዳልኩት፣ ኅብረተሰብ ትጥቁን ፍቶ፡ እጁን ወደ ሰማይ አንስቶ፡ ደም የጠማቸው፡ ዘረፋ ቆመብን ብለው ሕዝባችንን ለአደጋ እያጋለጡ ዛሬ በኢንጂነር ሰመኝ ግድያ እንደተደረገው፣ ሃገራችንን ወደ እርስ በእርስ ግጭት ለሚገፉ — ጥፋትና ቅጣት ተፋተዋል ብለው በሚያምኑ የታወቁ ከርሳቸው አምላኩ ሰላምችንን ለማጣትና የለውጥ አቅጣጫችንን ለመሳት አይደለም!

ይታሰብበት!

 

Ethiopian Nile dam manager shot & killed, possibly inside his car

26 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ADDIS ABABA (Reuters) – The project manager of a $4 billion Ethiopian dam being built on the river Nile has been found dead, a Reuters photographer said on Thursday.

The photographer observed blood stains along an arm rest inside his car – a Toyota Landcruiser – before an ambulance took away the corpse. State media also reported the death, without disclosing the cause.

“Engineer Simegnew Bekele was found dead in his car this morning in Meskel Square. His body has been taken to hospital for an autopsy,” Fana Broadcasting Corporation said, referring to an area in the center of the capital.

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

Simegnew project-managed the Grand Renaissance Dam, centerpiece of Ethiopia’s bid to become Africa’s biggest power exporter. The country plans to spend some $12 billion on harnessing its rivers for hydro power in the next two decades.

But talks with Egypt – whose main source of water is the Nile – and Sudan on disagreements over its impact on the river have been deadlocked for months.

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

A bone of contention for both Ethiopia and Egypt is the speed at which the dam’s reservoir would be filled.

In June, the leaders of Ethiopia and Egypt vowed to iron out their differences peacefully. They also agreed to take steps to put into effect an agreement – which also includes Sudan – to set up a fund for investing in infrastructure in the three countries.

 

ግመሎቹ ይሄዳሉ፣ ውሻዎቹ ይጮሃሉ

25 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር

በ1983ዓ/ም  ወያኔ ዓሳራ “ግመሎቹ ይሄዳሉ፣ ውሻዎቹ ይጮሃሉ!”ይል ነበር፡፡ከ2008ዓ/ም ጀምሮ ሕዝብ “ግመሎቹ ይጮሃሉ፣ ውሻዎቹ ዝም ብለዋል!”አላቸው!!!

የዴሞክራሲና የፀረ-ዴሞክራሲ ኃይሎች ፍልሚያ !!! 

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሕመድ  በ100 ቀናት ውስጥ የሰሩት አስደናቂ ሥራዎች በተለያዩ የባህር ማዶና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መደመጡ ዋቢ ምስክር አያስፈልገውም፡፡ ሌሎቹ የተለያዩ ሚንስትሮች ከተሾሙ ጀምረው ምን ሰሩ ምን ለመስራት አቀዱ፣ በየመሥሪያ ቤቱ ምን የእርምት እንቅስቃሴ አደረጉ፣ ለመገናኛ ብዙኃን በራቸው ክፍት አድርገዋል ወይ፣ ሙስናንና ሌብነትን ለመዋጋት ያላቸው ቁርጠኝነት ምን ድረስ ነው፣ ከሰራተኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዴት ነው፣ መስሪያ ቤቱ ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል፣ የመሳሰሉት ለግልፅነትና ለመልካም አስተዳደር የእርምት እንቅስቃሴ በር ይከፍታል እንላለን፡፡ ብዙዎቹ  ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች በድረ-ገፆቻቸው መረጃ ለሕዝብ መስጠትና ለዮኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የምጣኔ ሃብት፣ የማህበራዊ ጥናት ተመራማሪዎች ለጥናታቸው ግብዓቶች የሚሆኑ ስታስቲካል/ አሀዛዊ መረጃዎች የማግኘት መብት በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠ በመሆኑ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ እያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ኃላፊነትና ግዴታ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፣ ብሎም ተግባራዊ ካልሆነ ተጠያቂነት እንዳለባችሁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፣ የህዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን መስጠትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሃሳቦችና አመለካከቶች በነጻ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች በድረ-ገፆቻቸው ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣት የዲጅታል ቴክኖሎጂ ሙያተኞች በድረ-ገፆች መረጃ የማቅረብና የማሰራጨት ክህሎታቸውን የመጠቀም መብት አላቸውና፡፡ የዴሞክራሲ ኃይሎች እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ ክንውን ግምገማ ልዩ ልዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ባለስልጣኖች የሥራ እቅድና አፈፃፀም ለህዝብ ይፋ መሆን አለባቸው እንላለን፡፡

 • ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን የሃገሪቱን ሕዝብ ተልኮውን ሳይወጣ ህዝብ ሲሰልል፣ ሲያሳስር የከረመ ድርጅት ነው፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ ህዝብ ለአለፉት 20 አመታት የስልክ አገልግሎት በማቆረጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ያቆረጠ ድርጅት ነው፡፡
 • የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር፣ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድንና የኢዛና ወርቅ ማዕድኖች ያመረቱትን ወርቅ ወደ ብሄራዊ ባንክ ገቢ ሳያደርጉ ባህር ማዶ እየሸጡ እንደነበር ታጋልጦል፣ ጋዜጠኞች ጉዳዩን መርምሮ ፀሃይ እንዲሞቀው ማድረግ ያሻል፡፡
 • የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ሙስና ተጋለጠ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር የመንግስት የአንበሳ አውቶቡስ ውስጥ 120 አውቶብሶች ሊብሬ የሌላቸው በሌብነት ገንዘቡ የግለሰቦች መጠቀሚያ እንደሆነ ታውቆል፣ የኢፈርት አውቶብሶችና የጭነት መኪኖችም ይጋለጡ፡፡
 • የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቡድን ፀረ ዲሞክራቲክ ኃይል በመሆን የሃገረቱን ለውጥ ና ጸጥታ ለማደፍረስ የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ኮ/ል ቢንያም ወልደ ማርያም በቁጥጥር ስር በማድረግ የሰሩት ስራ ያስመሰግናል፡፡ የማረሚያ እስር ቤት ሁኔታን ማሻሻልና የግርፋት (ቶርቸር) ማስቀረት፣ ገራፊዎቹን ለፍርድ ማቅረብ፣ ማረሚያ ቤቱን ታራሚዎች አያያዝ ማስተካከልና በመገናኛ ብዙሃን የቀድሞ እስረኞችና የአሁን አያያዝ ሁኔታን በግልፅ ማሳየት  ወዘተ እርማቶች በማስተካከል ላይ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ ያሉ ስውር የወያኔ እስር ቤቶች ይጋለጡ፡፡
 • በኢፈዴሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲና የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ቤት ሰርተው የሚያከራዩ በመንግስት ቤቶችና በቀበሌ ቤቶች የሚኖሩ ሹማምንቶች እንዲሁም መከላከያ በሰራቸው ወታደራዊ ኮንዶሚንየም ቤቶች የሚኖሩ ጀነራል መኮንኖችና ደህንነቶች ብሎም ሁለትና ሦስት ኮንዶሚኒየም የተሰጣቸው ሌቦች ተጋልጠው ለፍርድ መቅረብ አለባቸው፡፡ የመንግሥት ቤት ካርታን በስማቸው ያዞሩ አዲሱ ለገሠ፣ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር፣ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ ስብሃት ነጋ፣ አዜብ መስፍን ወዘተ ሌሎችም ተጋልጠው በህግ ፊት ሁሉም ዜጋ እኩል መሆኑንና ለሌባ ፍርድ መስጠት የሃላፊነት ግዴታ ነው፡፡ ሙስናውን የሚያውቁ የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በተጠያቂነትና በተባባሪነት በህግ ይጠየቃሉ፡፡ በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች የሚገኙ ሠራተኞች ሙስናና ሌብነትን የማጋለጥ ባህላቸውን በማዳበር ከዴሞክራሲ ኃሎች ጋር መደመር የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የገማው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ይዘጋ፡፡
 • የኤፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሙስና የተዘፈቁ የሜቴክ ጀነራል መኮንኖች በተጠያቂነት ለፍርድ ማቅረብና ሌሎች የሌብነት ወንጀሎች ማጋለጥ ሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ አባላቶች ተሳትፎን ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥቶች የተፈረመው የሰላም ስምምነት በቀጣኝነትና በዘለቄታው ሠራዊቱን ወደ ቀድሞው ቦታ መመለስ ለሁለቱም ሃገራቶች የኢኮኖሚ ልማት የሚያስገኘው ፋይዳ አመታዊ ወጪ የሆነውን ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብርና ናቅፋን ስለሚያድን ለልማት ሥራ በማዋል መተግበር አለበት እንላለን፡፡የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከካንፑና ከምሽጉ ቀበሮ ጉድጎዱ ወጥቶ በአዲሱ አመት በእንቁጣጣሽ ከቤተሰቦቹ ጋር ይቀላቀል እንላለን፡፡
 • የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የሴቶችና ህጸናት ጉዳይ ሚኒስቴር፣ 24 ሽህ ህፃናቶችን በማደጎነት የሸጡና ከነዚህ ውስጥ 7 ሽህ ህፃናቶች ወላጆች ልጆቻቸው የት እንዳሉ እንደማያውቁ መስሪያ ቤቱን ሲጠይቁም መልስ አለማግኘታቸው ቢጋለጥም የሹማምንቶቹ ተጠያቂነትና ለፍርድ አለመቅረብ በኢትዮጵያ ፍትህ የጨለመ፣ ጋዜጠኞች ለህፃናቱ ህይወት አለመታገል፣ ያስቆጫል፡፡
 • የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ፣ የፍትህ ሚኒስትር በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲሁም በከፍተኛ ፍርድ ቤት 120 ዳኞች ሹመታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መፅደቁ ፍትህ ለተጠማ ህዝብ ትልቅ አስተዋፆኦ አለው፣ ለ27 አመታት ፍትህ ያዛቡ ዳኞች በተጠያቂነት ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የወያኔ የጅምላ መቃብር ሥፍራዎች በትግራይ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ በሎቄ ሲዳማና በአረካ የወላይታ፣ በኦሮሚያ፣ በሃረር፣ ወለጋ፣ በባሌ ዶሎመና፣ በሱማሌ ሁሉ ግዛት፣ በአማራ ጎንደር ወልቃይት፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረብርሃን፣ አዲስአበባ በወያኔ የጦር ሠፈሮች ውስጥ ተቆፍሮ ይወጣል!!! የወያኔ የዘር ፍጅት ተዋናዬች ተጠያቂ ለፍርድ ይቅረቡ፡፡
 • የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ በልዩ ልዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ያደረገው የኦዲት ሪፖርት ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፡፡

የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ም/ ቤት፣ በኦነግ፣ኦብነግና ግንቦት 7 ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኝነት ክስ መሠረዝ፣ የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የወጣ ህግና የቦዘኔ በተመለከተ ህግ ማምከን የዴሞክራሲውን ምህዳር ያሰፋዋል፡፡ እንዲሁም የመለስ ዜናዊ ክልሎች የበጀት ቀመር አድሎዊና ፍህታዊ ባለመሆኑ ዶክተር አብይ አህመድ ለሙያተኞች አስጠንተው በዘርና የልሳን ፌዴራሊዝም ላይ ያልተመሠረተ ሁሉንም ዜጋ የሚያካትት የበጀት ቀመር ማድረግ የሚነሳውን የማንነት ጥያቄ በጀትን የሽሮ መብያ ያደረጉ ዘውጌ ብሄርተኞችን የገቢ ምንጭ ያደርቃል እንላለን፡፡ የብሄርና የብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ በቀጥታ ከበጀት ድልድል ጋር የተያያዘ መሆኑን በተደረጉ ጥናቶች መረዳትና ወይም ማስጠናት ከዚህ የዘር ፍጅት፣ የሃብት ድርሻ፣ የመሬት፣ የግጦሽ ቦታ፣ ግጭቶችና የማንነት ጥያቄ እድገት መጨመር መንስኤው ወደ ልዮ ዞንና ፣ የክልል መንግስት ለማደግና በጀት ቅርምቱና ድልድል ገንዘብ ከማግኘት ጋር የተያያዘ መሆኑን ለቅጣት አንጠራጠርም፡፡ በሃገራችን የማንነት ጥያቄ የሽሮ መብልያ ጥያቄ ነው፣ ሲዳማ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ ወዘተርፈ እያለ 80ዎቹ ሁሉ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው መረዳት አልያም የማንነት ጥያቄን በሰውነት ጥያቄ ለውጦ ከጠባብ ብሄርተኝነት ህብረ ብሄራዊ ሃገር መገንባት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው እንላለን፡፡ የበጀቱ ቀመር በዘውጌና በልሳን ላይ የተመሠረተ አይሁን አልን እንጅ ክልሎች ባህላቸውን መጠበቅ፣ ልሳናቸውን መጠቀም፣ ማዳበር ስብአዊ መብታቸው መሆኑን ማክበር ሊዘነጋ አይገባም፡፡

የክልል መንግሥታት፣ የኦሮሞ ክልል ፕሬዜዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ  ለጨፌ ኦሮሚያ (ለኦሮሚያ ምክር ቤት) የክልሉ ፀጥታ መደፍረስ በንቃት ይከታተላሉ፣ ፀረ ዲሞክራቲክ ኃይሎችን የክልሉን ጸጥታ ለማደፍረስ የሞከሩትን ነቅሶ በማውጣትና  ከኦሮሚያ መንግሥታዊ መዋቅር በመንቀል አስፈላጊውን ቆራጥ ዕርምጃ በመውስድ ያደረጉት የፀረ ዴሞክራሲ ሃይሎችን ማዳከም ቆራጥ አቋም በሌሎች ክልሎች  መቀጠል ይኖርበታል። ዶክተር አብይ አህመድ በኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ያለውን ግጭት ለማስቆም የመከላከያ ሠራዊተወና  የፖሊስ ኃይል ማሰማራቱ የሚደገፍ ነው። በሌሎችም ቦታዎች በፍጥነት ማሰማራት በህይወትና ንብረት ውድመትን ያስቆማል፡፡ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ በሱማሌ ብሮድባንድ ለጋዜጠኞች ያቀረቡትን የጌታቸው አሰፋን ጉድ አዳመጠን፣ የአብዲ ኢሌ በህዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍ አወቅን መረጃ የማወቅ መብት በሃገራችን ሊበረታታ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የብአዴን የእንግዴ ልጆችን ጠርጎ መጣልና ፀረ ዲሞክራቲክ ኃይሎችን የክልሉን ጸጥታ ለማደፍረስ የሚሞክሩትን አረሞች በጊዜው ማረም አስፈላጊ ነው፡፡ ዳተኝነት አያዋጣም፡፡

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ቴሌቪዝን የእስረኞች አያያዝ ሁኔታን ለህዝብ ይፋ በማድረግ፣ የተለያዩ መንግሥት ሹማምንቶችን በጥያቄ ማፋጠጥ፣ የሜጋ ፕሮጀክቶችን ሁኔታ በግልፅነት መከታተል፣ ሃቁን ለህዝብ የማቅረብ የጋዜጠኝነት ሥነምግባር በመወጣት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት የቦርድ አባል አድርጎ ዶክተር መረራ ጉዲናን ሾሟል። የእርምት ንቅናቄው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት በግብር ከፋዩ ህዝብና በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለው መገናኛ ብዙኃን ላለፉት 27 አመታት የህወሓት/ኢህአዴግ ፖለቲካን ሲያናፉና በውሽት የተቀቀለ መረጃ ሲያቀርቡ የኖረ፣ ለሙስናና ሌብነት ከለላ ሲሰጥ የኖረ፣ ለዋልጌነትና ለምግባረ ብልሹነት ዋስትና የሰጠ ሲሆን፣ በመልካም አስተዳደር ሥነምግባር ብልሹነት፣ ለፀያፍ አነጋገርና ስነዜጋ ለጎደለው የሚዲያ የጋዜጠኝነት አቀራረብ፣ ተጠያቂነትና የችሎታ ማነስና በዘመድ አዝማድ መቀጠርና ከችሎታ ይልቅ በዘር ተኮር መመዘኛ ያተኮሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በእርምቱ እንቅስቃሴ በዩኒቨርሲቲ መምህራኖች ፈተና ወጥቶ ያለአንዳች አድሎ ተፈትነው የሥራ ብቃትና ችሎታ ያላቸው መስፈርቱን የሚያሟሉ ጋዜጠኞችና ሙያተኞች ቦታውን መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ዴማክራሲያዊ ጋዜጠኞች የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ የተገነዘቡ፣ ወገንተኝነት የሌላቸው፣ ሚዛናዊ ፍርድና የጋዜጠኝነት ሙያ ፍቅር ያላቸው፣ ለፕሬስ ነፃነት ማበብ አስተዋፅኦ ያበረከቱ፣ በባህር ማዶና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የተባረሩ ጋዜጠኞች ይቅርታ ተጠይቀው ተመልስው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በወያኔ የፖለቲካ ፓርቲ አደግዳጊነት የተሰጡ የብሮድካስት የቴሌቪዝን፣ ሬዲዬና ኤፍኤም ሬዲዬኖች ንብረት የግብር ከፋዮ የኢትዮጵያ ህዝብ የተገዙ ንብረቶች በሃቀኛ ሠራተኞች ተጋልጠው ለህዝብ የማሳወቅ ግዴታ አለባችሁ እንላለን፡፡ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አመዛኙን ብሮድካስቶች በግሉ ዘርፍ እንዲሸጡ ማድረግ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ አንድ ሽህ አንድ የኢትዮጵያ ብሮድካስት የውሸት ወሬ በቅፌን፣  አንድ ለናቱ ኢሣት እንደደባለቀውና፣ ኦኤምኤን እንደደቆሳቸው ህዝብ ያውቃል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች የ100  ቀናት የሥራ ክንውናቸውን በጋዜጠኞች መጠየቅና መመለስ የዴሞክራሲ ባህል መለመድ አለበት፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህጸናት ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
የኤፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የፌደሬሽን ም/ ቤት
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ታላቁ የህዳሴ ግድብ
የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ
የትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ
የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
የፌደራልና አርብቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የፌደራል ዋና ኦዲተር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኢትዮ አይሲቲ ቪሌጅ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የንግድ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኢትዮ ቴሌኮም
የፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
የእንሰሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
የትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍት ኤጀንሲ
የውሃ፣ መስኖና ኤሌትሪክ ሚኒስቴር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የፌደራል ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመንግስት ግዥና ንብረት ማወገድ አገልግሎት
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢፈዴሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የፌዴራል ኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ  ጽ/ቤት

ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች፣ ሙስናና ሌብነትን የማጋለጥ ቀጣይ ዘመቻ፣ በድረ-ገፆች የህዝብ ጥያቄንና አስተያየት መቀበል እንዲሁም የዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር፣ ተጠያቂነትን ማስፈንና  አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ከዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጊዜው ይደመሩ እንላለን!!! በመቐለ የመሸጉ የወያኔ ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይል የዓሳራ ግመሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡

‹‹ድር ቢያብር፣ አንበሳ ያስር!!!››  የመምህራን ማህበር፣የተማሪዎች ማህበራት፣ የሠራተኛ ማህበራት፣ የሴቶች፣ የገበሬዎች፣ የወጣቶች፣ የታክሲ ሹፌሮች  ማህበራት ተጠናክረው የዴሞክራሲ ኃይሉን መቀላቀል ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከካንፑና ከምሽጉ ቀበሮ ጉድጎዱ ወጥቶ በእንቁጣጣሽ ከቤተሰቦቹ ጋር ይቀላቀል!!!

አድርባይ ምላሳዊ ጋዜጠኞች ይወገዱ!!! የኢትዮጵያና ኤርትራውያን ህዝቦች ወዳጅነት ይጠንክር!!!

የዴሞክራሲ አብሪ ጥይቶች በሃገራችን ሰማየ ሰማያት ላይ ተተኩሰዋል!!!

( ሃምሌ 10 ቀን 2010ዓ/ም ተፃፈ )

/EthiopiaExplorer

Shukshukta (ሹክሹክታ) – ሞሳድ ዶ/ር ዐብይ ሊገደሉ ይችላሉ አለ ይባላል!

22 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

Masses of Ethiopians stand by Abiy Ahmed to shield him from TPLF-instigated assassination attempts! These ‘gogmangogs’  must think of the consequences of their cowardly actions!

 

%d bloggers like this: