Tag Archives: abuse of power

በተ/ከንቲባ አዳነች ቀጭን ትዕዛዝ በ8ፖሊሶች ተመሥገን ደሣለኝን የማሣሠር ሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲና የለውጥ ሂደት እንደግመል ሽንት የኋሊት መመለሱ ፈታኝ ግንዛቤ ትቷል!

17 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በእሥር ቤት ከአንድ ሌሊት አዳር በኋላ—ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ በስንፈልግህ እንጠራሃለን ግንዛቤ—የጉድ ሃገር ሐሙስ ከእሥር በጊዜያዊነት ተፈቷል!

ለማንኛውም ሲፈልጉ ማሠር፡ ሲፈልጉ መፍታት ሕገ ወጥ አሠራር መሆኑ እየታወቀ፣ የቸርነት ምልክት ይመስል፡ የዜጎች የዴሞክራሲ መብቶች መከበርና ሰብዓዊ መብቶቻቸው መሠረታዊነት ትርጉም ቅጣምባር የጠፋው የዐቢይ አስተዳደር ሃገርን መምራት ንጉሡ ደስ እንዳላቸው—ማለትም ደስ እንዳለው የፈለገውን ማድረግ የሚችልባትን ኢትዮጵያ መመሥረት —ተደርጎ መወሰዱ ነው የመላው ዜጎችን ነገ እጅግ አስፈሪ ያደረገው።

ከሚያዝያ 2018 በኋላ እንዴት ነው—ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀስ በቀስና ደስ እንዳለው፣ ብዙ ነገሮች በጥቅምት 2020 ኢትዮጵያ ውስጥ በዘፈቀደና የአንድን ግለሰብ ወይንም ቡድን ፍላጎት ወደሚያስፈጸሙበት አዘቅት እንደገና ያዘቀጥነው?

ሕገ ወጥ አሠራር መሆኑ እየታወቀ፣ የዚህን ዕውነታ ማፈረጥረጥ ግድ ስለሚል፡ የችግሩ ምንጭ በኢትዮጵያ መዋቅራዊ ዕድገትና አሠራር ሥረ መሠረት እንዳይኖረው እያደረገ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አሠራርና፣ በተለይም ራሳቸውን ለማንኛውም ነገር ማዕከል በማድረግ በሃገሪቱ መዋቅራዊ አሠራር ተግባራዊ እንዳይሆን እያደረጉ ነው።

መዋቅሮች ውክልናቸውና ኃላፌታቸው በብሩህ ቀለማት ቢጻፉም፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአመራር ጋር ተቀራርበው የሚሠሩትና አፈጻጸም የሚያዩ ከግለሰቡ አመራር ጋር ባላቸው ቅርበትና ወዳጅንት ብቻ መሆኑ ነው! በዐቃቢ ሕጉ በአጭሩ ቆይታቸው ወቅት እንዳየነው፣ ወይዘሮ አዳነችም ክብሪት ከጫሩ እውነትና ሃገርን አብረው ያቃጥላሉ!

አባባሌ ግልፅ ካልሆነ፡ ከሕግ አንፃር እንኳ ቢታይ፡ ሁሉም ዜጎች በሥራ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 25 አስተሳሰብ እንኳ “ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል” ይላል። ታዲያ ምነው ያ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ በወይዘሮ አዳነች ምክንያት ተፈጻሚነቱ ገደል ገባ?

በመሆኑም ተመሥገን ለምን ታሠረን ለጊዜው ወደወደጎን ገፍተን፡ ነገሩን በዘለቄታ መልኩ ስናጤን፡ አሁን መፈታቱ ቢያስደስተንም፣ ይህ ትላንትናን ናፋቂ ሕገወጥና ፊውዳላዊ ባህሪና ድርጊት—ለዐቢይ መንግሥትም አሣፋሪ ዕለት መሆን አለበት።

ለዚያውም አሣሪው ታሣሪውን —አንድ የሕወሃት እሥር ቤት በጅጉ ታማሚ አድርጎ ለለቀቀው፣ ዕውነትን ማኅተቡ ላደረገ ብሩህ አዕምሮና ልቡ በኢትዮጵያ ፍቅር የሚነድን ዜጋ—ለመያዝ ስምንት የፖሊስ ኃይል?

በተደጋጋሚ ፖሊስ የዶክትሪኑን ሪፎርም አካሄደ ሲባል ከአሥር ቀናት በማይበልጥ ጊዜ ድግግሞሹን ስምተናል። ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት አመራሮቹ ብቃት አላቸውን ወይንስ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የምልመላ መለኪያቸው ለእርሳቸው ያለው ታማኝነት ብቻ መሆን ይኖርበታልን?

ከሕዝባችን ደኅንነትና የሃገራችን ተቋማዊ አሠራር አንፃር ሲታይ፡ ዛሬም በጥቅም የተሣሠሩ ሰዎች ሥልጣናቸውን መከታ አድርገው ራሳቸውን የሚጠቅሙባት ኢትዮጵያ ለመገንባት መሯሯጣቸውን አመላካች ነው። ትላንት ሕዝቡ በትግሉ ያዘፈቀው ሥርዓት ዛሬም ጥርስ እንዲኖረው መደረጉን በገሃድ እያየን ነው። ምንም ይሁን ምንም ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ፣ ከእንግዲህ የትላንቱን ብልሹ አሠራር እነርሱ ሥራ ላይ እያዋሉ ለዘለቄታው በሰላም መኖር አይቻልም።

ከፊውዳላዊነቱ (ሠራዊቱ)፡ አዛዦችና መዋቅሩ ነፃ ባለመውጣቱ፡ የተ/ከንቲባ አዳነችንና መንግሥታዊ ደጋፊዎቿን ቃል ተቀብሎ ታዛዥና ቅጥረኛ መስሎ መታየቱም ለዜጎች እጅግ አሳዛኝ ሆኗል። እኔን ከማዳመጥ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፌስቡክን ብዙ ይጠቀማሉ። እዚህም ላይ ችግሩ ግን፡ ሌላው እንዳይጠቀምበት እርሳቸው ማጥላላትንና መሳደብን የፖለቲካ ብልጠት እርሳችው እንደሚጠቀሙበት ሁሉ ዜጎችም እንደማኅበራዊ ሚዲያነቱ ስለሚጠቀሙበት፡ በተመሥገን ደሣለኝ መታሠርና መፈታት ዙርያ የተጻፉትን— ከተቃዋሚ ፓርቲ [ተፋልሚዎቻቸው] ጋር ስብሰባ ላይ ቢውሉም— ቀደም ብለውም ሆነ ከዚያ በኋላ እንደተመለክቷቸው አልጠራጠርም!

ድንገት በሥራ ብዛት ምክንያት— ወይንም እንደሚሉት በመጠየፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳያነቧቸው ቀርተው ከሆነ—ዋናው የዜጎች ስሜት በተፈጸመው እሥር እንዲሁም ተመሥገን ሕግ ፊት ሳይቀርብ—ስትፈለግ ትመጣለህ ተብሎ ወደቤቱ እንዲሄድ መደረጉ፡ ሃገራችን ውስጥ በሕግ ስም እየተማለ፡ ሕግ ፊት እኩልነት፡ ፍትህና ነፃነት በየቀኑ መደፍጠጣችውን አመላካች ሆኗል።

በመሆኑም ስለዜጎች ስሜት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጠቃለለ ግንዛቤ እንዲያስጨብጥ፡ የዐባይ ሚዲያን “አውድማ – እራስን የመከላከል ጥሪ” ጋብዥያቸዋለሁ!

ከላይ ቀደም ሲል “የተ/ከንቲባ አዳነችና መንግሥታዊ ደጋፊዎቿን” ስል የጠቀስኩት አቶ ታዬ ደንደአ በእሥር ዘመኑ የከፈለውን መሥዋዕትነት በማሰብና ኢትዮጵያዊነትን ደግፎ የጻፋችውን በማስታወስ ያሳደረብኝን ከበሬታ ስለተፈታተነበኝ በመበሳጨት ነበር። ሌላው ቀርቶ እኔ እስከዛሬ ከትሬዥሪ ገንዘብ ወጥቶ ለብልፅግና አባላት ሴሚናር የውሎ አበል ለመክፈል ይዞ የሄደውን ሁለት ሚሊዮን ብር ደብረዘይት ላይ ‘በተመሳሳይ ቁልፍ ከመኪና ውስጥ ወሰዱብኝ’ ታዬ ደንዲአን በሌብነት ጠርጥሮ ገንዘቡን አዘርፎ ነው የሚል ድምጽ ያልተሰማበትን ምክንያት—ስገምት—ሕዝቡ ይህ ሰው ንፁህ ነው የሚል ስሜት ይዞ ይመስለኛል።

ከዚህ በፊት የዚህ ዐይነት የግለስብ ጥብቅና ውስጥ አቶ ታዬ ለመግባቱ እርግጠኛ አይደለሁም! አሁን ግን የሃገራችን ፖለቲካ ብቻ ሣይሆን፣ አቶ ታዪም ትዝብት ላይ የወደቀ ይመስለኛል!

ለማንኛውም አብዛኛው ሕዝባችን ድሃና መሃይምነት የተጫነው ቢሆንም፣ በድን ደንቆሮ አድርጎ ሁሉንም እንዲውጥ መጠበቁ ተላላነት ነው!

የቀድሞው የፖርላማ አባልና የአሁኑ አዲሱ ምክትል አፈጉባኤ ተስፋዬ ግን ቀደም ሲል የገነቡት የሕዝብ ድጋፍ ስለመኖሩ እስከዛሬ ምንም ማስረጃ አላየሁም! ከአሁኑ አጀማመራቸው፣ በአፈጉባዔው ቢሮ ይህን ዕድል ያገኛሉ ብዬ አላምንም!

ለነገሩ ማኅበራዊ ሚዲያ ታዪ ደንዴአ ላይ እንጂ—ምክትል አፈ ጉባዔ ተስፋዬ ላይ ስለቀድሞ ማንነታቸው አንዳንዶች ነካ ካደረጉት ውጭ ––በፓርላማ በነበሩበት ወቅት በሕወሃት ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ካደረጓችው ጥረቶች ውጭ እምብዛም ትኩረት ስበው አላላየሁም!

ዋናው ጥያቄ ግን የዜጎች ጉጉት ወደጎን በሥርዓቱ አቀንቃኞች ተረግጦ ለምንድነው ሃገራችን ከቀን ቀን እንዲህ እያሽቆለቆለች ያለችው? እንዴት ነው ያን የመሰለው የዜጎች የዴሞክራሲና በሃገር በሰላምና በሕግ የመተዳደር መብት ጥማት —ያላንዳች ሃፍረት—በዚህ ደረጃ ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ የመጣው?

አምና እኮ በዚህ ወቅት ሃገሪቱ ኃዘን ላይ ነበረች 86 ዜጎቻችን ታርደውና በሌላም መንገድ ተድገድለው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ጭንቀት ለሃገር፡ ለሟቾች ቤተሰብ ሣይሆን፣ ፌዴራል መንገድ የዘጉትን እንኳ ለመገሰጽ ነፍሰ ገዳዮቹን ለማውገዝና በሕግ እንዲታይ ለማበረታት ያሉበት እንኳ አልታወቀም ነበር።

ይህም እንደ አባገዳ ሠንበቶ አቆጥቶኝ ስለነበር በእንግሊዝኛ ታህሳስ 1/2019 አንድ Open Letter ጽፌልዎ ነበር። PART Iን ተከትሎ ለተወሰኑ ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ የኔ ብሎግ THE ETHIOPIA OBSERVATORY (TEO) እንዳይነበብ መዘጋቱን ተገነዘብሁ!

እኔም PART IIን ስልክልዎ ገጼ መዘጋቱንና ደብዳቢየን እርስዎም አንብበው የሚወስዱትን እርምጃ ቢወስዱ ለሃገር እንዲሚጠቅም እንጂ በሩን መዝጋት የማይጠቅም መሆኑን ነበር። ለማንኛውም ብዙም ሳይቆይ ገጼም ከእሥር ቀን በኋላ መለቀቁን ተገነዘብሁ!

ይኽ የመንግሥትዎ impulse ወደ ሚያዋጣ መንገድ አይመራም!

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

8 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
(ኢሳት) የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል ፖሊሶችና አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል።
Continue reading

ሕወሃት በሪዮ ኦሊምፒክ ለተገኘው አሳፋሪ ውጤት በአትሌቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥያቄ ሲቀርብበት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት የላችሁም ብሎ የቀዣበረው ቅጥፈት! ይሉኝታና ስብዕናችን ምን ሆነ ይሆን?

28 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የኢትዮጵያ አትሌቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ ይገባል የሚል ጥያቄ ባቀረበ ማግሥት፣ ኮሚቴውን ሕጋዊ መብትም ሆነ ውክልና የላችሁም በማለት የሠጠው መልስ ሕወሃት ሃገራችንን የፈለኩትን ላደርጋት እችላለሁ፤ እፈንጭባታለሁ የሚል መሆኑን ጋሃድ አድርጓል፡፡
Continue reading

ዘራፊውና ነፍሰ ገዳዩ ሕወሃት ዙርያውን ተወጠረ!    የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ እንደሚገባ የአትሌቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አሳሰበ! በአንድ ሣምንት ውሳኔ ላይ ካልተደረስ “መሄድ ያለብንን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል!”             እንኳን ለዚህ አደረሰን፣ መነቃቃት በኢትዮጵያ!

25 Aug

የቀድሞ ታዋቂ አትሌቶች አትሌት ኃይሌ ገብረእግዚአብሔር፡ አትሌት ገዛኽኝ አበራ፥ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያም፥ አትሌት ሻምበል ቶሎሣ ቆቱን አሠልጣኝ ኮማንደር አበበ መኮንንበቁጣ በግነው ስብሰባ በአንድ ሣምንት ውስጥ ካልተጠራና ውሳኔ ላይ ካልተደረስ “መሄድ ያለብን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል” (Credit Fana)


 

“We want a general meeting of the Ethiopian Athletics Federation within a week to take the appropriate decisions. If not, we would go the distances it would take us to see the results Ethiopia needs. And we are prepared for what it takes!”, says the provisional coordinating committee of Ethiopian athletes.
 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ ይገባል እንደሚገባ የአትሌቶች ጊዜዊ ኮሚቴ አስተባባሪ አሳሰበ።

ኮሚቴ በዘንድሮው የሪዮ ኦሎምፒክ ሀገራችን ደካማ ውጤት እንደታዝመዘገብ ምክንያት የሆነው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ የአሰራር ክፍተት ነው ብሏል።
Continue reading

Ban tells African leaders at their summit to stop use of legal loopholes or undemocratic means to “cling to power”

1 Feb

Editor’s Note:

Can there be any better example and lesson to what the United Nations Secretary-General is putting before African leaders at their regional summit than the crime Pierre Nkurunziza has committed on the people of Burundi; or, among others, the TPLF’s gigantic engagement to end its rejection by the people and protests against its robberies and illegitimate rule through torture, mass execution, mass imprisonments and disappearances of Ethiopians; or the systematic persecution Paul Kagame and Yoweri Museveni are committing on the peoples of Rwanda and Uganda respectively?

While these are all good points about the international community is fully aware, I am disappointed in the UN Chief failing to mention the TPLF in Ethiopia, more particularly in the face of its horrendous human rights crimes and mass murder of university and high school students in Oromia region of Ethiopia!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

“Leaders must protect their people, not themselves…I commend those leaders who committed to stepping aside and respect constitutional term limits.”

ADDIS ABABA (Reuters) – U.N. Secretary General Ban Ki-moon told African leaders on Saturday they should not use legal loopholes or undemocratic constitutional changes to “cling to power”, and that they should respect term limits.
Continue reading

የኢትዮጵያ ሙስና ስፋትና ጥልቀት አሁን ገና ሥዕሉ በትንሹ መታየት ጀመረ! ግን ማነው ያልተነካካው?

23 Oct

በታምሩ ጽጌ ከሪፖርተር – Posted by The Ethiopia Observatory

ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ያስገቡት 20 ድርጅቶች:

    ኒያላ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያና መለዋወጫ ዕቃ አስመጪ፣ ፔትራም፣ ሞኤንኮ፣ ጌታስ ትሬዲንግ፣ አልሳም፣ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ አይካ አዲስ (የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ)፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ፣ ሆላንድ ካርስ (ከስሮ ተዘግቷል)፣ ቶታል ኢትዮጵያ፣ ሚድሮክ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን፣ ድሬ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ፣ ኢትዮ ሌዘር፣ ኢትዮ ቆዳ ፋብሪካ፣ ባሰፋ ትሬዲንግ፣ ነፃ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ጌታስ ኢንተርናሽናልና ኮሜት ትሬዲንግ ናቸው፡፡
    Continue reading
%d bloggers like this: