Tag Archives: Activists’ contribution

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ካዘጋጀው “የሃሣብ ማዕድ” የተገኙ ሃሣቦች

19 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በዛሬው “የሀሳብ ማዕድ” የተነሱ ነጥቦች!

 

አክቲቪስቶች ለሀገራዊ ጥቅም ምን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ?

አቤል ዋቤላ

“አክቲቪስቶች አንድ ላይ ብንሆን የፖለቲካ ስለልጣንን መግራት እንችላለን፡፡ ይህም ማለት አንድ ስልጣን ላይ ያለ ሰው ስልጣኑን ሲጠቀም ሁሉም አክቲቪስት በጋራ በመተባበር መኮነንና ስልጣንን በአግባቡ እንዲጠቀም ማስቻል ላይ በጋራ መስራት እንችላለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉት ክፍተቶች ሁሉም አክቲቪስቶች ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡ በዚህ መተባበር እንችላለን፡፡”

ታምራት ነገራ:

“አሁን ያለው ስርዓት ሰዎች የመጨረሻውን ጥግ ይዘው እንዲቆሙና በዛ ትርፋማ እንደሚሆኑ ማሰባቸው ነው፡፡ ብሔራዊ መግባባት የሚባል ነገር የለም ሁሉም ስርዓት ጽንፈኛ የሚያደርግ ነገር ነው ያለው፡፡ ከዛም በላይ ስርዓትና ህግ ማስጠበቅ ወደ ማይቻልበት ሁኔታ እየሄድን ስለሆነ ሰዎች ስለ ጋራ መግባባት ሲያስቡ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው የሚችል ነገር ሳይሆን ስለጎጥ ሲታሰብ ነው ተጠቃሚ እየሆነ ያለው ስለዚህ ስርዓቱ በራሱ ሀገራዊ ተግባቦት እንዲሆን አያስችልም፡፡”

ፍጹም ብርሃነ:

“አዲስ አበባን እንደ ኢትዮጵያ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ ወጣ ብለን ማህበረሰቡን እንመልከት ለጋራ ምንቆምበት ነገር ብንቆም መግባባት ይፈጠራል፡፡”

ዶ/ር እንዳለማው አበራ:

“እኩልነት ምንድነው? የሰውዓዊ ክብር ምንድነው? በነዚህ ነገሮች ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብንሰብክበት ግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ቢቻል ቢያንስ በዚህ ላይ በጋራ መስራት እንችላለን፡፡”

ኪያ ፀጋዬ:

“ሶሻል ሚዲያው ላይ ላለው አክቲቪስት የፖለቲካ ታሪካችን ውጤት ነው ብዬ ነው ማስበው፡፡ ምን አስተዋጽዖ ማድረግ ችላሉ ለሚለው ግን ብዙ ማድረግ ይችላሉ ባይ ነኝ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን ለመልካም ዓላማ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የአክቲቪስቶች ስራ ሙሉ ሰዓት መቃወም ብቻ አይመስለኝም ሀገራዊ ስራዎች ላይ ሰላም ላይ መስራት ይቻላል።”

አሁን ላይ የሚታየው የሚዲያና የአክቲቪዝም መደበላለቅ እንዴት ትመለከቱታላችሁ?

• ሚዲያና አክቲቪዝም መለያየት ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ከአክቲቪዚሙ ይልቅ ለፖለቲካ አቋም ያላቸው አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች በዝተዋል በግሌ ይሄ መሆን አለበት ብዬ አላምንም (ታምራት ነገራ )

• ፐብሊክ ሚዲያው ነጻ መሆን አለበት፡፡ የመንግስት የአቋም መግለጫ ሙሉውን የሚያነብ ሚዲያ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስብሰባ እንኳን ሳይጠቅስ ያልፋል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ (ዶ/ር እንዳለማው አበራ)

• አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ሚዲያ ኖሮ አያውቅም፡፡ አሁን ላይ የሀሰት ዜናዎችን እያሰራጩ ያሉት የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን ሶሻል ሚዲያውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም አለብን በሚለው ላይ ተስፋ ይታየኛል፡፡ (ኤቤል ዋቤላ)

• በተለይ ዋና ዋና አክቲቪስቶች ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ከሁሉም ክፍል ያሉ ህዝባችንን እንወክላለን ያሉ ተሰብስበው በፈቃደኝነት ተሰብስበው ለራሳቸው ህግ ቢያወጡ ጥሩ ነው፡፡ በተረፈ ግን እንደ ሀገር ያለንበትን ጉዳይ አልተረዳነውም ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ እያገናዘብን እንቀሳቀስ እንጂ በዲሞክራሲና በፕሬስ ሚዲያ ሩቅ የደረሱ ሀገሮችን እንደ ምሳሌ እየጠቀስን መነቃቀፍ የትም አያደርሰንም። (ኪያ ፀጋዬ)

• ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ብሔርና እንደ ፖለቲካ የተመሰረተ ሚዲያ እንጂ ነጻ ሚዲያ የለም፡፡ አሁን ላይ ስለ ሚዲያ ማውራት አንችልም። (አልበርቱ ቢጠና)

ክፍል ሁለት!

አክቲቪስቶች በጋራ ሆነው የሚመሩበት ህግ በማውጣትና እርስ በእርስ መገማገሚያ መድረክ ቢያመቻቹ ጥቅሙ ምንድን ነው?

• ይህንን ማድረግ የፖለቲካ ስርዓቱ መስተካከል አለበት፡፡ ፖለቲከኞቹ ባለመግባባታቸው ህግ እየተከበረ አይደለም በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ግጭት የሚፈጥሩ ሰዎች በህግ ተጠያቂ እየሆኑ አደለም ስለዚህ መጀመሪያ ህግ መፍራት ለህግ ተገዢ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ከዛ ይልቅ ግን እንደዚህ አይነት መድረኮች መኖራቸው እርስ በዕርስ ተቀራርቦ ማውራቱ ቀዳሚ መሆን ይኖርበታል። (ዮናታን ተስፋዬ)

• አክቲቪዚሙ በራሱ በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ እንጂ ሌላውን ማህበረሰብ ለማካተት አይፈቅዱም፡፡ አሁን ያለው አክቲቪዝም ላይ ያሉ አክቲቪስቶች ቁጭ ብሎ ለማውራት እንኳን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡(በፍቃዱ ሀይሉ)

• መጀመሪያ ላይ ችግሩ ላይ መስማማት ያለብን ይመስለኛል። በዚህ ላይ ካልተስማማን የራሳችንን ጽንፍ ይዘን እንቀሳቀሳለን እንጂ መግባባት አንችልም፡፡ አቋም እንዳለን እንስማማ አንድ ላይ ቁጭ ብለን ስንደራደር መፍትሔ እንደምናገኝ እንመን ሁላችንም ያገባናል የምንል ከሆነ ሀሳባችንን ለድርድር ማቅረብ አለብን፡፡

• አብዛኛው ሰው ተስፋ የቆረጠ ነው፡፡ ይህ ደግሞ መሸሸጊያ ምሽግ እንዲፈልግ ያደርገዋል፡፡ እንደዚህ አይነት መድረኮች መኖሩ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ ይሰጣል፡፡(ያሬድ ሹመቴ)

• መሰረታዊ ችግሩን ሳናወራው ስለመፍትሔ ማውራ መፍተሔ አያመጣም፡፡ የጋራ ሀገራዊ ማንነት ላይ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ የብሔር ማንነትና ብሔራዊ ማንነትን ማስታረቅ በጣም ያስፈልጋል፡፡ ጥላቻን ማደስ ላይ ተጠምደናል፡፡ (አንሙት አብርሀም)

 

 

%d bloggers like this: