Tag Archives: addis abeba city administration

አቶ አምባሳደር አለፎም የየካ መሬት ዘረፋ፣ቅርምትና ስላስከተሏቸው ችግሮች የሠጡት ምሥክራዊ ቃለ መጠይቅ

18 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

ገሃዱ ማን አለብኝነት በዜጎች ገንዘብ:         የ40/60 ባለ አንድ መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ድርጊት ተፈጽሞብናል አሉ

10 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by The Reporter
 

ከአዘጋጁ፦ ከራሱ ጥቅሞች ውጭ ለሕዝቡ ችግሮች ደንታ የሌለው የሕወሃት አስተዳደርን ቀጣፊነትና ዘራፊነት የሚያጋልጥ ጽሁፍ!

ለፖለቲካው ብልሹነትና መግማማት ግንዛቤ መንበብ ያለበት!

 

“ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ባንኩ ውል መፈጸሙን የገለጹት አቶ በቃሉ ውል የፈጸሙት ከባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን 324 ባለ አራት መኝታ ቤቶች የተገነቡ ቢሆንም፣ እነሱን በሚመለከት ውል የፈጸመ አካል ባለመኖሩ ሁለት አማራጮችን ማስቀመጣቸውን ጠቁመዋል፡፡ ለባለ ሦስት መኝታ ቤት የተመዘገቡ ለባለ አራት መኝታ ቤትም ላይ እንዲወዳደሩ፣ ነገር ግን አቅም የለንም የሚሉ ከሆነ ቤቶቹን ለአስተዳደሩ እንደሚያስረክቡ አክለዋል፡፡ የባለ አንድ መኝታ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ጥያቄ የተቀረበላቸው አቶ በቃሉ፣ ለሙከራ በተሠሩት የክራውንና የሰንጋ ተራ ሳይቶች ባለ አንድ መኝታ ቤት አለመገንባቱን ተናግረው በቀጣይ በ2010 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 20 ሺሕ ቤቶች ውስጥ እንደሚካተቱ አስረድተዋል፡፡ ሙሉ ክፍያ በተገለጸው ወቅት ከከፈሉ 11,088 ተመዝጋቢዎች ውስጥ ሦስት በመቶ ዳያስፖራዎች እንደሚሳተፉ፣ 20 በመቶ የመንግሥት ሠራተኞችም እንደሚካተቱ አቶ በቃሉ አክለዋል፡፡ በመንግሥት ሥራ ላይ ሆነው የተመዘገቡ፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት ሥራ የለቀቁ ከሆኑ ዕጣ ቢወጣላቸውም ቤቱ እንደማይሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ በሁለቱ ሳይቶች ከተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተወሰኑት ለመንግሥት ተቋማት በሽያጭ ስለመተላለፋቸው የተጠየቁት ኃላፊዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው አንድም ቤት ለማንም አካል እንዳልተሰጠ ገልጸዋል፡፡ በሁለቱ ሳይቶች የተገነቡት ቤቶች 972 መሆናቸውንና 320 ሱቆችም እንዳሉ ጠቁመው፣ ሁሉም በዕጣና በጨረታ የሚቀርቡ መሆናቸውን በማስረዳት ቤቶቹ አለመሸጣቸውን በተደጋጋሚ አስረድተዋል፡፡
Continue reading

በዘመናችን ከሚታዩት መንግሥታዊነት ብቃት ማነስ የተከሰቱ የአስተዳደር ጉድለቶችና ለሕይወትና ንብረት ተጠያቂነት አለመኖር ተጠቃሽ መሆን ከሚገባቸው የአዲስ አበባ ምሣሌዎች መካከል

17 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በአዲስ አበባ በሚገኙ ዋና ዋና የቀለበት መንገዶች ላይ 132 የንብረት ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሰልጣን አሰታወቀ።
Continue reading

ወ/ሮ ዛይድ ተስፋይ፥                                     ‘ጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ቋንቋቸውንና ባህላቸውን ሳይረሱ የማህበረሰብ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል’ – አሁንም ጎዳና ላይ ቢሆኑም!

1 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

    የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮበአሰሩም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የምክር ቤት አባላት በተገኙበት ‘በአደራ ቤተሰብ ክብካቤን’ ዙሪያ ሥልጠና ሠጥቻለሁ ይላል!

 

ጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትና ቤተሰቦቻቸው - ከመካከላቸው ቤቶቻቸውንና መሬቶቻቸውን በሕወሃት ሰዎች የተነጠቁ ይኖራሉ! (ፎቶ፡ ኢዜአ)

ጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትና ቤተሰቦቻቸው – ከመካከላቸው ቤቶቻቸውንና መሬቶቻቸውን በሕወሃት ሰዎች የተነጠቁ ይኖራሉ! (ፎቶ፡ ኢዜአ)


 
አዲስ አበባ ግንቦት 22/2007 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት የማህበረሰብ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡ ቢሮው በአሰሩም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የምክር ቤት አባላት በተገኙበት ‘በአደራ ቤተሰብ ክብካቤን’ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
Continue reading

“ማሞ ቂሎ” የሊዝ አዋጁ እንዲሻሻል ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ አቀረበ

23 Nov

የአዘጋጁ ትዕዝብት:

    ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም – እንደመለስ ሁሉ የቡድኑ አባልና ግንባር ቀደም ተጫዋች በመሆናቸው – ባለፈው ነሐሴ ወር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአብዛኞቹ መሬቶቻቸውን ሥራ ላይ ካላዋሉት ባለሃብቶድ፤ አላሙዲን ጨምሮ፤ መሬቶቹን ሲነጥቅ፡ አስካሁን በታወቀው፡ የሼክ አላሙዲ ግን በአንድ አፍታ በኃይለማርያም ደሣለኝ ትዕዛዝ እንዲመለስላቸው ተደርጓል። ሕወሃትና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በአንድ በኩል፤ ሼክ አላሙዲና የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ዐይነት ሕግ የማንተዳደር መሆኑ እየታወቀ፡ ይህ ጥያቄ እንደገና ለአስፈጻሚው መቅረቡ ትርጉም የለሽ ነው። ለዚህም ነው – ለስድብ ሳይሆን – አርዕስቱ ላይ “በአዲስ አበባ አስተዳደር” ስም ፈንታ “ማሞ ቂሎ”ን ያስገባነው።
    Continue reading

የምርጫ 2015 ሥራ በገሃድ መጀምሩን በስም ፀረ-ሽብር ዝግጅት ለአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠው ሥልጠና አረጋገጠ

12 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን በፀረ ሽብርተኝነት ለማንቀሳቀስ ኢሕአዴግ አዲስ ዘመቻ ጀመረ፡፡ ኢሕአዴግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን ባለፈው ዓርብ ሰብስቦ በፀረ ሽብርተኝነት ወቅታዊ ክስተቶችና በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
Continue reading

አዲስ አበባ ውስጥ በአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ላይ የተጣለው እገዳ ተቃውሞ ቀረበበት

6 Oct

በነአምን አሸናፊ: ከሪፖርተር Posted by The Ethiopia Observatory

የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ባለፈው ማክሰኞ በአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በማሠልጠኛ ተቋማት ላይ የተጣለውን እገዳ ሕገወጥና አሳፋሪ ነው በማለት ተቃውሞን ገለጸ፡፡
Continue reading

የመንጃ ፈቃድ ሰልጣኞች በየትኛውም የማሰልጠኛ ተቋማት ትምህርት መጀመር እንደሌለባቸው ወ/ሮ ትብለጽ አስግዶም አስታወቁ: ፋና ስለዚህ ምናለ?

3 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory

Tiblets Asgedomአዲስ አበባ መስከረም 21/2006 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ማንኛውም የመንጃ ፈቃድ ሰልጣኝ ከጥቅምት 1ቀን 2006 በፊት በማናቸውም የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ትምህርት መጀመር እንደሌለበት አሳሰበ። ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ያደረገውን ግምገማ ውጤይ ይፋ አድርጓል።
Continue reading