Tag Archives: addis abeba

የአዲስ አበባ ስንብት!

12 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በተመስገን ደሳለኝ

 

 

 

 

 

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠሚር ዐቢይ የሠጧቸው አስተያየቶች!

25 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

 

 

 

አዲስ አበባ ኦሮሚያ አይደለችም በታሪክም ሆና አታዉቅም!

11 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከተማችን አዲስ አበባ በህግም በታሪክም የፌዴራል መንግሥት መቀመጫና ባለቤትነቷም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሆነች ከአምስት ሚሊየን በላይ ሕጋዊ ነዋሪዎች ያሏት ከተማ ናት፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ይህን ነባር ባለ ይዞታ ሕዝብ በራሱ ከተማ ተጠቃሚ እንዳይሆን ለማድረግ የሚፈልጉና “እኛ በወሰንልህ እደር” ለማለት የሚዳዳቸዉ አካላት ፈተና ሆነዉበት ይገኛል፡፡ ማኅበራችን “አዲስ አበባችን ወጣቶች ጎልማሶችና ምሁራን ማኅበር” ከተማችን አሁን ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት የሚከተሉትን ጥያቄዎች በአጽንዖት ያቀርባል፡፡

1 .የአዲስአበባ ሕዝብ በከተማይቱ እድገት ዉስጥ ሙሉ አሰተዋፅዖ ያለዉ በላቡ ከተማዉን ገንብቶ አሁን ያለችበት ደረጃ ያደረሰና ለመላው አፍሪካ ጭምር መጠጊያ የሆነ ነባር ባለ ይዞታ እንጂ ሰፋሪ ወይም መጤ አይደለም በመሆኑም የከተማችንን ነዋሪ ሰፋሪ ወይም መጤ ለማስመሰል በመንግሥት አካላትም ሆነ በሌሎች የሚደረጉ ንግግሮች እና ድርጊቶች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን፡፡

2. በከተማይቱ ላይ የተሾሙ አካላት ለአዲስአበባ ሕዝብ የተሾሙ ሳይሆኑ በአዲስአበባ ሕዝብ ላይ የተሾሙ እስኪመስል ድረስ የከተማይቱን ሕዝብ ድምፅና ብሶት ሲያዳምጡ አይታይም በመሆኑም አሁን የአዲስአበባ ሕዝብ ያለበትን ችግር ባስቸኳይ ተረድተዉ በ አንድ ሣምንት ጊዜ ዉስጥ ሁሉም ምክትል ከንቲባዎች በጋራ ሆነው በየክፍለ ከተማው ከአዲስአበባ ሕዝብ ጋር ዉይይት እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡

3. በሃገሪቷ የተለያዩ ከተሞች ” አዲስ አበባ የኛ ብቻ ናት” የሚል ጥያቄ ይዘዉ የሰላማዊ ሰልፍ መርህን በጣሰ መልኩ በእጃቸዉ ጉዳት ማድረሻ መሳርያዎችን በመያዝና የአዲስአበባ ሕዝብ ላይ ዛቻ እና ስድብ በመሰንዘር ተቃዉሞ የሚያደርጉ አካላትን የኦሮምያ መንግሥትም ሆነ የፌደራል መንግሥት ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ያደርጉ ዘንድ እናሳስባለን፡፡

4. ሃገራችንን እየመራ የሚገኘው ግንባር አባል የሆነዉ ኦዴፖ በከተማችን ጉዳይ ያወጣዉ መግለጫ መንግሥት ሆኖ ሀገር እያስተዳደረ ከሚገኝ አካል የማይጠበቅ ለአዲስአበባ ሕዝብ ያለዉን ንቀት የሚያሳይ እና የአዲስአበባ ነዋሪ ላቡን አፍስሶና ገንዘቡን ቆጥቦ የሰራዉን መኖርያ ቤት በሀይል ለመዝረፍ ያለመ መሆኑን በመረዳት የምንቃወም መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይም ሆነ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ ጉዳይ የባለቤቱ የአዲስአበባ ነዋሪ እንጂ በፖርቲ የተሃድሶ ስምምነት የሚወሰን አለመሆኑን በአጽንዖት እናስገነዝባለን፡፡

5. በተለያዩ ቦታዎች የጥላቻ ንግግሮችን እየተናገሩ የአዲስአበባ ሕዝብ ላይ የሞት ድግስ እየደገሱ ያሉ አክቲቪስቶች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

6. በጋራ መኖርያ ቤት ግንባታ ወቅት ከመሬታቸዉ የተፈናቀሉት ገበሬዎችን በተመለከተ ተገቢውን ካሳ ያልከፈለውም ሆነ በሕገ ወጥ መንገድ ያፈናቀለዉ መንግሥት ሆኖ እያለ በመንግሥት ስህተት ድሀዉ የ አዲስአበባ ነዋሪ ቆጥቦ የሰራዉን መኖርያ ቤት በጉልበት መዘረፍ ሕገ ወጥነት መሆኑን አየገለፅን ለአዲስአበባ ነዋሪ ሕጋዊ መኖርያ ቤቱ እንዲመለስ አበክረን እንጠይቃለን፡፡

7. ከላይ በተዘረዘሩ ጉዳዮች መንግሥት ኃላፊነቱን ሳይወጣ በመቅረቱና የከተማችን ነዋሪ ሕጋዊ መብቱን ለማስከበር በሚያደርገው ማንኛዉም እንቅስቃሴ ግጭቶች ቢከሰቱ ለሚደርሰው ማንኛውንም ጉዳት ኃላፊነት የመንግሥት መሆኑን አያሳሰብን መንግስት ለከተማው ነዋሪ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

8. የአዲስአበባን ሕዝብ መብት ለማስከበር የሚደረጉ ማንኛውም እንቅስቃሴዎች ማህበራችን የሚደግፍና ለተፈፃሚነቱም በጋራ የሚሰራ ሲሆን የፊታችን እሁድ 1/7/2011 በጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ አስተባባሪነት የተጠራዉን ስብሰባ በሙሉ ልባችን በመደገፍ መላው የማኅበራችን አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም መላዉ የአዲስአበባ ነዋሪዎች ተገኝተዉ በጋራ ጉዳዮቻቸዉ ላይ እንዲመክሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በተጨማሪም ማህበራችን የአዲስአበባ ዝብ ከመቸዉም በላይ ለጋዊ መብቶቹ በጋራ የሚቆምበት ወቅት ላይ የደረሰ በመሆኑ ከጥቃቅን ልዩነቶች ወጥቶ በጋራ እንዲቆም እየጠየቅን መጋቢት15/7/2011 በአዲስአበባ መስቀል አደባባይ በሚደረገዉ ዝባዊ ሰልፍ ላይ መላዉ የአዲስአበባ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን በማስተላለፍ የሰላማዊ ሰልፉን ሰዓትና መነሻ ቦታ በቀጣይ ቀናት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

በመጨረሻም መላው ኢትዮጵያዊ አሁን በአዲስ አበባ ላይ እየተፈጸመ ያለው ገ ወጥነት አዲስ አበባን ከመላው የሃገሪቷ ዝቦች የመንጠቅ ፍላጎትና ከፍ ሲልም በኢትዮጵያዊነት ላይ የተቃጣ አደጋ መሆኑን በመረዳት የአዲስአበባ ዝብን መብት ለማስከበር በምናደርገው ማንኛዉም እንቅስቃሴዎች ሁሉም የሃገራችን ዜጎች ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ መሰል ማኅበራት ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ በአክብሮት አንጠይቃለን፡፡

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

አዲስ አበቤነት = ሰብዓዊ ማንነት + ምክንያታዊነት + ልሕቀት

 

 

በፍንዳታው የተጎዱ ዜጎች የሠጡት ምሥክርነት፣አፈንጅ አንድ ሴት ታይዛለች!

23 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

አቶ አምባሳደር አለፎም የየካ መሬት ዘረፋ፣ቅርምትና ስላስከተሏቸው ችግሮች የሠጡት ምሥክራዊ ቃለ መጠይቅ

18 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

With TPLF impunity at its highest, not only civilians! See Agazi attacking Addis Abeba Police — foot on policeman’s head…

22 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Credit Abyssinia Fikir


 

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ኦዲት በስድስት ወራት ብቻ 1,439 ጉዳዮች ላይ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን አጋለጠ! ማን ግድ ቢሠጠው?

31 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሪፖተር
 

ቢሮው ባወጣው የስድስት ወራት ሪፖርት እንዳስታወቀው ከመመርያ ጥሰቶች መካከል ያላግባብ ክፍያ ማስከፈል፣ የመስክ ልኬት ሳይደረግ በጂአይኤስ ታይቶ ብቻ ካርታ አትሞ መስጠት፣ በባዶ መሬት የስም ዝውውር መፈጸም፣ በሽንሻኖ ከፀደቀው ካሬ ሜትር በላይ ካርታ አዘጋጅቶ መስጠት፣ ለየብቻቸው መልማት የማይችሉ ይዞታዎች በተነፃፃሪ (ፕሮፖርሽን) ከመሥራት ይልቅ ማካፈልን መምረጥ፣ እንዲሁም ከምትክ ቦታ አሰጣጥ ጋር ያሉ ችግሮች ዋና ዋናዎቹ ሆነው ቀርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ባላቸው አገልግሎቶች ላይ ባካሄደው ኦዲት፣ 1,439 ጉዳዮች የአሠራርና የመመርያ ጥሰት ያለባቸው መሆኑን ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

የከተማው መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ያካሄዳቸውን ሥራዎች በገመገመበት ሪፖርት ላይ እንዳስታወቀው፣ በ2010 በጀት ዓመት በመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት 4,736 አገልግሎት አሰጣጦችን ኦዲት አድርጓል፡፡

ኦዲት ከተደረገባቸው አገልግሎቶች ውስጥ 1,344 የሚሆኑት የአሠራር ጥሰት፣ 95 የሚሆኑት ደግሞ የመመርያ ጥሰት ያለባቸው መሆኑን አረጋግጧል፡፡
Continue reading

ሕወሃት ኢትዮጵያውያንን ሲተናኮል አዲስ አበባ መጻዒነት ላይ የሕወሃት ‘ትግራይም’ መወሰን አለባት ይላል — ሌላው ቀርቶ ‘ብሔራዊው ምክር ቤት’ እንኳ በሕዝብ የተመረጡ ተወካዮች ሳይኖሩበት!

30 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by አዲስ ዘመን
 
ሕገ-መንግሥቱ የሁሉንም ሕዝቦች መብቶችና ጥቅሞች ያስጠብቃል። ዋና መነሻውም አንድ ጠንካራ ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው።የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ልዩ ጥቅም በህገ-መንግሥቱ እንዲሰፍር ያደረጉትም የኦሮሞ ሕዝብን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው፡፡ልዩ ጥቅም ሲባል ምን ማለት ነው?
Continue reading

%d bloggers like this: