Tag Archives: Attorney General

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ደንብን አቃቤ ሕጓ ይፋ አደረጉ

11 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማሥፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ይፋ አደረገ።

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅጽደቁ ይታወሣል።


የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ይዘት በሚመለከት ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 93 ንዑስ ቁጥር 4 መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ማውጣት እንዳለበት ይደነግጋል።

በዚህም መረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ዝርዝር በሚመለከት ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።

ማስፈፀሚያ ደንቡ አጠቃላይ አራት ዋና ዋና ከፍሎች ያሉት ሲሆን ይሄውም ክልከላን የሚያስቀምጥ፣ ግደታዎችን የሚጥል፣ የአስፈፃሚ አካላትን ክንውን እንዲሁም ልዩ ለዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

 

ክልከላን በሚመለከት ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ ዕቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

ከአራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ሕጓ አብራርተዋል።

ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።

 

ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ሥንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድትዋል።

በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስውጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

 

ሠራተኞችን መቀነስና የሥራ ቅጥር ውል ማቋረጥም መከልከሉን ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።

በዚህ ደንብ መሠረት ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የሕፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ሥፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ መሆኑን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡

 

 

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፓርላማ: “የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ተጣርቶ ቢገለጽ ጥሩ ነው!”           

29 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከሰኔ 15 ግድያ ጋር በመጠርጠር በአዲስ አበባ የተያዙት ለለውጡ ሲባል እንዲለቀቁ መወሰኑን ገልጿል

ክልሎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት 1,596 ተጠርጣሪዎችን ለሕግ ማቅረብ አልቻልኩም ብሏል

በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረና እያስጨነቀ የሚገኘውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታገት አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተጠየቀው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ‹‹ተጣርቶ ቢገለጽ ጥሩ ነው፤›› የሚል ምላሽ ሰጠ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አመራሮች ማክሰኞ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. የስድስት ወራት፣ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በምዕራብ ወለጋ የሚገኘው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታገትን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከምክር ቤቱ በአባላቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር።

ይህንንና ሌሎች ወንጀል ነክ ጉዳዮችን አስመልክቶ የምክር ቤቱ አባላት ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት በተቋሙ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ፣ የታገቱት ተማሪዎችን በተመለከተ ምርመራ መጀመሩንና ይህ ጉዳይ ተጣርቶ ዝርዝር ሁኔታው ቢገለጽ የተሻለ እንደሚሆን አመልክተዋል።

ይህንን የዕገታ ድርጊት አስመልክቶ በተለያየ መንገድ ከሚነገረው ውጪ ምርመራ ተደርጎ ከተጣራ በኋላ ቢገለጽ ጥሩ ነው ብለው እንደ ባለሙያ እንደሚያምኑ፣ አቶ ፍቃዱ ለምክር ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል። ‹‹እነ ማን ናቸው የታገቱት? አጋቾቹ ማን ናቸው፣ እንዴትና መቼ ነው የታገቱት? ስንት ናቸው? የሚለው ጉዳይ ተጣርቶ ለሕዝብ ቢገለጽ ነው ጥሩ የሚሆነው፤›› ሲሉም አክለዋል።

Continue reading

“በአንድ አገር የዳኝነት አካል አስፈላጊነቱ ምንድን ነው?” ለአቶ ሰለሞን አረዳ የፌ/ጠ/ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት የቀረበ ጥያቄ

25 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“በፍርድ ቤት ላይ እምነት ማጣት በመንግሥት ላይ እምነት ማጣትን ያስከትላል፡፡

ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ስለሀገር ግንባታ ማሰብ አይቻልም”

አቶ ሰለሞን አረዳ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት

 

አቶ ሰለሞን፤ በተቻለ መጠን ማሻሻያዎቹ ያደጉ አገራትን ልምድ አምጥቶ መገልበጥ ሳይሆን፣ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲዛመዱ የተደረጉ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቶቻችን ሊለውጡ ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን አዳዲስ አሠራሮችንና አስተሳሰቦችን በህግ ማሻሻዎቹ ላይ አካትተናል፡፡ ለምሳሌ የዳኝነት ነጻነት ትልቁ ችግራችን ነው ብለን አንስተናል፡፡ የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ምን መደረግ እንዳለበት፣ እንዴት ቢደራጅ የተሻለ እንደሚሆን፣ የዳኛውን ግላዊ ነጻነትንም የዳኝነት አካሉን ተቋማዊ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችና የሕግ ጥበቃዎች ዝርዝር ድንጋጌዎችን አስቀምጠናል፡፡

የዳኛውን ግላዊ ነጻነት፣ የዳኝነት አካሉን ተቋማዊ ነጻነት፣የበጀት ችግር ለመመልከት ተችሏል፡፡ዳኝነት ሥራ ነው፡፡አገልግሎት በእቅድ የሚሠራ እንደመሆኑ የሚለካውም በአቅም ልክ ነው፡፡ ሃብት ሳታፈስ አንድን ነገር መጠበቅ አትችልም፡፡ እንዲህ ዐይነት መሠረታዊ ችግሮች አሉ፡፡ ሲታቀድ ቅልጥፍናን ውጤታማነትን  እንዲህ አደርጋለሁ፣ ምቹ የሥራ ሁኔታን እፈጥራለሁ ተብሎ ይታቀዳል፡፡ እነዚህ ሃብት የሚጠይቁ ከሆነና ያንን ለማስፈጸም የሚያስችል ሪሶርስ ከሌለ መጀመሪያውኑ መሞከርም መታሰብም የለበትም፡፡”

“አቶ ሰለሞን፤ ወደኃላፊነቱ እንደመጣን ሰሞን ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት ፍርድ ቤት በመንግሥት ተጽዕኖ ሥር ወድቋል፣ በወንጀል ወይም በፍትሃ ብሄር ጉዳይ መንግሥት ተከራካሪ ሆኖ ሲቀርብ ሁል ጊዜ እረቺ ይሆናል እንጂ አይረታም፣ በእዚህም ሰው ተስፋ ቆርጧል የሚሉ አስተያየቶች በተደጋጋሚ ይነሱ ነበር፡፡ በተለይም በጣም ወሳኝ በሆኑ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ነው የሚያነሱት፡፡ በእዚህ ጉዳይ ላይ እኛም የተገነዘብናቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ከዳኞች ጋርም በግልፅ ውይይት አድርገንባቸዋል፡፡ ከጊዜ ቀጠሮ መዝገብ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ከሆኑ ጉዳዮች ጋር፣ ዳኞች ምስክር የሚሰሙበት፣ ማስረጃ ከመመዘን አንጻርና ከመሳሰሉት ለመንግስት የሚያደሉ አሠራሮች እንደነበሩ በአስተያየት ይነሳ ነበር፡፡”

“አንድ ሰው መለቀቅ ካለበት መለቀቅ ይኖርበታል፣መቀጣት ካለበትም መቀጣት አለበት፡፡ መለቀቅ ያለበትን ሰው ከቀጣ ተጠያቂነትን ያስከትላል፣መቀጣት ያለበትን ደግሞ አላግባብ ከለቀቀ ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ የእኛ የተጠያቂነት ደረጃ በዳኝነት ማህበረሰብ በተለይ በወንጀል ተከስሶ የተቀጣ ሰው አላግባብ ነው የተቀጣሁት ብሎ በዳኛ ላይ ተጠያቂነትን የማስከተል አሰራር አልተለመደም፡፡ ብዙ ጊዜ ተጠያቂነትን ሊያስከትል የሚችለው መንግሥት ነው በማለት ለምን ተለቀቀ ብሎ አተኩሮ መስራት ላይ እንጂ በዋስትና መለቀቅ ያለበትን ሰው ዋስትና ከከለከለ ብዙም ተጠያቂነት አልነበረም፡፡ ተጠያቂነት በሁለቱም ተከራካሪዎች መካከል ሚዛናዊ መሆን አለበት፡፡ ይሄንን ለማስገንዘብ ውይይት ተደርጓል፡፡ በተቻለ መጠንም ይህ አስተሳሰብ ፍርድ ቤቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ተገንዝበናል፡፡”

“ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቁልፍ ባለድርሻ አካላችን ነው፡፡ የማይካድ ሃቅ ነው፡፡ አብረው በሚያሰሩን ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን፡፡ ምክንያቱም የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነት በፍርድ ቤት ላይ የሚለካው ፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግ ውጤታማ ሲሆኑ ነው፡፡ የፍርድ ቤቱም የዳኝነት አገልግሎቱም ውጤታማ ሊሆን የሚችለው እነዚህ አካላት ጠንካራ ሲሆኑ ነው፡፡ እዛ አካባቢ ላይ ውጤታማነት ከሌለ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ግልጽ በሆኑ በጋራ ጉዳዮች አብረን እንሠራለን፡፡”

“ያ ማለት ግን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መንግስትን ወክሎ የሚከራከር ሲሆን ከሌሎች ተከራካሪዎች እኩል ሕግና ማስረጃ በመመዘን የዳኝነት አገልግሎት መሰጠት የለበትም ማለት አይደለም፡፡ይህንን ለማስተካከል በርካታ ርቀቶችን ተጉዘናል፡፡ ይህንን የህብረተሰቡን አስተሳሰብ ሊቀይር በሚችል መልኩ ከአቀራረብ ጀምሮ ለመለወጥ እየተሰራ ነው፡፡ ችግር የለም ማለት አይደለም፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ ችሎት ሥነ ሥርዓት ላይ የቱ ዐቃቤ ሕግ ነው የቱ ዳኛ ነው ብለን መለየት በሚያቅተን ደረጃ ላይ ደርሰናል›› የሚሉ ስሞታዎች ይነሳሉ፡፡ አቃቤ ሕጎች ዳኞች ሲሰየሙ ተከራካሪ ወገኖችም ሆኑ ሌሎች ከወንበራቸው ሲነሱ አብረው መነሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም መንግሥትም እንደ አንድ ተከራካሪ ሆኖ ከሌሎቹ እኩል ስለሚቀርብ ነው፡፡ ግን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝ የሚያደርጉ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ፡፡ መስተካከል አለባቸው ብለን ከዳኞች ጋር በየጊዜው ውይይት እናደርጋለን፡፡ ከዐቅም በላይ ነገር ካጋጠማቸው ሕጋዊ እርምጃ  ወይም የማስተካከያ ርምጃ እንዲወስዱ እንነግራቸዋለን፡፡ ይህንን እኛም ትልቅ ችግራችን ነው ብለን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እንዲህ ዐይነት ነገሮች እንዲስተካከሉ ጥረት እያደረግን ነው፡፡ ያ ማለት በዐቃቤ ሕግ ተጽዕኖ ሥር ሆኖ ሳይሆን ከዕይታ ብንመለከት ችሎት ላይ ዳኛው ሲናገር ሌላው ተከራካሪ ቆሞ እያወራ ዐቃቤ ሕግ ተቀምጦ የሚናገር ከሆነ ዓቃቤ ሕጉ ዳኛውን እያዘዘው ነው ብሎ ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ዐይነት ነገሮች እንዳይኖሩ ለወደፊቱም እየጠራ እንዲሄድ እንፈልጋለን፡፡ እንደምናደርገውም ተስፋ አለኝ፡፡”

“ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ዴሞክራሲን፣ ሕገ-መንግሥታዊነትን፣የዜጎች መብት ጥበቃን፣ ዘላቂ ሰላም፣ ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ መረጋጋት ሊታሰብ አይችልም፡፡ መንግሥትና ኅብረተሰቡም መገንዘብ ይገባቸዋል፡፡በተለመደው አካሄድ አገርን እንገነባለን፣ዘላቂ ሰላም እናመጣለን፣ ሕገ መንግሥታዊነት እንዲጎለብት እናደርጋለን የሚለው አያስኬድም፡፡ ዴሞክራሲን እናሰፍናለን፣የሕግ የበላይነትን እናረጋግጣለን ብሎ ማሰብም አይቻልም፡፡ በፍርድ ቤት ላይ አለመተማመን አጠቃላይ አገዛዙ ላይ ዕምነት ማጣት ነው፡፡ ይህ እንደ አንድ ተግዳሮት ይታያል፡፡በአገር ግንባታ ላይም ተጽእኖ ያስከትላል፡፡ በመሆኑም ሁሉም በጋራ መረባረብ ይገባዋል፡፡ ሃላፊነቱ የፍርድ ቤት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው፡፡ ስለዚህ ማኅበረሰቡም  የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል፡፡ መንግሥትም ቁርጠኛ መሆን አለበት፡፡”

 

 

በዘላለም ግዛው ከአዲስ ዘመን፡- 

አቶ ሰለሞን፡-የዳኝነት አካል በህብረተሰብ እድገት ውስጥ መንግሥት የሚባለው አካል ከተመሰረበት ጊዜ ጀምሮ አብሮ የተፈጠረ፥ በዓለማችን ላይ ረጅም ታሪክ ያለው ነው፡፡ፍርድ፥ ፍትህ የሚባለውን አገልግሎት የሚሠጥ፤ ከጥንት የዓለም ሥልጣኔ ጀምሮ በእያንዳንዱ የዓለም ኅብረተሰብ ዕደገት ውስጥ የነበረ በተለይም ከሥነ መንግሥት ጋር ተያይዞ እያደጉ ከመጡት አስተሳሰቦችና ዕድገቶች ጋር በየጊዜው እየጎለበተና እያደገ የመጣ የፍትህ አገልግሎትን የሚሠጥ አካል ነው፡፡

በዘመናዊ አስተሳሰብ መንግሥት ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥት ሶስት አካላት አሉት፡፡እነዚህም ህግ አውጪው፥ሕግ አስፈፃሚ፥ ሕግ ተርጓሚ ወይም የዳኝነት አካል የሚባለው ነው፡፡የዳኝነት አካል ሕግን በመተርጎም የዜጎች መብቶች መከበራቸውን የሚያረጋግጥ፥ለዜጎች መብት መከበር ዋስትና የሚሰጥ፥ጥበቃ የሚያደርግ፥ ለህገ መንግሥታዊነትና ለሕገ መንግስት መከበር ዘብ የሚቆም በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ለዜጎች ቅርብ የሆነውና በጣም ጠቃሚና ቅድሚያ የሚሰጡት ተቋም ይህንን የዳኝነት አካል ነው፡፡

የዳኝነት አካል ዋናው ተግባሩ ሕግን በመተርጎም ለዜጎች ፍትህ መስጠት ነው፡፡የፍትህ አገልግሎት የዜጎች መብት በሚጣስበት ጊዜ መብቴ ተጥሶብኛል የሚለው ወገን የመብቱ መጣስ እንዳይቀጥል ወይም እንዲቆምና ሌሎች መብቶቹ የሚጠበቁለት ወደዚህ አካል መጥቶ ነው፡፡ህግ የተላለፈ አካልም ግዴታውን እንዲወጣና የሌሎችን ሰዎች መብት እንዲያከብር ለማድረግ ቁልፍ ሚና የሚጫወተው ይሄው የዳኝነት አካል ነው፡፡ በተለይ ጉልበትና ሃይል አለው ተብሎ የሚታሰበው መንግስት የዜጎችን መብት እንዳይጥስና እንዳይጎዳ ሊያስቆም የሚችለው ይህ የዳኝነት አካል ነው፡፡በዚህ መሰረት ደግሞ ውሳኔዎችን በመስጠት፥ ፍትህ በማረጋገጥ፥ ለህገመንግስቱ መከበርም ዘብ የሚቆም አካልም ነው፡፡

አሜሪካኖች ዛሬ ለደረሱበት የኢኮኖሚ ዕድገት፥ የህግ የበላይነት መከበር፥ የዜጎችና የግለሰቦች መብት ጥበቃ ሕገ መንግስታቸውን ካፀደቁበት ጊዜ ጀምሮ እያደገ ያለው ይህ የዳኝነቱ አካል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ ስለዚህ የዳኝነቱ አካል ሰብአዊነትን ከማስከበርና ኢኮኖሚን በማበልፀግ ትልቅ ሚና አለው፡፡በአጠቃላይ ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ስለሀገር ግንባታ ማሰብ አይቻልም፡፡በሃገር ግንባታ ውስጥ ህገመንግስታዊነት፥ የህግ የበላይነት፥ስርዓት ያለው የመንግስት አወቃቀር፥ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት፥ ሰላም፥ ደህንነት፥ ዋስትና የሚባሉት ነገሮች ሁሉ ያለዳኝነት አካሉ ሊታሰቡ አይችልም፡፡ለዚህ ነው እንግዲህ የዳኝነት አካሉ ለዜጎችም ሆነ ለአንድ አገር የማይተካ ሚና የሚጫወተው የምንለው፡፡

አዲስ ዘመን፡-በኢትዮጵያ የዳኝነት አካል አሠራር ምን ይመስላል? በተለየዩ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ የነበረውን አሰራር እያነፃፀሩ ይግለፁልኝ?

አቶ ሰለሞን፡-እንግዲህ የዳኝነት አካል በኢትዮጽያ በስነመንግስት ረጅም ታሪክ አለን፡፡ በተለይም ደግሞ በዘመናዊ መንግስት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ወይም በንጉሥ  ኃይለሥላሴ ዘመናዊ ሕጎች በኢትዮጽያ እንዲወጡ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ከአውሮፓ በመውሰድ ከአገር ሁኔታ ጋር እንዲዛመዱ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ያንን መነሻ በማድረግ ዘመናዊ ፍርድ ቤቶችም በተወሰነ መልኩ ተደራጅተዋል፡፡በተለይም እ.ኤ.አ 1955 የወጣው ህገመንግስት የዘውዳዊ ስርዓትን መነሻ ያደረገ፤ እውቅና የሰጠ ነበር፡፡ ስለዜጎች መብት፥ ስለመንግስት አወቃቀር፥ ስለፍርድ ቤቶች ስልጣንም፥ ዝርዝር ድንጋጌ ያለው ነው፡፡

ይህ ሕገ መንግሥት የመንግሥ ትንና የሶስቱን አካላት ሥልጣን የማደበላለቅ ነገሮች ቢኖሩም፤ ንጉሱ በሁሉም አካላት የበላይ ነው፥ የስራ አስፈፃሚውም፣ የህግ አውጪውም የበላይ ነው፤ የዙፋን ችሎት የሚባልም ነበር፡፡ የዳኝነት ስራ ሃላፉነትም አላቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች እንግዲህ በስልጣን ክፍፍል ወቅት የመደበላለቅ ነገር ቢኖርም በተወሰነ መልኩ በአገራችን ዘመናዊ ህጎች መተግበር ተጀምሮ ለዚያ ህግ ደግሞ የውጭ ባለሙያዎችን ተቀጥረውነው የመጀመሪያዎቹ ህጎች እንዲወጡ የተደረጉት፡፡እነዚያን ህጎች ለመተርጎም ያስችል ዘንድም የዳኞቹም ብዙዎቹ የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ፡፡ ታዋቂ የውጭ ባለሙያዎችን በማምጣት የዳኝነት አካሉ ስር እንዲሰድ በጥልቅ ሁኔታ ላይ የተገነባ እንዲሆን በጎ ጅምሮች ነበሩ ተብሎ ይወሰዳል፡፡

የኢትዮጽያ የዳኝነት አካሉ ኢትዮጽያ ከምትከተላቸው የፖለቲካ መስመሮችና አካሄዶች ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው፡፡ለዚህ ነው በደርግ ጊዜ በተለይም በኃላ ላይ አገሪቱ የተከተለችበት መስመር ግራ ዘመም የፖለቲካ አስተሳሰብ ከመሆኑ አንፃር የኢትዮጻያ ፍርድ ቤቶች የተደራጁትም የግራዘም የፖለቲካ መስመርን ከማሳካት አንፃር ነው፡፡አንዱ የመንግስት አካል ሌላውን እንዲቆጣጠርና እንዲከታተል፥ ህገመንግስታዊነት እንዲሰፍን፥ ጥበቃ ከማድረግ አንፃር ስራዎቻቸውን ሲያከናውኑ አልነበረም፡፡ይህ እንደትልቅ ክፍተት ይወሰዳል፡፡

በወቅቱ ከነበረው አስተሳሰብ ጋር አብሮ የመቆራኘት ነገር ነበር፡፡በኋላም የስርዓት ለውጥ ከመጣና በ1987ዓ.ም ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ ህገመንግስቱ በጣም ዘመናዊ ተብሎ የሚወሰድ ነው፡፡በተለይ ነፃ የዳኝነት አካል እንደሚደራጅ፥ የዳኝነት አካል ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት እንደሚሰጥ እና ሰብአዊ መብት ጥበቃዎችና ዝርዝር ድንጋጌዎች በህገመንግስቱ እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡በዚያ መልኩ የዳኝነት አካሉ የተደረጃ በመሆኑ ህገመንግስቱም ዘመናዊ ህገመንግስት ተብሎ የሚወሰድ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ሌሎች ችግሮችም አሉ፡፡ ነገር ግን የፍርድቤትን ስልጣን ምሉዕ ከማድረግ አንፃር የእኛ ህገመንግስት አሁንም ክፍተት ይታይበታል፡፡

ፍርድቤቶቹ በእውነት ለዜጎች መብት መከበር ዘብ ሆነው ሲሰሩ ነበር ወይ? የዜጎች መብቶች ጥበቃ እንዲያገኙ የሚያደርጉ ተቋማት ነበሩ ወይ?ህገመንግስታዊነት እንዲጎለብት በተሰጣቸው ስልጣንና ሃላፊነት ልክ እየተንቀሳቀሱ ነበር ወይ? ቢባል በርካታ ክፍተቶች አሉባቸው፡፡ አሁን ያለንበት ሁኔታም ይህንኑ ያንፀባርቃል፡፡

አዲስ ዘመን፡- ስለኢህድሪ ህገ መንግስት እስቲ ትንሽ ያብራሩልን?

አቶ ሰለሞን፡- እኔ እንደተረዳሁት የኢህድሪ ህገመንግስት የቆየችው ከ1980 ጀምሮ ሶስት ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከሶቭየት ህብረት መንግስት የተገለበጠ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ስለዜጎች መብቶች ጥበቃ ያደርጋል፡፡የእኛ አገር ህገመንግስቶች ሲቀረፁ በተቻለ መጠን ወቅቱ የሚጠይቃቸውን ዘመናዊ አስተሳሰቦች ሁሉ ያካትታሉ፡፡ዋናው ችግር ግን እነዚያን ነገሮች ወደመሬት አውርዶ ተግባራዊ ማድረጉ ላይ ነው፡፡ለዚህ ነው እንግዲህ በወቅቱም ስለደርግ ጊዜ ፍርድቤት በሚነገርበት ጊዜ በተወሰነ መልኩ እኔም የቀሽብር ችሎት ላይ በምሰራበት ጊዜ ያስተዋልኩት ያለፍርድቤት ትዕዛዝ ሰዎች ይገደሉ ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ መሰረታዊ የሰው ልጅ መብት ህይወት እስከሚያሳጣ ድረስ ውሳኔ ሊወስን ፥ በሰውልጆች የንብረት መብትም፥ የሌሎች ነፃነትና መብቶችን ያለፍርድ ቤት ውሳኔ መንግስት የሚባለው አካል በመንግስትነቱ ብቻ የሚያደርጋቸው ከሆነ ፍርድቤት የሚባለው ነገር መኖሩን አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡ ይህ በደርግ ወቅት በስፋት የሚታይ ክስተት ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- በኢህአዴግ ዘመን የዳኝነት አካሉ መጠቀሚያ ሆኗል በሚባለው ሃሳብ ይስማማሉ?

አቶ ሰለሞን፡- በአገራችን ፍርድ ቤት ላይ ሰዎች እምነት አጥተዋል ይባላል፡፡ የፍርድ ቤት እምነት ማጣት መሰረቱ በመንግስት ላይ እምነት ማጣት ነው፡፡ አንድ ሰው በፍርድ ቤት ላይ እምነት ካጣ በአጠቃላይ በስርዓቱ ላይ እምነት ያጣል፡፡ ያን ጊዜ ነው እንግዲህ በአጠቃላይ በአገሪቱ ሰላም ማጣትና ያለመረጋጋት ይሰፍናል፡፡ ከዚህ አንፃር ክፍተቶች አልነበሩበትም ወይ? ብለህ ከጠየቅከኝ በትክክል ችግሮች ነበሩበት፡፡

እምነት ያጣነው እነዚህ ፍርድቤቶች በሚሰሯቸው ተፈጥሯዊ የዳኝነት አካሉ ሚና መወጣት ባለመቻላቸው ነው፡፡ አሁንም ትኩረት ሰጥቼ መናገር የምፈልገው ህዝብ በፍርድ ቤት ላይ እምነት አጣ ማለት በህግ ላይ እምነት ያጣል፡፡ ይህም የመንግስትን ቅቡልነት አደጋ ላይ ይጥለዋል፡፡ ያን ጊዜ የመንግስት ተፈጥሯዊ ባህሪ ሰዎች በሰላም ወጥተው በሰላም መግባት የሚችሉበት ሁኔታ አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ አጠቃላይ ቀውሶችም ይፈጠራሉ፡፡ይህ የሚታወቅና የኖርንበትም ነው፡፡ ከዚህ አንፃር እንግዲህ ፍርድቤቶች ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ማለት አይቻልም፡፡ ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ስለህጋዊነት፥ ስለህግ የበላይነት፥ ስለሀገር ግንባታ፥ ስለህገመንግስታዊነት፥ ስለህግ የበላይነት መናገር አይቻልም፡፡ ባለፉት 27 ዓመታትም የተፈጠረው ክፍተት ይሄ ነበር፡፡

አዲስ ዘመን፤ የዳኞች ስራ ይመዘናል ብለው ያምናሉ?

አቶ ሰለሞን፤ የዳኝነት ስራ አይመዘንም የሚሉ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ የዳኝነት ምዘናን ከዳኝነት ነጻነትና ጣልቃ ገብነት ጋርም የሚያያይዙ አሉ፡፡ በበርካታ አገሮችም አልዳበረም፡፡ በምዘና ሰበብ ስራን እንዲህ አልሰራህም በሚል በስራዬ ውስጥ ጣልቃ ገብነትና ጫና መፍጠሪያ ነው ብለው የሚወስዱም ዳኞች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አሁን እየጎለበተ የመጣው ዳኝነት ማለት ሙያዊ አገልግሎት (professionalism) ነው፡፡ የሙያ አገልግሎት ደግሞ በሙያ መሰረት መሰራቱና አለመሰራቱ መመዘን አለበት፡፡ ሙያው የሚጠይቀውን እውቀት መነሻ በማድረግ ሊሰራ የሚችል በመሆኑ ባግባቡ መተግበሩ መታየት አለበት ብለው የተለያዮ አገራት የምዘና ስራ ተግብረዋል፡፡
ለእዚህ ነው እኛም ሌላ ነገር እንዳያስነሳ በሚል አለም አቀፍ ልምድ ያለው አሜሪካዊ ዜጋን ቀጥረን በተለያዮ አገሮች ልምድ መነሻነት ስራው ከጥራት አንጻር እንዴት እንደሚመዘን የሰራነው፡፡ የዳኝነት ነጻነትንም በማይጋፋ የዳኛውን የመወሰንና የመተርጎም ሚናውን በማይነካና መንገድ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ዳኞች አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ተግባራዊ ሲደረግም በተሻለ መንገድ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ የተወሰነ ለውጥ እናመጣለን የሚል እምነት አለኝ፡፡

አዲስ ዘመን፡- የዳኝነት አካሉን ነፃ ለማድረግ ምን እየሰራችሁ ነው?

አቶ ሰለሞን፡- ተጨማሪ አዳዲስ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዲመጡ አድርገናል፡፡ የህግ ማሻሻያ ለውጦችንም ለማካሄድ ሁለት ህጎች ላይ ዝርዝር ጥናቶች አድርገን ረቂቅ ህጎችን ለምክር ቤት ልከናል፡፡የአሰራር ስርዓቶችን ለማዘጋጀት በውጭ ባለሙያዎች ጥናቶች ተሰርተዋል፡፡ የዳኞች ስነምግባር ኮድ ኦፍ ኮንዳክት እንደአዲስ ተጠንቷል፡፡ የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ማለትም ጉዳዮች ፍርድ ቤቶች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁበት ድረስ እንዴት መመራት እንዳለባቸው የሚገልጽ የጊዜ መለኪያዎችን አዘጋጅተናል፡፡

የፍርድ ቤቶች መርህ አስማሚነትን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ጉዳዮችን ለመቀነስ ፍርድ ቤቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ የድርድር ማዕከላትን በየፍርድ ቤቶች አደራጅተን በአዲሱ ህግ ውስጥ አካተናል፡፡ የንግድ ችሎቶችን በሚመለከት አሰራሮችን ለማሻሻል የሚያስችል ጥናት ተካሂዷል፡፡

አዲስ ዘመን፤ የፍርድ ቤቶች እንደገና ማሻሻያ አዋጆች ማለትም፤ የዳኝነት አስተዳደር አዋጅና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማደራጃ አዋጅ ምን አዳዲስ ነገሮች ይዘዋል?

አቶ ሰለሞን፤ በተቻለ መጠን ማሻሻያዎቹ ያደጉ አገራትን ልምድ አምጥቶ መገልበጥ ሳይሆን ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲዛመዱ የተደረጉ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቶቻችን ሊለውጡ ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን አዳዲስ አሰራሮችንና አስተሳሰቦችን በህግ ማሻሻዎቹ ላይ አካትተናል፡፡ ለምሳሌ የዳኝነት ነጻነት ትልቁ ችግራችን ነው ብለን አንስተናል፡፡ የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ምን መደረግ እንዳለበት፣ እንዴት ቢደራጅ የተሻለ እንደሚሆን፣ የዳኛውን ግላዊ ነጻነትንም የዳኝነት አካሉን ተቋማዊ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችና የ ሕግ ጥበቃዎች ዝርዝር ድንጋጌዎችን አስቀምጠናል፡፡

የዳኛውን ግላዊ ነጻነት፣ የዳኝነት አካሉን ተቋማዊ ነጻነት፣የበጀት ችግር ለመመልከት ተችሏል፡፡ዳኝነት ስራ ነው፡፡አገልግሎት በእቅድ የሚሰራ እንደመሆኑ የሚለካውም በአቅም ልክ ነው፡፡ ሃብት ሳታፈስ አንድን ነገር መጠበቅ አትችልም፡፡እንዲህ አይነት መሰረታዊ ችግሮች አሉ፡፡ ሲታቀድ ቅልጥፍናን ውጤታማነትን እንዲህ አደርጋለሁ፣ምቹ የስራ ሁኔታን እፈጥራለሁ ተብሎ ይታቀዳል፡፡ እነዚህ ሃብት የሚጠይቁ ከሆነ እና ያንን ለማስፈጸም የሚያስችል ሪሶርስ ከሌለ መጀመሪያውኑ መሞከርም መታሰብም የለበትም፡፡

ከበጀት ጋር ተያይዞ በአለም አቀፍ ደረጃ የተለመደው ነገር በጀቱ በፓርላማ ይጸድቃል፡፡ በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ይሄ ነገር አለ፡፡ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ አቅርበን በፓርላማ አጸድቀናል፡፡ ለገንዘብ ሚኒስቴር በጀታችንን አልላክንም፡፡በህጉም ዝርዝር ነገር ነው ያስቀመጥነው እንጂ ዋናው ነገር በህገ መንግስቱ ተቀምጧል፡፡በቀጥታ ህገ መንግስቱ ለምክር ቤት አቅርበን የበጀት ጥያቄያችንን እንደምናጸድቅ ይደንግጋል፡፡ባለፈው ዓመት እኛ ወደ ሃላፊነት እንደመጣን ያደረግነው ይህንን ነው፡፡ በጀታችንን በቀጥታ ለምክር ቤት አቅርበን አጸድቀናል፡፡ ይሄ ባለፉት 27 ዓመታት ከተሰራው ውስጥ አንዱ ፡፡ ጫና ፈጥረን ነው ወደ ምክር ቤት የሄድነው፡፡

በማሻሻያው ያካተትነው ሌላው ነገር በጀትን የሚመለከት ነው፡፡ ሌሎች አገሮች በጀት ሲመደብላቸው መስፈርት አላቸው፡፡እኛ የሚመደብልን በጀት አገሪቱ ከምትመድበው በጀት ዜሮ ነጥብ ዜሮ ሶስት (0.03) በመቶ ነው፡፡በአለም አቀፍ ደረጃ የተሰሩ ጥናቶችን እንዳየነው ለፍርድ ቤቶች የሚመድቡት እስከ ሶስት በመቶ አጠቃላይ የአገሪቱ በጀት ይደርሳል፡፡በቂ ሃብትና በጀት ሳትመድብ ስለ ህግ የበላይነት፣ ስለህገ-መንግስታዊነት፣ ስለፍትህ ማረጋገጥ ማሰብ አይቻልም፡፡ መንግስትም ግዴታውን አልተወጣም ማለት ነው፡፡ መንግስት በግብር ከፋዮ ገንዘብ ዜጋው ይህንን አገልግሎት እንዲያገኝ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት ፍርድ ቤቱ የተሰጠውን ሃላፊነት እንዲወጣና ተልዕኮውን ማሳካት እንዲችል ለማድረግ ትግበራውን ማከናወን የሚያስችል በጀት መመደብ አለበት፡፡እኛ እየጠየቅን ያለነው የአሜሪካው አይነት ፍርድ ቤት አይደለም፡፡አገሪቱ አቅም የላትም፡፡ የምንጠይቀው ግን የአገሪቱ ኢኮኖሚ ካመነጨው ፍትሃዊና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በጀት ለፍርድ ቤቱ እንዲመደብ ነው፡፡

በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ከአጠቃላይ የአገሪቱ በጀት እስከ ሶስት በመቶ ይሄዳል፡፡ ይሄ ቀርቶ አንድ፣ አንድ ነጥብ አምስትና ሁለት በመቶ ቢመደብልን ፍርድ ቤትን መለወጥ እንችላለን፡፡ በጀት መመደብ ብቻ ሳይሆን ሌላ አገር የሚደረገው (Consolidated judiciary Fund) ጥቅል በጀት ከተመደበ በኃላ ራሳቸው የፍትህ አካላቱ ይወስናሉ፡፡ ግን ስራ ላይ ስለመዋሉ በመንግስት ኦዲት ይደረጋል፡፡ከተያዘው በጀት ርእስ መውጣት አይቻልም፡፡ ይችንም የሚቆጣጠጠረው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው፡፡ ይሄ አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አይደለም፡፡

መንግስት የግብር ከፋዮን ገንዘብ የመመደብ ግዴታ አለበት፡፡ ከፍርድ ቤቶች ከዳኝነት የሚሰበሰቡ ገቢዎች አሉ፡፡ ሌሎች አገራት ይህንን ገቢ ለመንግስት ገቢ አያደርጉም፡፡ ያደጉት አገራትም በህገ መንግስቶቻቸው ላይ ያስቀምጣሉ፡፡ ለምሳሌ የጋናን ህገ መንግስት ብንመለከት ‹‹ከፍርድ ቤት የሚሰበሰበው ገንዘብ የፍርድ ቤቱ አጠቃላይ የበጀት አካል ይሆናል›› ይላል፡፡ ይህንን ዝርዝር ድንጋጌ አድርገን ለምክር ቤት ከተላከ በኋላ ይጸድቃል ብለን እናስባለን፡፡

የጉዳዩች ፍሰት አስተዳደርን በሚመለከት ጉዳዮች ከተጀመሩበት አንስቶ እስከሚጠናቀቁ ድረስ በጊዜ መመዘኛ ከፋፍሎ ለማስቀመጥ የሚያስችል ህጋዊ ጥናት አስጠንተናል፡፡ያንን የሚደግፍ ህጋዊ እውቅና እንዲኖረው አሰራርን የሚያቀል የጉዳዮች መዝገብ አያያዝ አሰራር ይዘናል፡፡በህጋችን የተለመደው ክስ የሚቀርብበት፣መልስ የሚቀርብበት፣ ማስረጃ የሚቀርብበት በጽሁፍ መሆኑን ነው፡፡ አሁን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ብንጀምር ህጋዊ መሰረት የለንም፡፡ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመዝገብ አያያዝ ስርዓት ፍርድ ቤቱ ይዘረጋል ፤ዝርዝሩን ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል የሚል ድንጋጌ አውጥተን በእዚህ የህግ ማዕቀፍ አካትተናል፡፡

ይህ የሚጠቅመን ብዙ ፍርድ ቤቶች ክስን በወረቀት ፎርም ብቻ ሳይሆን በሲስተም ላይ ማስቀመጥ ጀምረዋል፡፡ ክስ፣ የምስክሮች ቃል፣ መልስ፣ የሰነድ ማስረጃዎች ኮምፒውተር ላይ የሚቀመጡበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ዳኞች የሚሰጡት ትእዛዞች፣ ውሳኔዎች ጭምር ይቀመጣሉ፡፡ የጊዜ መመዘኛ ከተቀመጠ የትኛው ጉዳይ በምን ያህል ጊዜ እንዳለቀ፣ ከአንድ ፍርድ ቤት ወደሌላው ፍርድ ቤት ምልልሱ በሶፍት ኮፒ ለማድረግ፣ ዳኞች ወረቀት አንብበው አንዱ ለሌላው የማስረዳት ሳይሆን እያንዳንዱ ዳኛ በሲስተም ያለውን በመመልከት ለውይይት ብቻ እንዲገናኙ ለማድረግ ታስቧል፡፡ ይህ የዳኛውን ስራ በጣም ያቀላጥፋል፡፡ ግን ለዚህ የህግ ማዕቀፍ የለንም፡፡ በአዲሱ አዋጃችን ይህንንም አስገብተናል፡፡

ዳኝነት የሙያ አገልግሎት ነው፡፡የዳኞች እጥረትም ይኖራል፡፡ሌሎች አገሮች ስራዎች የሚሰሩት በቋሚ ዳኞች ብቻ አይደለም፡፡ጊዜያዊ ዳኞች ከቀድሞ ዳኞች፣ ከጠበቆች፣ ከዐቃቤ ህጎች መካከል ይቀጥሩና ለስድስት ወራት፣ለአንድ ዓመት እንዲሰሩ አድርገው ያንን ችግሮቻቸውን ይፈቱበታል፡፡ ልዮ እውቀት ያላቸውን ሰዎችም አስገብቶ የመጠቀም ሁኔታ የተለመደ ነው፡፡እውቀት፣ሙያና ችሎታ ያለውን ሰው በማንኛውም ጊዜ መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ሹመት ቢያስፈልግም ለስድስት ወራትና ለአንድ ዓመት ማድረግ ይቻላል፡፡ሃላፊነቱንም እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡በሰፊው ብዙ አገራት እየሰሩበት ነው፡፡ እንደአዲስ በህጉ ውስጥ ካካተትናቸው ያልተለመዱ አሰራሮችም ውስጥ ይሄ አንዱ ነው፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት፣ምክትል ፕሬዚደንት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይሾማል ይላል፡፡ ሲነሱ እንዴት እንደሚነሱ ሕጋዊ አሰራር አልተቀመጠም፡፡ በአዲሱ አዋጅ ይህ እንድካተት አድርገናል፡፡ በሌሎች አገሮች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚታዮት ትላልቅ አገራዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡በእኛም ሀገር ከትግራይ፣ ከጎንደር፣ከቦረናም፣ ከአሶሳም ከጅግጅጋም ይመጣል፡፡ዜጎች ወደ ሙግት በሚገቡበት ጊዜ ያዋጣኛል ፤አያዋጣኝም የሚል ስሌት ሰርተው አይደለም፡፡ ይህ የዜጎችን እንግልት ፈጥሯል፣ ፍርድ ቤቶች ላይም ጫና አሳድሯል፡፡ጠቅላይ ፍርድ ቤትም መስራት ያለበትን የአገሪቱን የህግ ስርዓት የመምራትና ማሻሻል ቢሆንም እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በትናንሽ ጉዳዮች የመዋጥ ሁኔታ ይታያል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላይ ወደ 43 ገደማ ዳኞች አሉን፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም የዳኛ እጥረት አለን፡፡ በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለ350 ሚሊየን ህዝብ ያሉት ዘጠኝ ዳኞች ሲሆኑ፤የጠቅላይ ፍርድ ቤት ስልጣንን አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ በመገደባቸው ባሉት ውስን ዳኞች ተግባራቸውን መወጣት ችለዋል፡፡ አሁንም ወደታች ያለውን ፍርድ ቤት አጠናክረን አብዛኛው ሰራ እዛ እንዲሰራ እያደረግን ነው፡፡ የሰበር ስልጣንንም የመፈተሸ ስራዎች በአዲሱ አዋጅ ተሰርቷል፡፡ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዲሆን ጉዳዮች በአብዛኛው ወደ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እንዲወርዱ እንዲሁም የወንጀልና ፍትሃ ብሄር ጉዳዮችንም ስልጣን ወደ ታች እንዲወርዱ ለማስቻል ስራዎች ሰርተናል፡፡

ሌላው ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛውን የሚመለከት ነው፡፡ እነዚህ የአስተዳደር ሰራተኞች ደጋፊዎች አይደሉም፡፡እነዚህ ሰራተኞች የዳኝነቱ አካል ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የአስተዳደር አካሉ በሲቪል ሰርቪስ ይተዳደር ነበር፡፡ብዙ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ስር ነው የሚሆነው፡፡ ይህን ህጋዊ ማዕቀፍ ሊቀይር በሚችል መልኩ ህጉ ውስጥ ከትተናል፡፡የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የአባላትን ስብጥር አብዛኞቹ ዳኞች እንዲሆኑ የሚያስችል ለማድረግ ታቅዷል፡፡በዳኞች ጉዳይ ዳኛው እንዲወስን የቀድሞ አወቃቀርን የሚቀይር ድንጋጌ ከትተናል፡፡ ዝርዝር በርካታ አዳዲስ ነገሮች ተካትተዋል፡፡ በቀጣይነት በምክር ቤት ውይይት ይደረግበታል፡፡

አዲስ ዘመን፤ አንዳንዶች የዳኝነት አካሉ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተጽእኖ ስር መውደቁን ያነሳሉ፡፡ ከዐቃቤ ህግ ጋር በምትሰሩት ስራ ላይ ምን ያህል ጥንቃቄ ታደርጋላችሁ ?

አቶ ሰለሞን፤ ወደኃላፊነቱ እንደመጣን ሰሞን ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት ፍርድ ቤት በመንግስት ተጽእኖ ስር ወድቋል፣ በወንጀል ወይም በፍትሃ ብሄር ጉዳይ መንግስት ተከራካሪ ሆኖ ሲቀርብ ሁል ጊዜ እረቺ ይሆናል እንጂ አይረታም፣ በእዚህም ሰው ተስፋ ቆርጧል የሚሉ አስተያየቶች በተደጋጋሚ ይነሱ ነበር፡፡በተለይም በጣም ወሳኝ በሆኑ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ነው የሚያነሱት፡፡ በእዚህ ጉዳይ ላይ እኛም የተገነዘብናቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ከዳኞች ጋርም በግልፅ ውይይት አድርገንባቸዋል፡፡ ከጊዜ ቀጠሮ መዝገብ፣ ከፍተኛ የመንግስት ከሆኑ ጉዳዮች ጋር፣ ዳኞች ምስክር የሚሰሙበት፣ ማስረጃ ከመመዘን አንጻርና ከመሳሰሉት ለመንግስት የሚያደሉ አሰራሮች እንደነበሩ በአስተያየት ይነሳ ነበር፡፡

አንድ ሰው መለቀቅ ካለበት መለቀቅ ይኖርበታል፣መቀጣት ካለበትም መቀጣት አለበት፡፡ መለቀቅ ያለበትን ሰው ከቀጣ ተጠያቂነትን ያስከትላል፣መቀጣት ያለበትን ደግሞ አላግባብ ከለቀቀ ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ የእኛ የተጠያቂነት ደረጃ በዳኝነት ማህበረሰብ በተለይ በወንጀል ተከስሶ የተቀጣ ሰው አላግባብ ነው የተቀጣሁት ብሎ በዳኛ ላይ ተጠያቂነትን የማስከተል አሰራር አልተለመደም፡፡ ብዙ ጊዜ ተጠያቂነትን ሊያስከትል የሚችለው መንግስት ነው በማለት ለምን ተለቀቀ ብሎ አተኩሮ መስራት ላይ እንጂ በዋስትና መለቀቅ ያለበትን ሰው ዋስትና ከከለከለ ብዙም ተጠያቂነት አልነበረም፡፡ ተጠያቂነት በሁለቱም ተከራካሪዎች መካከል ሚዛናዊ መሆን አለበት፡፡ ይሄንን ለማስገንዘብ ውይይት ተደርጓል፡፡ በተቻለ መጠንም ይህ አስተሳሰብ ፍርድ ቤቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ተገንዝበናል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቁልፍ ባለድርሻ አካላችን ነው፡፡ የማይካድ ሃቅ ነው፡፡ አብረው በሚያሰሩን ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን፡፡ ምክንያቱም የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነት በፍርድ ቤት ላይ የሚለካው ፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግ ውጤታማ ሲሆኑ ነው፡፡ የፍርድ ቤቱም የዳኝነት አገልግሎቱም ውጤታማ ሊሆን የሚችለው እነዚህ አካላት ጠንካራ ሲሆኑ ነው፡፡ እዛ አካባቢ ላይ ውጤታማነት ከሌለ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ግልጽ በሆኑ በጋራ ጉዳዮች አብረን እንሰራለን፡፡

ያ ማለት ግን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መንግስትን ወክሎ የሚከራከር ሲሆን ከሌሎች ተከራካሪዎች እኩል ህግና ማስረጃ በመመዘን የዳኝነት አገልግሎት መሰጠት የለበትም ማለት አይደለም፡፡ይህንን ለማስተካከል በርካታ ርቀቶችን ተጉዘናል፡፡ ይህንን የህብረተሰቡን አስተሳሰብ ሊቀይር በሚችል መልኩ ከአቀራረብ ጀምሮ ለመለወጥ እየተሰራ ነው፡፡ ችግር የለም ማለት አይደለም፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ ችሎት ስነስርዓት ላይ የቱ አቃቤ ህግ ነው የቱ ዳኛ ነው ብለን መለየት በሚያቅተን ደረጃ ላይ ደርሰናል›› የሚሉ ስሞታዎች ይነሳሉ፡፡ አቃቤ ህጎች ዳኞች ሲሰየሙ ተከራካሪ ወገኖችም ሆኑ ሌሎች ከወንበራቸው ሲነሱ አብረው መነሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም መንግስትም እንደአንድ ተከራካሪ ሆኖ ከሌሎቹ እኩል ስለሚቀርብ ነው፡፡ ግን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝ የሚያደርጉ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ፡፡ መስተካከል አለባቸው ብለን ከዳኞች ጋር በየጊዜው ውይይት እናደርጋለን፡፡ ከዐቅም በላይ ነገር ካጋጠማቸው ህጋዊ እርምጃ ወይም የማስተካከያ ርምጃ እንዲወስዱ እንነግራቸዋለን፡፡ ይህንን እኛም ትልቅ ችግራችን ነው ብለን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እንዲህ አይነት ነገሮች እንዲስተካከሉ ጥረት እያደረግን ነው፡፡ ያ ማለት በዐቃቤ ህግ ተጽእኖ ስር ሆኖ ሳይሆን ከእይታ ብንመለከት ችሎት ላይ ዳኛው ሲናገር ሌላው ተከራካሪ ቆሞ እያወራ ዐቃቤ ህግ ተቀምጦ የሚናገር ከሆነ ዓቃቤ ህጉ ዳኛውን እያዘዘው ነው ብሎ ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እንዲህ አይነት ነገሮች እንዳይኖሩ ለወደፊቱም እየጠራ እንዲሄድ እንፈልጋለን፡፡ እንደምናደርገውም ተስፋ አለኝ፡፡

አዲስ ዘመን፤ የዳኝነት አካሉን እያወኩ ያሉ ችግሮች ምንድን ናቸው?

አቶ ሰለሞን፤ አሁን በጀት ትልቁ ችግራችን ነው፡፡የማስቻያ ቦታዎች እጥረት፣ የምንገለገልባቸው በቂ ህንጻዎችና ምቹ የመስሪያ ቦታዎች አለመኖራቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ እንደአገር ታዳጊ ነን፡፡ ግን ከድህነታችንም ላይ ቆንጥረንም ቢሆን ለተቋሙ የሚገባውን በማድረግ በኩል ችግር እየገጠመን ነው፡፡ የአሰራር ስርዓቶች እየዘረጋን፣የህግ ማሻሻያዎች እያደረግን እንገኛለን፡፡ በዘላቂነት ብዙ ነገር ያስፈልጉናል ብለን እናስባለን፡፡ የዳኞችን ጥቅማጥቅሞችን ከማማላት አንጻር ከፍተኛ ፈተና እየገጠመን ነው ፡፡ የፍርድ ቤት ነጻነት ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤት ነገሮችን ሊሰራ የሚያስችልበት ስልጣንም ሊኖረው ይገባል፡፡ህገ መንግስታዊነት እንዲሰፍን የሚያደርግ፣ በመንግስት አካላት መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ያንን ሊፈታ የሚያስችል መሆን አለበት፡፡

በፌዴራል መንግስታት አስተዳደር ውስጥ እንደመገኘታችን በፌዴራልና በክልሎች መካከል አለመግባባቶችን፣ግጭቶች፣አንዱ ሌላውን ስልጣኔ ውስጥ ገብቷል የሚሉትን ነገሮች የሚያስችለውን የህገ መንግስትና የህግ ነጻነት እንዲጎናጸፍ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ይህ ካልሆነ የፍርድ ቤት ስራው ምሉዕ አይሆንም፡፡ ካልሆነ ደግሞ ተአማኒነት ይጎድላል፣መንግስት ላይም እምነት ይታጣል፡፡ አሁንም እዚህና እዚያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከመቅረፍ አንጻርም ፍርድ ቤቶች ሚናቸውን ሊጫወቱ የሚያስችል ስልጣን ሊኖራቸው ይገባል፡፡

እዛ አካባቢ ያሉትን ችግሮች መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ዴሞክራሲን፣ ህገ-መንግስታዊነትን፣የዜጎች መብት ጥበቃን፣ ዘላቂ ሰላም፣ ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ መረጋጋት ሊታሰብ አይችልም፡፡መንግስትና ህብረተሰቡም መገንዘብ ይገባቸዋል፡፡በተለመደው አካሄድ አገርን እንገነባለን፣ዘላቂ ሰላም እናመጣለን፣ህገ-መንግስታዊነት እንዲጎለብት እናደርጋለን የሚለው አያስኬድም፡፡ዴሞክራሲን እናሰፍናለን፣የህግ የበላይነትን እናረጋግጣለን ብሎ ማሰብም አይቻልም፡፡በፍርድ ቤት ላይ አለመተማመን አጠቃላይ አገዛዙ ላይ እምነት ማጣት ነው፡፡ይህ እንደ አንድ ተግዳሮት ይታያል፡፡በአገር ግንባታ ላይም ተጽእኖ ያስከትላል፡፡በመሆኑም ሁሉም በጋራ መረባረብ ይገባዋል፡፡ሃላፊነቱ የፍርድ ቤት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው፡፡ ስለዚህ ማህበረሰቡም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል፡፡መንግስትም ቁርጠኛ መሆን አለበት፡፡

 

ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም ሰለሞን አረዳ ፌስቡክ

በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩና የሽብር ጥቃት በሃገሪቱ ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

12 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩና የሽብር ጥቃት በሃገሪቱ ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አቶ በርሃኑ ፀጋዬ በሰጡት መግለጫ እንደጠቆሙት፥ በሶስት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ የተቋማቱን የስራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ጨምሮ 59 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

አቶ ብርሃኑ በመንግሥት ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ የተፈፀመ ከባድ ወንጀሎችን በተመለከተ ባለፉት ሶስት ወራት
ምርመራ መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህ ምርመራም በወንጀሎቹ የደረሰውን ጉዳትና ተጠርጣሪዎቹ ያደረሱትን ብክነት ተመርምሯል ነው ያሉት።

በብዛት ሙስና ይፈፀማል ተብሎ የሚታመነው በግዢ ሂደት በመሆኑ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ተቋም ላይ ምርመራ ተካሂዷል ብለዋል።

ይህ ተቋም ላይ በተካሄደው የምርመራ ውጤት መሰረትም ከ400 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ ጋር በተያያዘ በጥቅም በመመሳጠር ተጠርጣሪዎቹ በመንግስት ላይ በአጠቃላይ 23.7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህ ግዥ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎቹ የዳቦ ዕጥረት እንዲከሰት በማድረግ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸው ተነግራል፡፡

ከኮምፒውተር ግዥ ጋር ተያይዞ የቴክኒክ ምርመራ ያለፉ አቅራቢ ድርጅቶ እያሉ ምርመራውን ካላለፉ ተቋማት ግዥ እንዲፈፀም ተደርጓልም ነው ያሉት፡:

በውሃ ስራዎች ኮንስትራክን ኮርፖሬሽን ውስጥ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች እርስ በርሳቸው በመመሳጠር ከ55 ሚሊየን ብር በላይ ያለ አግባብ በተፈፀመ የብረት ግዢ ውስጥ የተፈፀመ የሙስና ወንጀል መኖሩንም ገልጸዋል።

እንዲሁም የመድሃኒት ፈንድ ኤጀንሲም ከግዥ ስርዓቱ ውጭ የ79 ሚሊየን ብር ግዥ መፈጸሙን አቃቢ ሕጉ አንስተዋል።

 

በአመራሮች ላይ እየተካሄደው ባለው ማጣራት ካላቸው ገቢ በላይ ንብረቶችን አፍርተው እንደተገኙ መረጋገጡንም ነው የተናገሩት።

 

አቶ ብርሃኑ በመግለጫቸው ከፍተኛ የሽብር ጥቃት በሃገሪቱ ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ቁጥራቸው ያልተጠቀሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ጠቅሰዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከሌሎች ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሽብር የሚፈፅሙበትን ስልት በመቀየስና ቦታ በመለየት ላይ እንደነበሩ አውስተዋል።

ለሽብር ጥቃቱ በዝግጅት ላይ ነበሩ ያሏቸው ተጠርጣሪዎች ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባባር በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አመላክተዋል።

በእጃቸው በተያዙ ሰነዶች መሰረት የሽብር ጥቃቱን ቢፈፀሙ የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ ይችሉ እንደነበር ጠቅሰው፥ በተዘጋጁ እና በሂደት ላይ በሚገኙ አዋጆች ዙሪያ ለጋዜጠኞቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በሀገሪቱ ያለውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመከላከል የሚያስችል አዋጅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

አዋጁ በሃገር አቀፍ ደረጃ ሕጋዊ የጦር መሣሪያ አያያዝን ለማስተካከል የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተለይ በማዘዋወር፣ በመጫንና በተለያዩ መንገዶች በሚሳተፉ አካላት ላይ ከፍተኛ ቅጣትን የሚያስከትል መሆኑን በመጥቀስ።

በተመሳሳይ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃዎችን ሥርጭት ለመከላከል ታስቦ የተዘጋጀው አዋጅ ከሕገ መንግሥቱና ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች ጋር እንዳይጣረስ ሆኖ መዘጋጀቱንም ነው በንግግራቸው ያነሱት።

አቶ ብርሃኑ አዋጆቹ የፓለቲካ ምዳሩን ለማስፋት፣ የሰብዓዊ መብትን ለማረጋገጥ እና የስራ አድል ፈጠራን ለማሻሻል እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

 

የግዢ መመሪያ በመተላለፍ ግዢ የፈፀሙ 59 የመንግሥትና ግል ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

12 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ ሚያዚያ 4/2011 ( ኢዜአ) የግዢ መመሪያን ተላልፈው ግዢ ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 59 የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የአራት የመንግስት ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለሃብቶች ናቸው ተጠርጥረው የተያዙት።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በዋና ዋና ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህ ወቅት ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እንዳሉት፤ በመንግስት ተቋማት የተፈፀመ ከባድ የሙስና ወንጀል ላይ ላለፉት 3 ወራት ምርመራ ሲደረግ ቆይቷል።

በዚህም በተለይ የመንግስትን መመሪያ ሳይከተሉና ያለአግባብ ግዢ የፈፀሙ አራት የመንግስት ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ ይገኙበታል።

የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚና የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ፣ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ናቸው።

በተጨማሪም ሌሎች የተቋማቱ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ  በጥቅም የተሳሰሩ ግብረ አበሮችና ባለሃብቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው አቶ ብርሃኑ የተናገሩት።

የመንግስት ግዢ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን የ400 ሜትሪክ ቶን ስንዴ በአለም ዓቀፍ ጨረታ በጥቅም በመመሳጠር በመንግስት ኃብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ከፍተኛ ኃላፊዎቹ ከ94 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያቀረበ ድርጅት እያለ ያለአግባብ ለሌላ ድርጅት በመስጠታቸው ወደ 19 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያለአግባብ እንዲከፈል አድርገዋል ነው የተባለው።

ይህ በከፍተኛ ዋጋ ስንዴውን ያቀረበው ድርጅት በኢትዮጵያ መርከብ ድርጅት መጠቀም ሲገባው ባለመጠቀሙ ከመርከብ የሚገኘውን 4 ሚሊዮን ዶላር  ጨምሮ በአጠቃላይ ከ23 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ  ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውም ነው የተብራራው።

ለተለያዩ መስሪያ ቤቶች የኮምፒውተር ግዢ ሲፈፀም የቴክኒክ ግምገማ ያላለፈ የንግድ ድርጅት ህገወጥ በሆነ ትዕዛዝ እንዲያልፍ ተደርጎ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲያደርስና ኮምፒውተሩ በተቋማት ተሰራጭቶ በሚሰራበት ጊዜ ስራው ውጤታማ ሊሆን እንዳልቻለም ተነግሯል።

የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች በመመሳጠር የብረት ክምችትን ታሳቢ ሳያደርጉ ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ ያለአግባብ የግንባታ ብረት ግዢ እንዲፈፀም ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።

ለተቋሙ ከፍተኛ ክሊኒክ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችንና መድሃኒቶችን ለመግዛት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉም በህዝብና መንግስት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል።

የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲም የግዢ መመሪያን በመተላለፍ ከአንድ አቅራቢ በቀጥታ በድምሩ 79 ሚሊዮን ብር እና 479ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ ሕገ-ወጥና ከመመሪያ ውጪ የመድሃኒት ግዢ ፈፅሟል ነው የተባለው።

እንዲሁም በዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበ አቅራቢ ሊገዛ የሚገባውን የመድሃኒትና የህክምና መገልገያዎች የእቃ ግዥ መመሪያ ከሚፈቅደው ውጪ 92 ሚሊዮን ብር ግዢ እንዲፈፀም በማድረግ መንግስት ላይ ጉዳት መድረሱም ተነግሯል።

ግልፅ ጨረታ በማውጣት ግዢ መፈፀም እያለበት በውስን ጨረታ የ23 ሚሊዮን እንዲሁም ግልፅ ጨረታ መገዛት ሲገባቸው የ24 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒት ግዢ እንዲፈፀም መደረጉም ተብራርቷል።

የመድሃኒት መጋዘን ግንባታ አገልግሎት ተጨማሪ ማስፋፊያ በሚል ከዋናው ጨረታ ከእጥፍ በላይ በመክፈል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት እንደደረሰም ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ተናግረዋል።

በአራቱም ተቋማት በተደራጀ ቡድን በተሰራው ስራ በበቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ በተደረገው ምርመራ ከገቢ በላይ ኃብት አፍርተው የተገኙ እንዲሁም ቤታቸው ሲበረበር የተለያዩ የቤት ካርታዎችና የባንክ አካውንቶች እንደተገኘና መረጃው እየተጠናቀረ መሆኑንም አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

አብዛኛው መረጃ የተያዘ በመሆኑ የፍርድ ሂደቱ በፍጥነት እንደሚካሄድም ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ጠቁመዋል።

 

 

 

61 ሙሰኛ የተባሉ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በቁጥጥር ሥር ዋሉ! ዐቃቤ ሕጉ ዛሬ መግለጫ እንደሚሠጡ ታውቋል!

12 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የፌደራል ፖሊስ አንድ የመንግሥት ተቋም ዋና ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሙስና የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተዘገበ።

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር፣ የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት፣ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውስጥ የሚገኙ ስድሳ አንድ ሰዎች ናቸው በፖሊስ የተያዙት።

የፀረ ሙስና ዘመቻው አንድምታዎች

ከተያዙት ሰዎች መካከል እስካሁን ማንነታቸው የተጠቀሰው የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይገዙ ዳባ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በኅላፊነት የሚሰሩ ሌሎች 60 ሰዎች ናቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማስጠንቀቂያ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በመንግሥት ሃብት ምዝበራ፣ በሙስናና በኢኮኖሚያዊ ሻጥር ተጠርጥረው መሆኑንም የተለያዩ ምንጮች ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በጋራ በመሩት ዘመቻ ትናንት ሲሆን በተጠረጠሩበት ወንጀል ላይ አስፈላጊው መረጃ መሰብሰቡም ተጠቅሷል።

 

 

 

%d bloggers like this: