Tag Archives: Corruption

በሰላም ነው ምርጫው ሲቃረብ ታከለ ኡማ ሁሉን ነገር በሥራቸው ማጠቃለል መፈለጋቻው? ከራስ በላይ ነፋስ ማለታቸው ይሆን?

8 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

አያሌ ገንዘብ ላይ ኃላፌነት ያላችውን መ/ቤቶች

ም/ከንቲባው በቁጥጥራቸው ሥር ማድረጋቸው ድፍረት ነው!

 

በዘመናዊ አስተዳደር ጥበብም አፍራሽ ነው!

 

የራሱ የሆነ ከሕወሃት  ዘረፋም  ያገጠጠ  ዓላማ’ ሊኖረው ይችል ይሆን?

 

ይህ ሕዝብ አፍዝ አደንግዝ ተደርጎበታልን? የመጣው ሁሉ ሲዘርፈው ዝም ብሎ መጋጥ?

 

 

 

 

ይሀ ውሳኔ 

ከተ/ከንቲባው ባሻገር ሊሆን ሊገመት ይችላል!

 

ያልጠረጠረ ተመነጠረ አሉ፣ እትዬ ዘቢደሩ!

 

 

ዐቢይ አሕመድ ታከለ ዑማን ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ያሰየሙት ለመሬት ወረራ ነው መባሉ እውነት ኖሯልን?

6 Jan

The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ተንታኝ  ኤርሚያስ ለገሠ መረጃ አለኝ በማለት እንደነገረን፣ ዶር ብርሃኑ ነጋ 

በእውነት የከተማዋ መሬት አስዘራፊ ነበርን?

ማነው ቁንጮ ተጠቃሚው? ምን በምን ይገመታል—እንዴትስ  ይለካል?

የዐቢይና የብርሃኑስ ትርፍ ፖለቲካ ወይንስ ገንዘብ?

 

 

 

 

ዐቢይ አሕመድ የጽንፈኛ ኦሮሞችን የአዲስ አበባ አጀንዳ ለማስፈጸም

ነው የመጣው ማለት ነውን?

ከሆነስ ‘ገዥዎቹ’ ለምን ከዐቢይ ይልቅ ጃዋርን መረጡ? ፖለቲካ?

 

ዐቢይም ጃዋር ለኢትዮጵያውያን ነፍስ መጥፋት በወንጀል ተጠያቂ ሆኖ ሳለ፥ ዜግነቱንም ለመረከብ አምስት ዓመት መጠበቅ ካላበት ለምንድነው ከሕጉ ውጭ የኢትዮጵያን ፓስፖርት እንደገና እንዲያገኝ የተፈቀደለት?

ተልዕኮው ተጠናቀቀ?

 

የሥልጣን ብልግና እንዴት የኦሮሞ ፓለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ይሆናል?

ብዙ ነፍስ ሠቃይ ችግሮች እንዳላጣን፣ ለምን አሁን ይህ?

 

በሽቀላው መሃል፣

 

ኢትዮጵያ! እስከ ዛሬ የተማመንሽባቸው እግዚአብሔርና ብርቱ ልጆችሽ

ብቻ  ክንድ ይሁኑሽ!

 

 

 

Passport slowdown in Ethiopia means more corruption!

30 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

The long wait for renewing passports has opened room for brokers, dealers and government employees to take bribes in order to speed up the process of getting a passport.

People are being asked to pay up to 50,000 birr as a bribe for a new passport. Normally a passport costs 600 birr.

Ethiopian Passport (Credit: Capital)

According to Capital sources, the case is more serious for individuals who want to renew their passport for business. They will be asked for up to 100,000 birr by the dealers who have contact with the agency employees and will get their passport renewed within five days.

Wendowessen (his name is changed for privacy) is a business man who has license in the import and export business and frequently travels to China and Dubai, Waiting for more than five months puts him out of the game, so he chooses to go beyond the curtain to get his passport renewed.

“The agency has no alternate procedures for business people who are engaged in import and export which encourages people to break the law,” said a Capital source.

Under normal circumstance, it takes two months to get a new passport through normal procedures, which costs 600 Birr for 32 pages and 900 Birr for a 64-page passport. However, applicants can get their passport expedited to between three and five days after paying 2,186 birr.

For individuals who need to go abroad for medical purposes, they should get a document from the medical board to get the service.

Though there is less magnitude, the long waits are also observed in Adama, Semera, Dire Dawa, Jigjiga, Hawassa, Jimma, Dessie, Bahir Dar and Mekelle,

“The agency is trying to alleviate the existing problems still we are importing passports and the shortage of hard currency complicates the problem,” said Desalegn Teressa, Communication Director.

On average, the Agency spends USD five million to print passports every year. The Agency, was issuing an average of 2,000 passports daily. Previously, any individual with a kebele identification card and birth certificate can obtain a passport from the agency, as long as they present documents from the government institution as a letter of recommendation, Individuals with medical case, for individuals who have active visa, and for individuals who engage in import-export trade. It will not take more than a week.

 

/Capital

የመከላከያና ደኅንነት ተቋማትን የማያካትት የአስፈጻሚ አካላት መቆጣጠሪያ አዋጅ ቅሬታ አስነሳ!

11 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች አስተዳደርን ጨምሮ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የአሠራር ሥነ ሥርዓት በሚመለከት፣ በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የቀረበው ረቂቅ የመከላከያ፣ የደኅንነትና የፖሊስ ተቋማትን አይመለከትም መባሉ ቅሬታ አስነሳ፡፡

ረቂቂ አዋጁ በዋናነት የሚመለከተው ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮችና የፌዴራል አስተዳደር ተቋማትን ሲሆን፣ ተቋማቱ በሕግ የተሰጣቸውን አስተዳደራዊ ውሳኔ የመስጠትና መመርያ የማውጣት ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ሲያውሉ በሕግ መመራታቸውን፣ ከተፈቀደላቸው የሥልጣን ክልል አለማለፋቸውን፣ እንዲሁም የዜጎችን የተሳትፎና የመደመጥ መብት ማክበራቸውን ማረጋገጥና ዕርማት የሚደረግበት ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑ በስፋት ተገልጿል፡፡

የረቂቅ አዋጁ መቅረብ በአገሪቱ እየታየ ያለውን የመንግሥት ተቋማትን ብልሹ አሠራር በተወሰነ ደረጃ የሚያሻሽልና ተገልጋይ ዜጎችም በአስፈጻሚ ተቋማትና አመራሮች ላይ እስከምን ድረስ መብት እንዳላቸው ግንዛቤ የሚሰጥ ቢሆንም፣ በዋናነት ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገባው የፖሊስ፣ የመከላከያና የደኅንነት ተቋማት ግን ከአዋጁ ውጪ መደረጋቸው ወይም ‹‹እነሱን አይመለከትም›› መባሉ ተገቢ እንዳልሆነ፣ ስለረቂቅ አዋጁ በተደረገ ውይይት ላይ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡

ሦስቱንም ተቋማት ከሕግ በላይ በማድረግ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ሆነው መኖራቸውን የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የሕግ የበላይነት በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለ መሣሪያ መሆኑን፣ አዋጁም እነዚህን ተቋማት አደብ የሚያስገዛ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የአስተዳደር ተቋማት ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም ከሚያደርሱት በደል ዜጎችን መጠበቅና በደል ሲደርስባቸውም መፍትሔ የሚያገኙበት ሥርዓት መዘርጋት ስለሚያስፈልግ፣ ሦስቱም ተቋማት በዚህ ሥርዓት ውስጥ መካተትና አዋጁ እነሱንም የሚያቅፍ መሆን እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡የፌዴራል የአስተዳደር ተቋሞች የአሠራር ሥነ ሥርዓትን አዋጅ አስፈላጊነት ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና የመመርያ አወጣጥ መርሆዎችንና ሥነ ሥርዓት፣ እንዲሁም በአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመርያዎች ቅር የተሰኘ ሰው የውሳኔዎቹንና የመመርያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ፣ የግልጽነትና ተጠያቂነት ባህል በማዳበር አስተዳደራዊ ፍትሕን ማስፈጸም ስለሚያስፈልግ ሦስቱም ተቋማት በዋናነት በአዋጁ መካተት እንዳለባቸውና ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለበርካታ ዓመታት በረቂቅ ደረጃ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሳይደረግ የቆየው የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመለከተውና ለመጀመርያ ጊዜ በጌትፋም ሆቴል ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለውይይት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ በአራት ንዑስ ክፍሎች፣ 57 አንቀጾችና 67 ንዑስ አንቀጾችን የያዘ ነው፡፡

ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በተገቢው ጊዜ መመርያ ማውጣት እንዳለበት ግዴታ የሚጥለው አዋጁ፣ መመርያ ባያወጣ እንኳን መብቱ ወይም ጥቅሙ የተነካበት ማንኛውም ሰው ተቋሙ ውሳኔ እንዲሰጠው የመጠየቅን መብት ያጎናፅፋል፡፡ ተቋሙ ተገቢውን መመርያ ሳያወጣ ቢቀር እንኳን፣ ማንኛውም ሰው ተገቢውን መመርያ እንዲያወጣ በጽሑፍ ማቅረብ እንደሚችልና የተቋሙ አመራር በ30 የሥራ ቀናት ውስጥ መመርያውን የማውጣት ሒደት መጀመር እንዳለበት፣ ወይም በጽሑፍ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠት እንዳለበትም ያስረዳል፡፡

የአስተዳደር ተቋማቱ መመርያ ከማውጣታቸው በፊት ስለሚያወጡት መመርያ ረቂቁን በጋዜጣ፣ በተቋሙ ድረ ገጽና በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ዝርዝር መረጃዎችን ማውጣት እንዳለበትም ረቂቅ አዋጁ ያስረዳል፡፡

የተቋማቱ አስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ በጽሑፍ ሆኖ እንደ ሁኔታው በአካል፣ በተመዘገበ ፖስታ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴዎች ሊቀርብ እንደሚችልና ለቀረበው ጥያቄ ወዲያውኑ ውሳኔ የማይሰጥ ከሆነ ለጥያቄ አቅራቢው ደረሰኝ መስጠት፣ ጥያቄው በተገቢው ጊዜ እንዲመዘገብና ለውሳኔ እንዲቀርብ ማድረግና ጉዳዩ የሚታይበትን ቀነ ቀጠሮ ለባለጉዳዩ የማሳወቅ ግዴታ ይጥላል፡፡ ውሳኔ የሚሰጠው የተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም ሥልጣን የተሰጠው የተቋሙ የሥራ ኃላፊ ብቻ መሆን እንዳለበትም ይደነግጋል፡፡ ውሳኔ የሚሰጠው ኃላፊ ተገልጋዮች ያቀረቡትን ፍሬ ነገርና ማስረጃ መመርመር፣ እንደ ሁኔታው የሦስተኛ ወገን አስተያየት ማዳመጥ እንዳለበትም ግዴታ ይጥላል፡፡

ቅሬታ አቅራቢው ውሳኔ ከሚሰጠው ኃላፊ ጋር በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ካለው ወይም በማንኛውም ሁኔታ ግጭት የሚያስከትልበት ከሆነ ጉዳዩን ማየት እንደሌለበት፣ በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት መጠን፣  በትውልድ ሁኔታ፣ ወይም በሌላ ምክንያት ልዩነት ሳያደርግ ማስተናገድ እንዳለበትም አዋጁ ያስጠነቅቃል፡፡በፌዴራል ተቋማት ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተገልጋይ ለአስተዳደር ተቋሙ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችል፣ ተቋሙም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ማቋቋምና ለተገልጋዩም ይፋ ማድረግ እንዳለበት፣ የቀረበው ቅሬታ ተመርምሮ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ እንዳይፈጸምም እንደሚደረግ ረቂቂ አዋጁ ያብራራል፡፡ የአስተዳደር ተቋሙ ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑን የተረዳ ሰው፣ ውሳኔው በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችልና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመጨረሻ እንደሚሆንም ደንግጓል፡፡ የክለሳ አቤቱታው መመርያውን በሚመለከት ከሆነ መመርያው ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ መሆኑን፣ የአስተዳደር ውሳኔን ለማስከለስ ከሆነ ደግሞ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበትም አዋጁ ያስረዳል፡፡ ፍርድ ቤቱም ውሳኔው ሊመረመር ይገባዋል ብሎ ሲያምን ቅሬታ የቀረበበት ተቋም በ15 ቀናት ውስጥ የጽሑፍ መልስ እንዲሰጥ ማዘዝ እንዳለበት ይገልጻል፡፡

የአስተዳደር ተቋማቱ በሚያወጡት መመርያ ወይም በሚሰጡት ውሳኔ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ተገልጋይ፣ የአስተዳደር ተቋሙን (የመንግሥት አስፈጻሚ ተቋማትን) አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ካሳ እንዲከፍል መጠየቅ እንደሚችልም ረቂቅ አዋጁ ለተገልጋይ ሕጋዊ መብት ሰጥቷል፡፡

/ሪፖርተር

 

 

ወታደራዊ አመጽ ኢትዮጵያን ያሠጋል!— የተመስገን ደሣለኝ ዕይታ!

7 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

Suspects of Corruption Probe, Alleged Human Rights Abuse Appear Before a Judge as Late as 9pm

12 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

A Court has denied 64 suspects the right to bail when federal police brought them before a federal judge at the 10th Criminal Bench of Lideta Division, as late as 9:00pm today.

Among the suspects are 28 employees of the state owned military-industrial complex, Metal & Engineering Corporation (MetEC), including its deputy CEO, Tena Kurunde (B. Gen).

The remaining are from the Federal Police, national security and intelligence agency and prison administration. All but two of the suspects have appeared before the court, after they were arrested late last week. One of the suspects, Mulu Woldegebriel (Col.), was arrested near Awash town, according to police. The two suspects – Chernet Adane and Gebremedhin Gebresellasie (Let. Gen) – remain at large, says police.

Adanech Tessema, a spouse of Yared Zerihun, former deputy head of national intelligence, is among the suspects brought before the judge, accused of an attempt in helping her husband flee, according to police statement to the court.Many of the suspects wore sport suits and appeared tired. They were made to wait outside the court room for two hours until the Judge presides over the case began the session. A suspect working for MetEC was seen crying while another suspect serving the Federal Police Commission brought along an infant.

Suspects told the Judge that they were arrested without a court warrant after called on for a meeting.

Federal investigators who alleged misuse of office, conducting procurement without following the rules and causing damage to public interest, were granted by the court the right of custody for 14 days, the time they have appealed for.

The alleged misuse and embezzlement were conducted with state mega projects such as the GERD, Yayu Fertiliser Project and a procurement of a vessel from the state owned shipping company, according to police sources.

Nonetheless, heads of the two agencies where many of the suspects have been working for were not included among the suspects brought before court today.

 

/Addis Fortune

ተዛማጅ:

ሕወሃት መቀሌ የከተሙትን በወንጀል ተጠርጣሪዎች ለሕግ እንዲሰጡ ተጠይቀው መልሳቸው እምቢታ ሆኖአል

 

 

 

 

MetEC undergoes two-way split: commercial and defence entities

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Prime Minister orders  MetEC to be divided into separate commercial and defence entities

The Metals & Engineering Corporation (MetEC), the state-owned, military-industrial conglomerate, is splitting into two parts – commercial and defence – following an order by Prime Minister Abiy Ahmed (PhD).

To facilitate the split, eight separate committees incorporating members of the Corporation, the National Defense Forces and the Ministry of Defense have been formed. A lead committee chaired by Minister of Defense Motuma Meqassa that includes Berhanu Jula (Gen.), operations chief of the Ethiopian National Defense Force, and Molla Hailemariam (Lt. Gen), chief of the Army Logistics Department, has also been formed.

Though the idea of splitting the corporation into two entities was floated in the air for the past couple of months, the final decision was made by the Prime Minister three weeks ago, according to sources close to the case. The Prime Minister has also directed that the split and handover of the companies be completed in September, sources disclosed to Fortune.

Once the split is concluded, a defence industry section will be established under the Ministry of Defense with the mandate to administer the new company involved in the manufacture ofdefence-related machinery and equipment only, according to the same source.

The defence wing of MetEC now produces armoured vehicles, personnel carriers, assault vehicles, ambulances and command and surveillance vehicles. It also manufactures ammunition ranging from 7.62mm bullets to 130mm artillery shells, as well as defence and security vehicles and military utility aircraft. The commercial wing manufactures tractors, trucks, buses, television sets, energy meters, turbines, construction machinery and engines among many other products.

The late Prime Minister, Meles Zenawi, put forward the establishment of MetEC as one of the major tools for industrialisation with the aim of transforming Ethiopia into a middle-income country. When MetEC was established eight years ago, it registered 10 billion Br in capital and incorporated 15 military and civilian companies. The company was given seven main mandates: building the technological capabilities of the country’s defence forces; the design, building and commissioning of manufacturing industries; the manufacturing of industrial machinery; the enhancement of engineering and technological capabilities; the manufacturing, maintaining, overhauling and upgrading of weapons, equipment and parts of the military; and the sales of its weaponry products.

However, MetEC has often been criticised by members of parliament and the public for delaying the nation’s mega-projects, including the 10 sugar plants that were expected to be completed six years ago but have not yet been delivered. MetEC is also blamed for the delay of Yayu, a Multi-Complex Industries Project, and recently for the delay in the construction of the Great Ethiopian Renaissance Dam.

“Though the corporation was established with a positive objective of changing the country, the approach has many problems,” said Prime Minister Abiy on August 25, 2018, during his meeting with members of the media.

He also stated that the country was supposed to complete the four-billion-dollar dam within five years, yet seven or eight years later the country cannot make a single turbine operational.

“Salini Impregilo, the prime contractor of the dam, has demanded compensation for the delays caused by others,” he said. “Studies we made show that if we cannot oust MetEC from the project, it will take even longer.”

“According to the law, when a company is hired to fulfill a contract but fails to deliver a project, or lacks the capacity to perform on a contract, it can be terminated. This is what happened in this case,” said Abiy, referring to MetEC’s contract on the dam project.

During the press conference, the Prime Minister also disclosed that three sugar projects contracted to MetEC were also terminated, and the government is in the process of selecting other companies with experience to complete the projects.

Five months ago, the founding CEO of MetEC, Kinfe Dagnew (Maj. Gen.) tendered his resignation from the office and was replaced by Bekele Bulado (PhD), former minister of Trade. MetEC has over 19,500 employees, both members of the military and civilians, working at 98 subsidiary companies.

At the beginning of last week, MetEC terminated the contracts of nearly 1,000 employees following the termination of its sugar factory contracts. Ethiopia Power Engineering Industry, one of the subsidiaries of MetEC that employs 3,000 people, discharged most of its employees on a one-month forced-leave to cut administrative costs, according to sources close to the case.

According to an expert with intimate knowledge of MetEC, the split may take more time than the time allotted due to the intertwined nature of the commercial and military operations of the company.

“For instance, Bishoftu Automotive Industries manufactures both commercial and military vehicles,” said the expert. “It will be difficult to split this company,” he concluded.

/Addis Fortune

 

Related:

ከዚህ በፊት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)”ይገነባቸው በነበሩ” የስኳር ፕሮጀክቶች ውስጥ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች እንደሚቀነሱ ተገለጸ!

በረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሙስና መፈጸሙንና የዶር ደብረጽዮን እጅ እንዳለበትም የውስጥ ምንጮች አጋለጡ!

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(ኢሳት ዜና) ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም  ከ120 ሚሊዮን ዶላር ወይም አሁን ባለው ምንዛሬ ከ3 ቢሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ተመድቦለት የተሠራው የአዲስ አበባ ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከውል ስምምነት ጀምሮ ሙስና የተፈጸመበት እንደሆነና ለዚህም ዋናው ተጠያቂ በወቅቱ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ቦርድ ዳይሬክተር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል።

በዶ/ር ደብረጺዮን ትዕዛዝ ሥራው ከ5 አመት በፊት ፕሮጀክቱ ኬምብሪጅ እንዱስትሪስ ሊሚትድ ለተባለ ኩባንያ ያለግልጽ ጫረታ መሰጠቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ መብራት ሃይል ያለ ጨረታ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለውጭ ኩባንያዎች የሚሰጠው ኩባንያዎቹ የውጭ አገር ገንዘብ ይዘው መመጣታቸው ሲረጋገጥ ቢሆንም፣ ኬምብሪጅ ኡንድስትሪስ ኩባንያ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሚሸፈን ወጪ ያለጨረታ ስራውን እንዲሰራ የተሰጠው በመሆኑ የተለዬ ያደርገዋል።

ኬምብሪጅ ኩባንያ የውጭ አገር ኩባንያ አለመሆኑን የሚገልጹት ምንጮች፣ ኩባንያው በብሪቲሽ ቨርጂን አይላንድስ እንደተመዘገበ በውል ስምምነቱ ላይ ሰፍሮ የሚገኝ ቢሆንም፣ የኩባንያው የአክሲዮን ባለቤቶች የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

ብሪቲሽ ቨርጂንያ አይላንድስ የተለያዩ ኩባንያዎች ባለቤቶች ታክስ እንዳይከፍሉ ሃብታቸውን ህገወጥ በሆነ ሁኔታ የሚደብቁበት ቦታ መሆኑን ፋይናንሻል ታይምስ ካፒታል ኢኮኖሚክስን ጠቅሶ ዘግቧል። ኢሳት ኬምብሪጅ ኢንዱስትሪስ ኩባንያ በውል ስምምነቱ ላይ በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት በጎግል ፍለጋ ቢያደርግም፣ ስለኩባንያው የሚገልጽ ምንም ነገር ማግኘት አልቻለም። ኬምብሪጅ ከረጲ ጋር በተያያዘ ከከፈተው ዌብሳይት በስተቀር ፣ ስለድርጅቱ የሁዋላ ታሪክም ሆነ በአለማቀፍ ደረጃ ስለሰራቸው ስራዎች የሚያመለክት ምንም መረጃ የለም።

የኩባንያው ዋና ዳይሬክተር ተብለው የተጠቀሱትን ሮበርትስ ብሩክን ማንነት ለማወቅ በጎግል ፍለጋ ብናካሂድም ግለሰቡ፣ ከፋይናስ ጋር በተያያዘ ስራ እንደሚሰሩ ከመገለጹ ውጭ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ስለሳቸው የወጣ አንድ መለስተኛ መረጃ እንደሚያሳየው ግለሰቡ ማኔጅንግ ዳይሬክተር እንዳልሆኑ፣ ከኬምብሪጅ ኡንዲስትሪያል ግሩፕ ጋር አጋር ማኔጀር ( ማኔጂንግ ፓርትነር ) መሆናቸውን ብቻ ተጠቅሷል።

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ምንጮች እንደሚሉት ኬምብሪጅ ኢንዱስትሪስ የተባለው ድርጅት በሃይል ማመንጨት ስራ ምንም ልምድ የሌለው መሆኑን በማወቅ የቀድሞው የመብራት ሃይል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምህረት ደበበ ኮንትራቱን ለማቋረጥ ሙከራ አድርገው እንደነበር፣ ይሁን እንጅ ዶ/ር ደብረጺዮን “ የኩባንያውን ማንነት ለማወቅ ለምን ትፈልጋለህ፣ ምን አገባህ” ብለው እንደጮሁበት፣ አቶ ምህረት ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድም ፊቱ ላይ እንደወረወሩበትና አቶ ምህረትም ተገደው ኮንትራቱን እንዲፈርሙ ተደርገዋል።

ኬምብሪጅ የመብራት ሃይል ጋር እንደተፈራረመ ወዲያውኑ ስራውን ሲ ኤን ኢ ኢ ሲ ለተባለ የቻይና ኩባንያ በመለስተኛ ተቋራጭነት ሰጥቶ ማሰራቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ ኬምብሪጅ ምንም ስራ ሳይሰራ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን ጽ/ቤት ሳይከፍት ገንዘብ መውሰዱን ይገልጻሉ።

ኩባንያው በስምምነቱ መሰረት 50 ሜጋ ዋት ሃይል እንደሚያመነጭ ቢጠበቅም፣ ውሉን በመተው 25 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ዲዛይኑን መቀየሩን፣ ዶ/ር ደብረጺዮንም የመብራት ሃይል ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩትን ወ/ሮ አዜብ አስናቀን አስገድደው አዲሱን ዲዛይን እንዲቀበሉና ክፍያ እንዲፈጽሙ ማደረጋቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

ኬምብሪጅ በኮንትራት ስምምነቱ መሰረት ማሟላት ያለበትን ነገር ሳያሟላ ፕሮጀክቱን ለማስረከብ ፍላጎት ያለው ቢሆንም፣ የመብራት ሃይል ሰራተኞች ፕሮጀክቱን ለመረከብ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር። ወ/ሮ አዜብና የፕሮግራም ዳይሬክተሩ አቶ ፍሰሃ ገብረመስቀል፣ የሰራተኛውን ውትወታ ባለመስማት ፣ ስራው ሳይጠናቀቅ የምረቃ ዝግጅት እንዲዘጋጅ ያደረጉ ሲሆን ፣ እነዚህ ሰዎች የአመራርና የጥገና ሥራውን ለኬምብሪጅ ኩብንያ እንዲሰጥ ሲያሳስቡ ቆይተዋለ።

ዶ/ር አብይ በጉዳዩ ላይ በፍጥነት ገብተው የተፈጸመውን ሙስና እንዲጣራ ትዕዛዝ እንዲሰጡ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት ሰዎች አሳስበዋል።
ፕሮጀክቱ በቅርቡ በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ተመርቆ መከፈቱ ይታወቃል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመብራት ሃይል ባለስልጣናትን፣ የኬምብሪጅ ሃላፊዎችን፣ አቶ ምህረት ደበበንና ዶ/ር ደብረጺዮንን ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በጉዳዩ ዙሪያ ስማቸው የተጠቀሱት ግለሰቦች መልስ የሚሰጡን ከሆነ በሚቀጥለው ዘገባ ይዘን እንቀርባለን።

 

 

%d bloggers like this: