Tag Archives: Crime & punishment

“አቅጣጫ የጠፋበት የኢሕአዴግ አቅጣጫ!”

17 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

“ባለፈው አንድ ዓመት በአጠቃላይ በጸጥታው ዘርፍ ጠንካራ ስራዎች ቢከናወኑም በርካታ ተግዳሮቶች እያጋጠሙ መሆናቸው ኮሚቴው ገምግሟል፡፡”

 

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደነንት ስኬታማ ሥራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

ኮሚቴው የሃገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ገምግሟል፡፡

ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በጸጥታና ደህንነት ተቋማት የሪፎርም ስራዎች መካሄድ መጀመራቸው፤ የደህንነት ተቋም አመራሮች ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዱ እንዲሆኑ የሚያስችል የአመራር ለውጥ መደረጉን በጠንካራ ጎን የገመገመው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመከላከያ ሰራዊት ባለፈው አንድ ዓመት ጠንካራ ሪፎርም ካደረጉ ግንባር ቀደም ተቋማት አንዱ እንደሆነና ከአደረጃጀቱ ጀምሮ አጠቃላይ የመከላከያ መዋቅሩን ለማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውንም አይቷል፡፡

ባለፈው አንድ ዓመት በአጠቃላይ በጸጥታው ዘርፍ ጠንካራ ስራዎች ቢከናወኑም በርካታ ተግዳሮቶች እያጋጠሙ መሆናቸው ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

ተግዳሮቶቹ በዋናነት ከጽንፈኛ ብሔርተኝነት፣ ከኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወይም ደቦዎች፤ ከህገ-ወጥ የጦር መሳርያ ዝውውር እንዲሁም ከማህበራዊ ሚድያ ሀሰተኛ ዜናዎች ተጽዕኖ ጋር የተያያዙ መሆናቸውንም ተመልክቷል፡፡

እነዚህ ተግዳሮቶች ለዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና የደህነንት ስጋት ምክንያት መሆናቸውንም አስምሮበታል፡፡

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ በጥልቀት ከተወያየ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

በዚህም ብሔራዊ ደህንነትን ማረጋገጥንና የህግ የበላይነትን ማስከበር የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸን አፅንኦት በመስጠት የዜጎችን የሰላም ዋስትና የሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ መረባረብ እንደሚገባ ውሳኔ አሳልፏል።

ለደህንነት ተግዳሮቶች መነሻ ወይም ችግሩን በአጭር ጊዜ እንዳይቀረፍ ከማድረግ አንጻር ዋነኛው ችግር ያለው ከፖለቲካ ስራ ጋር የተተያያዘ እንደሆነ በመለየት የደህንነትራው ከፖለቲካ ሥራው ጋር ጎን ለጎን ተያይዞ እንዲሠራና በአንዱ የጎደለው በሌላው እየተሞላ አስተማማኝ ሰላም በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እንዲከናወን አቅጣጫ አስቀምጧል።

ከአንዳንድ የአስተዳደር ወሰኖች ጋር በተያያዘ ሲስተዋሉ የነበሩ የጸጥታ ስጋቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻሎች ያሳዩ ቢሆንም፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ክልሎች ከክልሎችና ክልሎች ከፌደራል መንግት ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት እንዲሁም የክልል የጸጥታ ሃይሎች ቅኝትና አወቃቀር በሚመለከት የሚስተዋሉ ችግሮች በህገ መንግስቱ መሰረት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው ለማድረግ የሚያስችል ስራ እንዲሰራ ኮሚቴው ወስኗል።

የጸጥታ ኃይሎች ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ባረጋገጠ መልኩ የዜጎች በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ እንዲሁም ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ለማስከበር በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የየአካባቢያቸውን ሰላም ለማስከበር እንዲሰሩ ያሳሰበው ኮሚቴው ሰላም ወዳዱ ህዝብ እንደወትሮው ሁሉ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ በንቃት እንዲረባረብ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ፍላጎትን በኃይል ለማስፈጸም የሚደረጉ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ሁለንተናዊ ርብርብ እንደሚያስፈልግም አስምሮበታል፡፡

ኮሚቴው የደህንነት ስጋት ምንጮችን በዝርዝር በመለየት ተግዳሮቶቹን በአጭር ጊዜ በመፍታት የተሟላ ሰላም ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ዝርዝር ተግባራት ላይ ተወያይቶ የአፈጻጸም አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን ማጠናቀቁን የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

 

 

 

 

ወንጀል የፈጸሙ በሕግ ይጠየቁ፣ ጉዳተኞች ካሣ እንዲያገኙና አፋኝ ሕጎች እንዲነሱ የሕግ ባለሙያዎች አሳሰቡ

3 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(ኢሳት ዜና ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመታት ሕግን ተገን በማድረግ ለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ፤ ወንጀሎቹ በገለልተኛ አካል ተጣርተው ለ ሕግ መጠየቅ አለባቸው። ጉዳተኞቹ ለደረሰባቸው ጉዳቶች ተገቢውን የሞራል ካሣ ሊያገኙ እንደሚገባና የሕግ ተቋማት ዳግም በባልሙያና በገለልተኛ አካል ሊዋቅቀሩ ይገባል ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ።

የሕግ ጠበቃና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ እንዳሉት ‘’አፋኝ የሆነው የጸረ ሽብር ህጉና የወንጀለኛ አንቀጽሕጎች መሻር አለባቸው። ይህን ያስፈጸሙ ግለሰቦች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል። በፌደራል ፖሊስ ውስጥ የጸረ ሽብር ግብረኃይል መፍረስ አለበት። ከሕግ ውጪ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ህክምናን ጨምሮ የሞራል ካሣ ሊከፈላቸው ይገባል። በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል የተፈጸሙት ወንጀልለኞች ጉዳይ በገለልተኛ ዓለም አቀፍ አካል ተጣርቶ በህግ መጠየቅ አለባቸው። በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤትም ሊቆሙ ይገባቸዋል። አንድ ሽብርተኛ መንግስት ይቅርታ ጠይቆ አገር ሊያስተዳድር አይችልም። ስልጣኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማስረከብ አለባቸው።’’ ብለዋል።

_____________________________________________________________________________________________________________________________________

__________________________________________________________________________________________________________________________

በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴን በመጠቀም በውጭ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገራቸው መመለሳቸው መልካም ጅምር መሆኑን የሕግ ባለሙያው አስምረውበታል። ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የራሳቸውን ሥርዓት መዘርጋት ይገባቸዋልም ብለዋል። ‘’አሁን ያለው አስተዳደር የሞግዚት አስተዳደር ሊያበቃ ይገባዋል። አገዛዙ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ማስረከብ አለባቸው። ኢሕአዴግ ማለት የቅኝ ግዛት ሥርዓት ማለት ነው።ሕወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር የዘረጋው ስርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን ገለልተኛ ተቋማትና መንግስት ሊያቋቁም ይገባል።’’ ሲሉ አቶ ተማም አባቡልጉ አስተያየታቸውን ደምድመዋል።

የሕግ ባለሙያ የሆኑት ጠበቃ አምሃ መኮንን በበኩላቸው እንዳሉት ‘’ብዙ መስዋእትነት ተከፍሎ አሁን ላለንበት ለውጥ ደርሰናል። አሁን የተጀመረው የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የለውጥ እንቅሳሴ መልካም ጅምር ነው። ጅምሩ ውጤታማ እንዲሆን በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ሊታገዙ ይገባቸዋል። ለውጡ ሊቀለበስ በማይችል ደረጃ ተጀምሯል። ከዚህ በኋላ ሁላችንም ዳር ቆመን መመልከትና ጉድለቶችን ብቻ እያጎላን ከመቀመጥ ቀረብ ብለን ለውጡን እየመራ ያለውን ኃይል ማገዝ አለብን። ብዙ የሚቀሩ ነገሮች አሉ። በተጀመረው ለውጥ ግን ደስተኛ ነኝ።’’ ብለዋ።

በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጸሙ ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠበቃ አምሃ ሲመልሱ ‘’ዳግመኛ እንደዚህ ዓይነት ወንጀሎች እንዳይደገሙ በማስረጃ ተደግፎ አጣሪ ኮሚሽን በገለልተኛነት ሥራውን እንዲሰራ መፍቀድ ያስፈልጋል። ተጨባጭ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል። ተቋማቱ በባለሙያ ሊመሩ ይገባል። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም አቤቱታ በቀላሉ የሚቀርቡባቸው ተቋማት ሊኖሩ ይገባል።

ፍርድ ቤቶች ሚናቸው በጣም ወሳኝ ስለሆነ እንደገና ሊታዩ ይገባቸዋል። አሁን ባላቸው አደረጃጀት ይህንን ሚና ሊወጡ ይችላሉ ብዬ በኔ በኩል ብዙም እምነት የለኝም።” ሲሉ አቶ አምሃ መኮንን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

%d bloggers like this: