Tag Archives: displacements

በምዕራብ ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር መፈታቱን በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ አስታወቁ

17 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ዋና አዛዡ ሜጀር ጀኔራል አስራት ደኔሮ (ኢዜአ)

አሶሳ ታህሳስ 7/2011 (ኢዜአ) በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ሲያጋጥም የነበረው የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴ መስተጓጎል ችግር መፈታቱን በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ አስታወቁ።

ዋና አዛዡ ሜጀር ጀኔራል አሥራት ደኔሮ ለኢዜአ እንደገለጹት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች የታጠቁ ኃይሎች የፈጠሩት የጸጥታ ችግር በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ከአሶሳ አዲስ አበባ፣ ከነቀምት አዲስ አበባ፣ ከነቀምት አሶሳ እና ከነቀምት ቡሬ መስመር የንግድና የትራንስፖርት መስተጓጎል ሲያጋጥም መቆየቱን ተናግረዋል።

“ችግሩን ያስከተሉት የታጠቁ ሃይሎች ከሃገር መከላከያ ሠራዊት አቅም በላይ ሆነው አይደለም” ያሉት አዛዡ የብሄራዊ ጸጥታና ደህንነት ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ሰሞኑን የምዕራብ እዝ ሃይል አካባቢውን መቆጣጠሩን አስረድተዋል።

ሠራዊቱ ከሁለቱ ክልሎች ጋር በመተባበር ባካሔደው የተጠናከረ ፍተሻ አካባቢው መረጋጋቱን ገልጸው በአማራ ክልል ከቅማንት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የተከሰተው የጸጥታ ችግርም ካለፉት ሁለት ሣምንታት ወዲህ ወደ ሰላም መመለሱን ተናግረዋል።

ለተገኘው ውጤት የህብረተሰቡ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰው ሠራዊቱ እስከ ህይወት መሥዋዕትነት እንደከፈለም አዛዡ ጠቁመዋል፡፡

የግጭቶቹ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት መደገፍ የሰራዊቱ ትኩረት መሆኑን ጠቁመው ከየአካባቢው አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስና የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም ሃገሪቱ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት ድንበር በኩል የሚከሰተውን ህገ-ወጥ የሰዎች እና የጦር መሣሪያ ዝውውር በትኩረት እየተከታተለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

 

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ግጭት የማያባራው ለምን ይሆን? ግጭቱን የሚያነሳሱትና የሚያባብሱትን ለምን መንግሥት ተጠያቂ አይደርግም?

22 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

“በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የብሔር ግጭት እንዲቀሰቀስና የበርካቶች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋ ያደረጉ ሥርዓቱ ውስጥ ያሉ ጥገኞችን በተመለከተ መፍትሔ ካልተሰጠ በስተቀር፣ ግጭቱን ማቆም እንደማይቻልም [ኃይለማርያም ደሣለኝ] ጠቁመዋል። ‹‹መፍትሔው ፖለቲካዊ ነው። ጥገኞቹን በመድፈቅ መፍትሔ ካልተሰጠ በስተቀር መቼም ቢሆን ግጭቱን ለማስቆም አይቻልም››።

“…በአካባቢው በሚስተዋለው ግጭት ከፍተኛ የዶላር አዘዋዋሪዎችና የኮንትሮባንድ ንግድ አደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት አካላት ስለመኖራቸው የመንግሥት አመራሮች ድምዳሜ ላይ ቢደርሱም፣ ይኼንን ሕገወጥ እንቅስቃሴ ማፍረስ አልተቻለም…”

“ከጥቂት ወራት በፊት ፓርላማ የተገኙት የገቢዎችና የጉምሩክ ባለሥልጣን አመራሮች በዚህ የኮንትሮባንድና የዶላር ዝውውር የሚሳተፉ እነማን እንደሆኑ በመለየት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚመለከታቸው አመራሮች ሪፖርት ማድረጋቸውንና ዕርምጃ የመውሰድ ውሳኔ የከፍተኛ አመራሩ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡ የተዋናዮቹን ማንነት እንዲገልጹ በፓርላማው ቢጠየቁም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር ቀውስ ውስጥ ብትገባም ከአገር ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ ግን እንደቀጠለ መሆኑን መረጃዎች ያሳዩ ነበር፡፡ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በአንድ ቀን በተደረገ ዘመቻ ብቻ 591,453 ዶላር አዋሽ ላይ ሲያዝ በወለንጪቲ ከተማ ደግሞ 495,390 ዶላር ተይዟል…”

“በሌላ በኩል የግጭቱ አነሳሽነት ሚና ያላቸውና ለዜጎች ዕልቂት፣ መፈናቀልና ለአገር ሀብት ውድመት ምክንያት የሆኑ ሹማምንትና የፀጥታ አካላት አመራሮች በሕግ አለመጠየቃቸው ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ሕግ ባለበት አገር ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሰቆቃ የሚፈጽሙ ሰዎች ለምን ዝም ይባላሉ? ማንነታቸውስ ለምን ይፋ አይደረግም? ሲሉም በቁጭት ይጠይቃሉ፡፡”

 

በሪፖርተር

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከመስከረም ወር 2009 ዓ.ም. አንስቶ ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች በስተቀር እምብዛም ወሬው አልተሰማም ነበር፡፡

የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮችም ስለዚህ ግጭት የዘገቡት መረጃ አልነበረም፡፡ በታኅሳስ ወር 2009 ዓ.ም. ለአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ነበሩ፡፡ በሌሎች አካባቢዎች ከሚታየው ብሔር ተኮርና ከወሰን ጋር በተገናኘ ግጭት አዘል እንቅስቃሴ ራስ ምታት የሆነባቸው፣ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት እንደሆነ ለመጀመርያ ጊዜ ይፋ አድርገዋል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም መረጃውን ይፋ ባደረጉበት ሰሞን የተቀሰቀሰ ግጭት ሳይሆን ላለፉት አራት ወራት (ከመስከረም ወር ጀምሮ ማለታቸው) የዘለለና መፍትሔ ያልተገኘለት አሳሳቢ ግጭት መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር፡፡ የሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የፀጥታ አካላት ጭምር የተሳተፉበት ግጭት በመሆኑ ከባድና ውድመቱም የዚያን ያህል ነበር፡፡ በፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ግጭቱ ጋብ ካለ በኋላ፣ የግጭቱ ምክንያት ከወሰን ጋር የተገናኘ መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም በወቅቱ የሰጡትን ማሳሳቢያ ተከትሎም፣ የሁለቱ ክልሎች ፕሬዚዳንቶች በፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር አግባቢነት ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የግጭት ምክንያት ነበሩ የተባሉ አስተዳደራዊ ወሰኖችን ለማካከል ሚያዝያ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይሁን እንጂ በስምምነቱ የአስተዳደር ወሰኖችን የማካለል ተግባር በመከናወን ላይ እያለ ደግሞ ግጭቱ ማገርሸቱን፣ ከፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር በወቅቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተለይ ከሐምሌ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በኋላ ወደለየለት ጦርነትና አሰቃቂ ግድያ በሁለቱም ወገኖች በኩል የተገባ ሲሆን፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 800 ሺሕ የሚገመቱ ወገኖች በብሔራቸው ምክንያት ኑሯቸውን ከመሠረቱበት ቀዬ እንዲለቁና ሕይወታቸውን በመጠለያ ካምፖች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲገፉ ተገደዋል፡፡

በጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት የወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም፣ ቀደም ብለው የግጭቱ ምክንያት እንደሆነ ካስታወቁት የተለየ መረጃ ለምክር ቤቱና ለመላው የአገሪቱ ሕዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡

‹‹ይኼ ግጭት የወሰን አይደለም፡፡ በዚህ አካባቢ ያለውን የጫት ንግድ ለመቆጣጠር የሚደረግ ሩጫ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በዚህ መስመር ከፍተኛ የሆነ ሕገወጥ የዶላር ዝውውርና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል የብሔር ግጭት መቀስቀስ አዋጭ እንደሆነ ያመኑ፣ በእኛው ውስጥ ያሉ የሥርዓቱ ጥገኞች የቀሰቀሱት ግጭት ነው፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ለቀውሱ መፍትሔ ለማምጣት በማሰብ ‹‹እታገላለሁ›› ያሉት በወቅቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከአፈ ጉባዔነት ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው፣ የድርጅታቸውን የኢሕአዴግ ውሳኔ እየተጠባበቁ ነበር፡፡ አቶ ኃይለ ማርያም የአቶ አባዱላን የመልቀቂያ ጥያቄ በተመለከተ ማብራርያ እንዲሰጡ በወቅቱ ከምክር ቤቱ ተጠይቀው፣ በአቶ አባዱላ መልቀቂያ ላይ ኢሕአዴግ ገና እየተወያየና ውሳኔ ያላገኘ መሆኑን በመግለጽ በአፈ ጉባዔነታቸው ቢቀጥሉ እንደሚመርጡ አስታውቀው ነበር፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የብሔር ግጭት እንዲቀሰቀስና የበርካቶች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋ ያደረጉ ሥርዓቱ ውስጥ ያሉ ጥገኞችን በተመለከተ መፍትሔ ካልተሰጠ በስተቀር፣ ግጭቱን ማቆም እንደማይቻልም ጠቁመዋል፡፡

‹‹መፍትሔው ፖለቲካዊ ነው፡፡ ጥገኞቹን በመድፈቅ መፍትሔ ካልተሰጠ በስተቀር መቼም ቢሆን ግጭቱን ለማስቆም አይቻልም፤›› ብለዋል፡፡

በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉት ነዋሪዎች ቁጥር ከፍተኛ የሆነበት ምክንያት በአካባቢው የነበረው የመከላከያ ሠራዊት ለሌላ ተልዕኮ ተሰማርቶ የነበረ በመሆኑ፣ በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የነበረው አማራጭም በሥፍራው የቀረው ጥቂት የመከላከያ ሠራዊት ጥቃት ይደርስባቸዋል የሚባሉ ነዋሪዎችን በራሱ ተሽካርካሪዎች በማጓጓዝ ከቀዬአቸው እንዲወጡ ማድረግ ብቻ እንደነበር፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከወራቶች በፊት መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡

የተፈናቀሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ግን የመከላከያ ሠራዊቱ ፈጥኖ ባለመድረሱ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡

ግጭት ከተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች የሁለቱም ክልሎች የፀጥታ አካላት ለቀው እንዲወጡ ከተደረገና በአካባቢዎቹ በፌዴራል ፖሊስና በመከላከያ ሠራዊት ከተሰማሩ በኋላ፣ አንፃራዊ መረጋጋት በጥር ወር 2010 ዓ.ም. ሰፍኗል፡፡

በግጭቱ የተሳተፉ የመንግሥት መዋቅር አካላት በቁጥጥር ሥር ለማዋልና ለሕግ ለማቅረብ በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ቢከናወንም፣ ውጤቱ ግን እስካሁን በዚህ አካባቢ ከተከሰተው ግጭትና ከአጠቃላይ የአገሪቱ ፖለቲካዊ ቀውሶች ጋር በተያያዘ ለመፍትሔ ይበጃል ያሉትን ውሳኔ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ይፋ አድርገዋል፡፡ ይኸውም ‹‹የመፍትሔው አካል ለመሆን ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በፈቃዴ ለመልቀቅ ወስኛለሁ ይኼንን የድርጅቴ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተቀብሎታል፤›› የሚል ነበር፡፡

እሳቸውን ለመተካት በኢሕአዴግ ውስጥ የነበረውን ፖለቲካዊ ትግል አሸንፈው ወደ ሥልጣን የመጡት የኦሕዴድ ሊቀመንበር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በፓርላማው በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሰየሙ በኋላ በቀናት ውስጥ ወደ ሶማሌ ክልል በመጓዝ፣ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኞች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭትና ዳግም የማገርሸት ሥጋት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲፈታ የሁለቱን ክልሎች ፕሬዚዳንቶች አሳስበውና በሕዝብ ፊት እጅ ለእጅ አያይዘው ተመልሰዋል፡፡ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና ዕርቅ ለማከናወን፣ የተፈናቀሉትን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስና ለማቋቋም የሁለቱም ክልሎች አመራሮች በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም. ቃል ገብተዋል፡፡

ሁለቱ ክልሎች ሰላም ለማውረድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በተገኙበት ቃል ቢገባም፣ በፍጥነት ወደ ተግባር አልገቡም፡፡ ይልቁንም በቦረና አካባቢ ተመሳሳይ ግጭቶች በሁለቱ ክልሎች ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት ጭምር ተስተውሏል፡፡

ከሐምሌ 2009 ዓ.ም. አንስቶ በአካባቢዎቹ ግጭቶች የተሳተፉትን ለሕግ ለማቅረብ ሁለት መርማሪ ቡድን ተቋቋሞ መቀመጫውንም በድሬዳዋ ከተማ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፣ እስካሁን ተጠርጣሪዎችን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል አልተቻለም፡፡ ለዚህ የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ ሁለቱም ክልሎች ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ ለመስጠት ተባባሪ አለመሆናቸው ነው፡፡ በአካባቢው በሚስተዋለው ግጭት ከፍተኛ የዶላር አዘዋዋሪዎችና የኮንትሮባንድ ንግድ አደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት አካላት ስለመኖራቸው የመንግሥት አመራሮች ድምዳሜ ላይ ቢደርሱም፣ ይኼንን ሕገወጥ እንቅስቃሴ ማፍረስ አልተቻለም፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት ፓርላማ የተገኙት የገቢዎችና የጉምሩክ ባለሥልጣን አመራሮች በዚህ የኮንትሮባንድና የዶላር ዝውውር የሚሳተፉ እነማን እንደሆኑ በመለየት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚመለከታቸው አመራሮች ሪፖርት ማድረጋቸውንና ዕርምጃ የመውሰድ ውሳኔ የከፍተኛ አመራሩ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡ የተዋናዮቹን ማንነት እንዲገልጹ በፓርላማው ቢጠየቁም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር ቀውስ ውስጥ ብትገባም ከአገር ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ ግን እንደቀጠለ መሆኑን መረጃዎች ያሳዩ ነበር፡፡ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በአንድ ቀን በተደረገ ዘመቻ ብቻ 591,453 ዶላር አዋሽ ላይ ሲያዝ በወለንጪቲ ከተማ ደግሞ 495,390 ዶላር ተይዟል፡፡

ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለፓርላማው ያቀረቡት የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ፣ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ አመራሮችና ግለሰቦች ለሕግ እንዲቀርቡ መንግሥት በሰጠው አቅጣጫ በሰባት መዝገቦች የምርመራው ውጤት የተደራጀ ቢሆንም፣ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራው አለመከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ግጭቱን ለማረጋጋትና ወደ ቀድሞ የሰላም ሁኔታ ለመመለስ መንግሥት በልዩ ሁኔታ ትኩረት እንዲሰጠውና የተለያዩ የተግባር እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም፣ ‹‹በፌዴራልና በክልሎች እንዲሁም በክልሎቹ መካከል ሊኖር የሚገባው ቅንጅት፣ መናበብና መደማመጥ መሆን በሚገባው ደረጃ ላይ ባለመድረሱ ምክንያት ግጭቶችን ፈጥኖ መቀልበስና አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ ላይ እንቅፋት ሆኗል፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ግጭት ጋር በተያያዘ ውጤታማ ሥራ እንዲሆን ሚኒስትሩ አቶ ከበደ የገለጹት አንድ ጉዳይ፣ ግጭቱ ከኢትዮጵያ አልፎ አካባቢያዊ ግጭት እንዳይፈጥር የተደረገውን ጥረት ነው፡፡ ግጭቱ በጂቡቲ፣ በሶማሊላንድ፣ በፑንትላንድና በኬንያ ውስጥ ወደሚኖሩ ተመሳሳይ ሕዝቦች ተዛምቶ አካባቢያዊ ግጭት እንዳይፈጠር ለሁሉም አገሮች የመንግሥት ኃላፊዎች ስለሁኔታው በማስረዳት መቆጣጠር መቻሉን ገልጸው ነበር፡፡

ሐምሌ 2010 ዓ.ም.

ሚኒስትሩ አቶ ከበደ በቅርቡ ባቀረቡት ሪፖርት የተረጋጋ ሁኔታ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኞች በመፈጠሩ፣ በፍጥነት ወደ ወሰን ማካለልና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙት መግባት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ነገሮች እንደ እርሳቸው ፍላጎት አልሆኑም፡፡ ተረጋጋ የተባለው ግጭት በድንገት አገረሸ፡፡

በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ አካባቢዎች ለአብነት ያህልም በጭናክሰን፣ በባቢሌ፣ በሚኤሶ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በቦረና፣ በጉጂና በሞያሌ አካባቢዎች ግጭቱ በሐምሌ ወር ተካሮ የበርካቶችን ሕይወት መቅጠፍ ያዘ፡፡

‹‹በአካባቢዎቹ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ግጭቶች የተከሰቱ ቢሆንም፣ የሰሞኑ ግጭት ግን ሰፊ አካባቢዎች የሸፈነና የበርካታ ዜጎች ሕይወት ያለፈበት ነው፤›› ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ባለፈው ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሲቪል የለበሱ ነገር ግን ከባድ የጦር መሣሪያ የታጠቁ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ የሶማሌ ክልልን የልዩ ፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች በመዝለቅ በነዋሪዎች ላይ በቀጥታ የመተኮስና የመግደል፣ ቤት የማቃጠል ተግባር ከፈጸሙ በኋላ የሶማሌ ክልል ባንዲራ ተክለው እንደሚመለሱ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ስለሁኔታው አስረድተዋል፡፡

‹‹መታወቅ ያለበት ጉዳይ ግን በዚህ መታለል የለብንም፡፡ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ምንም ዓይነት ለግጭት የሚያደርስ ምክንያት የለም፤›› ብለዋል፡፡

ቀድሞ የነበረው የዚህ አካባቢ ግጭት በመንግሥት ላይ ፈጥሮት የነበረው ሥጋት በጎረቤት አገሮች የሚኖሩ የሶማሌ ብሔረሰብ ነዋሪዎችን በማነሳሳት፣ በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢያዊ ግጭት እንዳይቀሰቀስ ነበር፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ግን ይህ እንዲፈጠር ፍላጎት መኖሩን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች በአኗኗር ዘይቤያቸው ምክንያት መሣሪያ የታጠቁ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡ በመሆኑም የታጠቁት ኃይሎች በድንገት ጥቃት ሲያደርሱባቸው ጥቃቱን እነማን እንዳደረሱባቸው እንኳን ሳይረዱ፣ ታጣቂዎቹ ወደ መጡበት አቅጣጫ በመዝለቅ እነሱም አፀፋዊ ጥቃት ሰንዝረው እንደሚመለሱ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ወቅት ‹‹ኦሮሞ ገደለን›› የሚል መረጃ በጎረቤት አገሮች ወደሚገኙ የሶማሌ ሕዝቦች ማሰራጨት መሆኑን፣ ይህ የሚያሳየውም ቀጣናዊ ግጭት በምሥራቅ አፍሪካ ለመቀስቀስ እንደሆነ ያስገነዝባሉ፡፡

‹‹ይህ በግጭት መነገድ ነው፤›› የሚሉት ነገሪ (ዶ/ር)፣ ምክንያቱ ደግሞ ኢኮኖሚያዊም ፖለቲካዊም እንደሆነ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኩል መተንተኑን ጠቅሰዋል፡፡

ፖለቲካዊ ዓላማ የኦሮሚያ ክልልን እንዲሁም ቀጣናውን በማተራመስ ማዕከላዊ መንግሥትን ማዳከም ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ከተሰየሙ በኋላ ከኤርትራ ጋር ዕርቅ ማውረዳቸውን በበጎ ያልተመለከቱ፣ ወይም ያከስረናል ብለው የሠጉ ‹‹የፖለቲካ ቁማርተኞች›› ከጀርባ የቀሰቀሱት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኢኮኖሚያዊ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ በዚሁ በፖለቲካ ቁማር ውስጥ ቀንደኛ ተዋናዮቹ ከመሀል አገር አንስቶ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል በማለፍ ጎረቤት አገሮች ድረስ የዘረጉት ግዙፍ የኮንትሮባንድ ንግድና ሕገወጥ የዶላር ዝውውር ተሳታፊ መሆናቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ይኼንን የተደራጀ የዘረፋ ኔትወርክ መበጣጠስ በመጀመራቸው መሆኑን ነገሪ (ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡

አካባቢያዊ ግጭት የመቀስቀስ አዝማሚያ ስለመኖሩ ምልክቶች መታየታቸውን ይጠቁማሉ፡፡ የኦሕዴድ የገጠር የፖለቲካ አደራጃጀትን የሚመሩት የፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አዲሱ አረጋ በማኅራዊ ሚዲያ ድረ ገጽ ላይ፣ በአዋሳኝ የኦሮሚያ አካባቢዎች ጥቃት በመሰንዘር ተጠርጥረው ከተያዙት መካከል የሶማሊያ (ሞቃዲሾ) መታወቂያ የያዘ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ግጭት በዚህ አካባቢ በሰፊው በተቀሰቀሰበት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ ሕገወጥ የዶላር ዝውውር መጨመሩን፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ቀደም ሲል ሕገወጥ የዶላር ዝውውሩ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል በኩል ባመዛኙ ይደረግ የነበረ መሆኑን፣ አሁን ግን ይኼንን መስመር ሳይለቅ በቦሌ ኤርፖርት በኩል መስፋፋት መጀመሩን የባለሥልጣኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

በኤርፖርት መንገደኞች አነስተኛ መጠን ዶላር በመያዝ የማስወጣት አዝማሚያ መኖሩን ለመረዳት መቻሉም ታውቋል፡፡ በአንድ ሳምንት ወስጥ ብቻ 48,600 ዶላር ከተለያዩ መንገደኞች መያዙን ያገኘነው መረጃው ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ሰኞ ሐምሌ 9 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢቲቪ በኩል ባስተላለፉት መልዕክት የውጭ ምንዛሪና በመኖሪያ ቤቶች ከፍተኛ የኢትዮጵያ ብር ያከማቹ በፍጥነት ወደ ባንክ ሥርዓት እንዲያስገቡ፣ ዶላሩንም ለባንኮች በማቅረብ እንዲመነዝሩ አሳስበዋል፡፡

ዶላር ያከማቹ አገሪቱ በቂ የውጭ ምንዛሪ እያስገባች በመሆኑ ኪሳራ እንዳይደርስባቸው በማሰብ የተናገሩት ቢሆንም፣ ከባንክ የተሸሸገ ሀብት ባከማቹ ላይ መንግሥት ዕርምጃ እንደሚወስድ ግልጽ አድርገዋል፡፡

አያይዘውም የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት በፍጥነት ገብተው በአነስተኛ ኪሳራ እንዲቆጣጠሩ አዘዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የፌዴራል የፀጥታ አካላት ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ መሰማራታቸውን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

‹‹ከግጭቱ ጀርባ ያሉት አሁን በአገሪቱ እየታዩ ያለውን ሰላምና መረጋጋት እንዲቀጥል የማይፈልጉ ኃይሎች ናቸው፡፡ እነዚህን አካላት ነጥሎ የማውጣትና የማስታገስ ተልዕኮውን የመከላከያ ሠራዊቱ ይወጣል፤›› ሲሉ አቶ ሞቱማ መቃሳ ሰሞኑን ተናግረዋል፡፡ በሁለቱ ክልሎች ውስጥ መሰንበቻውን በነበሩ ግጭቶች ቁጥራቸውን በውል ባይገልጹትም፣ የበርካቶች ሕይወት መቀጠፉን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል የግጭቱ አነሳሽነት ሚና ያላቸውና ለዜጎች ዕልቂት፣ መፈናቀልና ለአገር ሀብት ውድመት ምክንያት የሆኑ ሹማምንትና የፀጥታ አካላት አመራሮች በሕግ አለመጠየቃቸው ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ሕግ ባለበት አገር ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሰቆቃ የሚፈጽሙ ሰዎች ለምን ዝም ይባላሉ? ማንነታቸውስ ለምን ይፋ አይደረግም? ሲሉም በቁጭት ይጠይቃሉ፡፡

Fresh assessment confirms dispute over land root cause of Moyale conflicts

30 Jul

Editor’s Note:

  This latest round of conflict along the Ethiopia – Kenya border has caused huge displacements of people, mostly from Ethiopia into Kenya. However, reports that the movement of people is monodirectional, i.e., from Ethiopia to the Kenyan side of the border, is simply wrong.

  People are moving in all directions- southwards and northwards mainly, trying to escaping for their lives. This lastest conflict has involved and affected not only two communities, as the international media has been alleging, but also some others too from within Kenya itself, for instance, the Degothia.

  This situation has given rise to sparring amongst some local politicians, parliamentarians, over alleged protection of their constituencies. Because of that in northern Kenya they are now at each other’s throats at this time of campaigns in the presidential election in that country.

  Some seem angry at the local government, accusing it of not providing security for all the people. Others are angry by the mere fact that members of their constituency are moving from northern Kenya into southern Ethiopia to seek security and asylum, as KTN, Kenyan television reports. They are more seen being in clear denial of the situation that putting their heads together to seek lasting solution to the problem.

  It comes as no surprise that Kenyan police suspicion should be concerned with involvement of local politicians in the conflict. Having found evidence, they have arrested some four politicians and are also in pursuit of some others. In the final analysis, this may be a step in the right direction in the interim.

  Let there be no doubt that apprehension of such individuals may only go to an extent. What is needed is determined efforts on the part of the governments of the two countries to empower the local people to withstand the onslaught of failing resources – land and water – amongst the pastoralist populations. This has been the prime culprit that has been causing frequent conflicts.

  In 2012 alone, this is the third such conflict, entailing scores of deaths and several tens and thousands displaced. Evident now is that the cycles of the conflicts shortening and the costs in lives and properties have been enormous, with the situation exacerbated by climate change – which for East Africa is no longer theoretical but an everyday reality.

  Governments ought to take lessons, instead of dwelling on the problems and prescribing at its peak shortsighted solutions that could simply extinguish the immediate fire.

  As it happens, there hardly is better solutions than what the people are demanding, as the appeal by an elderly person from Wajir put it to IRIN: “We don’t need relief food, drought will be there next year. What we need is to be empowered. Our people have enough livestock; they need hay, water and markets for their livestock but not free food.”
   

  LATEST UPDATE ON THE SITUATION
   
  The latest assessment by a Kenya Red Cross Society (KRCS) team of these fierce conflicts since Thursday 26th July 2012, according to IRIN, has confirmed the same, causing deaths, injuries and loss of property with reports of massive displacements of populations.

  This displacement and subsequent migration of the Ethiopian population into Kenya has been occasioned by simmering dispute over land. It involves more than the Borana and Garre communities, with the Degothia community of North eastern Kenya pushing the Garris out of the areas. It also reveals inadequacies in earlier conflicts. The Garris happened to be occupants of the land, following the decision by the Ethiopian government to settle the Garris into the disputed lands that Boranas claim ownership.

  A huge number of the Ethiopian refugees, according to IRIN, are being hosted in Somare, Lami, Bori, Sessi, Biashara Street, Al-k-Rashid Primary School, Nana, Kinisa and Yaballo areas of Moyale. Most concentrations are at Somare Primary School.

  Unfortunately, there is no word from the Ethiopian side how many Kenyan refugees have moved in, what their condition is and where they are being taken care of.
   
  Transforming Ethiopia TE

%d bloggers like this: