Tag Archives: Dr. Abiy Ahmed

ነፃ ያልወጣው ነጻ አውጭ ጄኔራል ጥቅማችን ተቋረጠ በማለት ወያኔ ኢትዮጵያንና በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በኃይል ለማዳፈን መዘጋጀቱን ገለጸ! ወይ ወያኔዎች በሕዝብ መተፋታችውን አለመገንዘብ!

4 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“…ያለው ሁኔታ ከ[ዐ]ብይ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ሳይሆን እናይ በመሰረቱ ማየት ያለብን እንደጠላት ሃይል አድርገን ነው። እንደጠላት ሃይል አድርገን ካልወሰድነው እንዴት አምርረን እንደምንወጋውም ግልፅ ሊሆንልን አይችልም። ስለዝህ ሄዶ ሄዶ ከኢህአዴግ ውስጥ ተነስቶ እየበሰበሰ ራሱን እየበላ የኢህአዴግም ፕሮግራም ጭምር እየበላ በልቶ በልቶ ከጨረሰ ብሁዋላ በመጨረሻ በስልጣን ላይ የወጣው ሃይል ከኢህአዴግ ፕሮግራም ጋር የሚገናኝ ትንሽ የኢህአዴግ ሽታ እንኩዋን የለውም። ለእኔ ይህ የጠላት ሃይል ነው። እንደጠላት ሃይል እንውሰደው። አሁን የኢህአዴግ ሽታ የለውም ማለት ይህ ሃይል ህዝባዊ ሽታ ያለው አይደለም ማለት ነው። ከህዝባዊነት የወጣ ስላልሆነ ሄዶ ሄዶም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ለፌደራላዊ ስርአታችን ሊያጠፋ የሚችል አካሄድ እየሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።” Continue reading

ኢሳትና ኦ ኤም ኤን የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲሁም የዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ጃዋር መሀመድ ክሶች ተቋረጠ!

29 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተቀማጭነታቸው በውጭ ሀገር በሆነው ኢሳት እና ኦ ኤም ኤን የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲሁም በዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሀመድ ላይ የከፈተው ክስ እንዲቋረጥ ጠይቋል።

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአዋጅ ቁጥር 943//08 አንቀፅ 6 ንዑስ ቁጥር 3/ሀ/ መሰረት ክሱ እንዲነሳ ተወስኗል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስን ስለማንሳት በፃፈው ደብዳቤ በእነ ዶክተር መረራ ጉዲና መዝገብ ስር የሚገኙት እነዚህ ተቋማትና ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ዛሬ የጠየቀ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም ጥያቄውን ተቀብሏል።

ግለሰቦቹ በሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ ወንጀል እንዲሁም የቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ደግሞ ግለሰቦቹ የሚያስተላልፉትን ጥሪ በመቀበልና የሽብር ቡድን ድጋፍ በማድረግ በዋና ወንጀል ላይ ተካፋይ በመሆን የሽብር ተግባር ወንጀል ተከሰው እንደነበር ነው በወቅቱ የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ይገልፅ የነበረው።

ተዛማጅ:

ጠ/ሚሩ የዜጎችን ሰብአዊ መብት የማስከበርና የማክበር ተልዕኮ መግሥታቸው እንደሚያከብር አረጋገጡ!

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት የዜጎችን ሰብአዊ መብት የማስከበርና የማክበር ተልእኮን ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነ ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገለፀ።

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ጋር በሀገሪቱ በሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልፀዋል።

በውይይታቸውም በተለይ ኮሚሽኑ የሚወስናቸውን ውሳኔዎች በመቀበል እና በመተግበር በኩል የክልል እና ፌደራል ተቋመት ላይ ክፍተት እና የቁርጠኝነት ችግር እንዳለ መነሳቱንም አብራርተዋል።

በነዚህ አካላት ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግ ማሳሰቢያ መስጠት የሚያስችል ውይይት መደረጉንም ዶክተር አዲሱ አስታውቀዋል።

ዜጎች በሰብአዊ መብት ጉዳይ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ የማዳበር ስራ ከኮሚሽኑ በተጨማሪ የመንግስት እና የፍትህ አካላት ስራ ሊሆን እንደሚገባ መወያየታቸውንም ዶክተር አዲሱ ተናግረዋል።

ግንዛቤ የማዳበር ስራው የእነዚህን አካላት ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደሆነም በውይይቱ መነሳቱን አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ የዜጎችን ሰብአዊ መብት የማስከበርና የማክበር ተልእኮን ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆኑ በውይይቱ ማረጋገጣቸውን ነው ዶክተር አዲሱ የተናገሩት።

ከመብት ጥሰቶች ጋር ተያይዞም በዜጎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በመመለስ እና ኮሚሽኑ በምርመራ በሚለያቸው ጉዳዮች ላይ በመመስረት ቁርጠኛ እና ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ ማረጋገጣቸውንም ዶክተር አዲሱ ገልፀዋል።

ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር አያይዘውም፥ በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት የመብት ጥሰት ውስጥ የገቡ የአስፈጻሚ፣ የፀጥታ እና የአስተዳደር አካላት እንደተለዩም ተናግረዋል።

በእነዚህ አካላት የተፈፀሙ የመብት ጥሰቶች ዝርዝር መረጃንም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማቅረብ ኮሚሽኑ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ እና መድረክም እንደተያዘለት ነው ያስታወቁት።

ሕወሃት ኢትዮጵያን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢቸነክርም፣በዓለ ትንሣዔው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ሰላምና ዲሞክራሲ ማዋለጃውና ወደነጻነት የሚያደረገውን ሽግግር የሚጠናከርበት እንዲሆን እንመኛለን!

7 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

Easter Flower (AGM)


                           =====000=====
 

The renowned American five-star army general Dwight D. Eisenhower, who in post-World War II United States later became a statesman and US President (1953-1961), in his 1961 farewell address to the American people cautioned:
Continue reading

ዶር ዐብይ አሕመድ የሠጡት የመጀመሪያው ሲግናል: ሕዝቡ ለችግሮቹ መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል!

31 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

የሞያሌውን ግድያ እንዲያጣራ የተቋቋመው ቡድን ማጣራቱን እንዲያቆም ታዘዘ! የሠሩትን ስለሚያውቁ መረጃው አስፈርቷቸው መሆን አለበት!

30 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
ዋዜማ ራዲዮ– በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ስለተገደሉት ዜጎች ጉዳይ እንዲያጣራ የተሰየመውና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም የሚከታተለው መርማሪ ቦርድ የማጣራት ተልዕኮውን እንዲያቋርጥ መታዘዙን የዋዜማ ምንጮች አመለከቱ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ ስብሳቢ በአቶ ታደሰ ወርዶፋ የሚመራውና አስራ ሁለት አባላትን ያካተተው መርማሪ ቡድን ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 24 ድረስ ወደ ሞያሌ ተጉዞ ምርመራ የማካሄድ እቅድ ነበረው።
Continue reading

Abiy carries a landslide win of 108 votes to become EPRDF Chairman; he is the prospective prime minister

27 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Addis Fortune
 
The Council of the ruling EPRDF has elected Abiy Ahmed (PhD) its third chairman today.

The candidate from the OPDO, Abiy Ahmed (PhD), has carried a landslide votes of 108 against his rivals from SPDM, Shiferaw Shigute, who has received 59 votes and TPLF’s Debretsion Gebremichael’s (PhD), who did get only two votes, sources disclosed to Fortune.

The candidate from the ANDM, Demeke Mekonnen, has declined to accept a bid for the chairmanship of the EPRDF last minute, paving the way for many of the Council members voting for OPDO’s candidate, Abiy Ahmed (PhD), people close to the process told Fortune.

This led many of the Council members from the TPLF voting for a candidate other than their chairman, Debretsion Gebremichael (PhD), who has managed to receive only two votes.
 

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን የተቃወሙ የኦህዴድ ተመራጮች ከፓርላማ እንዲባረሩ ተጠየቀ

22 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
መጋቢት 13 /2010 (ኢሳት ዲሲ) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ስብሰባ ተከትሎ ማክሰኞ በተጀመረው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን የተቃወሙ የኦህዴድ ተመራጮች ከአባልነት እንዲሁም ከፓርላማ እንዲባረሩ ህወሓት ጠየቀ።

በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከተወሰነው ውጭ የቀረበው ይህ አጀንዳ ተቃውሞ ገጥሞታል።

የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራር አባላት በተጨማሪም በአቶ ለማ መገርሳ እና በዶ/ር አብይ አህመድ ላይ የተለያዩ ክሶች ማቅረባቸውም ተሰምቷል።

እነርሱም ጠንካራ ምላሽ ሰጥተዋል።
Continue reading

%d bloggers like this: