Tag Archives: Egypt’s colonial treaties

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው—”የግብፅ ዐባይን ለዘለዓለም ተቆጣጥሮ የመኖር ፍላጎት ለ20ኛው ክፍለ ዘመን ሠርቶ ሊሆን ቢችልም፣ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ግን አይሠራም!”

23 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሪፖርተር

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት፣ የዛሬ አንድ ዓመት ገደማ በሚያዝያ ወር 2011 ዓ.ም. ነበር፡፡ ከዚህ ሹመት አስቀድሞ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በመሆን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉት አቶ ገዱ፣ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጡት ከወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መልቀቅ በኋላ ለወራት ክፍት ሆኖ ቆየውን ኃላፊነት በመረከብ ነበር፡፡ አቶ ገዱ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጡበት ጊዜ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ለውጦች የተስተዋሉበት በመሆኑ የተነሳ፣ በርካታ ሥራዎች ይጠብቋቸው ነበር፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በዋናነት ከግብፅና ከሱዳን ጋር የሚደረጉትና እየተጧጧፉ የመጡት የህዳሴ ግድብ ድርድሮችና የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ስምምነቶች ሲሆኑ፣ ሁለቱም ጉዳዮች ከፊት ሆኖ የሚመራና ውጤት የሚጠበቅበት አመራር ይጠይቁ ነበር፡፡ በዚህም ሳቢያ አቶ ገዱ የመጡበት ጊዜ ፈታኝ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ፡፡ እሳቸው ወደ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመጡ በኋላ በህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች እየጦፉ ነው፡፡ በተለይ የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ በታዛቢነት በህዳሴ ግድቡ ድርድር መሳተፍ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የግድቡ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ገጽታን እየተላበሰ የመጣ ሲሆን፣ የአሜሪካ መንግሥት የግምጃ ቤት ኃላፊ ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበትን የመጨረሻ ውይይት አስመልክቶ ላወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ምላሽ ስትሰጥ፣ ግብፅ ደግሞ በበኩሏ ኢትዮጵያን መውቀስ ጀምራለች፡፡ ይኼም በተደጋጋሚ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የቃላት ጦርነት እንዲታይ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ አሜሪካ ሳትገኝበት ከቀረችው የውይይት መድረክ በኋላ በአገሮቹ መካከል በጉዳዩ ላይ የተደረገ ውይይት ባለመኖሩ፣ የዚህ ውዝግብ ጉዳይ መጨረሻ ምን ሊሆን ይችላል ሲሉም ብዙዎች ይጠይቃሉ፡፡ የህዳሴ ግድቡ ድርድር ቀጣይ ዕጣ ፈንታ፣ የግብፅ ተፅዕኖ፣ የአሜሪካ ለግብፅ ማድላት፣ በዓረብ ሊግ ውሳኔ የጂቡቲና የሶማሊያ አቋም፣ እንዲሁም የኢትዮ ኤርትራ ዕርቅን  የተመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት ብሩክ አብዱ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ሪፖርተር፡– በህዳሴ ግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ በኢትዮጰያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ሲደረግ የቆየው ድርድር ስምንት ዓመታትን ቢዘልቅም በአገሮቹ መካከል ለዚሁ ጉዳይ ገዥ ሊሆን የሚችል ሕግ ላይ ስምምነት ተደርሶ ሊፈረም አልቻለም፡፡ በስተመጨረሻም የአሜሪካ መንግሥት ከዓለም ባንክ ጋር በመሆን ድርድሩን በታዛቢነት አስኬዳለሁ በማለት የተሳተፈ ሲሆን፣ አሜሪካና የዓለም ባንክ ከሚናቸው ውጪ በመሄድ ስምምነት አርቅቀን እናቀርባለን በማለታቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሁለቱ ታዛቢነት ከሚደረገው የመጨረሻ ድርድር ራሱን አግልሏል፡፡ ይኼንን ተከትሎ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ያወጣውን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት አሳዝኖኛል በማለት ለግብፅ ያደላ እንደሆነ በማስታወቅ አጣጥሎታል፡፡ ነገር ግን የአሜሪካና የዓለም ባንክ የሚታዘቡት ድርድር ላይ ከመገኘታችሁ አስቀድሞ፣ በተለይ አሜሪካ ለግብፅ ልታደላ እንደምትችል መገምገም አልተቻለም ነበር?

አቶ ገዱ፡– የህዳሴ ግድብ ድርድር ወደ አሜሪካ ሲሄድ አሁን ወደ መጨረሻ አካባቢ የታየው አዝማሚያ እንደሚኖር አልተገመተም ወይ ለሚለው፣ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ሐሳቦች ነበሯቸው፡፡ ምን ማለት ነው? በተለይ ግብፆች የሚያሳዩት ባህርይ ስለነበረና አሜሪካን ለምነው ስለሆነ ወደዚያ የሄዱት የእነሱም ባህርይ እንዲታረቅ፣ እንደገና ደግሞ አሜሪካ የሁለቱም አገሮች ወዳጅ ስለሆነች ልዩነቱ የሚቀራረብበትን መንገድ ይፈልጋሉ፣ ያግዛሉ በሚል ነው፡፡ ዋናው የቴክኒክ ጉዳይ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዞሮ ዞሮ አማካሪዎቹ ይኼ ይሁን፣ ያ አይሁን ብለው ይመጣሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ይፈታል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አሜሪካኖች ጉዳዩን በጥልቀት ስለማይገነዘቡት፣ እንዲሁም በጉዳዩ እየገቡ ያሉት በግብፅ ግፊት ስለሆነ ኢትዮጵያን እንጉዳ ብለው ቢያስቡ እንኳን ከዕውቀትም ማነስ፣ ወይም ደግሞ ግብፆች የበለጠ እንደተበደሉ አድርገው በመገንዘብ ያልሆነ አቅጣጫ እንዲይዝ ሊያደርጉት ይችላሉ በማለት፣ ጉዳዩ አሜሪካ መሄዱ ለኢትዮጵያ ላይጠቅማት ይችላል የሚሉም ነበሩ፡፡ ስለዚህ ሁለቱም ወገኖች የየራሳቸው ግምት ነበራቸው ማለት ነው፡፡ በመንግሥት በኩል ግን እርግጠኛ የምንሆነው በአንድ ነገር ነበር፡፡ አሜሪካኖች እናግዛችሁና ችግራችሁን እናንተው ፍቱ፣ እኛ እናቀላጥፍላችሁና ይህንን ጉዳይ አቃልላችሁ በሌላ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጉ፣ ይኼ ቀጣና ለትብብርና ለሰላም እንጂ ሌላ ግጭት እንዲፈጠርበት አንፈልግም ብለው ሲጋብዙን አንገኝም ማለት ከድርድር እንደ መራቅ ይቆጠራልና ለዲፕሎማሲያችንም ጥሩ አይሆንም፡፡ ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ያለብን የምናካሂደው ድርድር አሜሪካም፣ ካይሮም፣ ካርቱምም ሆነ አዲስ አበባ ተካሄደ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ መስጠት የማይቻል መሆኑን እርግጠኛ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት እርግጠኛ የነበረው በተያዘው አቋም ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር እስከሆነ ድረስ ድርድር ነውና ድሮውንም ቢሆን የታችኞቹን አገሮች መጉዳት ፍላጎታችን ስላልነበረ፣ በድርድሩ አንዳንድ ነገሮችን ሰጥተን በሰጥቶ መቀበል ችግሩ የሚቃለል ከሆነ ምንም ችግር የለውም ብለን ነው የገባንበት፡፡

Continue reading

Grand Nile compromise—a Sisyphean task?

22 Mar

Egypt and Ethiopia are unlikely to strike terms over GERD without agreeing a new legal framework governing the Nile Basin (Credit: Ethiopia Insight)

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

By Ethiopia Insight

Egypt and Ethiopia are unlikely to strike terms over GERD without agreeing a new legal framework governing the Nile Basin

Disagreement over the filling and operation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) has sparked new tensions between Ethiopia and Egypt, with some even warning of an African water war.

Ethiopia recently rejected Egypt’s proposal on the filling and operation of the GERD. In a growing diplomatic spat, Egypt warned Ethiopia not to move forward with the filling and operation of GERD, saying that it “will have negative consequences for the stability in the region.”

Egypt also said the GERD negotiations have reached a deadlock, calling for international interventions to overcome the impasse. Ethiopia, on the other hand, “accused Egypt of trying to maintain its [colonial era] grip over the waters of [the] Nile,” and dismissed Cairo’s call for international mediation.

Although disguised in talks over filling and operation of GERD, the current tension between the two countries is mainly related to their longstanding dispute over the validity of the colonial and 1959 agreements [the ‘Nile Water Agreements’].

Cairo wants Ethiopia to guarantee the supplies allocated to it under the Nile Water Agreements and to ensure adequate water for Egyptian power generation and irrigation. But Ethiopia has long rejected the validity of these Agreements. Addis Ababa also fears that accepting the Egyptian demand will put “ GERD hostage to High Aswan Dam [HAD]”, the Egyptian facility completed in 1970.

Continue reading

%d bloggers like this: