Tag Archives: EPRDF

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሉ አቶ አብዲ በአቶ ጌታቸው ላይ ያቀረቡትን ክስ ኢሕአዴግ እንደማያውቀው ገለፀ

13 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በቢሲ አማርኛ

”ባለፉት ዓመታት ለክልሉ ህዝብ ልማት የተለያዩ ሥራዎችን ሰርተናል። በሥራዎችችን ውስጥ ደግሞ ስህተት ፈጽመናል። ጊዜው የይቅርታ ነው። ስለዚህ ስለሰራነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን። ስህተትን የማይቀበል ሴጣን ብቻ ነው”—አቶ አብዲ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር የሆኑት አቶ አብዲ ሞሃመድ ከክልላቸው የመገናኘ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሯቸው ነገሮች አነጋጋሪ ሆኗል።

አቶ አብዲ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን የመጀመሪያዎቹን 100 ቀናት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ የለውጥ ውሳኔዎች እንደሚደግፉ ገልጸው፤ ”ባለፉት ዓመታት ለክልሉ ህዝብ ልማት የተለያዩ ሥራዎችን ሰርተናል። በሥራዎችችን ውስጥ ደግሞ ስህተት ፈጽመናል። ጊዜው የይቅርታ ነው። ስለዚህ ስለሰራነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን። ስህተትን የማይቀበል ሴጣን ብቻ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ከአቶ አብዲ መግለጫ ውስጥ የበርካቶችን ትኩረት የሳበው የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት የሰጡት አስተያየት ነው። ”ጌታቸው ሙሰኛ፣ ሌባ እና ራሰ ወዳድ ነው” ሲሉ አቶ አብዲ ተደምጠዋል።

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

 

• “ከሞቱት አንለይም” የሶማሌ ክልል እስረኞች

• የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሱ

አቶ አብዲ ”የክልል አስተዳዳሪ ሆኜ ወደ ጌታቸው ቢሮ መግባት የቻልኩት ከ10 ዓመታት በኋላ ነው። አቶ ጌታቸው ለላፉት 27 ዓመታት ለምን ከሚዲያው ተደብቆ ቆየ? የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሃላፊ እንኳ ህዝብ ፊት ወጥቶ መግለጫ ይሰጣል። እሱ ተንኮል እየሰራ ካልሆነ በቀር ለምን ተደበቀ?” ብለዋል።

የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ላይ ህዳር 29/2006 ዓ.ም በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ጅግጅጋ እንዳይሄዱ የከለከለው አቶ ጌታቸው ነው በማለት አቶ አብዲ ተናግረዋል።

”አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ የክልል መስተዳድሮችን ይሾማል” ያሉት አቶ አብዲ ”አቶ ጌታቸው አሁን ለመጣው ለውጥ እንቅፋት ይሆናል” ሲሉም ተደምጠዋል።

የአቶ አብዲክስ አሁን ለምን?

Abdi Iley (BBC Somali foto)

አቶ አብዲ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በርካቶች ተጠያቂ ያደርጓቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ለእሳቸው ተጠሪ በሆነው በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ለሚፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊቶች አቶ አብዲ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ሂዩማን ራይስት ዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ያሳስባሉ።

በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዎች ”ዊ አር ላይክ ዘ ዴድ” (ከሞቱት አንለይም) በሚል ርዕስ ባወጣው ሪፖርት በሶማሌ ክልል የሚገኙ እስረኞች የዘፈቀደ እስራት፣ ድብደባ፣ መደፈርና የሰው ልጅ ማሰብ ከሚችለው በላይ እንግልት እንደሚደርስባቸው አትቷል።

በሪፖርቱ መሰረት ይህንን ሲፈፅሙ የነበሩት የእስር ቤቱ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች፤ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ናቸውም ብሏል።

አቶ አብዲ በቅርቡ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርነት እንዲነሱ የተደረጉትን አቶ ጌታቸው አሰፋን በከፍተኛ ደረጃ መውቀስ ለምን አስፈለጋቸው? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የሶማሌ ክልል የፖለቲካ ምህዳር እና የአቶ አብዲን አስተዳደር ጠንቅቄ አውቃለው የሚሉት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ አቶ ሙስጠፋ ኡመር ሁለት ምክንያቶችን በዋናነት ያስቀምጣሉ።

እንደ አቶ ሙስጠፋ ከሆነ አቶ አብዲ ይህን መሰል ወቀሳን መሰንዘር ያስፈለጋቸው፤ “የአዲሱ የፖለቲካ ለውጥ አካል ሆነው ስልጣን ላይ መቆየት ስለሚፈልጉ ነው። አቶ ጌታቸው እና ሌሎች ግለሰቦች ይፈጽሙ የነበሩትን በይፋ ማውጣት ‘ታዓማኒነትን ያተርፍልኛል’ የሚል ስሌትን በመያዝ ያደረጉት ነገር ነው” ይላሉ።

”ከቀናት በፊት የክልሉ ምክር ቤት ተሰብስቦ ባለበት ሰዓት አቶ አብዲ አንድ ጥቁር ቦርሳ ይዘው መጡ። ከዚያም ‘በዚህ ሻንጣ ውስጥ በርካታ ሚስጥሮች አሉኝ። የክልሉ ባለስልጣናት እና የፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ሚስጥር እዚህ ውስጥ አለ። ገንዘብ የከፍልኳቸው ባለስልጣናት አሉ። እኔን ቢነኩ ይህን ሚስጥር አወጣለሁ’ በማለት ሲያስፈራሩ ነበር” በማለት ተናግረዋል።

የአቶ ሙስጠፋ ሌላኛው ምክንያት ”አቶ ጌታቸው አቶ አብዲን ከስልጣናቸው በተደጋጋሚ ለማንሳት ሙከራ አድርጓል። ይህንንም ለመበቀል ያደረገው ሊሆን ይችላል” በማለት ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።

አቶ አብዲ በቴሌቪዥኝ በተላለፈው መግለጫቸው ላይ ‘አብዲ ጌታቸው ከተባረረ በኋላ ነው ስለሱ የሚያወረው ሊለኝ የሚችል አመራር የለም። ለሁሉም የኢህአዴግ ማዕከላዊ የኮሚቴ አባላት አቤት ብያለው” ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኮሚኬሽን ኃላፊ ሆኑትን አቶ ሳዳት ጠይቀን ነበር። ”አቶ አብዲ የሰጡትን መግለጫ ተመልክቻለሁ። አቶ አብዲ በጽሁፍም ሆነ በስብሰባዎች ላይ ይፋ በሆነ መልኩ ያቀረቡት ጥያቄ ስለመኖሩ የምናውቀው ነገር የለም። ለከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ያላቸውን ቅሬታ አንስተው ሊሆን ይችላል። በጽ/ቤት ደረጃ ግን የምናውቀው ነገር የለም” ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበርና የኢህዴግድ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔርም ”ስለ ጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም። ለእኔም በግሌ የነገረኝ ነገር የለም፤ ሊነግረኝም አይችልም። እንዲህ አይነት ቅሬታም ካለ ህግ እና ሥርዓትን በመከተል ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ማቅረብ ነው ያለባቸው። ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም። ይህ አይነት አቤቱታ ለማዕከላዊ ኮሚቴ የሚቀርብ አይደልም። የማውቀው ነገር የለም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው አሰፋ ማናቸው?

አቶ ጌታቸው አሰፋ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን ለበርካታ ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት ይምሩት እንጂ ስለማነነታቸው እና ሥራቸው በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

ትውልዳቸው መቀሌ ከተማ ስለመሆኑ እና በወጣትነት ዘመናቸው ዊንጌት ስለመማራቸው በስፋት ይነገር እንጂ ይህም ቢሆን እውነትነቱ የተረጋጋጠ አይደለም።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከቦታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ ግለሰቦች መካከል አቶ ጌታቸው አንዱ መሆናቸው ይታወሳል። ከሳምንታት በፊት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ባውጣው መግለጫ ጄነራል አደም መሃመድ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው አቶ ጌታቸውን ተክተዋል።

የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ መንግሥት አያያዝና ፕሮፌ ብርሃኑ ነጋ በወቅቱና መጭው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ ያደረጉት ውይይት!

1 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

Tampere University of Technology sought to honor Ethiopian tyrant with honorary degree – its opponents expect an apology

30 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Mikko Paakkanen* Helsingin Sanomat  

  The Tampere University of Technology (TUT) was about to honor the Ethiopian tyrant with honorary doctorate degree. This action by the university has caused offense and there is a feeling apology is in order.
  Continue reading

Crocodile tears: UK’s unease by recent election outcome completing Ethiopia’s transformation into single-party rule

23 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

UK Foreign & Commonwealth Office Press Release

Minister for Africa James Duddridge calls on Ethiopian government to increase diversity in parliament and ensure the voices of all citizens are heard.

Commenting on the election results, Minister for Africa James Duddridge said:

  “I welcome the fact that the recent Ethiopian parliamentary elections were conducted in a generally peaceful environment and that the Ethiopian people turned out in large numbers. I agree with European Union concerns about the negative impact on the electoral environment of arrests of opposition members and journalists, closure of media outlets, and obstacles faced by the opposition while campaigning.

  “In light of the results I urge the Ethiopian government to explore ways to increase the diversity of political parties in future parliaments, and to ensure those who voted for other parties this time still feel their voice is heard in the next five years. I hope that they will comprehensively address all the issues raised in the African Union Election Observation Mission report. The UK stands ready to offer support which might help in this regard.”

 

Ethiopian opposition parties face difficulties from election board entering in upcoming election

14 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Marthe van der Wolf, VOA

ADDIS ABABA— Ethiopian opposition parties say they are facing roadblocks in their efforts to register for the May elections. The parties say the National Election Board is complicating procedures for no good reason, and raising doubt that the elections will be free or fair.
Continue reading

TPLF claims ‘UN accords its human rights accomplishments highest regard & acknowledgement’, Part II

25 Jul

By Keffyalew Gebremedhin, The Ethiopia Observatory (TEO)

  “Authorities have always recognized that to control the public they control information. The initial possessor of news and ideas has political power – the power to disclose or conceal, to announce some parts and not others, to hold back until opportunistic moments, to predetermine the interpretation of of what is revealed.”

  Prof. Ben H. Bagdikian, The Media Monopoly (1987)

 

        I. The clash between lies & reality & the inescapable consequences

Part I of this article appeared under the title: Are official lies becoming TPLF’s preferred ways of running Ethiopia? That article’s goal has been to expose the endless lies and political propaganda by the TPLF regime, which in this case relates to what transpired in the morning of May 6, 2014 in Geneva when the United Nations examined Ethiopia’s human rights record under what is commonly known as the Universal Periodic Review (UPR) mechanism.
Continue reading

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም: “ድርጅታችን ከዚህ ተነስተህ ወረዳ ታገለግላለህ የሚለኝ ከሆነ የወረዳ ሊቀመንበር ሆኜ እሠራለሁ”

12 Feb

በከፍያለው ገበረመድኅን – The Ethiopia Observatory

  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ስሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ ጉባኤ፡ መለስ ዜናዊን ጠቅስው ስለወደፊት ጽዋ ፈንታቸው ሲናገሩ መስማቱ በዕውነትም ምን ያህል በሌሳ ግለስብ ፕሮፎርማ ብቻ ሳይሆን፡ የሚረግጧትንም መሬት የቀዳሚያቸው እግር ያረፈበት ላይ መሆኑን በማረጋገጥ ጭምር በመሆኑ፡ ነጻ መሪ አለመሆናቸው ፖለቲካዊ መክፋቴን አጠናክሮታል። ስለወደፊቱ ጉዞዋቸው ለማንኛውም፡ ሪፖርተር ኃየለምርያምን ጠቅሶ፡ የሚክተለወን መተንፈሳቸውን አሳውቆናል:-
  Continue reading

Which Way Ethiopia: Revolution, Civil War, or National Reconciliation? A must read!

22 May

By Prof. Messay Kebede

Since the death of Prime Minister Meles, the political situation of Ethiopia has entered a phase of uncertainty with no clear momentum toward stabilization. Despite predictions of the imminent collapse of the EPRDF, either under the pressure of a popular uprising or splits within its ranks, the political situation shows no sign of heightened challenge to the regime.
Continue reading

%d bloggers like this: