Tag Archives: ethiopia

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እንደሚንቀሳቀስ አዲሱ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ አስታወቁ!

19 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

*     መንግሥት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማገልገል አኳያና የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ብቃት ያለው የብሔራዊ  መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ይደረጋል

*     ብሔራዊ  መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሕዝብን እኩል የሚያገለግል ተቋም ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ሥራ ተገብቷል

*      ሕውሃት ለአመራሩ ተጠቃሚነትና ፖለቲካው  በኢትዮጵያ  የዘራው  መርዛማ የአንድ ዘር የበላይነት ሊያከትም ነው!

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 12፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እንደሚንቀሳቀስና እንደሚሰራ አዲሱ የአገልገሎቱ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ አስታወቁ።

በዛሬው ዕለት ድሬክተር ጄኔራሉን ጨምሮ አዲሱ የአገልግሎቱ አመራር ከተቋሙ ሠራተኞችና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ (ፋና ፎቶ)

በዚህ ወቅትም ውይይት የተካሄደ ሲሆን፥ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ  ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚደረገዉ ጥረት ተቋሙ ተልዕኮዉን ሲፈጽም ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

ተቋሙ የግዳጁን አፈጻጸም ዉጤታማነት ከፍ ለማድረግ መንግሥት በሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት በተቋሙ ውስጥ የሪፎርም ሥራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ድሬክተር ጄነራሉ ለሕዝብ የሚተጋ፣ የሚሠራ እንዲሁም የሃገርና ሕዝብ ጥቅም የሚያስከብርና የሚያስቀጥል ተቋም ይደረጋል ብለዋል።

መንግሥት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማገልገል አኳያና የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ብቃት ያለው ተቋም እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈ ማንኛውንም ሕዝብ እኩል የሚያገለግል ተቋም ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ሥራ እንደተገባ ታውቋል።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለፓርላማ ያቀረቡት የመጀመሪያው ግልፅና አስገራሚ ሪፖርት!

18 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

‘የደብረ ማርቆሱ ደፋር ወጣት’

17 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

የፕላን ኮሚሽነሩ ያሳዩት ግልጽነት ከዚህ በፊት ያልታየ በመሆኑ፣ ይልመድቦት እንላለን

11 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከፊል ምንጭ: የብድር ጫና እና የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት መንግስት የልማት ድርጅቶችን በአክስዮን ለመሸጥ እንዲወስን አስገድድል!

የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከፍተኛ ወደሚባል ደረጃ መሄዱና ሃገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የውጭ ምንዛሪ እጥረት መከሰቱ መንግስትን የልማት ድርጅቶችን በአክስዮን ለመሸጥ እንዳስወሰነው የብሄራዊ የፕላን ኮሚሽን ተናገሩ።

የብሄራዊ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ እንደሚሉት፥ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በወጭ ንግድ መዳከምና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ አደጋ ውስጥ መግባቱ ለውሳኔው ምክንያት ሆኗል።

ባለፉት ጥቂት አመታት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች የሚገኘው ገቢ በአማካይ ሶስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ላይ ሲቆም፥ ከውጭ ምርቶችን ለማስገባት የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ ደግሞ 16 እና 17 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።

ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ሙሉ ለሙሉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ከተላኩት ምርቶች የማይገኝ መሆኑም፥ ኢኮኖሚውን ጤነኛ አላደረገውም፤ ይህ ደግሞ ሀገሪቱን የእዳ ጫና ውስጥ ጨምሯታል።

የእዳ ጫና፦ የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የብድር ጫና እንደገባና፥ የብድር ምጣኔዋም የአጠቃላይ አመታዊ ምርቷን 59 በመቶ መያዙን ይገልጻል።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት — በተለይም ሕውሃት — ሃገሪቱ የብድር ደረጃዋ ከከፍተኛዎቹ ይመደባል የሚለውን እስከ ቅርብ ሣምንታት ሳይቀበል ቆይቷል።

የብሄራዊ የፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ግን ሃገሪቱ አሁን ላይ ወደ ከፍተኛ የብድር ጫና ውስጥ እየገባች መሆኑን ይገልጻሉ።

በዚህ ምክንያትና ኢኮኖሚውን ማንቀሳቀሻ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ስለሚያስፈልግም ውሳኔው መተላለፉን ገልጸዋል።

ዶክተር ይናገር ለአሁኑ የውሳኔ አስፈላጊነት ጥቂት ቁጥሮችን በማሳያነት ያስቀምጣሉ፤ የሀገሪቱ አጠቃላይ እዳ 26 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተሻግሯል።

ይህ ሁኔታ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ምርት ጋር ሲታይ አንድም የውጭ ባለሀብቶችን እንዳይመጡ ያደርጋል፥ በሌላ በኩል የባለሀብት መተማመንን ያጠፋል።

የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት፦ በሌላ በኩል ሀገሪቱ ለቀጣይ ሁለት አመታት ብድር ለመክፈል ስድስት ቢሊየን እንዲሁም፥ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ለሁለት አመታት ለማከናወን ደግሞ ሰባት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋታል።

ይህ በመንግስት በኩል የሚፈለግ ሲሆን እንደ ነዳጅና ሌሎች የፍጆታ ሸቀጦችን ማስገቢያና የሁሉም ዘርፍ ሲታይ ደግሞ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት እጅጉን ከፍ ያደርገዋል።

እንደ ስኳር ላሉ ፕሮጀክቶች የተወሰደው ብድር ደግሞ ወደ ምርት ሳይገባ እዳ መክፈያው ጊዜ ደርሷል፤ ኮሚሽነሩም እነዚህ ምክንያቶች ተደማምረው የፈጠሩት ችግር ለውሳኔው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

ዶክተር ይናገር እንደሚሉት ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችቷን በሚፈለገው ደረጃ ለማስቀጠል ጥረት አድርጋ ቢሳካላትም አሁን ላይ ግን መንገዳገድ ውስጥ በመገባቱ እርምጃው አስፈልጓል።

ሀገሪቱ እዚህ እጥረት ውስጥ የገባችው በግብርናና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ የታሰበው ባለመሳካቱ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ እነዚህን ለማስተካከል የረጅም ጊዜ አቅጣጫ ተቀምጧልም ነው ያሉት።

የአሁኑ እርምጃም የአጭር ጊዜ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፥ ኢኮኖሚው በቀጣይ አመታት በወጭ ንግድ አፈጻጸም ታግዞ እንዲቀጥል በተለይም ግብርናውን እና አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ለውጥ እንዲመጣ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

ላለፉት አመታት በጥሩ ሁኔታ የመጣውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ውድቀት ውስጥ እንዳይገባም የአሁኑ ፕራይቬታይዜሽን እንደ መፍትሄ መቀመጡንም አንስተዋል።

Addis Fortune wrote on several occasions about Ethiopia being exposed to massive corruption and courts quietly freezing the assets of some, but not of others — more conspicuous though!

High-level corruption & Ali Suleiman’s anti-corruption fables helped the thieves, not the nation!

Quoting the Auditor-General, Addis Fortune wrote in 2015/16  ‘illegitimate transactions close to 20 billion Br in 158 federal institutions during the 2015/16  fiscal year – over twice that of the gap seen in 2014/15’ was found and reported to parliament.

The Office of Attorney General kicked off an investigation of the institutions which were mentioned for audit gaps and arrested a dozen of individuals alleged for involvement in a corruption case. Given the magnitude of the theft and the individuals caught in the action, they were only given a slap on the wrist.

Recall that even the United States found itself in dilemma. It did not want to throw its ally to the crucifiers, when it established much of the aid it provides for HIV/aids cure was not also spared. On getting wind of this, on January 13, 2013, The Ethiopia Observatory

 (TEO) wrote about US slashing HIV/aids funding to Ethiopia by 79%.

The nation’s universities were also found among the culprits, according to Addis Fortune — the Auditor-General as its alibi.

In 2014-15, among the public universities, the Auditor-General exposed, Addis Ababa University (AAU), which took the lead with an audit gap of 1.2 billion Br. It was followed by Addis Abeba Science & Technology University (AASTU) and the University of Gonder with audit gaps of 472 million Br and 126 million Br, respectively.

Same time, Mekele University also had its share of irregularities in 2015/16, ranging 64 million birr.

In 2015/16, the Auditor-General came up with other shocking reports, according to the Reporter, the sum of which indicated:

“Ten missing cars and more than two billion birr unaccounted for. Lost, undocumented, misused, and damaged public properties. These were just some of the shocking facts revealed in the report of Gemechu Dubiso, Auditor General, on Tuesday in a presentation to Parliament. The concerns raised by Gemechu and the fact that it is getting from bad to worse had MPs irritated. Subsequently, MPs called for swift action” only to prove paper-tigers confronted by the TPLF.

የአሁኑ የኢትዮጵያ የኤኮኖሚና የገንዘብ ቀውስ ምክንያቶች የዕዳ ጫናና የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ብቻ አይመስሉንም!

ለዚህ ነው ባለፈው ሣምንት ኢሕአዴግ ያሣለፋቸውን የሃገር ንብረትና ጥሪቶችን ለሃራጅ ሺያጭ የማቅረቡ ጉዳይ የመጭውን ትውልድ ዕጣ ፈንታ አጉል እንዳያደርገው እሠጋለሁ! !

ውድ ማዕድናትና የውጭ ገንዘቦችን በሻንጣ እያስጭኑ ወደ ውጭ ሃገር ዘመዶቻቸውና ደንበኞቻችችድው ሲያሸጋግሩ የነበሩት እነማን እንደሆኑ የሕወሃት አገዛዝ ያውቃል! ለምን እነዚያ ግለሰቦችና ተባባሪዎቻቸው በዚህ ዐይነት ያሸሱትን ገንዘብ እንዲመልሱና — መንግሥትም ሂሣቡን ካሰላና ከተረከበ በኋላ —ምህረት አይሰጣቸውም?ለምን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብዬ ሳስብ፡ የሕወሃቶች ደባ እንዳይሆን እሠጋለሁ!

እግራቸው ገና አዲስ አበባን እንደረገጠ ነበር የኢትዮጵያን አየር መንገድ ከነስሙ ጭምር ስለጠመዱት፣ ‘የአፍሪካ ቀንድ አየር’ እንዲባል ሃሣብ እንደነበራቸው እስከ ኒውዮርክ ድረስ ይወራ እንደነበር አስታውሳለሁ!

ወደብ ያሣጧትን ሃገር የአየር በረራ ቢነሷት ያስገርማልን?

የመጀመሪያው አፈጉባዔ ያመጡት ታሊባንነት ነው የሚሉ የሕወሃት አፈ ቀላጤዎችን አባባል መስማቴንም አስታውሳለሁ!

ውዱና ድንቁ ቴዲ አፍሮ አለምክንያት እኮ አይደለም “ኢትዮጵያ” በተሰኘው አልበሙ፡የሚከተለውን ያንጎራጎረው፡-

የሰለሞን ዕጽ ነሽ የቅዱሳን ዕንባ ያበቀለሽ ቅጠል
ዛሬ አዲስ አይደለም በለኮስው እሳት የነካሽ ሲቃጠል…

በገንዘብ ዕጥረት ምክንያት፣ኢትዮጵያ መንግሥታዊ የዱቤ በጀት ልትጀምር ነው! ሕወሃት ሃገራችንን አከሠራት አይደል?

10 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሪፖርተር

ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ዘንድሮ መሰብሰብ አልተቻለም

የ2011 ዓ.ም. በጀት 59 ቢሊዮን ብር ጉድለት አለበት

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የገንዘብ እጥረት ቀውስ እንደገጠመው፣ እጥረቱ በፍጥነት መፍትሔ ካልተገኘለት ኢኮኖሚውን በመጉዳት ማኅበራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል መንግሥት በይፋ አስታወቀ፡፡

ይህንን የተናገሩት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ የፌዴራል መንግሥትን የ2011 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ሐሙስ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ክስተቱ መፈጠር ከጀመረ ረዥም ጊዜ ቢሆነውም ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግን የገንዘብ እጥረቱ ጎልቶ በመውጣት ወደ ኢኮኖሚ ቀውስነት የመሸጋገር አዝማሚያ እየታየበት መሆኑን፣ ሚኒስትሩ ካቀረቡት የበጀት መግለጫ ንግግር መረዳት ተችሏል፡፡

‹‹ከኤክስፖርት የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ደካማ በመሆኑ ለልማት የሚያስፈልጉ የካፒታል ጥሬ ዕቃዎች፣ እንዲሁም በአገር ውስጥ የማይመረቱ መሠረታዊ ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ፈታኝ ሆኗል፤›› ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያመነጨው የውጭ ምንዛሪ ደካማ ስለሆነ፣ የአገሪቱን ልማት ለማስቀጠል የውጭ ፋይናንስ በተለይም የውጭ ብድር ለማግኘት እንቅፋት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሚኒስትሩ ንግግር የሚያስረዳው አገሪቱ ከኤክስፖርት የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ አነስተኛ ስለሆነ፣ የውጭ ዕዳ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን፣ የአገሪቱ የብድር አጋር የነበሩ የውጭ መንግሥታትና ተቋማት ጭምር አዲስ ብድር ከመስጠት መቆጠብ መጀመራቸውን ነው፡፡

ሪፖርተር ያገኘው የሁለት ዓመት ተኩል የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዶክመንት እንደሚያስረዳው፣ መንግሥት በቀጥታ የተበደረው የውጭ ዕዳ ክምችት በዚህ ዓመት 24.75 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ በ2009 ዓ.ም. 13 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ አገሪቱ ስታገኝ የነበረው የውጭ ብድር በኢንቨስትመንትና ለኢንቨስትመንቱ በሚያስፈልገው ቁጠባ መካከል የሚታየውን ልዩነት ለመሸፈን ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ይህ የውጭ ብድር ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱና ከኤክስፖርት ይገኝ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ መጠን መጨመር ይቅርና በነበረበት ማቆየት እንኳን ባለመቻሉ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ ከታክስ ይገኝ የነበረው ቢሆንም በ2008 እና በ2009 ዓ.ም. እንደቅደም ተከተላቸው 15.2 እና 10.3 በመቶ ብቻ ማደግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በ2009 ዓ.ም. ታቅዶ ከነበረው የታክስ ገቢ 39 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንዳልተቻለ፣ ለዘንድሮው በጀት ዓመት ከታቀደው የታክስ ገቢ ደግሞ 50 ቢሊዮን ብር እንደማይሰበሰብ ከወዲሁ መታወቁን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የተነሳ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ወደ በ2011 ዓ.ም. እንዲሸጋገሩ መንግሥት መገደዱን፣ ይህ ሁኔታም በመንግሥት ላይ የበጀት ጫና መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የ2011 ዓ.ም. በጀት ሲዘጋጅ ከፍተኛ የበጀት አጠቃቀም ዲሲፕሊን ይኖራል በሚል መርህ የታክስ አሰባሰቡ ላይ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ በመገንዘብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሠረት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተለያዩ ዕቃዎችን ከውጭ በሚያስገቡ የመንግሥት ተቋማት ላይ መሰብሰብ የሚገባውን የጉምሩክ ታክስ በማስላት፣ ንብረቶቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው እንዲገቡ እንደሚያደርግ በረቂቁ የ2011 ዓ.ም. በጀት ላይ ተገልጿል፡፡ ባለሥልጣኑ ከአስመጪ የመንግሥት ተቋማት የሚጠበቀውን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የገንዘብ መጠን ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርና ለተቋማቱ እንደሚያሳውቅ፣ በዚህ መሠረትም ያልተከፈለው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የተቋማቱ ዓመታዊ በጀት አካል እንደሚሆን ተወስኗል፡፡ የ2011 ዓ.ም. በጀት 346.9 ቢሊዮን ብር ሆኖ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 59.3 ቢሊዮን ብር በአገር ውስጥ (የገንዘብ ኅትመትን ጨምሮ) የሚሸፈን እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከቀረበው የ2011 ዓ.ም. በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 91.7 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 113.6 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ 135.7 ቢሊዮን ብር ሆኖ፣ በዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚካተት ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ስድስት ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል፡፡

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ግዙፍ የልማት ድርጅቶችንና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በከፊልና ሙሉ በሙሉ ለግል ባለሀብቶች ለማዘዋወር ሰሞኑን የወሰነ ቢሆንም፣ የ2011 ዓ.ም. በጀት ግን ከእነዚህ ተቋማት የአክሲዮን ድርሻ የሚገኝ ገቢን አላካተተም፡፡ ረቂቅ በጀቱ ለተጨማሪ ዝርዝር ዕይታ ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

Ethiopia loosens throttle on many key sectors, but privatization still far off

6 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

“However, unless implemented with skill, knowledge and focus,” Abiy [Ahmed] said, “it can lead to a repeat of the pervasive theft seen in many African countries and a destruction of Ethiopia’s wealth.”

ADDIS ABABA (Reuters) Ethiopia’s decision to sell stakes in its lucrative telecoms monopoly and other assets could open one of the world’s largest untapped markets to huge potential investments by firms willing to work with a government still wary of private enterprise.

The stake sales are part of a raft of measures announced by Abiy Ahmed, a young former army officer who became prime minister in April, saying a new start was necessary to end crisis and chaos in a country of 100 million people, where some 40 percent are aged under 15.

While some fear Ahmed is moving too fast to challenge entrenched interests in his ruling EPRDF coalition, there is also hope across the region that his reforms will help ease crippling unemployment, foreign currency shortages and poverty.

The stake sales were announced on Tuesday, the same day Ethiopia said it would implement a 2000 peace deal with neighboring Eritrea and cede disputed territory on the border it has occupied for nearly 20 years[L5N1T75WX].

Companies have been waiting in the wings for Ethiopia to open its state monopolies and Tuesday’s news was welcomed.

South Africa telecoms group MTN told Reuters that it was excited by the potential opening up of the Ethiopian market “as it would be a natural fit for MTN’s existing pan-African footprint.” 

South African peer Vodacom said, “Vodacom has said on many occasions that Ethiopia is an attractive market so it follows that there would be interest. Naturally this is dependent on what might become available and if it fits within our investment parameters.”

It is unclear whether the government would consider licensing foreign mobile operators. Interest might be limited if the only option is a minority stake in the monopoly.

Analysts have said the government’s move falls far short of enabling full competition by multinationals. They note that by selling minority stakes the EPRDF is underscoring its view that the state should be a key player in the economy.

But the step is still radical for the EPRDF, in power since it took over from the communist Derg regime in 1991, and could indicate how 41-year-old Abiy plans to steer the country.

The economic reforms come two months after Abiy took power promising political changes to address roiling anger among young people over ethnic marginalization and unemployment.

The invitation to private investors to take shares in state companies including highly profitable Ethiopian Airlines is an acknowledgment the public sector alone could not provide adequate jobs or push export earnings higher, said one Addis Ababa-based analyst who spoke on condition of anonymity.

“There is a realization that you might need the private sector’s help,” he said.

In a statement issued Tuesday evening after a day-long meeting, the EPRDF’s executive committee said it recognized that economic reforms needed to be taken to sustain economic growth that has averaged near 10 percent for the past decade.

The statement referenced foreign exchange shortages that are draining shops of goods that suppliers cannot access hard currency to import. Foreign reserves are estimated by economists to cover less than two months’ of imports.

ECONOMIC TRANSFORMATION

The government has poured earnings from the national flag carrier and Ethio Telecoms into its infrastructure projects, part of an ambitious strategy to transform an agrarian nation into an industrialized one where the manufacturing sector provides large export earnings.

More revenues are needed, government spokesman Ahmed Shide told reporters after the coalition’s announcement.

Calling state-owned corporations a “huge source of wealth”, Shide said allowing private investors to buy shares “will enable us to generate even more wealth through them”.

But the morning after the premier himself suggested that, while the reforms are necessary, they come with risks.

“It is progressive. This new economic decision will afford us the opportunity to resolve widespread unemployment, ease foreign currency shortages, and reduce weaknesses in market connectivity,” Abiy said on Wednesday.

“However, unless implemented with skill, knowledge and focus,” Abiy said, “it can lead to a repeat of the pervasive theft seen in many African countries and a destruction of Ethiopia’s wealth.”

“The government is still deeply skeptical about capitalism and ‘speculative investors’”, said Charlie Robertson, global chief economist at Renaissance Capital, an emerging market investment bank.

Despite being Africa’s fastest growing economy, Ethiopia is a poor nation where GDP per capita is less than $800 per year and affordability of items like a smartphone is low.

The stakes sales also raise the question of what the government will do with the exchange rate. Foreign investors will want an easily convertible local currency. The Ethiopian birr is overvalued by at least 15 percent, according to the black market spread.

Still, there is undoubtedly huge untapped potential in the market given its size and under-served population, said Jacques Nel at research group NKC African Economics.

“Ethiopia remains a difficult place in which to do business, with inadequate infrastructure and opaque regulatory requirements, while the government remains deeply involved in most facets of the economy,” Nel said. “Foreign investors will still have to contend with these challenges.”

ሕዝብንና ሃገርን ባለዕዳ በሚያደርግ ሁኔታ ኤፈርት ከሕግ ውጭ ከወጭ ሃገር ባንኮች ብድር ሲወስድ መቆየቱ ይፋ ሆነ!

2 Jun

Posted byThe Ethiopia Observatory (TEO)

ይህንን ሁኔታ በማመቻቸት ለንግድ ባንክ ሃላፊዎች ትዕዛዝ ሲሰጡ የቆዩት የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ መሆናቸውም ተመልክቷል።

ይኽው ሕገ ወጥ ድርጊት በመቀጠሉ የኤፈርት ንብረት የሆነው አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና መውሰዱ ታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በሚሰጡት ትዕዛዝ  ኤፈርት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና ልዩ  ልዩ ብድሮችን ከውጭ ሃገራት  ለዓመታት ሲወስድ ቆይቷል።

ይህ በዋናነት ለመንግስታዊ ኩባንያዎች ብቻ የሚሰጠው ዋስትና ለኤፈርት ሲሰጥ የቆየው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በሥርዓቱ ውስጥ ባለው የበላይነት እና እንደ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ባሉ ለሕወሃት መሪዎች ታማኝ በሆኑ ግለሰቦች አማካኝነት እንደሆነም ተመልክቷል።

ለብድሩ የሚሰጠው ዋስትና ከኩባንያው ካፒታል ከ5 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት የባንኩ አሰራር ቢያስገድድም ፣ለሕወሃት ኩባንያዎች ለብድሩ መቶ በመቶ ዋስትና ሲሰጥ መቆየቱንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።

ይኽው ብድር በመቀጠሉ የአቶ መለስ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ኤፈርትን ከመልቀቃቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ለኤፈርቱ አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ መቶ ሚሊዮን ዶላር  ከቻይና ባንክ ብድር ተወስዷል።

ለዚህም እንደተለመደው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቶ በመቶ  ዋስትና ሰጥቷል።

Click to magnify

ኤፈርት የወሰደውን ገንዘብ ወደራሱ አካውንት ያስገባ አያስገባ እንደማይታወቅ  እንዲሁም ከብድሩ በፊት የሚያስፈልጉ የብድር ስምምነቶች እንደማይጠየቅም የኢሳት ምንጮች በዝርዝር ይገልጻሉ።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተወሰደና ባልተመለሰ 1.7 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ሕወሃት/ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ከተሞችን ሲቆጣጠር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከተለያዩ ተቋማት በተዘረፈ ገንዘብና ሃብት መቋቋሙ ይገለጻል።

ኤፈርት  በአሁኑ ወቅት እያንዳንዳቸው በቢሊዮን ብሮች ካፒታል የሚንቀሳቀሱ በርካታ ኩባንያዎች ባለቤትም ነው።

https://twitter.com/EthiObservatory/status/1002122847937064960?s=19

የቀድሞው የኤፈርት ሥራ አስፈጻሚ እና የሕወሃት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ከ 5 ዓመት በፊት በሰጡት ቃለምልልስ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በሃብት ኤፈርትን የሚያህል ኩባንያ የለም።

 

Amnesty requests Ethiopia to stop the murderous Liyu Police in its Somali Region!

1 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

The Ethiopian government must immediately withdraw and disband the Liyu police unit of the Somali regional state, whose members are unlawfully killing people in neighbouring Oromia region, Amnesty International said Thursday.

Members of the unit, set up by the Somali state as a counter-terrorism special force, this week burnt down 48 homes belonging to Oromo families who were living in Somali Region, forcing them to flee to Kiro in the regional state of Oromia.

The Ethiopian authorities must immediately demobilize the Liyu unit and replace them with police that abide by international human rights law. These rogue officers must not be allowed to brutalize people at will.

Joan Nyanyuki, Amnesty International Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes says: 

“The Ethiopian authorities must immediately demobilize the Liyu police and replace them with police that abide by international human rights law. These rogue officers must not be allowed to brutalize people at will.”

On 23 and 24 May the unit also attacked four neighborhoods in the Chinaksen district of East Oromia, killing five farmers and burning down around 50 homes. These attacks caused residents to flee their homes looking for safety.

“The authorities must put an end to what appears to be state-sanctioned violence. The first step is to ensure all policing in Oromia is respectful of human rights. The next is to hold those responsible for these attacks to account through thorough, impartial and independent investigation.”

In 2017, incursions into Oromia by the unit led to the deaths of hundreds and the displacement of more than one million, according to a report by Ethiopia’s National Disaster Risk Management Commission and the United Nations Office for the Coordination of Humanitarian Affairs.

Amnesty International is calling on the Ethiopian authorities to implement the recommendations of the 2004 referendum, which voted for a clear demarcation of the Oromia-Somali border, as a means of addressing the root causes of tensions in the region.

In Amharic from BBC Amharic:

መንግሥት ልዩ ፖሊስን እንዲበትን አምነስቲ ጠየቀ!

በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ይፈፅማል ያለውን የልዩ ኃይል ፖሊስን መንግሥት እንዲበትን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጠው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

አምነስቲ እንዳመለከተው በአጎራባች የኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመግባት ግድያን ይፈፅማሉ ያለቸውን የሶማሌ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይልን የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያስወጣና እንዲበትን ጠይቋል።

በሶማሌ ክልል የፀረ-ሽብር ልዩ ኃይል ሆኖ የተቋቋመው የዚህ ቡድን አባላት በዚህ ሳምንት በሶማሌ ክልል ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን 48 ቤቶች በማቃጠል ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲሸሹ ማድረጉን ጠቅሷል።

መግለጫው ጨምሮም የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን የልዩ ፖሊስ ክፍልን በአስቸኳይ በመበተን ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎች ተገዢ በሆነ የፖሊስ ኃይል እንዲተካም ጠይቋል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሃይቆች ዳይሬክተር የሆኑት ጆዋን ኒያኑኪ እንዳሉት “የልዩ ኃይሉ አባላት እንደፈለጉ በህዝብ ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ መፈቀድ የለበትም” ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት ልዩ ኃይሉ በምሥራቃዊ ኦሮሚያ ጭናቅሰን ወረዳ ውስጥ በሚገኙ አራት መንደሮች ላይ በፈፀመው ጥቃት 5 አርሶ አደሮች ሲገደሉ 50 የሚጠጉ ቤቶች በእሳት ተቃጥለዋል።

በዚህም ሳቢያ ነዋሪዎች ነፍሳቸውን ለማትረፍ መኖሪያቸውን ጥለው መሄዳቸውን የአምነስቲ ሪፖርት አመልክቷል።

“የመንግሥት ባለሥልጣናት ይህ ጥቃት እንዲያበቃ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ያሉት ጆዋን ኒያኑኪ “ለዚህ ደግሞ የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት ፖሊስ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብር ማድረግና በጥቃቱ ተሳታፊ የሆኑትን በነፃና ገለልተኛ ምርመራ በመለየት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

ልዩ የፖሊስ ኃይሉ ባለፈው ዓመት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞትና ከአንድ ሚሊዮን ለሚልቁ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማጠቃለያው በአካባቢው ላለው ውጥረት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት፤ የኦሮሚያንና የሶማሌ ክልሎችን ድንበር ለይቶ ለማስቀመጥ በ1996 በተካሄደውን ህዝበ-ውሳኔ የተገኘውን ውጤት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ይህንን ሪፖርት ተከትሎ የኢትዮጵያን መንግሥት ባለሥልጣናትን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

 

%d bloggers like this: