Tag Archives: ethiopian human rights commission

ኮቪድ-19ና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸምና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በኢትዮጵያ

27 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የኮቪድ-19 ወረርሸኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በኢትዮጵያ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ማስፈጸሚያ ደንብ በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተከናወነ የሕግና ሰብዓዊ መብቶች ትንተና

ግንቦት 2012
***********************************************************************

Legal/Human Rights Analysis of the Declaration of State of Emergency in Ethiopia in the Context of the COVID-19 Pandemic
7 May 2020
***********************************************************************

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመቆጣጠር መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀ ሲሆን ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን ተቀብሎ አፅድቋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አውጥቷል፡፡ ኢሰመኮ የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የማስፈፀሚያ ደንብ የግድ የሚያስብል አንገብጋቢ የማህበረሰብ ጤና ጉዳይ መኖሩን እና ይህም አካሄድ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን በይፋ በሕግ እንዲታወጅና ሕግን መሠረት አድርጎ እንዲተገበር ከሚያዘው የሕጋዊነት መርህ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ይገነዘባል፡፡

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ባደረገው ጥናት የተወሰኑ የአስቸኳይ ጊዜ ደንቡ ድንጋጌዎች ከኢፌዲሪ ሕገ መንግስትና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መርሆች ጋር የማይጣጣሙ ሆነው በመገኘታቸው፤ ከሕገ መንግሥቱና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ እንደገና እንዲመረመሩና ተገቢው ማሻሻያ እንዲደረግ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና ደንቡ የሚመነጩ አንኳር ስጋቶች እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊና ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች መርሆችን ሳይሸራረፉ ለማረጋገጥ አበርክቶ ያላቸው የኮሚሽኑ ምክረ ሀሳቦች የተካተቱበትን ሙሉ የሕግና የሰብዓዊ መብቶች ትንተና ሰነድ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ለማግኘት ከታች የተመለከተውን ማስፈንጠርያ ይጫኑ፡፡

ማስታወሻ፡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ በኮሚሽኑ በተዘጋጀዉ የሕግ ትንተና እና ምክረ ሃሳቦችን አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የማስፈፀሚያ ደንቡ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 93ን መሰረት በማድረግ እንዲሁም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 93 /4/ ሐ ስር እና ሀገሪቱ ፈርማ ባፀደቀቻቸው የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ የማይታገዱ (non-derogable) ናቸዉ ተብለው የተጠቀሱትን መብቶችና ነፃነቶች በማይጥስ መልኩ እና ወረርሽኙን ለመከላከል እና እንዳይስፋፋ ለማድረግ የሚያግዙ እርምጃዎችን ብቻ መሰረት በማድረግ የወጡ እንደሆኑ አስረድቷል። በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎቹ ዋነኛ አላማ መብቶችን ለመገደብ ሳይሆን “የመብቶች ሁሉ እናት የሆነውን በህይወት የመኖር መብት ለማስጠበቅ እና በዚህም እነዚህን እርምጃዎች ሳንወስድ ብንቀር ሊከሰት የሚችለውን ሌሎች በርካታ የዜጎች መሰረታዊ መብቶች የሚጣሱበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመከላከል እና ለማስቀረት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል” በሚል ገልጿል።

Legal/Human Rights Analysis of the Declaration of State of Emergency in Ethiopia in the Context of the COVID-19 Pandemic (7 May 2020)

On 8 April 2020, the Ethiopian Government declared a national state of emergency to combat the spread of the COVID-19 pandemic and the Federal House of Peoples’ Representatives approved the state of emergency proclamation on 10 April 2020. The Council of Ministers has subsequently issued the Regulation to implement the state of emergency. EHRC recognizes the public health emergency needs for the issuance of the State of Emergency Proclamation and Regulation by the Ethiopian Government which is also consistent with the principle of legality that any such emergency powers should be officially declared and exercised in accordance with the law.

On the other hand, a study by EHRC has identified some provisions of the Emergency Regulation which are inconsistent with the Constitution and international human rights standards and need to be considered for review and possible amendment with a view to ensuring their full compatibility with the Constitution and international human rights standards.

Click on the link below to download Amharic and English versions of the full analysis outlining key human rights concerns arising from the State of Emergency Proclamation and Regulation as well as EHRC’s recommendations.

Note:

In response to EHRC’s analysis and recommendations, the Office of Federal Attorney General explained that the state of emergency was proclaimed in accordance with Article 93 of the FDRE Constitution and in a manner that does not impinge on the rights and freedoms that are not subject derogations under Article 93 (4) (c) and human rights treaties ratified by Ethiopia and based solely on measures that are meant to prevent and control the spread of the pandemic. Furthermore, it stated that the primary purpose of the emergency measures is not to restrict rights, but to “protect the right to life which is the mother of all rights and to prevent the infringement of many other fundamental human rights that would otherwise occur if [government] failed to take these actions.”

 

 

/  Ethiopian Human Rights Commission

 

 

 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና በሰብዓዊ መብቶች መስክ የሚሠሩ የሲቪል ማኅረሰብ ድርጅቶች ኅዳር 30/2012 በጋራ የሠጡት መግለጫ

12 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከኮሚሽነር ዳኒኤል በቀለ ፌስቡክ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እኤአ ዲሴምበር 8 ቀን 1948 ሁሉ አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ (Universal Declaration of Human Rights (UDHR) ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

ሰብዓዊ መብቶችን በሚመለከት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እንደመለኪያ የሚያገለግለው ይህ ሠነድ፣ የሰው ልጆችን የማይገሰስ ክብር ዕውቅና የሠጠ ሲሆን እነዚህም መብቶች ለዓለም ፍትህ፣ ነጻነትና ሠላም መሠረቶች ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

በሁሉ አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 2 ላይ ማንም ሰው በዘር፣ በሃይማኖት፣ ጾታ፣ ቀለም፣ ቋንቋ፣ እምነት፣ ፖለቲካዊ አቋም፣ ማህበራዊ መነሻ፣ ዜግነት ወይም ሌላ ማናቸውም ምክንያት ያለምንም ልዩነት ሁሉንም መብቶችና ነጻነቶች የተጎናጸፈ መሆኑንም ዕውቅና ይሠጣል፡፡

Continue reading

“በተከሰተው ሁከት በቀጥታ/ተዘዋዋሪ በጥፋቱ ተሣታፊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ አለበት!”—የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን!

30 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“ለዚህ ውዝግብ መነሻ በሆነው ጉዳይ ላይ በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የሚሹ ሰዎች ቢኖሩም ሁከት የቀሰቀሱ፣ የፈጸሙና ያስፈጸሙ እንዲሁም ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ድጋፍ የሰጡ ሰዎች መኖራቸው ግን አይካድም”

“በተከሰተው ሁከት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በጥፋቱ ተሣታፊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ አለበት!”

በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥና ተሃድሶ እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች እንዳስገኘ ሁሉ ውስብስብ ተግዳሮቶችም እየገጠሙት ይገኛል፡፡

በተለይ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀሰቀሰው ውዝግብና ሁከት የተሞላ ነውጥ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ከመጥፋቱ፣ የአካል ጉዳት ከመድረሱ፣ ንብረት ከመውደሙና የሰዎች መደበኛ ኑሮና ሰላማዊ ሕይወት ከመረበሹ በተጨማሪ፤ የሕግ በላይነትን በእጅጉ የተፈታተነና መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ከፍተኛ አደጋና ሥጋት ላይ የጣለ እጅግ አሳሳቢ ክስተት ነበር፡፡

በዚህ ሁከት ምክንያት ከሚዲያዎች ዘገባ መሠረት እስከ አሁን ባለው መረጃ ከ70 – 80 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ አስር ያህሉ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት በጥይት ተመተው የሞቱ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሰዎች በሁከቱ ተሳተፉ ሰዎች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ በግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በዱላ በድንጋይና በስለት ተደብድበው እንዲሁም በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚገመት የግለሰቦች፣ የሕዝብና የአገር ንብረት ወድሟል፡፡ እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት ሆን ተብሎ በተፈጸመ ጥቃት ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ማናቸውም ዐይነት ቅሬታ ወይም ጥያቄ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ሊቀርብ የሚችልበት ምቹ ሁኔታ መኖሩ ይታመናል፡፡

ለዚህ ውዝግብ መነሻ በሆነው ጉዳይ ላይ በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የሚሹ ሰዎች ቢኖሩም ሁከት የቀሰቀሱ፣ የፈጸሙና ያስፈጸሙ እንዲሁም ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ድጋፍ የሰጡ ሰዎች መኖራቸው ግን አይካድም፡፡

ማናቸውንም ዓይነት ቅሬታና ጥያቄ በአመፅ እና በእልቂት ማስፈራሪያ ለማስፈፀም የታየው ተግባር እና የአስከተለው ጉዳት የሕግ የበላይነትን፣ የአገር ሰላም እና ሥርዓትን በአደባባይ በመገዳደርና በመጣስ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ያስከተለ በመሆኑ በየደረጃው በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በጥፋቱ ተሣታፊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡

ይህን ጥፋት የፈፀሙና ወይም የጥፋቱን ተግባር እንደ መልካም ሥራ ያወደሱ ሰዎች ሁሉ በዱላና በስለት ተደብድበው በእሳት ተቃጥለው የተገደሉ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸውን ለአፍታ እንኳን በእራሣቸውና በቤተሰቦቻቸው ተክተው አለማሰባቸው የደረሰውን ጉዳት ይበልጥ መሪር አድርጐታል፡፡

የድርጊቱ ተሳታፊዎች በደረሰው ጥፋት ማዘን መፀፀትና ለሕግ የበላይነት መከበር የመተባበር ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው፡፡

መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎችን በሕግ ፊት ለማቅረብ ሳያወላውል እንደሚሠራ መግለጹ ተገቢ ሲሆን፤ ይህ የመንግሥት ኃላፊነትና ተግባር በስልታዊ የምርመራ ሥራና በሕጋዊ ሥርዓት በአፋጣኝ በሥራ ላይ ሊውል ይገባል፡፡

ከዚህ በመቀጠል ለሚደረገው የወንጀል ምርመራ ሥራ ማንኛውም ሰው በመተባበርና ውጤቱን በትዕግስት በመጠባበቅ፣ በየአካባቢው የተጐዱ ሰዎችንና ቤተሰቦችን በማጽናናት በመደገፍና በመጠገን፤ እንዲሁም የመንግሥት፣ የፖለቲካና የልዩ ልዩ ቡድኖች መሪዎች የፖለቲካ ውጥረቱን ከሚያባብሱ ቆስቋሽ ንግግሮችና ድርጊቶች እራሳቸውን በመቆጠብ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈንና ሰብዓዊ መብቶች ሁሉ እንዲከበሩ የሚደረገውን ጥረት ማገዝና ይህን የመሰለ ጥፋት ዳግም እንዳይፈጸም የሚመለከታቸው አካሎች ሁሎ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሊሰሩ ይገባል፡፡

 

 

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ከሰኔ ባሕር ዳርና አዲስ አበባ ግድያዎች ጋር በተያያዘ እሥር ላይ ያሉት ጋዜጠኞችና የዐብን አባሎች ከሕግ ውጭ መታሠራቸውን ገለጹ!

25 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሺነር ዶር ዳንኤል በቀለ ሕግ ከሚፈቅደው ውጭ ታሥረው የሚገኙ ሰዎች በዋስ ወይንም ያለ ዋስትና እንዲለቀቁ ይገባል አሉ፡፡

 

 

አንዳንድ ተጠርጣሪዎች በእሥር የቆዩበት ጊዜ አሳሳቢ መሆኑንና አፋጣኝ እልባት ማግኘት እንዳለበትም ዶር ዳንኤል በቀለ ገልጸዋል።

ካለፈው ሰኔ ባሕር ዳርማ አዲስ አበባ ጋር በተገናኘ የታሠሩትንና እያንዳንዳቸውን የፖለቲካ እሥረኞች መሆን ላይ የደረሱትን ጎብኝተው በስም እየጠሩ እንዳግባቡ እንዲለቀቁ ጠየቁ!

TPLF crackdown on protest claimed hundreds of lives: It must free wrongfully held detainees; independent inquiry needed

16 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Human Rights Watch
 

“Ethiopian security forces have fired on and killed hundreds of students, farmers, and other peaceful protesters with blatant disregard for human life.”

–   Leslie Lefkow, deputy Africa director
 

(Nairobi) – Ethiopian security forces have killed more than 400 protesters and others, and arrested tens of thousands more during widespread protests in the Oromia region since November 2015. The Ethiopian government should urgently support a credible, independent investigation into the killings, arbitrary arrests, and other abuses.
Continue reading

%d bloggers like this: