Tag Archives: External debt

በኢትዮጵያ ዕዳ ላጎበጠው ኢኮኖሚ የታሰቡ ለውጦች—’ልፋ ያለው…’

22 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(በዚህ ገጽ አዘጋጅ የሪፖርተር ዘገባ ላይ የተጨማመሩበት አሉ)!

የኢትዮጵያ መንግሥትና የልማት ድርጅቶቹ ከአገር ውስጥና ከውጭ ምንጮች የተበደሩት የገንዘብ መጠን በጠቅላላው 1.5 ትሪሊዮን ብር ገደማ መድረሱ በተዘገበ ማግሥት፣ የገንዘብ ሚስቴርም ስለዚሁ ጉዳይ በሳምንቱ መጨረሻ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በተሸኘው በጀት ዓመት የገንዘብ ሚኒስቴርን የ12 ወራት አፈጻጸም በማስመልከት የተሰጠው መግለጫ አንደኛው ቅኝቱ ይኼንኑ አገሪቱን የዕዳ ክምር የተመለከተ ነበር፡፡ በመሆኑም በ2011 ዓ.ም. ብቻውን ከ368 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 13 ቢሊዮን ዶላር ገደማ  ገንዘብ ማዕከላዊው መንግሥት ስለመበደሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህ የብድር መጠን በ2010 ዓ.ም. ከነበረው የ3001 ቢሊዮን ብር በ22.3 በመቶ ወይም የ67 ቢሊዮን ብር ዕዳ ጭማሪ አለው፡፡ ይህ የብድር ዕዳ መጠን ከአገር ምንጮች በተለይም ከመንግሥት ባንኮች በቀጥታ እንዲሁም ከቦንድ ሽያጭና ከመሳሰሉት የተበደረው የገንዘብ መጠን ነው፡፡

ማዕከላዊው መንግሥት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በነበረው አንድ ዓመት ውስጥ ከውጭ በአዳሪዎች 16 ቢሊዮን ዶላር ወይም 475 ቢሊዮን ቢሊዮን ብር መበደሩ ሲገለጽ፣ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሩ በጠቅላላው ከ830 ቢሊዮን ብር በላይ አሻቅቧል፡፡

ከማዕከላዊው መንግሥት ባሻገር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በዓመቱ የተበደሩት ብድር መጠን ወደ 407.5 ቢሊዮን ብር ማሻቀቡ ተወስቷል፡፡ ይህም በ2010 ከነበረው የ344 ቢሊዮን ብር ዕዳ አኳያ ከ63 ቢሊዮን ያላነሰ ጭማሪ የተመዘገበበት ሆኗል፡፡ በአቶ ሐጂ አኃዞች መሠረት ከታየ የማዕከላዊው መንግሥትና የልማት ድርጅቶቹ በጠቅላላው ከ1.2 ትሪሊዮን ብር በላይ የተከማቸ ብድር አስመዝግበዋል፡፡ እንደ አቶ ሐጂ ገለፃ፣ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ የአገሪቱ የወጪ ንግድ አፈጻጸም በማሽቆልቆል ላይ ይኛል፡፡

እያየለ በመጣው የብድር ዕዳ ጫና ሳቢያ መንግሥት የልማት ድርጅቶቹን ጨምሮ ሌሎችም መንግሥታዊ ተቋማት፣ ከፍተኛ ወለድ የሚታሰብበትና በአመዛኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከፈል (የንግድ ብድር ወይም ኮንሴሽናል ሎን) ውስጥ ብድር እንዳይወስዱ የብድር መመርያ በማዘጋጀት ቁጥጥር መጀመሩም ተጠቅሷል፡፡ ምንም እንኳ ይህ ይባል እንጂ የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የአጭር ጊዜ ብድር ለማቆም የገባውን ቃል በማጠፍ ከአንድ ሁለት ጊዜ ይህን መሰል ብድር ውስጥ ሲገባ መታየቱን ይፋ እንዳወጣ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ይህም ሆኖ አዲሱ አስተዳደር ከመምጣቱ በፊት ጀምሮ የአገሪቱ የዕዳ ጫና እያየለ በመምጣት ከዝቅተኛ የዕዳ ሥጋት ወደ ከፍተኛ ሥጋት የተሸጋገረችበት ደረጃ ላይ ስትደርስ አዲሱ አስተዳደርም ሥልጣኑን ከነዕዳው ተረክቧል፡፡ ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ አገሪቱ የዕዳ ጫና ተጋላጭነት ዝቅተኛ በሚባለው ደረጃ ላይ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሐጂ፣ ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ውስጥ መካከለኛ የሚባል የዕዳ ጫና ሥጋት ቀለበት ውስጥ ስትዋልል ቆይታ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮም ከፍተኛ የሚባለው የዕዳ ጫና ሥጋት ርከን ላይ መንሳፈፍ እንደጀመረች ካቀረቡት አኃዝ ለመረዳት ተችሏል፡፡ለመሆኑ የዕዳ ጫናው በምን ምክንያት እንዲሀ ጀርባ አጉባጭ፡ አህኑን ደግሞ መንፈስ ሠባሪ የሆኑበት ምክንያቶች ይታወቃሉን?

ሁለቱ ታዋቂዎቹ የ MIT ኤክስፐርቶች Daron Acemoglu & James Robinson (የWhy Nations Fail: The Origins of Power, Prosperity and Poverty ደራሲዎች) እንዳስተማሩን ችግሩን ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ አብጠርጥሮ ማወቅ ይቻላል!

ለመሆኑ የዕዳ ጫናው በምን ምክንያት እንዲሀ ጀርባ አጉባጭ፡ አህኑን ደግሞ መንፈስ ሠባሪ የሆኑበት ምክንያቶች ይታወቃሉን?

የመንግሥት ባለሥልጣኖችና መዋቆሮቻቸው አውቀናል ብለው ልባቸው ውልቅ ብሏል። ዕዳው ግን ከ2006 ወዲህ በየዓመቱ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መህኑን እነርሱም ይመሠክራሉ!

እነዚህ ሁለቱ ምሁራን Daron Acemogluና James Robinson የኢትዮጵያን የኢኮኖሚና የሰው ልማት ችግሮቹን እንዲፈትሹት ቢጋበዙ፣ ዐይነ ሥጋቸው ወደ Nogales Sorona, Mexico ከንፎ የኛንም ችግር ከሃገሪቱ ፖለቲካ ጋር ያይዙት ይሆናል ብዬ ገምታለሁ!

በሃገራችን ዕዳ መከፍል የሃገሪቱ አቅም የተሰለበው ከ2006 ጀምሮ ነው! ከዓመት በፊት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በእረመኔው መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ መታረዳቸው ማግሥት መሆኑ ይታወሳል።

ስለ Nogales ለሁለት መከፈል (Nogsles Arizona) መበልጸግና፣  ስለ Nogales Sorona, Mexico) አዘቅት መውረድ ምክንያት መጽሐፋችው ውስጥ እንደተረቡት፡ ኢትዮጵያ ውስጥም የ2005 ምርጫና ቀጥሎም የሃገሪቱን ፖለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተበላሽቶ ማረፉን እነዚህ ሁለት ምሁራን ያሠምሩበት ነበር። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜም በኢትዮጵያ ሕዝብና ሕወሃት መካከል በጦርነት እስከመፈላለግ ዘልቆ፡ ኋላም ሕወሃት በሽንፈት ሸሽቶ ልክ እንደሲሲሊ የመጨረሻ ምሽጉን መቀሌ ለማድረግ ተገደደ!

በወቅቱ ጣልያን የነበራት የቤኒቶ ሞሶሊኒ መንግሥት ሃገሪቱን ልዕልና ሲሲሊ ውስጥ ከመሸጉት ወንበዴዎች ጋር መካፈል እንደማይሻ (በሃገር አስተዳደር ሚኒስትሩ Luigi Federzoni) በኩል በ ሰኔ ወር 1924 የሚከተለውን ቴሌግራም አስተላለፈ “Your Excellency has carte blanche, the authority of the State must absolutely, I repeat absolutely, be re-established in Sicily. If the laws still in force hinder you, this will be no problem, as we will draw up new laws.”

ይህን ተከትሎ በአምስት ዓመት ሲሲሊ ውስጥ 11,000 ተጠርጣሪዎች ወድያውኑ ታሠሩ፤ 1,200 ተፈርዶባችው ታሠሩ፤ አያሌዎች ኢጣልያን ለቀው ተሠደዱ!

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያሉንን ምርቶች ለገበያ ማቅረብ አቅቶን ሃገሪቱ ያገኘችው የውጭ ንግድ ገቢ በዚህ ዓመት ወደ $2.1 ቢሊዮን አዝቅጧል! ለጊዜው በተሸፋፈነ አባባል ቄሮ/ኢጄቶ/ፋኖ…ምክንያት ተደረገ፤ አሁንም ራሳቸውን እንደመንግሥታዊ ኃይል የሚመለከቱ ጎረምሶች መንግሥት ሆነዋል! ዐቢይም ከነርሱ ጋር ሥልጣን መጋራቱን አልተቃወመም! አልፎ አልፎ መደምሰስ የሚፈልጋቸው ኃይሎች ሲነሡ፣ ቄሮን እንደሚልክባቸው በእስክንድር ነጋ ላይ በተደጋጋሚ የተፈጽመውን የሚያስታውሱ፣ እንዴት ወንጀለኛን እየተጠቀሙ፡ ወንጀልን መጸየፍ እንደሚቻል እያሰቡ ይገረማሉ!

ፖለቲካችን አሁንም ከባድ ችግር ላይ ነው!


የአገሪቱን የዕዳ ጫና ካባባሱት መሠረታዊ ምክንያቶች ውስጥም የውጭ ምንዛሪ ምንጮች ከሆኑት ዋነኛው የወጪ ንግዱ ዘርፍ ሲሆን፣ አቶ ሐጂ በጠቀሱት አኃዝ በ2011 ዓ.ም. ከዘርፉ የተገኘው ጠቅላላ ገቢ 2.34 ቢሊዮን ዶላር፣ ንግድ ሚኒስቴር በሚጠቅሰው አኃዝ 2.67 ቢሊዮን ዶላር (ከሁለት የአንዳቸውን አኃዝ እንዳስፈላጊነቱ መጠቀም ነው) ተመዝግቧል፡፡ የወጪ ንግዱ በየጊዜው እያሽቆለቆለ መጥቷል፡፡ እንደ አቶ ሐጂ ገለጻ ከሆነም፣ የአገሪቱ የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በማሽቆልቆል ላይ ይገኛል፡፡ የወጪ ንግዱን መዳከም የሚያባብሰውም የአገሪቱ የወጪ ምርቶችና ሸቀጦች እንደሚፈለገው በጥናትና በብዛት አለመመረታቸውም ነው፡፡

በተለይ የፖለቲካው ቁርሾና የእርስ በርስ ግጭቱ ያስከተላቸው ውጥንቅጦች ምርት ወደ ገበያ እንዳይወጣ እክል በመፍር፣ መንገዶችን በመዝጋት፣ አምራች ፋብሪካዎችን በማቃጠልና በመሳሰሉት ጥፋቶች ሲታመስ የቆየው የወጪ ንግድ ዘርፉ፣ ይባሱን እየተስፋፋ በመጣው የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ከዋጋ በታች በመሸጥና ወጪን በማናር (አንደር ኢንቮይሲንግ፣ ኦቨር ኢንቮይሲንግ) አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገቢ የሚያሳጡ ሕወገጥ ተግባራት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ይህንን የሚያረጋግጠው በቅርቡ የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው መረጃ ነው፡፡

በ2011 ዓ.ም. ብቻ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሸቀጦች በኮንትሮባንድ መያዛቸውን ሚኒስትሯ አዳነች አቤቤ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ያልተደረሰባቸውና ያመለጡ ቢሊዮኖችን ከመገመት በቀር በአኃዝ አስደግፎ የሚያጣቅስ መረጃ ማግኘት አዳጋች ቢሆንም፣ በተለይ በቁም እንስሳት ሕገወጥ ንግድ የሚታጣው፣ በወርቅና በሌሎች ማዕድናት የሚፈልሰው የአገሪቱ ሀብት የትየለሌ መሆኑ ይነገርለታል፡

የመንግሥት ዕዳ የሚያከብደው ሌላው ጫና የወጪ ንግዱ ማሽቆልቆሉ ብቻም ሳይሆን፣ የተቆለለውን ዕዳ ለመክፈል የሚደረገው መፍጨርጨርም ነው፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት 16 ቢሊዮን ብር መክፈሉንና በአዲሱ በጀት ዓመትም ከ22 ቢሊዮን ብር ዕዳ ለመክፈል መታቀዱ ነው፡፡ የተከማቸውን ዕዳ በዚህ መልኩ ለመክፈል የወጪ ንግዱ የሚኖረው ድርሻ የማይናቅ ነው፡፡ የምርት አቅርቦት እንደሚፈለገው መጠን አለመጨመር፣ የሕዝብ ቁጥር መብዛትና የንግድ ዘርፉ የሚታይበት ጉድለቶች ተጨማምረው የዋጋ ግሽበት እየተባባሰ እንዲመጣ አድርገዋል፡፡


ADDIS FORTUNE June 8 , 2019:

Debt Service Falls Short of Target by 33pc

Ethiopia has serviced 9.4 billion Br of external debts in the first 10 months of the current fiscal year, achieving 66pc of its plan. The country’s total external debt stands at 27 billion dollars. The federal government owes 15.8 billion dollars, while the rest, 11.2 billion, is owed by state enterprises. The government’s internal debt currently stands at 731 billion Br. The federal government owes 344 billion Br in internal debt, while state enterprises owe 387 billion Br. The government has also managed to get relief from debt interest from Chinese financial institutions, following a debt restructuring and extension of grace and repayment periods, according to Ahmed Shide, minister of Finance. The minister also disclosed that the country planned to get four billion dollars from international partners and foreign governments in the form of loans and grants but could manage to reach 3.5 billion dollars of it in the reported period.


መንግሥትም የዋጋ ግሽበቱ የሚያመጣውን ጫናና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሙሉ ለሙሉ ባይቀርፍም ከውጭ ስንዴና ሌሎችም የምግብ ሸቀጦችን በማስገባት ቢያንስ ታችኛው የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሕዝብ ለመታደግ ሲሞክር ኖሯል፡፡ በዚህ ዓመትም በተለይ እስከ ነሐሴ መጨረሻ ድረስ ተጓጉዞ የሚገባ 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ እየተጠበቀ እንደሚገኝ አቶ ሐጂ ገልጸዋል፡፡ ለመጪው ዓመት ከሚፈጸመው ግዥ ውስጥም እስከ ኅዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ተጓጉዞ የሚገባ ተጨማሪ ሚሊዮን ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለመግዛት ከወዲሁ ጨረታ መውጣቱንም አስታውቀዋል፡፡

የመንግሥትን የዕዳ ጫና ያበራከቱት ሌሎችና አነጋጋሪዎቹ ችግሮች መንግሥት ከአቅሙ በላይ የጀመራቸው የልማት ፕሮጀክቶች ያስከተሉት ኪሳራ ነው፡፡ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ያስወጡት የስኳር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በርካቶቹ የልማት ሥራዎች በመጓተታቸውና በሚፈለገው የጥራትና የብቃት ደረጃ ባለመግባታቸው ሕዝብም መንግሥትም ለችግር ተጋልጠዋል፡፡ በገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ መሠረትም፣ ከሁለት እስከ ሰባት ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የተጓተቱ 1,000 ፕሮጀክቶች በትንሹ የ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪና ኪሳራ አስከትለዋል፡፡

እንዲህ ያሉ ቀውሶችን ለመከላከል የተነሳው መንግሥት፣ በሁሉም መስኮች የሪፎርም ፕሮግራሞች ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ አዋጭነታቸው ችግር ያለበትን ጨምሮ ከፍተኛ ገቢ ሊያስገኙለት እንደሚችሉ ያመነባቸውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉም በከፊልም ለመሸጥ ከወሰነ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ግብርናው ባሉ መስኮች የመስኖ እርሻ በማስፋፋት፣ በተለይ በቆላማ አካባቢዎች ሰፋፊ እርሻዎችን በማልማት ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት ለማስቀረት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገውም እንደ አፋርና ሶማሌ ባሉት ክልሎች የሙከራ ምርት ተጀምሯል፡፡ ከ3,000 ሄክታር ያላነሰ መሬት በስንዴ ምርት መሸፈኑ ሲገለጽ እንደነበርና ይህም ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ የአገሪቱን የስንዴ ጥገኝነት ከውጭ ለማላቀቅ ተስፋ መስጠቱን ሚኒስቴሩ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ባሻገርም በቱሪዝም መስክ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በሥነ ጥበብና ኪነ ጥበብ መስክም መንግሥት ያሰባቸው ሥራዎች ለአገሪቱ የለውጥ ጉዞ ተስፋ የተሰነቀባቸው እንደሆኑ ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የ‹‹አዲስ ወግ›› የወይይት መርሐ ግብር ላይ ተጠቅሷል፡፡

/ ሪፖርተር

 

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለፓርላማ ያቀረቡት የመጀመሪያው ግልፅና አስገራሚ ሪፖርት!

18 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

የኢትዮጵያ ዕዳ መሸከም ጫናና ወለድ የመክፈል አቅም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል!

15 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማበር 

ከሳህራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት የዕዳ ጫናቸው እያደረ ወደ ሰማይ መጥቶል ምክንያቱም ከፍተኛ ብድርና ያጋጠማቸውን ኪሳራና እጥረት ለመሸፈን ሲሉ በእዳ ይዘፈቃሉ ምንም እንኮን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት እያደረጉም ቢሆን ይላል ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት፡፡ የአፍሪካ አገራት ከዓለም ዓቀፍ የብድር ገበያ ብድር ማለብ ቀጥለዋል እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ብድር ሪከርድ ሰብረዋል ባልተረጋጋው የኢንቨስተሮች ፍላጎት ለቀጣይ ምርት ሂደት፡፡  የዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዴሬክተር አበበ ዓዕምሮ ስላሴ ለሮይተር እንደገለጡት ድርጅቱን ያሳሰበውና የእዳው ጫና የእድገቱ ጭማሪ ከአማካዮ በላይ መሆኑ ነበር፡፡ ድርጅቱ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት 3.4 ከመቶ በ2018እኤአ ሲገመት በ2017እኤአ ከነበረው 2.8 በመቶ ዓለም ኣቀፍ እድገት የምርት ዋጋ መጨመር እንደሚኖር ገልፀዋል፡፡ ምንም እንኮን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራቶች   40 በመቶ አካባቢ የዕዳ ጫና በከፍተኛ አደጋና ስጋት ውስጥ ይገኛሉ፣ እዳቸውን ለመክፈልም ከፍተኛ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡IMF warns of rising African debt despite faster economic growth (REUTERS- Kwasi Kpodo, May 8,2018)

“Sub-Saharan Afrian nations are at growing risk of debt distress because of heavy borrowing and gaping deficits, despite an overall uptick in economic growth, the International Monetary Fund.

African government issued a record $7.5 billion in sovereign bonds last year, 10 times more than in 2016. And they have issued or plan to issue over $11 billion in additional debt in the first half of 2018 alone, the report said. Foreign currency debt increased by 40 percent from 2010-13 to 2017 and now accounts for about 60 percent of the region’s total public debt on average, IMF data showed. Average interest payments, meanwhile, increased from 4 percent of expenditures in 2013 to 12 percent in 2017. Six countries- Chad, Eritrea, Mozambique, Congo Republic, South Sudan and Zimbabwe- were judged to be in debt distress at the end of last year. And the IMF’s rating for Zambia and Ethiopia were changed from moderate to “high risk of debt distress.”   ”

አይኤምኤፍ፣የኢትዮጵያየዕዳመሸከምጫናናወለድየመክፈልአቅምአስጊደረጃላይደርሶልአለ!!!

‹‹የኢትዮጵያ የዕዳ መጠን እየጨመረ ነው›› ግንቦት 2 ቀን 2010ዓ/ም (ቢቢሲ አማርኛ ዜና ሜይ 10 ቀን 2018ዕኤአ)

አለም አቀፍ የገንዘብ ተቆም አይ ኤም ኤፍ ባወጣው የአፍሪካ ሃገራት  ምጣኔ ሀብታዊ ዘገባ፤ የኢትጵያ የእዳ ጫና መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት 56.2 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ ገለፀ፡፡  ባሳለፍንው አመት የ10.9 በመቶ እድገት ያስመዘገበችው ሃገር ይህን ያክል ዕዳ መሸከሞ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነች ያሳያል ብሎል መግለጫው፡፡ ከሳህራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን ምጣኔ ሃብታቸውን ለማሥቀጠል ሲሉ ከፍተኛ የሆነ ዕዳ ውስጥ እየገቡ እንደሆነ በየዓመቱ የሚወጣው ዘገባ ያትታል፡፡ 40 በመቶ የሚሆኑት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የሚባል የዕዳ መጠን አስመዝግበዋል፤ ወይም ወደዚያ እየተጠጉ ነው የሚለው ዘገባው እነዚህ ሃገራት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የማይወጡት ችግር ይገጥማቸዋል ሲል ይተነብያል፡፡ ኢትዮጵያ እና ዛምቢያ ከአጠቃላይ ሃገራዊ ምርታቸው ጋር ያተመጣጠነ ዕዳ እያስመዘገቡ መሆኑን የዓለም አቀፍ ተቆም ጥናት ያሳያል፡፡ በ2016 የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን ከሃገራዊ አጠቃላይ ምርቶ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 ደግሞ ቀላል የማይባል ለውጥ በማሳየት ወደ 56 በመቶ አድጎል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት አሁንም የመሠረተ ልማት ሥራዎቻቸውን ለማስቀጠልና ማህበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወደ ብድር መግባታቸው አይቀርም የሚለው ዘገባው ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ካለባቸው ግን የብድር መጠናቸውን መቀነስ ግድ ይላል፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሠራታዊ ፍጆታ የሚውሉ እቃዎች ዋጋ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ መጥቶል፡፡ በ2016እኤአ የሃገሪቱ አጠቃላይ የመሠረታዊ ፍጆታ ዋጋ በ6.7 በመቶ ብቻ ያደገ ሲሆን በ2017እኤአ ግን ከእጥፍ በላይ በመጨመር 13.6 በመቶ እድገት አሳይቶል፡፡››  የአፍሪካ አገራት በእዳ ጫና የተነሳ ለወሰዱት ብድር ወለድ መክፈል እማይችሉነት ደረጃ ደርሰዋል፡፡

Africa’s Public Debt seen Exceeding 50% of GDP in 2017, IMF says (Bloomberg- David Malingha, 0ct 30,2017)

“The median level of government debt in Sub-Saharan Africa will probably rise to more than 50 percent of gross domestic product this year, increasing strain on the financial sector and limiting much-needed stimulation for growth, the International Monetary Fund said. … Dollar- denominated bond issuance from the region’s markets was about $4.6 billion in the first half of this year compared with $750 million for the whole of 2016, the IMF’s African Departmnet Director Abebe Selassie said by phon before the release of the report. “High levels of public debt can be quite harmful,” he said. “ The debt-servicing cost can be a major source of drain of resources that could otherwise be used.” ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ የአፍሪካ ሃገራት የእዳ ጫና ባለፍት 18 ዓመታት ውስጥ ያልታየ ሲሆን ፣ ለወሰዱት ብድር ወለድ ለመክፈል እንዲረዳቸው ከፍተኛ ታክስ መሰብስብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ከሳህራ በታች ያሉ ሃገራት በአዲስ የዕዳ ጫና ዳፍንት ተመተዋል በዚህም ምክንያት 40 በመቶ የሚሆኑት ሃገራት በዕዳ ጫና ስቃይ ውስጥ ይዋኛሉ፣ በአምስት ኣመት ውስጥ እዳቸው በእጥፍ ጨምሮል፡፡ ስምንት የአፍሪካ አገራቶች  ለወሰዱት ብድር ወለድ ለመክፈል ባለመቻላቸው  ከዓለም ዓቀፍ የመበደር መብታቸውን አጥተዋል፡፡  ኣለም አቀፋዊ የእዳ ስረዛ ዘመቻ ሃብታም ሃገራት ለደሃ ሃገራት የሚያደርጉበት ዘመን አብቅቶል ምክንያቱም ደሃ ሃገራት የተበደሩት ከንግዱ ህብረተስብ ቱጃር ባለፀጎች በመሆኑ ምህረት የለሽ ነው፡፡

‘’ IMF officials at the spring meetings in Washington have urged African countries to increase the efficiency of public expenditure, hand over public investment to the private sector, and fully implemenet fiscal consolidation plans, including seeking new revenues from consumer taxes.’’(FINANCIAL TIMES)

የኢትዬጵያየውጪብድርክምችት፣ ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011 እኤአ 19.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 27 በመቶ ነበር፡፡ የመንግሥታዊ ልማት ዘርፎች ብድር  ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011እኤአ 20.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 42.0 በመቶ ሆኖል፡፡ በ2016/17 እኤአ የህወሓት መንግስትና ብሄራዊ ባንክ ባለሞሎች የሃገሪቱን ልትወጣ በማትችለው የውጪ ብድር ክምችት ከተው ኢኮኖሚውን አዘቅት እንደሚከቱት አጥኝዎች ተንብየዋል፡፡ ለዚህም ግልፅ ማሽረጃ የ2009 ዓ/ም ዓመት እቅድና አፈጻጸም፣ በተለይ የውጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል፣ የውጪ ብድር መክፈል አቅም መሽመመድና የውጪ ምንዛሪ እጥረት በቀጣይነት ተከስቶል፡፡ በ2008ዓ/ም የውጭ ዕዳ ክፍያ 1 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የወለድ ክፍያው በዓመት ከ350 ሚሊዩን ዶላር ከፍ ብሎል፡፡ በ2009ዓ/ም የውጭ ዕዳና የወለድ ክፍያ 1.5 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 እስከ 50 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 58% እጅ ይይዛል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሳ!!! የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

ምንጭ: Ethiopianexplorer.

 

%d bloggers like this: