Tag Archives: foreign exchange

መንግሥት: የምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን ማድረጉ ከኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር የሚተገበር እንጂ በፍጥነት የሚገባበት አይደለም!

8 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር እዮብ በዚህ መንገድም የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው በሚተገበርባቸው ሶስት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በገበያ የሚመራ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይኖራታል ብለዋል።

ቅድሚያ ግን አቅርቦትና ፍላጎትን በማቀራረብ የሚኬድበት እንጂ እንደ ከዚህ በፊቱ ብርን በአንዴ በማዳከም አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

ወደ ውጭ የሚላክ በቂ ምርትና ተወዳዳሪ ጥራት በሌለበት የተተገበሩ የተመን ለውጦች በመሆናቸው በሁለቱም ጊዜያት ገቢ ዕቃዎችን በእጅጉ በማስወደድ የዋጋ ንረትን ከመፍጠር የተሻለ ነገር ማስመዝገብ አልተቻለም።

እንደውም በ2010 ዓ.ም. የተደረገው የምንዛሬ ተመን ከዋጋ ግሽበት ባለፈ በባንኮችና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት ጭራሽ ባልተለመደ ሁኔታ አስፍቶታል።

የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ደግሞ በቂ የሚላክ ምርት በሌለበት ሁኔታ የኢትዮጵያን ብር ጠነከረ አልጠነከረ ብሎ እርምጃ መውሰድ ተገቢነቱ ሊጤን ይገባል ብለዋል።

 

Continue reading

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መንግሥት ማቀዱ ተሰማ

14 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ የሚወሰንበት አሠራር ተግባራዊ እንዲሆን መንግሥት ዘላቂ ወይም የረዥም ጊዜ ዕቅድ መያዙ ተሰማ።

አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ከሚደረግበት የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት እንዲያበቃ፣ በፍላጎትና አቅርቦት የገበያ መርህ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን እንዲወሰን መንግሥት አቅጣጫ አስቀምጧል።

በገንዘብ ፖሊሲ አስተዳደሩ ላይ በመንግሥት የተወሰነው ይህ የስትራቴጂ ለውጥ በፍጥነት ተግባራዊ የሚደረግ ሳይሆን፣ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የውጭ ምንዛሪ የግብይት ሥርዓት በቀጣይ በዘላቂነት የሚተካ እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል። ይህ የሚሆንበት ምክንያትም በቂ ዝግጅት የሚያስፈልግ በመሆኑ ነው።

ወደዚህ የውጭ ምንዛሪ የገበያ ሥርዓት ለመሸጋገር የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ሙያዊ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ ያለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት “Fixed Foreign Exchange Market” የሚባል ሲሆን፣ ዶላር የመግዛት አቅምን መሠረት በማድረግ የብር የምንዛሪ ዋጋ ተመን ላልተወሰነ ጊዜ በቋሚነት በአንዴ የሚወሰንበት፣ የሚጣልበት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ብር ከመግዛት አቅሙ በላይ ከፍተኛ ዋጋ እንዲይዝ እንዳደረገው የአይ.ኤም.ኤፍ መረጃ ያመለክታል። በኅዳር ወር 2011 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው የአይኤምኤፍ መረጃ እንደሚያስገነዝበው፣ የኢትዮጵያ ብር ዶላርን የመግዛት አቅም ከትክክለኛ የመግዛት አቅሙ በ20 በመቶ ከፍ ብሎ እንደሚገኝና ይህም የኤክስፖርት ዘርፉን እንደማያበረታታ በመግለጽ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በገበያ መርህ የሚወሰን የውጭ ምንዛሪ የገበያ ሥርዓት መፍጠር እንደሚገባው ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲያሳስብ መቆየቱንና ተቀባይነት አለማግኘቱን ይጠቁማል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ ሕግ እንዲወሰን ማድረግ ተገቢና ዘለቄታዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ያስረዳሉ።

ስለውሳኔው እንደማያውቁ የተናገሩት ባለሙያው፣ በገበያ ወደሚመራ የውጭ ምንዛሪ የገበያ ሥርዓት መሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያምናሉ።

ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ይኼንን በገበያ የሚመራ የውጭ ምንዛሪ የግብይት ሥርዓት መተግበር የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን በመጥቀስ፣ በፍጥነት ሊተገበር የሚችል ዕቅድ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ወደዚህ የግብይት ሥርዓት ለመግባት ቀዳሚ ከሚባሉት ቅድመ ሁኔታዎች ዋነኛው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መያዝ እንደሆነ የሚያስረዱት እዮብ (ዶ/ር)፣ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የውጭ ምንዛሪ ግብይቱ በገበያ እንዲወሰን ማድረግ የብር ምንዛሪ ተመን በከፍተኛ ደረጃ የማናር ውጤትን በማስከተል፣ የዋጋ ግሽበትን እንደሚያስከትል፣ የዕዳ መጠንን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያንርና አጠቃላይ ውጤቱም ማክሮ ኢኮኖሚውን እንደሚያዛባ በመጥቀስ በአሁኑ ወቅት ሊተገበር የሚችል አለመሆኑን አስረድተዋል።

ብሔራዊ ባንክ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት በአሁኑ ወቅት ያለው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለሁለት ወር ከቀናት የውጭ ግዥዎች እንደሚበቃ፣ ይኼንንም በጥንቃቄና የመሠረታዊ ፍላጎቶች አቅርቦቶችን በማስቀደም ወጪ እንደሚደረግ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

 

 

/ሪፖርተር

 

TPLF donkey meat and skins business rattles Ethiopians

5 Apr

By Keffyalew Gebremedhin The Ethiopia Observatory (TEO)
 

In the Great Donkey Rush, the Daily Maverick opened its major story of September 9, 2016 with the following theme:

“Forget gold, diamonds or rhino horn. The hottest commodity in Africa right now – the most prized ass-et, if you will – is the humble donkey, thanks to a critical donkey shortage in China.”

Continue reading

ልማት ባንክ ብድር የሚወስዱ “ደንበኞች ስኬታማ እስኪሆኑ የወለድ ምጣኔ ማበረታቻዎችን አልሰጥም አለ”! ገንዘቡም የለም! እንዲጠቀሙ የሚፈለጉት ግለሰቦችና ትሥሥሮች ብቻቸውን በልተዋል! ከእንግዲህ በሌለ ገንዘብ በዝርያ በመጠቃቀም ሕወሃቶችን ማድለቡን ማቆሙ ከሆነ ግልጽ ይደረግ፤ ኢሣይያስ ባህረም ያዘረፈው ሃብት ይመለስ!

14 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በወጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው የውጭ ምንዛሪን ለማምጣትና ከውጭ የሚገባን ምርት ለመተካት ብድር የሚወስዱ ደንበኞቼ ስራቸው ስኬታማ እስኪሆን የወለድ ምጣኔ ማበረታቻዎችን መስጠት አቆማለሁ አለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ።
Continue reading

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ተስፋ ያደረጋቸው የውጭ ኩባንያዎችና በእንጭጭ ያስቀሩት ዕቅድ – ስለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ጉዞ ከተነሳ ዘንዳ…

11 Nov

ከአዘጋጁ፡

  ባለቤትነትን የሚፈጥረው የራስ ጥረትና በራስ መተማመን መሆናቸውን ሕወሃት በብልሹ ፖለቲካው ምክንያት ዘንግቶ ዜጎችንም በማዘናጋት ላይ ነው! ለዝርዝሩ ሰሞኑን ዘኢኮኖሚስት (Nov 7th) የተሰኘው መጽሔት ስለኢትዮጵያና አፍሪካ የኢንዱስትሪ አስፈሪ ጉዞ አሰመልክቶ ሰለጻፈው ጉዳይ የሠጠነውን መልስ ይመልከቱ፡-

  Is Africa deindustrializing? The Economist praise of Ethiopia’s manufacturing efforts raises eyebrows

  “If the past is any guide to the present and the future, impetuous as the the TPLF regime has been in this quarter century of exercising state powers, it is in no position to translate these neatly laid out plans [Industrial Development Plan] into action, since the rulers themselves are in need of upgrading and undergoing their substantial transformations.”

  The Ethiopia Observatory (TEO)

 
Continue reading

Ethiopia’s wheat conundrum

5 Nov

Editor’s Note:

  Before Prime Minister Hailemariam’s announcement that Ethiopia has become food secure faded from the minds of Ethiopians, the National Bank of Ethiopia (NBE) signaled that it has arranged $600 million in loans for food imports (wheat mostly) and $120 mil for sugar to stave shortages-caused price hikes off.
  Continue reading

IR’s rejected insight becomes the truth, with TPLF focusing on power exports as Ethiopia gropes in darkness

18 Sep

By Keffyalew Gebremedhin – The Ethiopia Observatory (TEO)

When certain claim or argument is rejected as baseless, but in time turns out to become fact and actuality, doubters and rejectors of its underlying truths find themselves on the wrong side of reality. I penned this short piece this morning, after I read on ERTA the news story why the TPLF regime loves to export electricity; read it imagining what it means to be source of power.
Continue reading

ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ያወጣው መመርያ ተግባራዊነት እንዲዘገይ ተደረገ – ለምን ይሆን?

9 Mar

የአዘጋጁ አስተያየት፡

  ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ክፍተኛ ተጋድሎ እያድረገች ትገኛለች። ከሕወሃት ጄኔራሎችና ከመልዕክተኞቻቸው የተረፈው ጥቂቱ እስከ ድረስ ልማት ላይ እየዋለ ነው።

  በአንድ በኩል ሲታይ፡ ብሔራዊ ባንክ ሊወስድ የንበረው የሕግ ለውጥ እርምጃ ምናልባትም ከሚገመተው በላይ የዘገየና፡ ብዙዎቹ የሥርዓቱ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚ ተጠቃሚዎች ክፉኛ እንዲበሸበሱበት ሁኔታ የፈጠረ የረቀቀ ዘረፋና ምዝበራ ነበር። ነውም። በመለስ ትዕዛዝ ያለአንዳች ተጠያቂነት የሕወሃት ጂኔራሎቹና ደህንነት ባለሥልጣኖች በመንግሥት ገንዝብ የየግላቸውን ፎቆችና ቪላዎች ሠርተው ከሚያከራዩት ውጭ፡ በህብት የተንበሸበሹት ግለሰቦች፡ አንድም ይህንን የውጭ ምንዛሪ ቀዳዳ በመጠቀም መሆኑን፡ ብዙ ተንታኞች ምስክርነታቸውን በየጊዜው ሲያሰሙ ክርመዋል።
  Continue reading

%d bloggers like this: