Tag Archives: Grand corruption

ጄኔራል መላኩ ሺፈራው ሕወሃቶች በሜቴክ ስለፈጸሙት ዘረፋ መረጃዎችን አወጡ፤ ሕወሃት በኢትዮቴሌኮም የነበረውን አጠቃላይ የዜጎችን፡ባንኮች ወዘተ ዲጅታል መረጃዎች መቀሌ መውሰዱን አጋለጡ!

8 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(ኢሳት) ጳጉሜ 1/2010 በመሰረታዊ ብረታብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ ውስጥ የሚካሄደው ዘረፋ ብሔርን መሰረት ያደረገና እጅግ የተደራጀ ሌብነት መሆኑ ተገለጸ።

ሜቴክን ከምስረታው ጀምሮ የሚያውቁት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ለኢሳት እንደገለጹት በዘረፋው ሒደት በደላላነት በሚሊየን ዶላሮች የሃገሪቱን ሃብት የሚቀራመቱ ግለሰቦችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

ዘረፋውን በመቃወማቸውም ከተቋሙ የተባረሩና የተሰናበቱ የአማራ፣የኦሮሞና የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆችን ስም ዘርዝረዋል።

በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ መረብ ከፍተኛ ሃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ትራም ከተባለ ሃንጋሪ ከሚገኝ ኩባንያ ጋር የ6 ሚሊየን ዩሮ ስምምነት ከተደረገ በኋላ የአጠቃላይ ገንዘቡ 10 በመቶ ኮሚሽን ለእነ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የጥቅም ሸሪኮች ከተከፈለ በኋላ ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱን አስታውሰዋል።

በአፋር ክልል “ወያኔ”የሚል ስያሜ የተሰጠው ተክል ወደ ነዳጅ ለመቀየር በሚል ለተያዘ ፕሮጀክት ከውጭ ኩባንያ ጋር የ10 ሚሊየን ዩሮ ስምምነት ከተደረገ በኋላ የኮሚሽን ክፍያው ተፈጽሞ ፕሮጀክቱ መክኗል ጄኔራል መላኩ ሽፈራው እንደገለጹት።

በኮምቦልቻ ብረታ ብረት ፣በሕዳሴው ግድብ የነበረውንም የዘረፋ ሁኔታ በዝርዝር የተመለከቱት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው፣ከምንጣሮ ጋር እንዲሁም ከተርባይን ግዢ ጋር የተደረገውን የተቀናጀ ዘረፋም ተመልክተዋል።

 

በስኳር ኮርፖሬሽን፣በያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣በመብራት ሃይል የኢነርጂ ሜትር ግዢ እንዲሁም በመርከብ፣በታንክና በሌሎች የጦር መሳሪያዎች ግዢ ውስጥ የሜቴክና የሃገሪቱ ሃብት የባከነበትን ሁኔታ በዝርዝር ተመልክተዋል።

ሜቴክ 15 የግል መኖሪያ ቤቶችና ሆቴሎችን በመግዛት እንዲሁም በሰው አልባ አውሮፕላን ፕሮጀክት ያካሄደውን ዘረፋ የዘረዘሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው በዚህ ሒደት ዋናዎቹ ተዋናዮች ከድርጅቱ ሃላፊዎች በተጨማሪ በድለላ የተሰማሩትን ዘርዝረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ በድለላ ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩትም አቶ ደግነህን ጨምሮ ኮለኔል ተወልደ፣ኮለኔል ክብሮም፣ኮለኔል አታክልቲና ሌሎችንም በዝርዝር አስቀምጠዋል።

ይህንን በመቃወማቸውም ኮለኔል ጌትነት፣ኮለኔል ሽመልስ ክንዴ፣ኮለኔል አብዱሰላም ኢብራሒምና ሌሎች መኮንኖችም እንደሚገኙበት በቃለ ምልልሱ ላይ ገልጸዋል።

 

ተዛማጅ፡

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፉና ያባከኑ ሰዎች ሜቴክን እየለቀቁና ማዕረጋቸውን እየለወጡ በሲቪል አስተዳደርነት እየተቀጠሩ ነው — ለዋና ከተማችን ምክትል ከንቲባዎች ጭምር!

የሜቴክ ዘረፋ የተደራጀ ሌብነት ነው ተባለ

ከሕወሃት ዘራፊዎች በስተቀር የሕዳሴው ግድብ ገንዘብ የገባበትን የኢትዮጵያ መንግሥት አያወቅም! ግድቡም ገና አያሌ ዓመታትና ከፍተኛ ገንዘብ ያስወጣል!

ለስኳር ኮርፖሬሽን መውደቅ ሜቴክ ትልቅ ድርሻ አለው፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ አመራሮች መጠየቅ አለባቸው’ ተባለ – ሪፖርተር እንደዘገበው

TPLF mismanagement renders useless even existing sugar factories, much less Ethiopia becoming exporter as per GTP I & II

በረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሙስና መፈጸሙንና የዶር ደብረጽዮን እጅ እንዳለበትም የውስጥ ምንጮች አጋለጡ!

ከሕወሃት ዘራፊዎች በስተቀር የሕዳሴው ግድብ ገንዘብ የገባበትን የኢትዮጵያ መንግሥት አያወቅም! ግድቡም ገና አያሌ ዓመታትና ከፍተኛ ገንዘብ ያስወጣል!

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(ኢሳት)–ነሐሴ 30/2010 ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ ተሰብስቦ ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የገባበት አይታወቅም ተባለ።

ገንዘቡ የደረሰበትን ለማወቅም በመጣራት ላይ መሆኑን የሜቴክ የኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል።

በ5 አመት ይጠናቀቃል የተባለው የህዳሴው ግድብ ግንባታም ቢሆን ከ25ና ከ30 በመቶ በላይ አለመጠናቀቁም ታውቋል።

አቃቤ ህግ በበኩሉ በዚህ ሒደት ውስጥ ያሉ አካላት በሙሉ ተጠያቂ ይሆናሉ ብሏል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለቤትነት እንዲሁም በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እና ሳሊኒ ኩባንያ የስራ ተቋራጭ የሆኑበት የሕዳሴው ግድብ አፈጻጸም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ብክነትና ምዝበራ የተፈጸመበት መሆኑ ተገለጸ።

“ሕዳሴ ሲገለጥ” በሚል ርዕስ ዋልታ ኢንፎርሜስን ማዕከል ባዘጋጀው የምርመራ ዘገባ የሕዳሴው ግድብ በሰባት አመት ውስጥ ያለበት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ከ25 እስከ 30 በመቶ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።

በተለይም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን የተረከበው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) ያለጨረታ ፕሮጀክቱን አጠናቆ ለማስረከብ በ25 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር ተዋውሎ ስራውን መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር አብርሃም በላይ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ እስከ አሁን ድረስ ወደ 16 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር ክፍያ ተፍጽሞለታል።

ይህ ክፍያ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ክፍያ 65 በመቶ ይሸፍናል።

በሌላ በኩል የሜቴክ የስራ አፈጻጸም 42 በመቶ ያህል ብቻ መሆኑን ዶክተር አብርሃም አስታውቀዋል።

ክፍያው ላልተሰሩ ስራዎች ብቻ ሳይሆን ገና ይሰራሉ ተብለው ለሚታሰቡት መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

በሜቴክ የሚሰራው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ከ30 በመቶ በታች በመሆኑ ስራቸውን እንዳጓተተባቸው የሳሊኒ ኮርፖሬሽን አማካሪ ሚኒስትር ሮበርት ማሪጊኒ ይህ ደግሞ ለተጨማሪ ክፍያ ጥያቄ እንደገፋው ገልጸዋል።

ሳሊኒ የጠየቀው ተጨማሪ ክፍያ 3 ነጥብ 259 ቢሊየን ብርና 338 ሚሊየን ዩሮ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አስታውቀዋል።

አለም አቀፍ ስምምነት በመሆኑም ክፍያው የግዴታ እንደሚፈጸም አክለው ገልጸዋል።

ማንም ከሕግ በላይ ስላልሆነ አጥፊዎችን ተጠያቂ እናደርጋለን ያሉት የሜቴክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ ለዚህ ብክነት ሃገራዊ ሃላፊነት መውሰድ ግዴታ እንደሆነ አረጋግጠዋል።

 

Related:

ያ ያልነው ቀን ደረሰ መሰለኝ! ‘ለስኳር ኮርፖሬሽን መውደቅ ሜቴክ ትልቅ ድርሻ አለው፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ አመራሮች መጠየቅ አለባቸው’ ተባለ – ሪፖርተር እንደዘገበው

 ምዝበራ በየፈርጁ!

TPLF mismanagement renders useless even existing sugar factories, much less Ethiopia becoming exporter as per GTP I & II

%d bloggers like this: