Tag Archives: human rights violation

የዐቢይ አሕመድ መንግሥት የቫይረሱን አጋጣሚ የተቃውሞ ድምፆችን ሊያፍንበት አይገባም!

13 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በተመለከተ የተዛቡ መረጃዎችና መንግሥታዊ ምላሽ

ካርድ፤ ሚያዝያ 5፣ 2012

መግቢያ

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ነው። መንግሥትም ፈጣን ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታል። ይሁንና የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ፣ ሥርጭቱን መከላከያ መንገዶች ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ አሁን ሥርጭቱ ያለበትና ሊደርስ የሚችልበት ደረጃ ላይ የተለያዩ የተዛቡ መረጃዎች እየተሠራጩ ይገኛሉ፣ ለወደፊትም ሊሰራጩ እንደሚችሉ እንገምታለን። እነዚህ የተዛቡና ምናልባትም ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ መረጃዎች የሚመነጩት ደግሞ ከተለያዩ የእምነት መሪዎች/ሰባኪዎች፣ ከባሕል መድኃኒት አዋቂዎች፣ ከጋዜጠኞች (ጦማሪዎች) እና ሌሎችም እንደሆነ ተመልክተናል። ይህንን የመከላከል ሥራ መሥራት የመንግሥትና የሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ድርሻ ነው። መንግሥት ግልጽነትን በመጨመርና ተአማኒነቱን በማሳደግ፣ ሌሎች ብዙኀን መገናኛዎችና ሲቪል ማኅበራት ደግሞ የተጣሩ መረጃዎችን በማዳረስ ሰዎች በተዛቡ መረጃዎች እንዳይሳሳቱና እንዳይዘናጉ ማድረግ ይገባል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከተገኙ (መጋቢት 4፣ 2012) አንድ ወር የተቆጠረ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከተለያዩ አካላት የተለያዩ ሐሰተኛ መረጃዎች የተሰራጩ ቢሆንም፥ የመንግሥት ትኩረት ግን በጋዜጠኞችና ጦማሪዎች ወይም አክቲቪስቶች ላይ ሆኖ ተስተውሏል። ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተገናኘ የተዛባና ጉዳት ሊያስከትል የሚችል መረጃ አሰራጭታችኋል በሚል ሁለት ሰዎችን (ያየሰው ሽመልስ እና ኤልሳቤት ከበደን) አስሯል። የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) የተዛቡ መረጃዎች ሥርጭት ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ የሚረዳ ቢሆንም፣ የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት መከላከልም ይሁን መግታት የሚቻለው በእስር ነው ብሎ አያምንም። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደገለጽነው፣ የተዛቡ መረጃዎች ከመንግሥት ግልጽነት እና ተጠያቂነት አለመኖር፣ ከብዙኀን መገናኛዎች ሐቅን የማረጋገጥ ባሕል/ልምድ እጦት እና ከሲቪል ማኅበራት የብዙኀን መገናኛዎች አረዳድ የማሳደግ ሥራ አለመሥራት የሚመነጭ ነው። እነዚህን ችግሮች መቅረፍ የመፍትሔው አካል መሆኑንም እናሰምራለን።

Continue reading

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአማራው ክልልና በአዲስ አበባ ወጣቶችን እያፈኑ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በእስር ቤት ማጎር በአስችካይ እንዲቆም ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ጥሪ

2 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

 

ግሎባል አልያንስ ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ ለአለም አቀፍ መርሆወችና ለስብአዊ መብቶች መከበር በኢትዮጵያም ውስጥ ይሁን በወጪ አገራት ኢትዮጵያኖች በሚደርስባቸው የስብዓዊ መብት ጥስት በግንባር ቀደምትነት ስብአዊ መብታቸው እንዲከበር ለዓለም አቀፍ የስብአዊ መብት ተቋማትና ለኢትዮጵያ መንግስት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የዜጎቻችን መብት እንዲከበር የራሱን አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በተለይም ላለፍት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችና የመብት ተማጋቾች በነጻነት ሃሳባቸውን ስለገለጹ ብቻ ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሲታስሩ፤ ሲገረፉ፤ ሲገደሉ እና ሲስቃዩ ያሳለፉት ዘመናት ገና ሳይረሳ በተለይም በአሁኑ ስአት በሃገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጥቷል በሚባልበት ግዜ እና ሃገሪቱን የሚመሩት ጠቅላይ ሚንስትር በኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ይሁን ማን አስቀድሞ ማጣራት ሳይደረግና የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳይወጣ አንድም ስው እንዲታስር አንፍቅደም በማለታችው ምክንያት ከአለም አቀፍ ተቋማት አምንስቴ ኢንተርናሽናልና የመሳስሉት ድርጅቶች ሳይቀር እውቅና በተስጣቸው አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ፤ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ከሁለት መቶ ሰባ በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባና የሊሎች ነዋሪዎች ታፍነው ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። እየተገረፉ ነው።

በሽብርተኛነት እየተከሰሱ ነው። ይህ የህወሓት መራሹን አፋኝና ጨቃኝ መንግስት ስራ የሚያስታውሰንና የሚመስል አድራጎት በአገሪቷ ውስጥ መጥቷል የሚባለውን ለውጥ ተስፋ ስጪ መሆኑ ቀርቶ ኢትዮጵያዊያኖች መጪውን ግዜ በጭንቀትና በፍርሃት እንዲመለከቱት ከማድረጉም ባሻገር ያለፈው የመከራና የአፈና ዘመን መልሶ መምጣቱን ከወዲሁ አመላካች እንደሆነ ያሳያል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታየው ያለው የብሄር ልዩነቶች ከጊዜ ወደጊዜ መጠኑ ስር እየስደደ በመሄዱ መንግስት ለዚህ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ለመለፅ እንወዳለን:። በተለይ በዐማራውና ኦሮሞ ባልሆነው ሕዝብ ላይ በቡራዩ፤ በሰሜን ሸዋ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በልዩ ልዩ የኦሮሞ ክልል ስፍራዎች ላይን እጅግ የሚዘገንን ብሄር ተኮር እልቂትና አፈና እየተክሄደ ነው።

ይህ አድራጎት ጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአንድ ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች ታፍነው ከተያዙ በኋላ ወደ ጠቅላይ የጦር ማስልጠኛ ካምፕና ወደ ስንዳፋ የጦር ካምፕ ተወስደው ከፍተኛ ድብደባና የስብአዊ መብት ጥስት ከተፈጸመባቸው በኋላ በግድ አጥፈተናል እንዲሉ ከተደረጉ ከወር በኋላ ወደ የቤተስቦቻችው መመለሳቸው የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። አሁንም ቁጥራቸው የማይታወቅ ወጣቶች ወደ ሰንዳፋ ተወስደው እርህራሄ የጎደለው ግርፋትና እንግልት እየተፈጸመባቸው ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ኢንተርኔት እንዳይተላለፍ ስለከለከለ ሃቁን ለመከታተል አልተቻለም። የኢንተርኔት መገናኛ መቋረጥ ዋናው ዓላማ ለአፈናው አመች እንዲሆን ነው።

ስለዚህ በአሁኑ ስአት በማንኛውም ስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት የፍትህ አካላት እና የፓሊስ ሃይል ልብ ሊሉት የሚገባው ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝና የወንጀል ድርጊት ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ዜጎችን በድንገት አፍኖ እስር ቤት ማጎር አለም አቀፍ ህግጋትን የጣስና የግለሰብን ስብአዊ መብት በእጅጉ የሚጎዳ ከመሆኑ ባሻገር ይህንን ህገወጥ አድራጎት የሚፈጽሙትንም የመንግስት አካላት ተጠያቂ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ግሎባል አልያንስ ማሳስብ ይወዳል ።

ይህ ጭፍንና አደገኛ የፌደራል መንግሥት አፈና በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። የኢንተርኔት አገልግሎት ያለምንም ገደብ እንዲሰራጭ እንጠይቃለን። በመጨረሻም በአዲስ አበባ ውስጥ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታፍነው የታስሩ ዜጎቻችን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ በአስቸካይ ከእስር እንዲፈቱና ዳግመኛም እንዲህ አይነቱ ህገ ወጥ አስራር የሃገሪቱን ዜጎች እጅግ የሚያሳዝንና ሃገሪቱ የምታደርገውን የለውጥ እንቅስቃሴ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚያሸጋግር እናሳስባለን። በመጨረሻ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፤ የክልል ባለሥልጣናት፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፤ የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ መንፈሳዊ አባቶችና እናቶች፤ ወጣቶች፤ ምሁራንና ሌሎች ባለድርሻዎች በጋራ አስቸኳይ ብሄራዊ ውይይት እንዲያደርጉና ወደማይመለስ ጫፍ የደረሰችውን ኢትዮጵያን ከአደጋ እንዲታደጓት ጥሪ እናደርጋለን።

ሰብአዊ መብቶች ይከበሩ!!
አፈና በአስቸኳይ ይቁም!

 

ሕገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በፌስ ቡክ የሠጡት መግለጫ!

22 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ በስፋት እንዳለ ይታወቃል፡፡

እነዚህ ህገ ወጥ ግንባታዎች በሌሊት ጭምር በድብቅ የሚፈጸሙ (ጨረቃ ቤቶች) በመሆናቸዉ ለቁጥጥር አስቸጋሪና የከተሞችን ፕላን እና የመሬት ይዞታ አጠቃቀምን የሚቃረኑ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም በአንድ በኩል ህገ ወጥ ግንባታን የመከላከል፣ በሌላ በኩል ደሀ ተኮር ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ለዜጎች የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

ዜጎችን መጠለያ የማግኘት እና የትም ቦታ ተዘዋዉረዉ የመኖር መብት አላቸዉ፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ይህን የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ደሀ ተኮር መመሪያ በማዘጋጀት ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለመምህራን ለከተማ ነዋሪዎች፣ ለልማት ተፈናቃይ አርሶ አደር እና አርሶ አደር ልጆች ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታዎችን አዘጋጅቶ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ትላልቅ ከተሞች ለዜጎች በህጋዊ መንገድ አስተላልፏል፡፡ አሁንም እያስተላለፈ ይገኛል፡፡

ይህም ሆኖ ህገ ወጥ ግንባታ ሊቆም ባለመቻሉ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች በመሬት አጠቃቀም ዙሪያ ባሉ ህገወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን ማስከበር ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ዕርምጃዉ በማንኛዉም ህገ ወጥ ግንባታ ላይ በሁሉም የኦሮሚያ ከፊቼ እስከ ሞያሌ፣ ከደሚ ቢዶሎ እስከ ባቢሌ፣ ከአዳማ እስከ ሻሸመኔ፣ ከአሰላ አስከ መቱ ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ግንባታዎችን በመለየት ህብተሰቡን በማወያየት፣ የከተማ መሬትን ለማስተዳደር በወጣዉ ህግና ደምቦች መሰረት ወደ ህጋዊ መስመር መግባት የሚችሉት ህግን ተከትለዉ ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡ፣ በተለይም በመንግስት ዞታ እና ማህበራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ የተገነቡት (በትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በፈር ዞኖች የገበያ ቦታዎች መንገድ ሌሎች መሰረተ ልማቶች የሚገነቡባቸዉ ቦታዎች) ማፍረስ ግዴታ መሆኑን በማስረዳት አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡



ሰሞኑን እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ካሉ ከተሞች አንዱ በለገጣፎ ለገዳdhii ከተማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያም ጭምር ህገ ወጥ ግንባታ ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ በለገጣፎ ለገዳdhii ብቻ እየተደረገ ያለ እና ብሄር ለይቶ እርምጃ አስመስሎ እየቀረበ መሆኑን አስተዉለናል ፡፡ ይህ ስህተት ነዉ፡፡ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 25 ከተሞች በተደረገ እንቅስቃሴም ህግን ብቻ ባማከለ 36,117 ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡

በዛሬዉ ዕለትም በለገጣፎ ለገዳdhii ከተማ በመገኘት ከጠቅላይ ሚኒሰትር ጽ/ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚdhaጋ እንዲሁም ከከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ጋር በመሆን በከተማዉ ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ተዘዋዉረን ጎብኝተናል፡፡ በቆይታችን በከተማዉ የከፋ ህገወጥ (በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና ገደላማ ቦታዎች ሳይቀር እንዳለ ለመረዳት ችለናል፡፡ ከተማዋ በህግ ከተቆረቆረች ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ባሉት ጊዜያት 12,381 ህጋዊ ያልሆኑ ቤቶችና ይዞታዎች እንዳሉ ተለይተዋል፡፡ ከዚህ ዉስጥ 1,307 ያህል ቤቶች ህገ ወጥ መሆናቸዉ ተረጋግጦ አምና በተወሰደ እርምጃ እንዲፈርሱ ተደርጓል፡፡ 5,000 በላይ የሚሆኑት ዞታዎች እና ቤቶች ደግሞ በመንግስት ተቋማት፣ በገበያ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና ለመንገድ መሰረተ ልማት የማይዉሉ በአጠቃላይ የከተማዉን የመሬት አጠቃቃም ፕላን ጋር ተቃርኖ የሌላቸዉ መሆናቸዉ ስለተረጋገጠ ህግና ደንቦችን ተከትለዉ ወደ ህጋዊ ይዞታነት አንዲዞሩ ተወስኗል፡፡



በለገጣፎ ለገዳdhii ዛሬ ባደረግነዉ ጉብኝት ሰሞኑን በተደረገ ህግን የማስከበር እንቅስቃሴ በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ የትምህርት ቤት ቅጥር ገቢ ጨምሮ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጠናል፡፡ የተወሰደዉ ዕርምጃ አንድ ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ የማቀረቡም ሁኔታ ሀሰት መሆኑን ሚዲያዎች ባሉበት አረጋግጠናል፡፡

ህገ ወጥ ግንባታ እንደዚህ ሲስፋፋ በየደረጃዉ ያለዉ የአስተዳደር እና ህግ አስከባሪ አካላት ግንባታዉ ሳይከናወን አስቀድመዉ መከላከል አለመቻላቸዉ አንዳንድ ከተሞች ላይም ጉቦ ጭምር በመቀበል ህገወጥነትን በማስፋፋት የተሳተፉ አካላትን ለይቶ ለህግ የማቅረቡ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ግንባታ የተሳተፉት አካላት ምንም አማራጭ የሌላቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ዜጎቻችን ብቻ ሳይሆኑ በተለያዩ ደረጃ በመንግስት ሀላፊነት የሚገኙ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የራሳቸዉ ህጋዊ መኖሪያ ያላቸዉ ግለሰቦችና ባለሀብቶች እና የመሬት ደላሎችም ጭምር እተሳተፉበት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ስለሆነም የደሃ ደሃ የሆኑ ዜጎቻችንን በመጠለያ ዕጦት መንገድ ላይ እንዳይወድቁ ጥናት በመለየት ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ይሰራል፡፡ ከዚህ በተረፈ በመሬት ዙሪያ የሚሰሩ ህገ ወጥነት ላይ ችግሮቹን ከምንቻቸዉ ቀድሞ የመከላለከል ስራ መሰራት አለበት፡፡ ከዚህ በተረፈ መንግስት ህገ ወጥነትን ለመከላከል የሚሰራዉን ያህል የዜጎች በየትኛዉም አካባቢ ተንቀሳቅሶ መስራትና የመኖር ህገ ምግሳተዊ መብት ያለምንም አድልኦ እንዲከበር ይሰራል፡፡ በዚህ ረገድ የሚታይ ማንኛዉንም መዛነፍ ሲታይ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስረተን የእርምት እርምጃ በመዉሰድ የሚያስተካክል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ከዚህ በተረፈ ህገ ወጥ ግንባታዎች በቸልተኝነት የሚያዩ እና ብሎም በሌብነት የሚሳተፉ የአስተዳደር አካላት፣ ደላሎች እንዲሁም በህገጥነት ግንባታ ላይ በሚሳተፍ ማንኛዉም ዜጋ ላይ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

/ከአቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ፌስ ቡክ

*Republished

የዜጎችን መጠለያ የማግኘት ተፈጥሯዊ መብት በሕግ ስም መጣስ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል!

22 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ National Movement of Amhara

በአዲስ አበባና በዙሪያው ባሉ ከተሞች ዘርን መሠረት ያደረገ ቤት የማፍረስና የማፈናቀል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም የአማራ  ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያሳስባል። አብን ማንኛውም ዜጋ በመረጠው አካባቢ ጎጆ ቀልሶ የመኖር ተፈጥሯዊ መብት እንዳለው ይገነዘባል። ይሁን እንጅ «ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው» እየተባለ ከበሮ በሚደለቅበት በዚህ ሰዓት «አዲስ አበባ የእኛ ናት፤ ሌላው ከፈቀድንለት ብቻ ይኖራል» በሚል አክራሪ ቡድን ፊታውራሪነት የሚደረገው የዜጎች መጎሳቆል የሚያሳስበን መሆኑን እያሳወቅን፤ ይህ ነገር በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ ሁሉንአቀፍ ትግል በማድረግ ግፈኞቹን ፊት ለፊት የምንጋፈጣቸው መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን።

ስለሆነም በለገጣፎና እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ጎጆ ቀልሰው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ «ከእኛ ወገንአይደላችሁም» በሚል አክራሪነት የሚደረገው መፈናቀልና ንብረት ማውደም በዋናነት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራሉን መንግሥት ለተጠያቂነት የሚዳርግ መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲቆም፥ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችም ተመጣጣኝ ካሳ አግኝተው ሰላማዊ ኑሮ የሚኖሩበት ሁኔታ በመንግሥት ወጪ እንዲመቻችላቸው እየጠየቅን፥ መላው ኢትዮጵያዊያን ከተጎጂዎች ጎን በመቆም እንዲያጽናና እና ግፈኞች ለሕግ እንዲቀርቡ ከአብን ጎን ተሰልፎ ግፊት እንዲያደርግ አበክረን እንጠይቃለን።

የአNo photo description available.ማራብሔራዊ ንቅናቄ

ቅፅ 1 ቁጥር 14 የካቲት 15/2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት የአገር ውስጥ ደኅንነት ዋና ኃላፊ አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ

18 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የ192 ግለሰቦች የባንክ ሒሳብና 13 ድርጅቶች ዕግድ ተጣለባቸው 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን፣ በተጠረጠሩበት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ፈጽመውታል የተባለ አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ፡፡

አቶ ያሬድ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር ሲገባቸውና ሕዝብ እንዲያገለግሉ የተሰጣቸውን ሥልጣን ወደ ጎን በመተው፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ከነበሩት አለቃቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚቀበሉትን ትዕዛዝ ለበታቾቻቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች በማስተላለፍ፣ ዘግናኝና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውንና እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ቅድመ ምርመራ ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪው በርካቶች የግንቦት ሰባትና የኦነግ አባል እንደሆኑና በሽብርተኝነት እንዲጠረጠሩ እንዲታፈኑ ማድረጋቸውን፣ መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ የታፈኑ ዜጎች የታሰሩበትን ቦታ እንዳያውቁ ዓይናቸውን በጨርቅ በማሰር ወደ ሥውር የማሰሪያ ቦታ በመውሰድ፣ ከአምስት ወራት በላይ ታፍነው እንዲቆዩ ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡ በርካታ ዜጎች ታፍነው በተሰወሩበት ቦታ ከባድ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው፣ በካቴና በታሰሩ እጆቻቸውና እግሮቻቸው መካከል እንጨት በማስገባት ተሰቅለው እንዲደበደቡ፣ በኤሌክትሪክ በማንዘር (ሾክ በማድረግ)፣ በመግረፍ፣ ብልታቸው በፒንሳ እንዲጎተትና እንዲተለተል በማድረግ፣ ራቁታቸውን በቆሻሻ ቦታ በማቆየት፣ በጉንዳን እንዲበሉና ራቁታቸውን ጫካ ውስጥ እንዲጣሉ በማድረግ ከባድና ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውንም መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

አቶ ያሬድ የተጠርጣሪ ቤተሰቦችን በማገትና መያዣ በማድረግ ልጆቻቸውና ወገኖቻቸው ወደ ኤርትራ እንዲሄዱ ካደረጉ በኋላ፣ ድንበር ላይ በፀጥታ ሰዎች እንዲያዙ በማድረግ በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት ጋር ሊቀላቀሉ ሲሄዱ እንደተያዙ በማስመሰል ሐሰተኛ ክስ እንዲመሠረትባቸው ያደርጉ እንደነበርም በምርመራ መታወቁ ተገልጿል፡፡ በዚህ ድርጊታቸውም ሌሎች ዜጎች እንዲሸበሩና ተረጋግተው እንዳይኖሩ በማድረጋቸው፣ ከባድና ጭካኔ የተመላበት ኢሰብዓዊ ድርጊት በመፈጸም ወንጀል መጠርጠራቸውን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪው ለረዥም ጊዜያት የሕግ አስፈጻሚ ሆነው ሲሠሩ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ እንዲወጡ በከፍተኛ ገንዘብ በመደራደርና ያልተገባ ጥቅም በማግኘት፣ ያልተገባ ሀብት ማከማቸታቸውንና ሕዝብን ለማገልገል የተሰጣቸውን ሥልጣን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀልም መጠርጠራቸውን መርማሪ ቡድኑ አስታውቋል፡፡ አቶ ያሬድ በሕግ እንደሚፈለጉ እያወቁ በአግባቡ ቀርበው ለሌላው አርዓያ መሆን ሲገባቸው፣ ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመሰወራቸው በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ክትትል ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ አምስት ሰዓት በኦሮሚያ ክልል ዱከም አካባቢ በአንድ ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር አለማዋላቸውን ያወቁ ተጎጂዎች ወይም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመባቸው ዜጎች ፍርኃቱ ስላልለቀቃቸው የምስክርነት ቃላቸውን መቀበል አለመቻሉን፣ የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት መርማሪ ቡድኑ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቶ ያሬድ ፈጽመውታል የተባለው የወንጀል ድርጊት ግልጽ መሆን አለመሆኑን ጠይቋቸው ግልጽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለቀረበባቸው አቤቱታ ምላሽ የሚሰጡት በራሳቸው ወይም በሕግ ባለሙያ ታግዘው ስለመሆኑ ተጠይቀው፣ በችሎት የተገኙ ቤተሰቦቻቸውን ጠይቀው በሕግ ባለሙያ ለመታገዝ መልስ እንደሚሰጡም ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የእሳቸውን ክርክር በመስማት ለማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ ያሬድን ደብቀው እንዲሰወሩ (እንዲጠፉ) አድርገዋል ተብለው ተጠርጥረው የተያዙት የንስሐ አባታቸው አባ ሀብተ ማርያም ኃይለ ሚካኤልና የአቶ ያሬድ ሾፌር ነው የተባለው አቶ አሸናፊ ታደሰ፣ ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ የንስሐ አባት መሆናቸውን ያረጋገጡት መነኩሴው፣ የንስሐ አባት ያደረጓቸው የአቶ ያሬድ ባለቤት መሆናቸውንና አቶ ያሬድን የሚያውቋቸው በሰኔ ወር 2010 ዓ.ም. መሆኑንም ለፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ሁለቱንም ወደ ግሸን ይዘዋቸው መሄዳቸውን፣ አቶ ያሬድ ግን ‹‹መንግሥት ፈልጎኛል›› በማለት ከኮምቦልቻ ከመመለሳቸው ውጪ ምንም የማያውቁ መሆኑን ለፍርድ አስረድተዋል፡፡ የተናገሩት እውነት ስለመሆኑም በራሳቸው መስቀልና በመጽሐፍ ቅዱስ መማል እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡ አቶ ያሬድ ወንድሞችና አህቶች እያሏቸው ለእሳቸው ሚስጥር ሊነግሯቸው እንደማይችሉ ተናግረው፣ ስለእሳቸው የተባለው ሁሉ ሐሰት መሆኑንና እሳቸው ቤተ ክርስቲያንና ገዳማትን ከማሠራት ውጪ ሌላ ነገር እንደማያውቁም አክለዋል፡፡ እሳቸው የሚጠብቋቸው ሦስት ሕፃናት እንዳሉ በመጠቆም፣ ፍርድ ቤቱ ዋስትና ፈቅዶላቸው እንዲወጡና ባዘዛቸው ጊዜ እንደሚቀርቡ በመግለጽ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ አብሯቸው የታሰረውና የአቶ ያሬድ ሾፌር ነው የተባለው አቶ አሸናፊም የእሳቸው ረዳት እንጂ ሾፌር አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ አቶ አሸናፊም እሳቸው ያሉትን በማረጋገጥ ዋስትና እንዲከበርለት ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ግን ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ዋናው ተጠርጣሪ አቶ ያሬድ አለመያዛቸውን፣ የደበቁዋቸው ሰነዶችና ያጠፉትም ሰነድ ስላለ መረጃ ሊደብቁና ለተጠርጣሪውም መረጃ በመንገር ሊያሸሹ ስለሚችሉ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ፖሊስ አቶ ያሬድን ባለመያዙ ተጠርጣሪ መያዣ መሆን እንደሌለባቸው ለመርማሪ ቡድኑ በመንገር፣ ሰነዶችን በሚመለከት ግን ፍርድ ቤቱ ተገቢ ሆኖ ማግኘቱን በመግለጽ ከተጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ አሥር ቀናት ፈቅዷል፡፡ አቶ ያሬድ ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ሌሊት 5፡00 ሰዓት አካባቢ በቁጥጥር ሥር በመዋላቸው፣ መርማሪ ቡድኑ መነኩሴውንና ሾፌር ነው የተባለውን ግለሰብ ሊለቃቸው እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

ሌላው ባለፈው ሳምንት ኅዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በሑመራ በኩል ወደ ሱዳን ሊወጡ ሲሉ በትግራይ ክልል ልዩ ኃይል በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ በቀረበባቸው የወንጀል ድርጊት ላይ ክርክር አላደረጉም፡፡ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ተገልጾላቸዋል፡፡ ጄኔራሉ ከሰኔ 2 ቀን 2002 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. መጨረሻ ወር ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሠሩ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ቅድመ ምርመራ ያሳያል፡፡ መርማሪ ቡድኑ እንዳስረዳው በተለይ ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ በኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የውጭና የአገር ውስጥ ግዥ በእሳቸው ትዕዛዝ መፈጸሙን ጠቁሞ፣ ግዥዎቹ የተፈጸሙት ግን የኮርፖሬሽኑን የግዥ መመርያ ወደ ጎን በመተው ያለምንም ጨረታ መሆኑን አክሏል፡፡ ግዥዎች ሕግን መሠረት አድርገው መፈጸም ሲገባቸው፣ ሕዝብን ሊጠቅሙ የሚችሉ ትልልቅ ግንባታዎች፣ ማለትም የህዳሴ ግድብ፣ የህዳሴ ግድብ ደን ምንጣሮ፣ የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎች፣ የተለያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታዎችና ሌሎች የኢንዱስትሪ ሥራዎችን ማሠራት የሚችል በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከተለያዩ የፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች ጋር ውል መፈራረማቸውን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪው በገቡት ውል መሠረት ወይም በተቀበሉት ክፍያ ልክ በአግባቡና በገቡት ውል መሠረት አለመፈጸማቸውንም አብራርቷል፡፡ የመንግሥትና የሕዝብ ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው፣ ሕግን በመተላለፍ፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ኮንትራቶችንና ግዥዎችን ያለምንም ጨረታ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለቅርብ ጓደኞቻቸውና ሌሎች የውጭ ድርጅቶችን ለመጥቅምና ለመጠቀም በማሰብ፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም በርካታ የሕዝብ ገንዘብ እንዲዘረፍና እንዲባክን ማድረጋቸውንም መርማሪ ቡድኑ ተናግሯል፡፡ በከባድ የሙስና ወንጀል እንደሚጠረጠሩ እያወቁም ከአገር ሊወጡ በሑመራ በኩል ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አክሏል፡፡ በመሆኑም ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ጄኔራሉ ስለተጠረጠሩበት ጉዳይ ለፍርድ ቤቱ ካስረዳ በኋላ ዋና ዳይሬክተሩ ክርክሩን እንዴት እንደሚቀጥሉ፣ ማለትም በራሳቸው ወይም በሕግ ባለሙያ ተደግፈው ስለመሆናቸው በፍርድ ቤቱ ተጠይቀው፣ ሙያው ስለሌላቸው በሕግ ባለሙያ ተደግፈው መከራከር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም ሀብት ንብረት እንደሌላቸው፣ ያላቸው የወር ደመወዝ 4,000 ብር ብቻ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት የሕግ ባለሙያ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ሀብት እንዳላቸው ጠቁሞ ቢቃወምም፣ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በመሆኑም ምንም ዓይነት ሀብትና ንብረት እንደሌላቸው በመግለጽ መጽሐፍ ቅዱስ በመያዝ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት ተከላካይ ጠበቃ እንዲመድብላቸው ትዕዛዝ በመስጠት ለሐሙስ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዳር ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ሁለት ተከላካይ ጠበቆች የተመደቡላቸው ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ለክርክር ተዘጋጅተው የቀረቡ ቢሆንም፣ መርማሪ ቡድኑ ግን ሀብት እንዳላቸው፣ የፀረ ሙስና የሀብት ምዝገባ ሰነድ ይዞ በመቅረብ ተቃውሞ አቅርቧል፡፡ በሰነዱ ላይ የተመዘገበው 5,333 ብር፣ 80,000 ብር ግምት ያለው ተሽከርካሪና ቢሾፍቱ የሚገኝ መኖሪያ ቤት መሆኑንም አስረድቷል፡፡ ገንዘብ ወጪ ያደረጉበትን የባንክ ሰነድም አያይዞ አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሰነዱን ከተመለከተ በኋላ ጄኔራሉ እንዲያረጋግጡ ሰጥቷቸው ከተመለከቱት በኋላ፣ ‹‹እኔ ያስመዘገብኩት 5,000 ብር ብቻ ነው፣ ቤት የለኝም፡፡ ከተገኘብኝ ይወረስ፡፡ በባንክም ያለኝ ገንዘብ 2,500 ብር ብቻ ነው፡፡ የእኔ ሀብት ሰውነቴ ብቻ ነው (በእጃቸው አካላቸውን እየነኩ) የተመዘገበው ሀብት የእኔ አይደለም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ለደቂቃዎች ከተወያየ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ፣ ምንም እንኳን በፀረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበው ሀብት የእሳቸው መሆኑን ባያረጋግጡም፣ በ15 ቀናት ውስጥ ከባንክ 100 ሺሕ ብር ወጪ ማድረጋቸውን ሰነድ ስለሚያሳይ፣ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ፍርድ ቤቱ ገንዘቡ ያልቃል የሚል ግምት ስለሌለው፣ በራሳቸው የሕግ ባለሙያ ቀጥረው እንዲከራከሩ ብሏል፡፡ ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላቸው የሰጠውን ትዕዛዝም አንስቷል፡፡ በመቀጠልም ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ተጠይቀው፣ ‹‹ዘመዶቼ ካቆሙልኝ ልመካከር፤›› በማለታቸው፣ በችሎት ከተገኙ ዘመዶቻቸው ጋር ለደቂቃዎች እንዲነጋገሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ከተነጋገሩም በኋላ እስከ ማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ማግኘት እንደሚችሉ አስረድተው ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በእሳቸው የምርመራ መዝገብ የተካተቱት ወድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘውም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ኦፕሬሽን ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ፣ ከወንድማቸው ጋር በመመሳጠር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለኮርፖሬሽኑ እንዲሰጥ በማድረግ ከፍተኛ የሕዝብ ገንዘብ ብክነት እንዲደርስ ማድረጋቸውንና ተገቢ ያልሆነ ሀብት ማፍራታቸውን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡ ለተጨማሪ ምርመራም 14 ቀናት እንዲፈቀድለትም አመልክቷል፡፡

ተጠርጣሪው ፈጸሙ የተባለው ወንጀል ከተነገራቸው በኋላ እንዴት ክርክር እንደሚያደርጉ ተጠይቀው፣ ምንም ሀብትም ሆነ ንብረት እንደሌላቸው በመግለጽ፣ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ የእሳቸውንም ተቃውሞ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ስላላቸው ቋሚ ንብረት ጠይቋቸውም፣ ‹‹ምንም ነገር የለኝም፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛና የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን ሲያስረዱ፣ ደመወዛቸውን ፍርድ ቤቱ ጠይቋቸው፣ ‹‹አላውቀውም›› ካሉ በኋላ፣ ትንሽ አስበው ‹‹8,000 ብር ይሆናል›› ብለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የግለሰቡ ሀብት መኖር አለመኖር ወደፊት ታይቶና ተጣርቶ የሚወሰን መሆኑን በማስታወቅ፣ የመርማሪ ቡድኑን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ አድርጓል፡፡ ተከላካይ ጠበቃ ለኅዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርብላቸውም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ከሜቴክ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ከቀረቡት መሃል ተማሪ መሆኗን ለችሎቱ የገለጸችው ወ/ሪት ትዕግሥት ታደሰ፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ሠራተኛ ወ/ሮ ፍፁም የሺጥላና በድለላ ሥራ ላይ መሆኑ የተገለጸው አቶ ቸርነት ዳና ናቸው፡፡

ወ/ሪት ትዕግሥት በሕግ መፈለጉን እያወቀ ተሰውሯል ከተባለው በሜቴክ የኅብረት ማኑፋክቸሪንግ ግንባታ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ ጋር፣ የጥቅም ተባባሪ መሆኗን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡ ተፈላጊ ተጠርጣሪ የመንግሥት ሠራተኛ መሆኑን እያወቀች ከደመወዙ በላይ በሆነ ገንዘብ መኖሪያ ቤት፣ ተሽከርካሪና ሌሎች ጥቅማ ጥቅም በስሟ ማግኘቷንም መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡ ገንዘቡ የሕዝብ መሆኑንና ለሕዝብ ፕሮጀክት የሚውል እንደነበርም አክሏል፡፡

ወ/ሮ ፍፁም የሺጥላ ደግሞ፣ ‹‹ፍፁም ኢንተርቴይመንት›› በሚባል ድርጅት ከሜቴክ ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ለሕዝብ ፕሮጀክት ከተመደበ ገንዘብ ላይ 954,770 ብር ድጋፍ ተደርጎላት ጥቅም ማግኘቷንና በሕዝብ ገንዘብ ላይ ጉዳት ማድረሷን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበት ወንጀል ከተነገራቸው በኋላ፣ ክርክሩን እንዴት እንደሚቀጥሉ ተጠይቀው ምንም ዓይነት ሀብትም ሆነ ንብረት እንደሌላቸው ለፍርድ ቤቱ በመግለጽ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል፡፡ ሁለቱም ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ ተደርገው የተከላካይ ጠበቃ ጽሕፈት ቤት ጠበቃ እንዲሰየምላቸው በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተመድቦላቸዋል፡፡

የተመደቡላቸው ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና እንደማይከላከል፣ ተጨባጭ የሆነና የወንጀል ፍሬ የሌለው ጥርጣሬ በመሆኑ፣ የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው በውጪ ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ወ/ሪት ትዕግሥት ተማሪ መሆኗን ለፍርድ ቤቱ ገልጻ፣ የፈተና ወቅት በመሆኑ መፈተን እንድትችል ለፍርድ ቤቱ አመልክታለች፡፡ መርማሪ ቡድኑ ግን ገና የሚያጣራው ምርመራ እንዳለውና ተባባሪያቸውንም መያዝ እንደሚቀረው በማስረዳት፣ ዋስትናውን ተቃውሞ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፣ መርማሪ ቡድኑ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ አሥር ቀናት በመፍቀድ ለኅዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ወ/ሪት ትዕግሥት የመፈተኛ ፕሮግራሟን በማመልከቻ ስታሳውቅ እንደሚፈቀድላት ተነግሯታል፡፡

ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም ታስረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሳጅን ኪዳኔ አሰፋና አቶ ሳሙኤል ጊዴሳ ናቸው፡፡ ሳጅን ኪዳኔ ኦነግና የግንቦት ሰባት አባላት ናቸው ተብለው በሕገወጥ መንገድ ታፍነውና ዓይናቸውን ታስረው ሥውር እስር ቤት ገብተው የነበሩ በርካታ ዜጎችን በመግረፍ፣ በመደብደብና የተለያዩ ሥቃዮችን በማድረስ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡

አቶ ሳሙኤል የተባለው ተጠርጣሪ ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አባል የነበረ መሆኑን መርማሪ ቡድኑ ጠቁሞ፣ እሱም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከውጭ በር ላይ አፍኖና ዓይናቸውን አስሮ በመውሰድ ከአምስት ወራት በላይ በማቆየት ከፍተኛ የሆነ ድብደባና ሥቃይ በማድረስ፣ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን አስረድቷል፡፡ ግለሰቡ ሰበታ አካባቢ የሚገኙ ባለሀብቶችንና ነዋሪዎችን ‹‹ደኅንነት ነኝ›› በማለት፣ በማስፈራራትና በሐሰት ማስረጃ እንዲታሰሩ በማድረግ ተገቢ ያልሆነ ሀብት መሰብሰቡንም መርማሪ ቡድኑ ተናግሯል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ፈጽመዋል የተባለው የወንጀል ድርጊት ከተገለጸላቸው በኋላ ሀብት ንብረት እንደሌላቸው በመሃላ በማረጋገጣቸው፣ ተከላካይ ጠበቃ ተመድቦላቸዋል፡፡ የቆሙላቸው ጠበቆች ግለሰቦቹ ላይ የቀረበው ክስ ዋስትና እንደማይከለክል ገልጸው፣ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ቢጠይቁም መርማሪ ቡድኑ ተቃውሟል፡፡ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ከሰማ በኋላ ዋስትናውን ውደቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀናት በመፍቀድ ለኅዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ሌላው በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው በሜቴክ ሥር የሚገኘው የፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል አሰፋ ዮሐንስ ናቸው፡፡ ኮሎኔሉ የሜቴክ ሠራተኛ እንደነበሩ መርማሪ ቡድኑ ጠቁሞ፣ ወደ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ሲቀየሩ የጣና በለስ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካን ለማስገንባት ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር የ55,640,000 ዶላር ውል በመፈጸም፣ ኩባንያው ሥራውን ሳይሠራ ከአገር ሲወጣ ዝም ማለታቸውን አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል ከሌላ ኩባንያ ጋር ደግሞ የ6,400,000 ዶላር ውል ፈጽመው ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተከፈለው በኋላ፣ ሥራ ሳይሠራ ከአገር ሲወጣ ዝም ማለታቸውንና አገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ችግር እንዳለባት እያወቁ ገንዘብ እንዲሸሽ ማድረጋቸውን መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪው የሕግ ዕውቀት እንደሌላቸው ተናግረው ደመወዛቸው 8,000 ብር እንደሆነና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን፣ በስማቸውም ሌላ ምንም ቋሚ ንብረት እንደሌላቸው ተናግረው፣ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው በመሃላ አረጋግጠው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው ትዕዛዝ  ሰጥቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባልደረባ የነበሩትን አቶ ተስፋዬ ኡርጌና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ኮሎኔል ጉደታ ኦላናና ኮሎኔል ሰጠኝ ካሳዬ የተባሉ ግለሰቦችን መርማሪ ቡድኑ አስሮ ያቀረባቸው ቢሆንም፣ ለችሎቱ የቀረበው አቤቱታ የወጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግን የተከተለ ባለመሆኑ፣ ተስተካክሎ ለሰኞ ኅዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. የቦምብ ጥቃት ተጠርጥረው ከታሰሩ አምስት ወራት ሆኗቸዋል፡፡

ሰሞኑን ከኅዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር የዋሉና በመፈለግ ላይ የሚገኙ 96 ተጠርጣሪዎችና ቤተሰቦቻቸው የባንክ ሒሳብ፣ ንብረትና ድርጅቶቻቸው እንዳይሸጡ፣ እንዳይለወጡና ለሦስተኛ ወገን እንዳይዘዋወሩ በፍርድ ቤት ዕግድ ተጣለባቸው፡፡

ዕግድ ከተጣለለባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘና ቤተሰቦቻቸው፣ የብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዲና ቤተሰቦቻቸው፣ የብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትለ፣ የአቶ ጌታቸው አሰፋና ልጃቸው፣ የሀሺም ቶፊቅ (ዶ/ር)፣ የአቶ ያሬድ ዘሪሁንና የ14 ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በአጠቃላይ የ192 ሰዎች የባንክ ሒሳብ፣ ተንቀሳቃሽና ቋሚ ንብረት፣ እንዲሁም 13 ድርጅቶች እንዳይሸጡ፣ እንዳይለወጡና ለሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ዕግድ ተጥሎባቸዋል፡፡

 

 

/ሪፖርተር

 

 

አንዳርጋቸው ጽጌ ከቤተልሄም ታፈሰ ጋር!መታየትና መደመጥ ያለበት ቃለ መጠይቅ!

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

Why I disagree with UNSG Guterres’ appointment of ‘Gen. Gabre’ UNISFA Force commander, the walking terror tainted by human rights crimes & corruption in the Horn!

11 Apr

By Keffyalew Gebremedhin The Ethiopia Observatory (TEO)
 

PART One of two

Maj-Gen. Gabre, as they refer to him in Somalia, possibly picked from his twitter handle

The purpose of this article is to express the writer’s disappointment at and opposition to the April 4, 2018 appointment by United Nations Secretary-General António Guterres of Maj-Gen. Gebre Adhana Woldezgu as commander of the United Nations Interim Security Force for Abyei (UNISFA).
Continue reading

Trump’s Tough Approach to Ethiopia

9 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Rachel Ansley, The Atlantic Council
 
US Secretary of State Rex Tillerson traveled to Ethiopia this week to underscore US support for a crucial partner that finds itself in a crisis.

Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn resigned unexpectedly on February 15 in the wake of violent anti-government protests. The government then imposed a nationwide state of emergency that lawmakers endorsed earlier in March.
Continue reading

%d bloggers like this: