Tag Archives: investigation continues

መርማሪ ፖሊስ በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ እጅ ቦምብና የጦር መሣሪያ መገኘቱን ገለፀ: ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታን ማስተባበር ጋር የተያያዘ ነው!

23 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት የመምሪያ አዛዥ ናቸው ብሎ መርማሪ ፖሊስ ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታን በማስተባበር ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የሚገኙት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚሰሱ ግጭቶች እጃቸው እንዳለበት መርማሪ ፖሊስ አስታወቀ።

እንደ መርማሪ ፖሊስ ገለፃ፥ ይህንን ተከትሎ በተደረገ ምርመራም ቦምብ እና የጦር መሳሪያ እንደተገኘባቸውም ጠቁሟል።

ሌላም ያልተያዘ የጦር ማሳሪያ እንዳለ የጠቆመው ፖሊስ፤ ይህንን ለመያዝ እየሰራ መሆኑንም ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ 1ኛ የወንጀል ችሎት አስረድቷል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማና ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ያሉ ተጨማሪ የቃል ምስክሮችን ለመቀበል ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቃ በበኩላቸው ተጠርጣሪው እጃቸው ከተያዘ 43 ቀን በመሆኑ በዚህ ጊዜ ውስጥ በተሰጠ ተጨማሪ ጊዜ ፖሊስ ተመሳሳይ ጥያቄ ማንሳቱን ጠቁመዋል።

ጠበቃው አክለውም መጀመሪያ ከተጠረጠሩበት ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ውጭ አሁን ተጨማሪ ጊዜ እየተጠየቀባቸው ያለው በሌላ ወንጀል ነው፤ ይህ ተገቢ አይደለም ያሉ ሲሆን፥ ይህ የመርማሪ ፖሊስን አሰራርም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነውም ብለዋል።

ደንበኛዬ በዋስ ሊወጣ ይገባል ሲሉም የመርማሪ ፖሊስን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱ በበኩሉ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የተጠረጠሩበትን ዋና ጉዳይ እንዲያብራራ የጠየቀ ሲሆን፥ የተጠረጠሩበት የግድያ ነው ወይስ የወንጀል ነው ሲል መርማሪ ፖሊስ ግልፅ እንዲያደርግ ጠይቋል።

መርማሪ ፖሊስ በሰጠው ማብራሪያም አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ከእሳቸው በላይና በታች ካሉ ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የሰኔ 16ቱን የቦምብ ፍንዳታ በማስተባበር እንዲፈነዳ አድርገዋል፤ በዚህም የ2 ሰው ህይወት አልፏል ብሏል።

 በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች እንዲነሱ በማድረግ በሽብር ወንጀል የሚጠረጠሩ እንደሆነ እና በዚህ ላይ መርመራ እያደረገ መሆኑንም አብራርቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተደረገ ምርመራም ቦምብና የጦር መሳሪያ እንደተገኘባቸውም መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የተጠርጣሪ ጠበቃው በበኩላቸው፥ የመርማሪ ፖሊስ ምክንያት ተመሳሳይ ነው፤ ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የሌሎች ተጠርጣሪዎች ምርመራ ተጠናቆ ሳለ ለብቻቸው በሌላ ወንጀል ምርመራ በሚል ተጨማሪ ጊዜ ሊጠየቅ አግባም ሲሉ ተቃውሟቸውን አቅርበዋል።

ፖሊስም ከእሳቸው ጋር ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የሚገኙ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ምርመራ አለመጠናቀቁንና እስካሁንም ክስ እንዳልተመሰረተ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ፍርድ ቤቱም አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የተጠረጠሩበት የወንጀል ሁኔታ ወደ ሽብር የሚወስድና ክብደት ያለው ነው፤ ይህ ደግሞ ምርመራው በቀናት ብቻ የሚገመት አይደለም ዓመታትንም ሊወስድ ይችላል በሏል።

ፍርድ ቤቱ ከወንጀሉ ክብደት እና ውስብስብነት አንፃርም የዋስትና ጥያቄውን ወደ ጎን በመተው መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ሙሉ ጊዜ ሰጥቼዋለሁ ሲል ፈቅዷል።

Investigation stalls in case of 9 detained journalists and bloggers

18 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
By Reporters Without Borders

Nine journalists who were arrested on 25 and 26 April continue to be detained pending trial. When the latest detention hearing in their case was held on 14 June, a judge gave the police yet more time to complete their investigation and finally determine the charges.
Continue reading

Europe’s horsemeat scandal and lessons developing countries must draw (Part II)

21 Feb

By Keffyalew Gebremedhin

Since the publication of Part I of this article (here) on February 18, there have been some interesting developments:

      ♦   France has cooled of resulting in partial lifting of the ban on Spanghero’s license – the culprit behind the mislabeling of horsemeat as beef;

      ♦   Finland, which a few days ago indicated, it was being roped into the scandal via the German chain Lidl, has further confirmed finding mislabeled horsemeat packages. The latest finds include 200-300 boxes of frozen horseburger patties in ‘unnamed’ store(s) and kebab meals in K stores, which Pouttu has recalled. It is reported that K chain has stopped sales of Pirkka products by Pouttu as a precaution;

      ♦    Nestle, the world’s largest food producer has announced removing food items tainted with horsemeat from stores in Italy and Spain; and

      ♦    Finally, the reach of the scandal has extended into Asia, Hong Kong being the first with Findus lasagna emplaced in supermarkets.

Continue reading

Europe’s “equine exposé”: What could the next screwball be? Lessons for developing countries (Part I)

17 Feb

By Keffyalew Gebremedhin

In the circumstances, this seem to be the right question to ask, if you ask me. Some governments in Europe have known long in advance about the scandalous business in horsemeat, according to media reports. But they did nothing.
Continue reading

%d bloggers like this: