Tag Archives: Kerroo

በሕገወጥ መንገድ እየተሰባሰቡ ግጭት የሚፈጥሩ ወጣቶች ሥጋት መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

23 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች በሕገወጥ መንገድ በመሰባሰብ በየሠፈሩ፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በሕዝብ ትራንስፖርት መተላለፊያ መንገዶች ላይ ግጭት እየፈጠሩ ያሉ ወጣቶች፣ ሥጋት እንደሆኑ ነዋሪዎች ለሪፖርተር ተናገሩ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ በኮዬ ፈጬና በቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 አካባቢ ጥቅምት 9 እና 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰላማዊ ነዋሪዎችና በውይይት ላይ ይገኙ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ ሁከትና ብጥብጥ የፈጠሩ እነዚሁ ወጣቶች፣ በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ አቶ ሰለሞን ገብሬ፣ ወ/ሮ ብርቄ ጉተማና  አቶ መስፍን ገብረ ሥላሴ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ እሑድ ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ረብሻና ግጭት ተፈጥሯል፡፡

ምክንያቱን ሲገልጹ ጥቅምት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ኮዬ ፈጬ አካባቢ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ሲያደርጉ፣ ወጣቶቹ በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል፡፡ የተለያዩ ስለቶች፣ ዱላና ድንጋይ ይዘው በመጮህ የምክክር መድረኩን አስተባብረዋል ባሉዋቸው ግለሰቦች ላይ ድብደባ በመፈጸም ጉዳት ማድረሳቸውን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል፡፡አንዲት ወጣት የለበሰችውን ዓርማ ያለበት ቲሸርት በማስወለቅ መቅደዳቸውንና እንደ ደበደቧት ነዋሪዎቹ ገልጸው፣ ሕገወጥ ስብስቦቹ የአካባቢውን ሰው በማስፈራራትና ነዋሪዎች ተረጋግተው ኑሮአቸውን እንዳይመሩ ሥጋት እንደሆኑባቸው አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ኮዬ ፈጬ አካባቢ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት ስብሰባቸውን እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ሆ ብለው ወደ ስብሰባው የሄዱት ወጣቶቹ፣ የአፀፋ ምላሽ ከተሰብሳቢዎቹ በኩል ሊገጥማቸው ሲል የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው እንዳስቆሟቸውም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው በተወሰኑ ወጣቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም ለጊዜው ያንን ያህል የተጋነነ እንዳልሆነም አክለዋል፡፡

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የፀጥታ ሁኔታ መከታተልና መጠበቅ ያለበት የከተማው ፖሊሲ ቢሆንም፣ ቆሞ ከማየት የዘለለ ምንም ሲያደርግ አለመመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ውስጥ ተከስቶ የነበረው ግጭት በጠብመንጃ ተኩስ መበተን ባይቻል ኖሮ ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ከፍተኛ ይሆን እንደነበር ተናግረው፣ ወደ ሌሎች ቅርብና አጎራባች ወረዳዎች የመዛመት ዕድል ይኖረው እንደነበር ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በተለይ አሁን ካለው የፀጥታ ችግር አንፃር ጥብቅ ክትትል በማድረግ፣ የነዋሪዎችንና የከተማውን ሰላም ማስጠበቅ ቢኖርበትም ችላ ያለው እንደሚመስላቸው ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ነዋሪዎች መኖሪያ ብቻ ሳትሆን፣ የዓለም አቀፍ ተቋማትና የአፍሪካ መዲና በመሆኗ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሊያደርግበትና ሰላም እንዲሰፍን ተግቶ መሥራት እንዳበለት አሳስበዋል፡፡

የተለያዩ የአገሪቱ መውጫና መግቢያ መንገዶችን መዝጋትና መንገደኞች እንዳይተላለፉ የማገድ ሕገወጥ ባህሪ፣ በመዲና ከተማዋ ደግሞ በሕገወጥ ስብስቦች ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር ከቀጠለ ነገ የት ሊደረስ እንደሚችል መንግሥት ተረድቶ፣ የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ያነሱትን ሥጋትና የሕገወጥ ስብስብ ቡድን ስለተባለው ጉዳይ ማብራርያ እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎችን ሪፖርተር ለማነጋገር የሞከረ ቢሆንም፣ ‹‹በአጠቃላይ ስላለው ሁኔታ ማብራርያ እንሰጣለን ጠብቁ፤›› በመባሉ ምላሹን ማካተት አልተቻለም፡፡

/ሪፖርተር

Stand-off at Ethiopian activist Jawar Mohamed’s home amid tensions with PM Abiy Ahmed

23 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ADDIS ABABA (Reuters)  Hundreds of supporters of an Ethiopian ethnic activist and media entrepreneur gathered outside his house on Wednesday, a day after it was surrounded by security forces following a warning by the prime minister against media owners “fomenting unrest”.

At least 400 young men joined the protest at the property in the capital Addis Ababa, a Reuters witness said, chanting their support for activist Jawar Mohammed and against Prime Minister Abiy Ahmed, the winner of this year’s Nobel peace prize.

Jawar, who holds a U.S. passport, is the founder of the independent Oromia Media Network and has a very active presence of social media, with 1.4 million Facebook followers, which he has used in the past to organize strikes and protests.

Two dozen federal police had surrounded the house on Tuesday night, a Reuters witness said, forcing Jawar’s bodyguards to leave.

It was not clear why Jawar’s house was surrounded, but earlier on Tuesday Abiy, speaking in parliament, had warned unnamed media owners against fomenting unrest.

“Those media owners who don’t have Ethiopian passport are playing both ways. When there is peace you are playing here and when we are in trouble you not here,” he said.


 

ቢቢሲ አማርኛ ከአንድ ሰዓት በፊት እንደዘገበውና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ለመገናኛ ብዙኀን እንዳስረዱት፤ ጃዋር መሀመድ ለተከታዮቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ልታሠር ነው፣ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው ብለዋል። ዐቢይ ከመጣ ጀምሮ፡ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ የማላምነው የፖሊስ መግለጫዎችን ነው! ይህም የሚያሳየው ያንኑ ነው!


“We tried to be patient. But if this is going to undermine the peace and existence of Ethiopia, whether you speak Amharic or Oromiffa, we will take measures. You can’t play both ways.”

Amharic and Oromiffa are the languages of the country’s largest ethnic groups.

Jawar, who promotes non-violent activism and an “Oromo first” ideology, returned to Ethiopia from the United States in August last year, a few months after Abiy come to power. Oromo are the country’s largest ethnic group, to which both Jawar and Prime Minister Abiy belong.

The young men gathered outside Jawar’s house call themselves “Qeerroo”, an Oromo term meaning “bachelor” adopted by politically active young men.

Wearing hooded sweatshirts, they shouted “Jawar, Jawar” and “Abiy Down! Abiy Down!”

“I was about to go to bed when I saw Jawar’s post that his house was surrounded by security without his knowledge. I called three of my friends and came running and saw more Qeerroos and Qarrees when I arrived at his house,” Terefe Waltaji, a 27-year-old student, told Reuters.

Federal Police Spokesman Jeylan Abdi said they had not received any information on what was happening at Jawar’s house.

A spokesperson for Abiy did not respond to requests for comment.

Abiy, who won the Nobel prize this month for his peacemaking efforts with longtime enemy Eritrea, came to power in April 2018 and began introducing political and economic reforms.

Those reforms have opened up what was once one of Africa’s most repressive nations, but also stoked violence as emboldened regional strongmen build ethnic powerbases and compete over political influence and resources. REUTERS

 

 

%d bloggers like this: