Tag Archives: lack of accountability

የኢትዮጵያ የፊናንስ ተቋሞች ቢሊዮኖች ከፍለው የሸገርን ራት ቢቋደሱም ካልተፈቱት የሃገሪቱ ችግሮቻችንና ነገን አያመልጡም!

5 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ሪፖርተር ባለፈው እሁድ የኅዳር መግቢያ የሰሞኑን ዜና የያዘው ዕትሙ፡ ንግድ ባንክ ‹‹ገበታ ለአገር›› ፕሮጀክቶች የ1.1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ  ይላል። በተጨማሪ በዚህም ዘገባ እስካሁን “በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረበው ጥሪ ከተሰጡ ድጋፎች ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡”

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ “ለእነዚህ [ሶስት] ፕሮጀክቶች ለቀረበው ጥሪ ባንኩን የሚመጥን ዕገዛ ማድረግ መቻላቸውን ጠቁመው ‘ትልቅ ኩራት ይሰማናል’ ማለታቸው ተገልጿል—ምንም እንኳ ምንም እንኳ ይህ በዘፈቀደ በየወቅቱ የሚረጨው ገንዘብ የባንክ አስተዳዳሪዎቹ ባይሆንም!

ባንኩ ስለዚሁ ሥጦታ ጥቅምት 30/2020 እንዳሳወቀውና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በወቅቱ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላቀረቡት “የገበታ ለሃገር ፕሮጀክት የልማት ጥሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀዳሚውን ድርሻ ወስዶ ምላሽ መስጠቱ የሚያስመሰግንና ከአንድ ትልቅ የፋይናንስ ተቋም የሚጠበቅ ነው” ብለውታል። ባንኩ በራሱና በሠራተኞቹ ስም ስለዚሁ ባካፈለው መረጃ መሠረት፥

“የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠራተኞች መሠረታዊ ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ኦላኒ ሳቀታ እንዳሉት ደግሞ ሠራተኛው ለሃገራዊ የልማት ጥሪዎች የሚያደርገው ተሳትፎ የላቀ መሆኑን አስታውሰው፣ በገበታ ለሃገር ጥሪ ላይም የራሱን አሻራ ለማኖር የሚያስችለውን ምላሽ በዚህ መልኩ ማድረጉ ደስታን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ሸገርን ለማስዋብ ፕሮጀክት የ500 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያደረገው የ1.1 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የጎርጎራ፣ የወንጪና የኮይሻን ፕሮጀክቶች በማልማት ቱሪዝምን ለማስፋፋት ለተነደፈ “ገበታ ለሃገር” ፕሮጀክት የሚውል ነው።”

ተቋማዊ ግቦቻችንን ሥተናል!

በዚህ የሚሊዮኖችና ቢሊዮኖች ለመበተን በሌላው ወገን ደግሞ መሰብሰብ የመቻልን ብተና ነፃነትን ጉዳይ ሃሣቤን ወረቀት ላይ ሳሳርፍ ትዝ ይለኝ የነበረው የጀርመኑ ፈላስፋ ፍሬድሪሽ ሄግል ‘ታሪክ ራሱን ይደግማል’ ብሂል ነበር። ይህም የሆነው የነዐባይ ፀሐዬ ጥረት ለዘመናት እጅግ ፍሬያማ የነበረውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አኮላሽቶ፡ ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሸጋገሩ ነበር። በወቅቱ ለእኔም ያለተገለጸልኝ፡ በተለይም ለምን ማርክስን እንዳናደው ነበር።

ማርክስ የራሱን ምልከታ ለሄግል በጻፈው ምንባብ እንደተገለጸው፡ ይሁንልህና ታሪክም ራሱን ይድገም፤ ራሱን ከደገመ ደግሞ መሆን ያለበት: “አንዴ በኃዘን (tragedy) ሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በከንቱነት (farce) ይሆናል ያለውን ማስታወስ ለሃገራችንም በተለይም የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በዘረፋ መክሰም/ውድቀት ማሰላሰልና፡ አሁንም በ1942 ዓ. ም.የተቋቋመው ትልቁ ባንካችን—የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን —የወደፊት ጉዞ ለማሰላሰል ይረዳል በማለት ነው

ጋምቤላ ላይ ሕወሃት እንኳን በበድኑ ላስቀረው ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማስታወሻ ሃውልት ሊያሠራ፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ባንኩን በቦርድ ሊቀመንበርነቱ በበድኑ እንዲቀር  መንገዱን የቀየሰው ዐባይ ፀሐዬ ልማት ባንክን ሳይቀብር ነበር ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቦርድ አመራርነት ያቀናው።

ሥራው ነውና እንደደረሰም የዓላማ ትሥሥር ካለው ከበረከት ስምዖን ጋር የንግድ ባንኩን ለእነዓላሙዲ የገንዘብ ፋብሪካ ለማድረግ ብዙም አልፈጀባቸውም።  ይህም በወቅቱ በሚዲያ ብዙ ዜጎች እያነሱ ይከራከሩበት የነበረውን እሰጥ አገባ ልክ እንደዛሬ አስታውሳለሁ።የዐባይ ጸሐዬ ወደ ዕድሜ ጠገቡ (ዘንድሮ 78 ዓመቱ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማቅናት፡ የልማት ባንክ ጽዋም ወደ ንግድ ባንክ እንደሚመጣ እርግጠኛ የሆኑት ባለሙያዎች—እንደተወነጀሉት እሳቱን ማፋፋም የፈለጉ ሣይሆኑ—በሄግል ዕይታ ለሃገር ተቆርቋሪ ነበሩ ቢባል ለማይገባው ዋጋ  መሥጠት አይመስለኝም።

እስካሁንም በየወቅቱ ባንኩን እያጋጠሙ ያሉት ችግሮች አለመፈታታቸው ይህንኑ አመላካች ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ነባርና አዳዲስ ችግሮች በተለያዩ ወቅቶች በዝቅተኛ ውጤት ማለፉ ግን በረዥም ጊዜ የተጣለበትን ኃላፊነት ተወጥቷል፤ ይወጣልም ለማለት አያስችልም—በተለይም በአሁኑ ወቅት! እኔ ከብዙ ዓመታት በፊት ያየሁት Ranking of African Commercial Banks የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘመናዊ ሥርዓት የተያዘ ተብሎ ከአፍሪካ ባንኮች በ10ኛ ደረጃ ላይ ነበር። በብዙ ችግሮች መተብተቡና አሁን ደግሞ የዘር ፖለቲካ ም በተለይም በዘር መሳሳቡ፣ይህንን የሃገር ትልቅ ባንክ በካፒታሉ መሥፈርት ዛሬወደ54ኛ ደረጃ አሽቀንጥሮት ሳየው፣ የራሳችን ጠላቶች እኛው ራሳችን መሆናችንን አሳምኖኛል።

በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች ይመስላል፣ ረዥም ጉዞውን ከ15 ሃገራዊ ንግድ ባንኮች ጋር አወዳድሮ በ2019 የገመገመው የEuropean Journal of Business Science and Technolology  ጥናት እንዳሳየው፣ በነበረው ምቾት በአንዳንድ መስኮች ትልቁ ንግድ ባንክ ቀዳሚነት ቢያሳይም—ንግድ ባንኩ ሊይዝ የቻለው የስምንተኛነት ደረጃ ያለው አሳሳቢ ችግር ላይ ጣት ይጠነቁላል።

አሁን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ በገበታ ስም በተደጋጋሚ በፊናንስ ዘርፉ ላይ የሚካሄደው መታለብ፣ለወደፊቱ የከፋ አደጋን ያረገዘ ሆኖ ታይቶኛል። እኔን በቀዳሚነት የሚያሳስበኝ፡ ይህ በልማት ስም ያለተጠያቂነት ግራና ቀኝ የሚረጨው የሃገር ገንዘብ ጉዳይ ነው።

ለምንድነው ሌሎቹ የግል ባንኮች ገንዘብ ያላዋጡት—ያዋጡም ካሉ ሁለት ብቻ ከ30 ሚሊዮን ያልበለጠ የከፈሉት?—ገንዘቡ ባለቤቶች ስላለው አይደለምን? ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ያለው ግን ባለቤት የሌለው ገንዘብ በመሆኑ አይደለምን? ገና ሌላ ጉዶችም አሉ!

Picture credit: PM’s FB

እየተንገዳገደ ያለው ይህ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሠራተኞቹ 1.1 ቢሊዮን ብር ጥቅምት 30/2020 ዓ.ም. ‘ለገበታ ለሃገር’ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸውናል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባንኩ ያደረገውን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሃገሪቱ ለሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ልማቶች የፋይናንስ ምንጭ ከመሆኑም ባሻገር፣ በየጊዜው ለሚቀርቡ የልማት ፕሮጀክት ጥሪዎች ፈጣንና ከፍተኛ መጠን ያለውን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ነው”ብለዋል።

ይህ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተያያዙት አዲስ አበባን የማስዋብ ፕሮጄክት—ብዙ ማከናወን የሚያስችል መሆኑ ቢገመትም— ያላንዳች በሕገ መንግሥቱ ተቀባይነት ባለው ላዕላይ መዋቅር ክትትል፥ ዕቅድና የሥራ ዓላማው አፈጻጸም ግምገማ ተደግፎ የሚካሄድ ባለመሆኑ፣ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ቢታመንበት እንኳ—ዜጎችን ጥርጥር ላይ ጥሏል።

በተጨማሪም የበጎ ፈቃድ ሣይሆን፣ የጣሊያን ማፍያ ሥራ ይመስል፡ በብልፅግና ፓርቲ በየመሥሪያ ቤቱና በየደረጃው በተሰባሰቡ ማኔጀሮች፣ ባለሥልጣኖች አማካይነትና የመሠረታዊ ድርጅት አባላት በኩል ጥሪውን ያደረጉትን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማስደሰት፣ የወር ደሞዝ ከየመሥሪያ ቤቱ ለማሠባሠብ እንቅስቃሴ በግዳጅ እንደተደረገ ተሠምቷል!

በሥውር ግዳጅ ክፍያ ደሞዛቸውን እንዲያዋጡ የማስገደድ ተግባርም ስለሚፈጸም፡ በተለይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞችመካከል ቁጣ መቀስቀሱ በተለያዩ ሚዲያዎች በሠፊው ተሠራጭቷል። ለምን ይኽ ማስፈራራት (በወደፊት ዕድገትና የሥራ ድልድል፣ በገዥው ፓርቲ ድርጅታዊ ሕዋሳትም በሥውርም ደኅንነቱ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ጠነከረ ለሚለው —ተጠያቂነት በጠፋባት ኢትዮጵያ—ባንኩ ባለቤት እንደሌለው ተደርጎ በመቆጠሩ መሆኑንና ዜጎችተጠያቂነት በጠፋባት ኢትዮጵያ፡ ባንኩ ባለቤት እንደሌለው ተደርጎ በመቆጠሩ መሆኑንና የባንኩ የቦርድ አባላት እነማናቸው ለሚለው መልስ ማግኘት ይኖርባቸዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምነው ንግድ ባንኩ ላይ እንዲህ አተኮሩ?

በአብዛኛው የባንኩ የቦርድ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አብረው የሚሠሩ፣ የተቀራረበ ግንኙነትና የዓላማ አስፈጻሚነት ላይ የተሠማሩ ስዎች መሆናቸው፣ እስትንፋስን ያግታል።

ዝርዝራቸውን ከባንኩ  Board of Directors ገጽ ላይ፡ ከነፎቶግራፋቸው ጭምር ይመለከቱ!

ለምንደነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች ብዙ ገንዘብ ካለው ቁጥጥር የለበትም ከሚባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ አተኮሩ የሚለው ጥያቄ ተገቢው መልስ ሊገኝለት ይገባል! አለያ፣ ሃገራችን በዲሞክራሲ ነገዋ ችግሮቿ በረፓብሊካን ጋርድ (ምናልባትም መደበኛ ባልሆኑ ኃይሎች አፈና ጭምር) አደጋ ላይ መውደቁ ብቻ ሣይሆን፣ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚም የሃገራችን ሕዝብ ሃብትና ንብረት መሆኑ ይቀራል!

ስለሆነም፣ በአሳዛኙ የሃገራችን ልምድና ባሕሪም ምክንያት—እንደማናቸውም በዐቢይ አሕመድ አመራር እንደሚፈጸም ዕቅድና ሥራዎች ሁሉ—በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘ገበታ ለሃገርም’ በሌለ ሃብት ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍላጎት ከሌሎች አስፈላጊና አንገብጋቢ የኅብረተሰብ ችገሮች ልቆና ተሻሚ መሆኑ ከመንግሥታዊም ሆነ ከግል የአፈጻጸምና የሃብት አጠቃቀም ግምገማ ነፃ በመሆኑ፡ እጅግ ያሳስባል፤ አላስፈልጊ ላልሆነ ጥርጥርም በር ከፍቷል።

በሃገሪቱ ውስጥ መንግሥታዊ መዋቅሮች በሕግና ተጠያቂነታቸውን እንዳያዳብሩ ብልፅግና ፓርቲ በየርሥፍራው ሰው ለመብላት በተዘጋጁ ነፍሰ በላዎችና በጠቅላይ ሚኒስትሩና ላይ ካሉ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው የተባሉትን ብቻ አነብናቢዎችና ለሃገርና ሕዝብ አገልግሎት ከማበርከት ይልቅ፣ ግርድና የሚቀላቸውን በማይመጥኗቸው ሥፍራዎች በመትከል፣ ሃገራችን ላይ ‘ሥውር አደጋ’ እየተፈጸመ ነው! ይህ ሕገ ወጥንነት የሚፈጸመው ያለምክንያት አይደለም!

እንደሚታወስውም በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ እርሳቸው ከፍተኛ ገንዘብ እየፈሰሰባቸው የሚያሠሯቸው የሸገርን ማስዋብ ጉዳይና የቱሪስት መስህቦችን መፍጠር ለመንግሥታዊ ተቋም ግንዛቤና ክትትል ዘገባ ይቅረብ ቢባሉ፡ ‘ለምኜ ለማመጣው ገንዘብ—(በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ መዋቅሮችና መሬት ላይ ቢሆንም እንዳይታይ)—ፓርላማውንም ሆነ ማንንም አያገባውም ማለታቸው፣ ፓርላማውን አንገት ከማስደፋት ውጭ እስከዛሬ የፈየደው ነገር የለም!

ዐቢይ ፓርላማ አባላትን ማስፈራራት ይጀምር ይሆን?

ፓርላማው ኅዳር 3/2020 ባደረገው ስብሰባ፣ ወለጋ የዐቢይ መንግሥት ፊቱን አዙሮ ችላ ባለው ኦነግ ሸኔ በዜጎቻችን ላይ በየጊዜው የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ አሁንስ በቃን በሚል ተነሳሽነት በቁጣ የመንግሥት እጅ አለበት ብሎ ቁጣውን በብዙ አባላት እምባ ጭምር መግለጹ፣ ከእንግዲህ በባንኮቻችንና መንግሥታዊ ተቋሞቻችንን መንግሥት የሚፈጽመውን ጥፋት ብዙ ሊታገሠው ይቻላል ብሎ ማመን አይቻልም! የፓርላማ አባላትም ላይ ዐቢይ ማስፈራራት ሊፈጽሙ ስለሚችሉ፡ በዜጎች በኩል ይህንንም በቅርብ መከታተል አስፈላጊ የሚሆንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።

ኦዲተር ጄነራሉ በሕገ መንግሥት የተሠጣቸውን ሥራ ለምን እንዳይሠሩ ተደረጉ?

መሰል ኃላፊነት መሸከም የማይችል ፓርላማ፥ ሕወሃትን እግር በእግር እየተከታተሉ ያጋለጡትን ታዋቂው ኦዲተር ጄኔራል ገመቹ ዱቢሶ—በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55፥ 74፥ እና ሥራቸውንም የሚያከናውኑት በአንቀጽ 101 መሠረት ቢሆንም—ዐቢይ አሕመድ ከአፈ ጉባዔው ጋር በመተባበር ግለሰቡ ፓርላማ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጭምር እንዳይደርሱ ‘መታገዳቸው’ እየታወቀ አንዳችም እርምጃ አለመውሰዱ፣ በተለይም ጠለቅ ያለ ምርመራ እንዲካሄድ ባደረገና አፈ ጉባዔውን ካሥራቸው ሊያሳግድ በተገባ ነበር!

ከሁሉም የከፋውና የሃገሪቱ መፃዒ ደኅንነትም አደጋ ላይ መሆኑን የሚያሳየው ደግሞ፣ ባለፈው ሰኔ 30 የፌደራል መንግሥት 476 ቢሊዮን ብር በጀት የጸደቀው—ከሕገ መንግሥቱት ድንጋጌ ውጭ— ያለኦዲተር ጂኔራል ተሳትፎ መሆኑን በቻልኩት መንገድ ለማሰማት ሞክሪያለው—ዜጎችም ጉዳዩ የማይመለከታቸው ይመስል ችላ ቢሉትም፡ ነገ ግን ይህ banana republic አሠራር ሃገራችንን ይጎዳል ብዬ መጻፌን አስታውሳለሁ!

የዐቢይ አሕመድ ብልጣ ብልጥነት የሃገራችንን የዴሞክራሲ ተስፋንም በኢትዮጵያችን ፈጽሞ እያጨለመ ነው! ማንም የውጭ መንግሥት ከዚህ መፃዒ ጥፋት ኢትዮጵያን አያስጥልም! ይህን ማክሸፍ የሚቻለው ዜጎች በንቃት የሃገራቸውን ጥቅም በጋራ በማስከበር እንጂ፡ ‘አማራን ሰበርነው፡ አዲስ አበባን ዋጋ እንሳጣታለን…’ እያሉ አሁን ደግሞ የዓላሙዲ የወርቅ አውጭ ኩባንያ የጋርዮሽ ባለቤትነት ሊሠጣቸው በተዘጋጁ ዘረኞችና ዘራፊ ቡድን ሊሆን አይችልም!

ከሰሞኑ ስለኢትዮጵያ ሕዝብ የወቀቱ አስተሳሰብ AfroBarometer: Overwhelming majority of Ethiopians support democracy, seek accountable governance በሚልባ ወጣው ዘገባ፡ እጅግ የሚገርምና ለነገ ተስፋ የሚያሠጥ ጥናት አውጥቷል! የቀረበውን ግራፍ ልብ ብሎ ያየ ዜጋ ሌላ ነገር ማንበብ አያስፈልገውም!

Executive summary: US State Dept 2016 report on human rights practices in Ethiopia

5 Mar

Editor’s Note:

  Inside this year’s report, in its opening page what is reported about prosecution of corrupt officials is not entirely correct.

  It states that the Ethiopian regime “generally did not take steps to prosecute or otherwise punish officials who committed abuses other than corruption.” An individual or individuals in Ethiopia are seized and taken ‘to court’ for corruption under one major premise – the corrupt individuals are not TPLF leaders and generally Tigreans in good standing with the regime.

  By this operating procedure under the martial law, those who are penalized or their resources seized on mere suspicion are non-Tigrean Ethiopians, mostly Amharas and Oromos! This is a blind spot in this year’s human rights report.
  Continue reading

በዱባይ Burj Al Arab Jumeirah ሆቴል ሕወሃት የምስረታ በዓሉን ያከብራል! በጥልቅ መታደስ ይሉሻል ይህ ነው!

23 Feb
  አዘጋጁ፡

  በዓለም ውስጥ 15ቱ ውድ ሆቴሎች አንዱ ተብሎ ተዘግቧል!
   

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ/ም (ኢሳት ዜና):- በሕወሃት ኩባንያ ሙሉ ድጋፍ እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትብብር ሕወሃት የተመሰረተበትን 42ኛ አመት የልደት በዓል በአለማችን እጅግ ዘመናዊና ውድ በሚባለው ቡርጂ አል አራብ ጁሚራህ ሆቴል ውስጥ ከአርብ እስከ እሁድ እንደሚያከብር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
Continue reading

ተንዳሆ ከዕቅዱ ስምንት ዓመት ዘግይቶ፣ አምስት ዕጥፍ ወጪ ፈጅቶ ተጠናቀቀ፤ ተሃድሶ አለ ከተባለ ለምን አብካኞቹ ተጠያቂ አልተደረጉም?

13 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
ከአዲስ አድማስ የመነጨ 

870 ሚሊዮን ብር ተመድቦለት፣ 5.6 ቢሊዮን ብር ፈጅቷል

በአፋር ብሄራዊ ክልል ከ11 አመታት በፊት የተጀመረውና ግንባታው በ3 አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ታቅዶለት የነበረው የተንዳሆ የመስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ከታቀደለት ጊዜ በ8 አመታት ዘግይቶ፣ ከተያዘለት በጀት 5 እጥፍ ያህል ፈጅቶ ተጠናቅቋል።
Continue reading

ሕወሃት እንደሆን ቅሌት አይለቀው! የዘረፋ ልምድ አልላቀቀው ብሎ ለኢንዱስትሪ ፓርክ የተከለለውን መሬት ለጨረታ አቅርቦ መቸብቸቡን ተያይዞታል

11 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ከ400 በላይ የሚሆኑ ኩባንያዎች የኢንዱስትሪ መሬት በድርድር እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበው እየተጠባበቁ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በመካኒሳ ለቡ ኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ የሚገኝ መሬት ለጨረታ ማቅረቡ ጥያቄ አስነሳ፡፡
Continue reading

የቻይና ኩባንያዎችና ኤክሲም ባንካቸው ኢትዮጵያ ፓርኮች ውስጥ ብዙ አረፍ ማለት የፈለጉ ይመስላል፤ ሃገራችንስ ትለማለች? ከተከማቸባት የዕዳ ጫናስ ዕፎይታ ታገኝ ይሆን?

2 Jun

በከፍያለው ገብረመድኅን Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ኢትዮጵያ ውስጥ ዝናብ ይጥፋ፣ የሚበላ ምግብና የሚጠጣ ጠፍቶ፥ ድርቅ የሕዝብ ቁጥር እንኳ ቢቀንስ፡፣ ቻይና የምትሰጠውን ብድር አፍንጫ ሰንጋ በወቅቱ ለማስከፈል ስምምነት ታስገባለች፤ ማስከፈል እንደምትችልም አበክራ ታውቃለች።

በተመሳሳይ መንገድ፥ ሩስያም በደርግ ጊዜ ሃገሪቱ ለጦር መሣሪያ የተበደረችውንና በ1998 አምስት ቢሊዮን ዶላር የነበረውን ዕዳዋን ‘በክፍያና በዕዳ ቅነሳ’ አሁን ወደ $126 ሚልዮን ወርዷልና፣ ‘ዘላለም በዚህ ልንቀጥል አንችልም’ በማለት ሞስኮ ሰሞኑን፡ ኢትዮጵያ ቻይናን ከምትቀልባት ፕሮጀክቶች ለእነርሱም ኩባንያዎች ድርሻ እንዲሰጣትና ዕዳውም እንዲከፈል በማለት ግልጽ ጥይቄ ማቅረቧን ስፑትኒክ የተሰኝው የሩስያ ሚድያ አስምቷል።
Continue reading

A plundered Ethiopia being forced to cater to TPLF’s whetted appetite: Kombolcha & Mekelle Industrial Parks on rush to roll without let!

7 May

By Keffyalew Gebremedhin, The Ethiopia Observatory (TEO)

PART II

The era of industrial park projects

When Part I of this article was conceived, its intention was to subject to examination the thesis behind Ethiopia’s industrial parks projects under construction in Hawassa, Dire Dawa, Kombolcha and Addis Abeba.
Continue reading

In a nation heading toward a future of conflict & violence, Hawassa whets TPLF’s appetite: Should Ethiopians expect another Oromia or Gambella SNNPR becoming feeding tube to TPLF political cadres?

28 Apr

By Keffyalew Gebremedhin, The Ethiopia Observatory (TEO)
 

  “Planning ambitiously is mandatory. Economic growth is considered not a choice, but an existential issue”

  –   Hailemariam Dessalegn in parliament,
  –   December 25, 2015

 

Part I

The measure of TPLF’s huge generosity to the would-be-investors in Hawassa’s Industrial Park – up to 90 percent non-collateralized loans and credits – has become unfathomable, if not mind boggling, even to the regime’s shield-on-standby, such as The Ethiopian Reporter.
Continue reading

%d bloggers like this: