Tag Archives: lack of justice

ሽፍጥ የጎላበት ፖለቲካዊ ውሎ ዛሬም በኢትዮጵያ ፓርላማ!

19 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በየሥፍራው ንግግር ባደረጉ ወቅት፣ ስንቱን ጠቅሰን አጣቅሰን ለማመሳክር እንችላለን?

ዝም ብለን ብናልፍ፣ ጉዳዩ የሚታየው ሰልችቷቸው ተዉት በሚል ሣይሆን—’ኮንፍዩዝ አደረግናቸው’ ብለው ሽመልስ አብዲሣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንዳፌዙ—የዐቢይ አሕመድ እውነትን በነፃነት መደፍጠጥ ሕዝባችን ለዘለዓለም መቀለጃ ያደርጋል!

ነፃነቱንና ክብሩን የተለየ ሥፍራ የሚሠጥ ዜጋ ሁሉ ይህንን እምቢ ማለት አለበት! ውሸት በሉት ቅጥፈት፣ ምንጊዜም የእውነትና የሃቅ ጠላቶች ናቸው! ሃሰቱ ኅሊናን ማቁሰሉ ብቻ ሣይሆን ሰብዓዊነትን ማዋረዱ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው!

ሁልጊዜም ፖለቲከኞች ይዋሻሉ ይባላል። ይህንንም ሁላችንም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ በተደጋጋሚ ታዝበናል፤ ቀደም ሲል አብረዋቸው ከሠሩ የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቻቸውም ሠምተናል!

ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ፓርላማ ሲደመጡ፡ በፍትህ ጉዳይ በምንም መልኩ መንግሥታቸው ጣልቃ እንዳልገቡ ሲተረትሩ መስማትን የበለጠ የሚያሳዛን ነገር የለም! ለኔ እስክንድር ነጋ ወዳጅም ጓደኛም አይደለንም። ስለዚህ ለእርሱ ያለኝ አመለካከት፡ በራሱ መንገድ እውነቱ አድርጎ በያዘው አቋም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደኅንነት የሚታገል ስው አድርጌ አየዋለሁ። ይህ ማለት እኔ እርሱ የያዘውን መንገድ ደግፋለሁ ማለት ሣይሆን፣ ግለሰቡ በጥሩ ዕውነትና ለኢትዮጵያውያን የተሳካ ነገ የሚታገል ስው አድርጌ ተቀብየዋለሁ።

ዐቢይ አሕመድ ግን ግለሰባዊ መብቶቹን በመረጋገጥ ከቤተ መንግሥትዎ ‘ጦርነት ያወጁበት’ ሰው ሆኖ፣ ቄሮም የመንግሥትዎም ፖሊሶች እስከዛሬ የሚያሳድዱት ዜጋ ሆኗል!

የቀድሞ ዐቃቤ ሕግ አዳነች አቤቤ እንኳ በሚያሳፍር መንገድ ለአሜሪካ ድምፅ በሠጡት ቃለ መጠይቅ ክስ ከመሠረቱበት መካከል —ኦሮሞችን ማጥላላትና ቆሮ ላይ ጥላች ዘመቻ ማድረጉ ማለታቸውን በጆሮዬ ሰምቻለሁ! እነዚህን ነገሮች እስክንድር ያደርጋል ብየ አላምንም! ቄሮች ለፈጸሙት ወንጀሎች እንደዚያ ቢልስ—መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም ወይ ያንን ስለወንጀለኛው ቄሮ ያለው?

ሌላው አንድ አስገራሚ ነጥብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት ከሃቅ የራቀው ጉዳይ የሃገራችን 2012 የኤኮኖሚ ዓመታዊ ዕድገት 6.1% ማለታቸው ነው። ልክ ከሕወሃት በተገኘው ልምድ መሠረት፡ የዋጋ ግሽበቱ ሕዝቡን ባማረረበት ሁኔታ አፍሪካ ውስጥ ይህን መሰል ዕድገት እንደማይገኝ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቀደም አድርገው ቢተነብዩና ሕዝባችንም በግሽበቱ በሚገረፍባት ሃገር ለፈበረኩት ‘ሃቅ’ —ማለትም ባዶ ቁጥር መቆማቸው— በሚያሳዝን መንገድ ትዝብት ብቻ ነው ያተረፈላልችው!

ሰሞኑን ግራ የገባት የቤት እመቤት ዘይትን በምሣሌነት በማንሳት፡ መንግሥት ድጎማ በሠጠ መጠን ተጠቃሚው ቸርቻሪው ሲሆን፣ ዋጋው ታቹ ያለውን ኅብረተሰብን መዘንጋቱን ብቻ ነው ያሳየን ማለቷ ግርም ሲለኝ ነበር! ይህ ለእርሳቸው ትርጉም ባይሠጣቸው፡ እምብዛም አይገርምም ዛሬ አባባላቸው እንዳሳየን!

መቼ ይሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕውነትን ጋሻ የሚያደርጉት?

ሕወሃት መራሹ ኢሕአዴግ መቀሌ ላይ በወሰደው የፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ሃገራችን አንድ ግዙፍ እርምጃ ወደኋላ ትራመዳለች

31 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን – Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

መቀሌ በመካሄድ ላይ የነበረው አሥረኛው የኢሕአዴግ ስብሰባ “ሕዝባዊ አደራን በላቀ ዕድገትና ትርንስፎርሜሽን” ፖለቲካዊ፡ ኢኮኖሚያዊ፡ ማኅበረ ስብዓዊ፡ ድርጅታዊ፡ ልማታዊ፡ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ተግባራት አፈጻጸሞችን ከገመገመ በኋላ፥ እንደ ተጠበቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው በያዘው ድርጅታዊ ሊቀ መንበርነትና አስተዳደራዊ አመራር ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሥራቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል።
Continue reading

4 Eritrean bishops bemoan the state of desolate Eritrea

9 Jun

Posed by The Ethiopia Observatory (TEO)

Four Eritrean Catholic bishops have published a letter criticising life in the country – a rare move in one of the world’s most tightly controlled states.
Continue reading

Labor leaders give PM earful about difficulty in Ethiopia of freely organizing & negotiating to ensure respect for legally & internationally recognized rights

2 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory
Source: Ethiopian News Agency (ENA)

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት በነፃ የመደራጀትና የመደራደር መብቶች የተገደቡ መሆናቸውን የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፍ አስታወቀ

መንግሥት የሠራተኞችን መብት ሊያስጠብቁ የሚችሉ እርምጃዎችን ደረጃ በደረጃ እየተገበሩ ቢሆንም የሠራተኞች በነፃ የመደራጀትና የመደራደር መብት ያለመከበር ችግሮች እንዳሉ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ። የሠራተኛውን በነፃ የመደራጀትና የመደራደር እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት በሚቻልበት ዙሪያ በመጪው ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ውይይት ያካሂዳል።
Continue reading

Jihadawi Harekat’s linking of Ethiopian Muslim protests to jihadists entails concerns about situation & justice system

15 Feb

By William Davison

Ethiopia, a US ally in the battle against Al Qaeda-affiliated militants in Somalia, added to mounting worries about religious discord in the diverse east African state by screening a provocative documentary on Islamic extremism.
Continue reading

%d bloggers like this: