Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
-
“የተባበሩት መንግስታት ተወካይ ሆነው በዚምባቡዌ ሲሰሩ ፣ሮበርት ሙጋቤ ከእርሻ መሬታቸው ያፈናቀሏቸውን ነጭ ገበሬዎች አግኝተው ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ በግል ጠይቀው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ገበሬዎቹ አማራጫቸውን ሞዛምቢክ አድርገው በዘጠኝ ወር ውስጥ የሃገሪቱን ምርት በ3 እጥፍ መጨመራቸውን በመጥቀስ፣መንግስትም እንደነዚህ አይነት ባለሙያዎችን መጋበዝ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡”
*አድማስ ይህንን ሲጽፍ፡ የኛንስ ምርት አልባ የሆኑትን ሚሊዮኖች ማን እንደሚቀበል፤ ባለሙያው አለማሰባቸው፣ መጽሔቱም አለመጠየቁ ትንሽ ያስገርማል!
——-0——–
-
* በኪሎ 35 ብር የነበረው በርበሬ 55 ብር እየተሸጠ ነው
* በ115 ብር እንዲሸጥ የተተመነው ባለ 5 ሊትሩ ዘይት 150 ብር ገብቷል
* በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የስኳር፣ የዘይትና የዳቦ እጥረት ተከስቷል
——–0——-
-
“በየጊዜው የጤፍ ዋጋ ቀንሷል ቢባልም ሰው መግዛት ስለተወ እንጂ በእርግጥ በሚፈለገው መጠን ዋጋው ስለቀነሰ አይደለም …የሸቀጦችን ዋጋ በተመለከተ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ የሚያወጣቸው መረጃዎች ምን ያህል ትክክለኛ ናቸው የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡”
*[አዲስ አበባ ውስጥ] እስከ 2 ሚሊዮን የሚደርስ [የተፈናቀለ] ገበሬ ከተማዋን ተቀላቅሎ ሸማች ሆኗል የሚል ግምት አለ፡፡
ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ