Tag Archives: national budget

በገንዘብ ዕጥረት ምክንያት፣ኢትዮጵያ መንግሥታዊ የዱቤ በጀት ልትጀምር ነው! ሕወሃት ሃገራችንን አከሠራት አይደል?

10 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሪፖርተር

ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ዘንድሮ መሰብሰብ አልተቻለም

የ2011 ዓ.ም. በጀት 59 ቢሊዮን ብር ጉድለት አለበት

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የገንዘብ እጥረት ቀውስ እንደገጠመው፣ እጥረቱ በፍጥነት መፍትሔ ካልተገኘለት ኢኮኖሚውን በመጉዳት ማኅበራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል መንግሥት በይፋ አስታወቀ፡፡

ይህንን የተናገሩት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ የፌዴራል መንግሥትን የ2011 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ሐሙስ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ክስተቱ መፈጠር ከጀመረ ረዥም ጊዜ ቢሆነውም ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግን የገንዘብ እጥረቱ ጎልቶ በመውጣት ወደ ኢኮኖሚ ቀውስነት የመሸጋገር አዝማሚያ እየታየበት መሆኑን፣ ሚኒስትሩ ካቀረቡት የበጀት መግለጫ ንግግር መረዳት ተችሏል፡፡

‹‹ከኤክስፖርት የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ደካማ በመሆኑ ለልማት የሚያስፈልጉ የካፒታል ጥሬ ዕቃዎች፣ እንዲሁም በአገር ውስጥ የማይመረቱ መሠረታዊ ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ፈታኝ ሆኗል፤›› ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያመነጨው የውጭ ምንዛሪ ደካማ ስለሆነ፣ የአገሪቱን ልማት ለማስቀጠል የውጭ ፋይናንስ በተለይም የውጭ ብድር ለማግኘት እንቅፋት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሚኒስትሩ ንግግር የሚያስረዳው አገሪቱ ከኤክስፖርት የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ አነስተኛ ስለሆነ፣ የውጭ ዕዳ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን፣ የአገሪቱ የብድር አጋር የነበሩ የውጭ መንግሥታትና ተቋማት ጭምር አዲስ ብድር ከመስጠት መቆጠብ መጀመራቸውን ነው፡፡

ሪፖርተር ያገኘው የሁለት ዓመት ተኩል የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዶክመንት እንደሚያስረዳው፣ መንግሥት በቀጥታ የተበደረው የውጭ ዕዳ ክምችት በዚህ ዓመት 24.75 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ በ2009 ዓ.ም. 13 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ አገሪቱ ስታገኝ የነበረው የውጭ ብድር በኢንቨስትመንትና ለኢንቨስትመንቱ በሚያስፈልገው ቁጠባ መካከል የሚታየውን ልዩነት ለመሸፈን ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ይህ የውጭ ብድር ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱና ከኤክስፖርት ይገኝ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ መጠን መጨመር ይቅርና በነበረበት ማቆየት እንኳን ባለመቻሉ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ ከታክስ ይገኝ የነበረው ቢሆንም በ2008 እና በ2009 ዓ.ም. እንደቅደም ተከተላቸው 15.2 እና 10.3 በመቶ ብቻ ማደግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በ2009 ዓ.ም. ታቅዶ ከነበረው የታክስ ገቢ 39 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንዳልተቻለ፣ ለዘንድሮው በጀት ዓመት ከታቀደው የታክስ ገቢ ደግሞ 50 ቢሊዮን ብር እንደማይሰበሰብ ከወዲሁ መታወቁን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የተነሳ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ወደ በ2011 ዓ.ም. እንዲሸጋገሩ መንግሥት መገደዱን፣ ይህ ሁኔታም በመንግሥት ላይ የበጀት ጫና መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የ2011 ዓ.ም. በጀት ሲዘጋጅ ከፍተኛ የበጀት አጠቃቀም ዲሲፕሊን ይኖራል በሚል መርህ የታክስ አሰባሰቡ ላይ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ በመገንዘብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሠረት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተለያዩ ዕቃዎችን ከውጭ በሚያስገቡ የመንግሥት ተቋማት ላይ መሰብሰብ የሚገባውን የጉምሩክ ታክስ በማስላት፣ ንብረቶቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው እንዲገቡ እንደሚያደርግ በረቂቁ የ2011 ዓ.ም. በጀት ላይ ተገልጿል፡፡ ባለሥልጣኑ ከአስመጪ የመንግሥት ተቋማት የሚጠበቀውን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የገንዘብ መጠን ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርና ለተቋማቱ እንደሚያሳውቅ፣ በዚህ መሠረትም ያልተከፈለው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የተቋማቱ ዓመታዊ በጀት አካል እንደሚሆን ተወስኗል፡፡ የ2011 ዓ.ም. በጀት 346.9 ቢሊዮን ብር ሆኖ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 59.3 ቢሊዮን ብር በአገር ውስጥ (የገንዘብ ኅትመትን ጨምሮ) የሚሸፈን እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከቀረበው የ2011 ዓ.ም. በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 91.7 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 113.6 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ 135.7 ቢሊዮን ብር ሆኖ፣ በዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚካተት ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ስድስት ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል፡፡

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ግዙፍ የልማት ድርጅቶችንና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በከፊልና ሙሉ በሙሉ ለግል ባለሀብቶች ለማዘዋወር ሰሞኑን የወሰነ ቢሆንም፣ የ2011 ዓ.ም. በጀት ግን ከእነዚህ ተቋማት የአክሲዮን ድርሻ የሚገኝ ገቢን አላካተተም፡፡ ረቂቅ በጀቱ ለተጨማሪ ዝርዝር ዕይታ ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

Is every official & institution in TPLF’s Ethiopia thief & corrupt? So seem to put question marks the Auditor-General’s finds!

17 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

In his speech to parliament to report budget performance of the TPLF administration for the year 2014/15, Auditor-General Gemechu Dubiso pointed out:

  “የ2006 በጀት ዓመት ሂሳብ በወቅቱ መዝጋት ያልቻሉ መ/ቤቶች ከጠቅላላው ከ52% በላይ ናቸው፡፡ ይህ መሻሻል ሲገባው እየባሰበት የመጣው የባለበጀት መ/ቤቶች ሂሳብን በወቅቱ ዘግቶ ለኦዲት ያለማቅረብ ጉዲይ በአንክሮ ሊታይና ተገቢው ህጋዊ እርምጃ መውሰድን የሚያሻው ጉዲይ ነው፡፡…

  … ከመንግሥት ግንባታዎች ጋር በተያያዘ በተለያዩ ምክንያቶች በወቅቱና በተያዘሊቸው በጀት ያለመጠናቀቅ ችግር፤ መፌትሔ ሣያገኙ ለረጅም ወራትና ዓመታት ጭምር የግንባታ ሂደታቸው የቆሙ ፕሮጄክቶችና የሚገናቡ ፕሮጄክቶች ጥራት አፊጣኝ እርምጃ የሚያሻው በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊፈታ ይገባል…

  በወጪ የተመዘገቡት ሂሳቦች በፊይናንስ አስተዳደር አዋጅና ደንብ መሰረት በአግባቡ የተፈጸሙ፤ እንዱሁም መ/ቤቶቹ ላገኙት አገልግልት የተፈጸመ መሆኑን ለማጣራት ኦዱት ሲደረግ፡ በ11 መ/ቤቶች ለተለያዩ ግንባታና ግዢዎች ብር 28,175,126.27 እና በ16 መ/ቤቶች ደግሞ በውሎ አበልና ለሌሎች ክፍያዎች ብር 4,897,884.43 በጠቅላላው ብር 33,073,010.70 በብልጫ ተከፍሎ ተገኝቷል፡፡

  …በብልጫ የተከለው ሂሳብም በግዢ ሂደት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ እያለ ያለበቂ ምክንያት ከፍተኛ ዋጋ ካቀረቡት ዴርጅቶች ግዢ በመፈጸም፤ በዴጋሚ ወጪ በማዳረግ ወይም ከተገባው ውል ውጭ በመክፈል፣ ከውሎ አበል ተመን በላይ በመክፈል፣ እንዱሁም ለትርፌ ሰዓት፤ ለተለየያ ጥቅማ ጥቅም እና ለመኖሪያ ቤት አበል ከተተመነው በሊይ በብልጫ የተከፈለ መሆኑ የሚለት ይገኙበታል፡፡ ሊከፈል ከሚገባው በላይ ወጪ ማድረግ የመንግስት ሃብት ለብክነት የሚዲርግና ለሙስናም በር የሚከፍት ይሆናል፡፡”
  ≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈

  “The latest report by the Auditor General has also shown that the executive has spent billions without following the appropriate rules of the game. So much remains unaccounted for that it has become all the more difficult to distinguish money spent on the right thing from money siphoned off illegally.

  ….As it stands, the nation’s budgeting system does not provide the legislature clear, measurable and accountable targets to check the performance of the executive. Hence, the whole debate over the report of the OAG has been limited to accounting principles….

  There is no established linkage between budgeting and deliverables in Ethiopia. The entire budgeting process is guided by subjective assumptions. And in all cases, the assumptions are macro in nature. They are not sufficiently detailed to be used as instruments of oversight.”
  – Addis Fortune

 
Continue reading

EFFORT’s Sur sees revenue from construction doubling this year

10 Oct
  Editor’s Note:

  Since the past few months, in Addis Abeba within hours’ notice a citizen’s house is demolished. The property is built by the owners, i.e. the residents, in full compliance with the law – official permits and documents ascertaining ownership of the properties on hand. Nonetheless, to such an extent the TPLF officials feel powerful to come with armed guards and statement to claim that the land is ‘needed for development’.
  Continue reading

%d bloggers like this: