Tag Archives: No such protection for Oromos or Amharas or others

በአማራ ክልል ለትግራውያን የተለየ ጥበቃ እንዲደረግ ሕወሃት መወስኑ፡ሕግን የጣሰ፡ዘረኛና በዜጎች መካከል ለመፍጠር የሚሞክረውን ኮሾ የበላይነት ስሜት ለሃገሪቱ ችግሮች ምንጭነቱን ያሳያል!

6 Sep

የአዘጋጁ አስተያየት፡


  ሕወሃት በየቀኑ የሚያንገላታቸውን፣ የሚጨፈጭፋቸውን በገሃድና በሕቡዕ የሚገድላቸውንስ ማን ዘብ ይቁምላቸው? ይህ በሃገሪቱ የደም መፋሰስ ጎራ እንዲቀደድ የሚያደርግ የጥጋብ እርምጃ አይደለምን? ከሕጉም የበለጠ ለዘመናት የነበረውን አብሮ መኖርነትን፡ የነበረውንና ያለውንም መተሣሠርንና መከባበርን የሚደመሥሥ ይሆናል የሚል ሥጋት ፈጥሯል!

  ራሱ ሕወሃት በቀዳሚነት ያስደረስውም ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 25 ከታች እንደሠፈረው ሲታይም ለትግራውያን ለብቻ ይህንን መብት አይሠጣቸውም። ሁሉም ሰዎች [emphasis added] በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዐይነት ልይነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል” ይላል።

  ሠፋ በማድረግም እንዲህ ስከትላል፦

  “በዚህ ረገድ በዘር፥ በብሔር፡ ብሔረሰብ፡ በቀለም፡ በጾታ፡ በቋንቋ፡ በኃይማኖት፡ በፖለቲካ፡ በማኅበራዊ አመጣጥ በሃብት፡ በትውልድ ወይንም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ስዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው።”

  የሚገርመው ደግሞ የአማራ ክልል ይህ ጥያቄ መጀመሪያ ሲቀርብለት ትግራውያን እንደሌላው ኢትዮጵያዊ እንጂ ለእነርሱ ለብቻ የሚደረግ ጥበቃ አይኖሮም ብሎ ትክክለኛ ውሳኔ ማስተላለፉ ልብ ሊባል ይገባል!

  ‘መንግሥት’ የሚባለው ኃይል ቀዳሚ ግዴታው የእያንዳንዱን ዜጋ ደኅንነት ማረጋገጥ እንደመሆኑ፡ ሕወሃትም በኢትዮጵያውያን ዐይንም ለውድቀት የበቃው ሃገርንና ዜጎችን ለመንከባከብ አለመቻሉ መሆኑ የታወቀ ነው። ለምሣሌም ያህል፣ ዜጎቻችን ሊቢያ ውስጥ እንደእንስሳ ከታረዱ በኋላ፣ ሕወሃት ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው፡ ለለቅሶ በየአደባባዩ የተሰበሰበውን አዲስ አበባዊ በየመንደሩ እያሳደደ መደበደብ ነበር።

  ለምን? በለቅሶ አሳበው ሥልጣኔን ይነጥቁኛል ብሎ ስለፈራ ነበር። ይህን ሁኔታ በተደጋጋሚ ማየታችን፡ ለትግራውያን ለብቻ ጥበቃ ይሚለውን ዜጎች አበክረውእንዲቃወሙ ያስገድዳል።

===============
 
Continue reading

%d bloggers like this: