Tag Archives: Oromo Liberation Front (OLF)

በወለጋ በኦነግ ስም የታጠቁ ቡድኖችን ለማስፈታት በተጀመረው እንቅስቃሴ ጉዳት ደረሰ!

31 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በሪፖርተር

ትጥቅ ላለመፍታት ባሸመቁ ላይ በተወሰደ የኃይል ዕርምጃ በርካቶች መሞታቸውን እማኞች ገለጹ

በፀጥታ አስከባሪዎች ላይ በተሰነዘረ የቦምብ ጥቃትም የአካል ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል

የመከላከያ ሠራዊት በወለጋ አካባቢ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ስም የጦር መሣሪያ ታጥቀው የፖለቲካ ንቅናቄ የሚያደርጉ ቡድኖችን ትጥቅ ለማስፈታት የጀመረው እንቅስቃሴ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በሰው ሕይወትና አካል ላይ ጉዳት ማድረሱና በአካባቢውም የግጭት ውጥረት መንገሡ ተሰማ፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱ ከቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በምዕራብና በምሥራቅ ወለጋ አካባቢዎች መሰማራት መጀመሩን የሚገልጹት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአካባቢው ምንጮች፣ ሠራዊቱ እንደሚሰማራ ቀደም ሲል መረጃ የነበራቸው የአካባቢው ወጣቶች ከቅዳሜ በፊት በነበሩት ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ሠልፎችን በማድረግ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማውን ሲቃወሙ እንደነበር ጠቁመዋል።የመከላከያ ሠራዊቱ በአካባቢዎቹ እንዳይሰማሩ መንገዶችን በመዝጋት ድርጊት ላይ መሰማራታቸውን ምንጮች ገልጸው፣ የመከላከያ ሠራዊቱ የተዘጉ መንገዶችን በመጥረግ መሰማራት ቢቀጥልም በአንዳንድ አካባቢዎች በጦር መሣሪያ የታጀበ ግጭት እንደገጠመውና በዚህ ምክንያትም የኃይል ዕርምጃ መውሰድ መጀመሩን ገልጸዋል።

የታጠቁት ወጣቶች ለኃይል ዕርምጃው የአፀፋ ምላሽ እየሰጡ በማፈግፈግ ወደ ማኅበረሰቡ ውስጥ፣ የተቀሩት ደግሞ ወደ ጫካ በመሸሽ እንደተሸሸጉ ይናገራሉ። መከላከያ ሠራዊት አባላት የአካባቢው አመራሮችንና ሽማግሌዎችን በማስተባበር ትጥቅ የማስፈታት ተልዕኳቸውን ቤት ለቤት በመዞር ለመፈጸም ጥረት እያደረጉ መሆኑን፣ ነገር ግን መሽገው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች መንገድ በመዝጋትና ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር እየተሰወሩ መሆናቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ አይራ ጉሊሶ በሚባል አካባቢ መንገድ በመዝጋት የሠራዊቱን እንቅስቃሴ ለመገደብ በሞከሩ ቡድኖች ላይ ሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በተወሰደ የኃይል ዕርምጃ፣ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል። በምዕራብ ወለጋ ቤጊ በተባለ አካባቢ በተወሰደ ዕርምጃ ጉዳት ባይደርስም የታጠቁት ቡድኖች መሸሻቸውን፣ በደምቢዶሎ አካባቢ በመንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች ላይ በተሰነዘረ የቦምብ ጥቃት፣ በሦስት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል።

በቄለም ወለጋ፣ ሆሮ፣ ዋበራ በተባሉ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩንና ነዋሪዎችም አካባቢዎቹን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በቤጊና በነቀምት የአካባቢውን ነዋሪዎችና ወጣቶች በመሰብሰብ ሲያነጋግሩና ሲያግባቡ እንደነበር ምንጮች አስረድተዋል፡፡በአካባቢው ስለተጀመረው ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴና እስካሁን ስለደረሰው ጉዳት ማብራሪያ እንዲሰጡ ለመከላከያ ሚንስትሯ ወ/ሮ አይሻ መሐመድ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም የጉዳት መረጃ እንደሌላቸው፣ ወደ አስቸኳይ ሰብሰባ እየገቡ ስለሆነም ማብራሪያ ለመስጠት እንደሚቸገሩ ገልጸዋል።

ሪፖርተር የኦሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ለአቶ ሁሴን ፋይሶና የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ለአቶ ሌሊሳ ዋቆያ ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ ኃላፊዎቹ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ይሁን እንጂ አቶ ሁሴን በቀጣዮቹ ቀናት የተጠናቀረ መረጃ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ማክሰኞ ማምሻውን ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ፣ በምዕራብ ወለጋና በቄለም ወለጋ በኦነግ ስም በመታጠቅ ሕዝቡን ለችግር እየዳረገ ያለ አካል በአፋጣኝ ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ አሳስበዋል፡፡

መንግሥት እስካሁን እንዲህ ዓይነቱን ተግባር በትዕግሥት ሲመለከት ነበር ያሉት አቶ ለማ፣ ከዚህ በኋላ ግን መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት ለመጠበቅና ሕገ መንግሥቱን ለማስከበር እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

በወለጋ አካባቢ ትጥቅ የማስፈታት እንቅስቃሴውን ለማደናቀፍ የሚጥሩና ከጀርባ ሆነው ወጣቶችን የሚያሳስቱ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ፣ እንዲሁም መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚቀጥልና ምንም ዓይነት ትዕግሥት እንደማይኖረው አስጠንቅቀዋል፡፡

ሪፖርተር በአካባቢው ማግባባት ሲያደርጉ ታይተዋል የተባሉትን የኦነግ ሊቀመንበር በስልክ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

ጠ/ሚሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ትጥቅ መፍታት እንዳለባቸው አስገነዘቡ! የኦሮሞ ነፃነት ግንባሩ (ኦነግ) ዳውድ ኢብሣ ‘ትጥቅ ፈታ መባል ሴንሲቲቭ ጥያቄ’ ነው ይላሉ! ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው?

7 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

በቡራዩና አካባቢዋ በቅርቡ በደረሰው የንፁሃን ማፈናቀል፣ግድያና ዘረፋ—ምናልባትም የመጀመሪያው ግልጽ ሊባል የሚቻል—የ2 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕይታ!

24 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ተዛማጅ:

በቡራዩ አረመኔያዊውን ተግባር የፈጸሙት መንግሥት ‘የተደራጁ ኃይሎች’ ናቸው ብሎናል! መንግሥትም በተከታታይ ከመንግሥትነቱ እንዲያንስ በመደረጉ ኢትዮጵያዊነት ስለተጎዳ፣መንግሥትና ሕዝቡ በጊዜ በቃ ሊሉ ይገባል!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ!

30 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አባባ፣ ሰኔ፣ 23፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ።

ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሳ ነው የውሳኔ ሀሳቡን ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል

_________________________________________________________________________________________________________________________________

_________________________________________________________________________________________________________________________________

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።

ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ሀሳብም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ በሰለማዊ መንገድ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ መሆኑንም ገልፀዋል።

_________________________________________________________________________________________________________________________________

_________________________________________________________________________________________________________________________________

 

_________________________________________________________________________________________________________________________________

 

History repeating itself in the Horn of Africa: Is the crime in Darfur being replicated in Eastern, South & Southern Oromia Regional State of Ethiopia? A MUST-READ!

15 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by J. Bonsa (PhD), Special to Addis Standard
 

“Liyyu” is an Amharic expression to mean “special”, so Liyyu police denotes a “special police”. If the Janjaweed are devils on horseback, then Liyyu police can be described as demons maneuvering armored vehicles. It is instructive to examine why, where, and when the regime in Addis Abeba has created Liyyu police.

Addis Abeba, April 10, 2017 – It is saddening to witness repetitions of similar tragic events in history. Recurrences of such dreadful events can even sound farcical when they happen in a very short span of both time and space. This is exactly what is currently happening in the Horn of Africa. It is barely over a decade since the height of the Darfur genocide. One would hope that the international community has been well informed to avoid repetition of Darfur like tragedy anywhere in the world. However, it is depressing to observe that the Darfur crisis is in the process of being replicated in Ethiopia.

In this piece, I will explain how the scale of the crisis unfolding in Ethiopia’s Eastern and Southern regions (and those brewing up in other regions) can have a potential to dwarf the Darfur crisis. The Janjaweed militia (in the case of Sudan) and the so-called Liyyu police (in the case of Ethiopia) are the catalysts for the crisis in their respective regions. For this reason, I will focus my analysis on explaining missions and functions of these two proxy militias.
Continue reading

Ethiopia, Kenya discuss sustainable crossborder peace & economic transformation

28 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

On 19 December 2016, officials from Ethiopia and Kenya, UN agencies and donors//international financing institutions discussed the implementation of the Cross Border Integrated Programme for Sustainable Peace and Socio-economic Transformation in Marsabit County (Kenya) and Borena and Dawa zones of Ethiopia to reduce conflict and enhance regional development through the implementation of multi-sectoral projects. The initiative was launched by the leaders of the two countries in the border town of Moyale in late 2015 and the document under discussion will be signed in Nairobi sometime in April 2017. UN agencies in attendance were led by Ms. Ahunna Eziakonwa-Onochie, the UN Resident and Humanitarian Coordinator in Ethiopia and her Kenyan counterpart. The UN will be engaged in resource mobilization within the framework of UN delivering as one.
 
/Reliefweb
 

የኦሮሞ ምሁራን ስለኦሮሚያ የነፃነትና እኩልነት ትግልና ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ያደረጉት ውይይት

15 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)</em>
 

 

ተዛማጅ:
Continue reading

የኦነግ መሪ ዳውድ ኢብሳ ቃለ መጠይቅ:       ተቃውሞውን እየመሩ መሆኑን ገልጸው፣ በሕወሃት ሠራዊትና ቢሮክራሲ ውስጥ ያሉ ኦሮሞች ‘ብሔራዊ ግዳጅ’ መሆኑን ተገንዘበው ትግሉን እንዲቀላቀሉ ‘የመጨረሻ ጥሪ’ አደረጉ

9 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

%d bloggers like this: